🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

Description
ኦርቶዶክስ ኖት????

የዚህ ቻናል ዋና ዓላማ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮችን እና ትምህርቶችን ለሕዝብ ክርስቲያ ማስተላለፍ ነው።
ቤተሰብ ለመሆን ምንም መስፈርት አያስፈልግም ኦርቶዶክስ መሆን በቂ ነው ::
ለመረጃ
🤳🤳🤳🤳🤳
OWNER 🕺👉 @temaye
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago

2 days, 16 hours ago

💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

4 days, 19 hours ago

ነግሥ፦
0:01 - ሚካኤል ሊቀ መላእክት
0:32 - አርባዕቱ እንስሳ
1:12 - ነቢያት ወሐዋርያት
1:46 - ማኅበረ ቅዱሳን
2:08 - ማርያም እግዝእትነ
2:37 - ረከብኪ ሞገሰ
3:06 - ኀበ ተርኅወ ገነት

3:55 - ስማዓኒ ዜማ
4:58 - ንሽ ስምዓኒ
11:49 - ስምዓኒ ቁም
ማንሻ፦
7:13 - ስቡሕ ወውዱስ ቁም ጉረሮ
7:50 - ስቡሕ ወውዱስ ቁም ጸናጽል
8:36 - ስቡሕ ወውዱስ መረግድ
፪ኛ ማንሻ፦
9:23 - ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ቁም
10:22 - ሃሌ ሉያ ዘውእቱ መረግድ
ነግሥ፦
16:13 - ዳዊት ነቢየ
17:41 - ሚካኤል መልአክ
18:13 - ሰላም ለክሙ
18:54 - ማኅበረ መላእክት
19:28 - ወለወልድ ቃሉ
20:14 - ለገባሬ ኵሉ
21:31 - ዘእምቅድመ ዓለም ነጋሢ
22:04 - ወሰላም ለቅዳሴክሙ
22:56 - ሊቃናተ ነድ
23:42 - ወሰላም ለከናፍሪክሙ
24:29 - ሚካኤል ወገብርኤል
25:08 - ሊቀ መላእክት ሚካኤል
25:45 - ንሥረ እሳት ዘራማ
26:23 - ሰላም ለሚካኤል ዘነድ ሡራሑ
26:58 - ንዌጥን ዝክረ ውዳሴሆሙ
27:29 - ንዌጥን ዝክረ ወድሶታ
28:03 - ማኅፀንኪ እግዝእትየ ማርያም
28:39 - ምንተ አዐሥዮ
29:09 - ይትባረክ ስምኪ ማርያም (ዘላይ ቤት)
(ለአፉኪ)
30:06 - ለዝክረ ስምኪ

4 days, 21 hours ago

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰራት ቅዱስ መላዕክ ማን ይባላል?

1 week, 2 days ago

[📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?

📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
እና የሌሎችንም ...........](https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk)

የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻
👇👇👇

https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk

1 week, 2 days ago

🌎አንዴ ብቻ ይንኩት አለማትን የፈጠረውን ጌታ በሕይወት ያመስግኑ ፣ ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቦታ በጣም ይጠቅማቹሀል !
                 [👇👇👇

.            ✦              ‍ ‍ ‍ ‍                  ,    

.             .   ゚     .         🌑            .           .            

˚                     ゚     .               .      🌎 ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ,                * .                    .           ✦           ˚              *                      .  

.             .   ゚     .             .

,       .                               ☀️                                *         .           .             .                                                               ✦      ,         *   🚀        ,    ‍ ‍ ‍ ‍               .            .                                   ˚          ,                              .                 

*          ✦                                .                  .        .        .     🌑            .           .            

˚                     ゚     .               .](https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk)

1 week, 3 days ago
ዛሬ ምንቀበለው የጾመ ነብያት ምስጢር ምንድነው …

ዛሬ ምንቀበለው የጾመ ነብያት ምስጢር ምንድነው ? 

ጾመ ነቢያት  የገና ጾም ከልደት አስቀድሞ የሚጾም ጾም ነው
ከህዳር 15 ጀምሮ ለ 43ቀናት የሚጾም ሲሆን ፋሲካው  ፍቺው በልደት በዓል ነው ይህም ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳንና ምዕመናን ጾመውታል

ጾመ ነብያት ስያሜውን ያገኘው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት ነው በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምስጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ገዝፎ ጎልቶ እየተመለከቱ ትንቢት ተናገሩ  ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ጾሙ ጸለዩ

ነቢያት ከእመቤታችን ሾለ መወለዱ  ወደ ግብፅ ሾለ መሰደዱ በባሕረ ዮርዳኖስ ሾለ መጠመቁ ብርሃን በሆነው ትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ሾለ ማብራቱ  ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ሾለ መሰቀሉ  ሾለ ትንሣኤው  ሾለ ዕርገቱና ሾለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም..

ለአዳም የተሠጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ በየዘመናቸው አንሥእ ኃይልከ ፈኑ እዴከ እያሉ ጮኹ በጾምና በጸሎት ተወስነውም እግዚአብሔር ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት  በሳምንታት  በወራትና በዓመታት ቆጠሩ ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ሾለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