ትልማዊ ሐሳቦች

Description
ዕውቀት ወደ እውነት ታደርሳለች። እውነት አርነት ታወጣለች። አርነት በእምነት ትጸናለች።
Advertising
We recommend to visit

Books only!

This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !

Join and share @Books_worldd

አስተያየት @BooksWorlddd_bot !

@books_worlddd መወያያ ግሩፕ

#share

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Last updated 6 months ago

?"እውቀት የነብያት ውርስ ነው። ኡለሞች ደግሞ የነብያት ወራሾች ናቸው። እውቀትን እና የእውቀትን ባለቤቶች መውደድ የነብያትን ውርስ እና ወራሾችን መውደድ ነው።
?በደረጃ የሚለቀቁ
1:-ነህው
2:-ሶርፍ
3:-ተጅዊድ
4:-ተፍሲር
5:-ፍቅህ
6:-አቂዳ
7:-መንሀጅ
8:-ሀዲስ
9:-ሲራ
10:-ሙስጦለህ
11:-ቀዋኢደል ፍቅህ
12:-ኡስሉል ፊቅ
13:-አህላቅ ወል አዳብ
14፡-ስለሴቶቻችን
15:-ንፅፅር

Last updated 2 months, 3 weeks ago

4 months ago
[#ታሳ](?q=%23%E1%89%B3%E1%88%B3)! እኔን!

#ታሳ! እኔን!

(ሄኖክ በቀለ ለማ)

መሬቱ ለምለም ነው ፥ ውኃ በምድሩ ከርስ ውስጥ ይርመሰመሳል። አፈሩ እንደ ሕብስት ይቆረሳል። የተራሮች ሀገር ነው። የጀግኖች ምድር ነው። የትሑታን ምድር ነው — ጋሞ/ጎፋ። ታሳ! እኔን!
.
ተፈጥሮ ብዙ ባርኮት ብትሰጥ ፣ ጥቂት እርግማን አታጣም። ዛሬ መሬት ተከፍታ ደርባቦችን ዋጠች። የሰጧትን ከማትነሣ ምድር ዛሬ ሰው ተቆፍሮ ወጣ—ታሳ! እኔን!
.
እንግዳን ማንገሥ የሚያውቅ ሕዝብ ነው። መጥኖ የሚያጎርስ፣ አቅፎ የልብ የሚያደርስ ሕዝብ ነው — ሁሉም ከወላይታ ጀምሮ ወደታች እስካየሁት የሚወደድ ሕዝብ ነው። ገዜ ጎፋን አይቼዋለሁ —ጥቂት ቀንም ቢሆን። ተፈጥሮ ልትከዳው የተገባ ሕዝብ አልነበረም —ታሳ! እኔን!
.
አይዞን አንተ የምወድህ ሕዝብ
መጽናናት ይሁንላችሁ!

💡📚🛵
@Light_Book_Delivery
@Light_Book_Delivery

4 months ago
**ዘአድኃኖሙ እምዕቶነ እሳት

**ዘአድኃኖሙ እምዕቶነ እሳት
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል
ከማሆሙ ያድኅነነ
እምኵሉ ዘይትቃረነነ።
        (አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእሳት ባሕር ያዳናቸው እኛንም ከሚቃረነን ኹሉ አድነን።)
       ዚቅ ዘታኅሣሥ ገብርኤል

ማንም አልነበራቸውም። ኹሉም አምጾባቸው ወደእሳት እንዲወረወሩ ፈርዶባቸዋል። በተንኮል የከሰሷቸውም በእሳት እስከሚነዱ ለማየት ተጣድፈዋል። ንጉሡም ጨክኖባቸዋል። ወደ እሳት የሚጥሏቸውም እንደታዘዙት በጠንካራ መዳፎቻቸው ሊወረውሯቸው ነው። እነሱ ግን አንዲት ተስፋ አላቸው። ለንጉሡም ይኽንን ነግረውታል። ''የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው እሳቱ ዕቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅኽም ያድነናል''።
እንዲኽ ብቻም አላሉትም። ባያድናቸው እንኳን እርሱ ላቆመው ምስል እንደማይሰግዱ አስረግጠው ነገሩት።
ወደእሳቱ አስጣላቸው። የወረወሯቸውም በእሳቱ ወላፈን ሞቱ። እነኾም እነሱን መልኩ የአማልክትን መልክ የመሰለ አንድ አዳኝ በመካከላቸው ቆሞ አብሯቸው ታየ። እንዳሉትም እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አዳናቸው። የእምነታቸው ጽናት መልአኩን ከሰማይ ወርዶ እንዲያድናቸው አደረገ። ይኽ አዳኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው።

እኛስ ምን ያኽል በአምላካችን እንተማመናለን?
በየትኛው የሕይወት መከራ ውስጥ ኾነን ያወጣናል ብለን እናምናለን?
ባያድነን እንኳን አንተወውም ብለን እንጸናለን?

ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያወጣ ተራዳኢው መልአክ አይለየን!🙏

ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓል አደረሳችኹ!🙏

መልካም በዓል!**@Light_Book_Delivery@Light_Book_Delivery@Light_Book_Delivery_1@Light_Book_Delivery_1

4 months ago
የሰው ልጅ ውስብስብ ነው። እኔ ምድር …

የሰው ልጅ ውስብስብ ነው። እኔ ምድር ላይ ካሉ ጥናቶች በሙሉ ሰው ላይ የሚያተኩሩ ጥናቶች አስቸጋሪ፣ ውስብስብና ከባድ እንደኾኑ አምናለኹ። ሰውን አምላክን በምንገልጽበት ዕቅጭ እና ርግጠኝነት እንገልጸዋለን፣ እንረዳዋለን ማለትም ይከብደኛል።
ምክንያቱም ሰው ብዙ ነው። አንድ ሰው ራሱ ብዙ ሊኾን ይችላል። 'ፍቅር' ነው ያላችኹት በተመሳሳይ ጊዜ 'እጅግ የከፋ' ይኾናል፤ የተረጋጋ ነው ስትሉ ብስጩና ተናዳጅም ይኾናል፤ በአንድ ነገር 'እውነተኛ የኾነ ሰው' በሌላው 'ሐሰተኛ' ይኾናል...ሌላም። ይኼ ቅጣት ቢኾን ከአትላስም የበለጠ ቅጣት ነበር።
ሰው ውስብስብ ነው።

የሰውን አመለካከትና ጠባይ መረዳትን የመሰለ ከባድ ሸክም በምድር ላይ ያለ ይመስላችኋል? አለ ካላችኹ ምን?
እስከዛሬ ያልገባችኹ ሰው የለም? ሌላ ቢጠፋ እንኳን ራሳችኹ ትኾናላችኹ።

ራስን መረዳት ደግሞ ከዚኽም ይብሳል።

✍️ ፒያንኪያ

@Love_Of_Sophia
@Love_Of_Sophia

5 months, 1 week ago

??ከመጻሕፍት ዓለም... በዛሬው ጽሑፉችን ከባሕር ማዶ እንኼድና ከአንድ ታዋቂና ተወዳጅ መጽሐፍ ጋር ቆይታ እናደርጋለን። “ሌ ሚዝረብል” እና “ዣንቫልዣ” (አፈንዲ ሙተቂ) === እንደ መግቢያ === እነሆ የቪክቶር ሁጎ ታላቅ ሥራ የኾነውን “Les Misérables”ን ልንዘክረው ነው። ይህ ድርሰት የፈረንሳይ ምድር ካበቀለቻቸው የፈጠራ ሥራዎች መካከል በጣም ዝነኛው ነው፡፡ መጽሐፉ በዓለም ዙሪያ የሚታወቀው…

6 months ago

ስትስቂ ጊዜ...
የፈጠርኋት ዓለም ታብረቀርቃለች፤
ጥርስሽን ካየኹት...
የጨለመች ዓለም ደምቃ ታበራለች።

ፋኖስ ፀሐይ ኾና አገር ታሞቃለች
ሰማይ እንደምድር ትሸላለማለች
በአበቦች አብባ ገነት ትመስላለች
ምድር ከሰማይም ብሩህ ትኾናለች
ከዋክብት አርግዛ ውበት ታምጣለች
ልጆቿን ከጥርስሽ ትመጋግባለች።

ፒያንኪያ

@Love_Of_Sophia
@Love_Of_Sophia

7 months ago

እንታረቅ አልልሽም። ወደሽ መስሎኝ መሸሽሽ...ፈልገሽ መስሎኝ መጥፋትሽ...ከማየት አለማየት ይሻለኛል፣ ከድክመትኽ ጋር ከመዳበል ትዝታኽ ብቻ ይበቃኛል ብለሽ ወስነሽ መስሎኝ መሔድሽ? አይደለም? እስኪ ንገሪኝ!

የእኔ መኖር በአንቺ ኑረት ውስጥ ምንም ካልፈጠረ አለመኖሬን መሻትሽ ሐሰት ነው?

@Love_Of_Sophia
@Love_Of_Sophia

7 months, 3 weeks ago

**የሴትነት ከፍታ እናት ናት።
ብልኽ ናት። አይመስልኽም እንጂ ከእሷ በላይ የሚረዳኽ የለም፤ ሳትናገር ነው የምታውቅኽ። እንደ ጠባይኽ ብላ ያየችውን እንዳላየች ስለምታልፍና ነጻነትኽን ከማንም በላይ ስለምትጠብቅ እንጂ ስለአንተ ከራስኽ በላይ ታውቃለች።

እስከመጨረሻው አብራኽ የምትጓዘው እናትኽ ናት። ካላመንኸኝ በዕለተ ዐርብ እስከመስቀል አብሮት ማን እንደነበር እስከሞት የደረሰውን ጌታ ጠይቀው።

ሴት ልጅ የምትከብረው በመውለድ እንደኾነ ቅዱሱ መጽሐፍም ይነግርኻል። ስትወልድ የሰውነት ኹሉ ልክ ትኾናለች። ከፈጣሪኽ በታች አምላክኽ ትኾናለች።

እናትኽ...
ስትጨልም አብራኽ ትጨልማለች፣ ስትሰንፍ ፍጹም ልታበረታኽ አብራኽ ትሰንፋለች፣ ብርታቷን ልታጋባብኽ በወረት ሳይኾን በፍጹም ፍቅር የምትጥር ናት።
እሷ ጋር የአንተ በሽታ በሽታዋ ነው። ስለአንተ ደኅንነት እንጂ ለበሽታኽ ግድ አይሰጣትም።
እሷ ጋር የአንተ ዝቅተኛነት ሳይኾን መኖርኽ ብቻ ዋጋ አለው።
እሷ ጋር ከአንተ ሐዘን በላይ የሚያሳዝናት የለም።
እሷ ጋር ደሀ ብትኾንም ሀብትዋ እንደኾንኽ ትቆጥራለች።
እሷ ጋር መለዋወጥ፣ በአንተ ተስፋ መቁረጥ የለም።
ሰዎች መልክኽን፣ ዕውቀትኽን፣ ሞራልኽን፣ ሕመምኽን፣ ችግርኽን፣ ስንፍናኽን ተመልክተው ሊሸሹኽ፤ አይረባም ብለው ከሕይወታቸው ሊያስወጡኽና ተስፋ ሊቆርጡብኽ ይችላሉ።
እናትኽ ግን ስትወልድኽ እንደተደሰተችው ኹሉ እስከሕቅታዋ ድረስ ያው በአንተ ደስተኛ ናት።
ስለምታደርግላት አይደለም...በቃ ስላለኻት ስለተወለድኽላት ብቻ ደስተኛ ናት።
ከእሷ ውጪ የአምላክኽ ምድራዊ አምሳል ማን ሊኾን ይችላል?
ማንም የማይተካት የፈጣሪኽ ጸጋ ናት።**@Love_Of_Sophia@Love_Of_Sophia

8 months, 3 weeks ago

**በኹለት አጣብቂኝ ውስጥ መመላለስ
በመኾንና መሻት መኻል መዋዠቅ
በመፈለግና በማጣት መፈተን

እንደዚኽ የሚከብድ የሕይወት ፈተና ይኖር ይኾን?**

9 months, 3 weeks ago

የተስፋችኹ እንጥፍጣፊዎች አንድ ወይ ኹለት ጠብታ ብቻ ከቀሩ ምናልባትም መኖር ልትጀምሩ ይኾናል።

We recommend to visit

Books only!

This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !

Join and share @Books_worldd

አስተያየት @BooksWorlddd_bot !

@books_worlddd መወያያ ግሩፕ

#share

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Last updated 6 months ago

?"እውቀት የነብያት ውርስ ነው። ኡለሞች ደግሞ የነብያት ወራሾች ናቸው። እውቀትን እና የእውቀትን ባለቤቶች መውደድ የነብያትን ውርስ እና ወራሾችን መውደድ ነው።
?በደረጃ የሚለቀቁ
1:-ነህው
2:-ሶርፍ
3:-ተጅዊድ
4:-ተፍሲር
5:-ፍቅህ
6:-አቂዳ
7:-መንሀጅ
8:-ሀዲስ
9:-ሲራ
10:-ሙስጦለህ
11:-ቀዋኢደል ፍቅህ
12:-ኡስሉል ፊቅ
13:-አህላቅ ወል አዳብ
14፡-ስለሴቶቻችን
15:-ንፅፅር

Last updated 2 months, 3 weeks ago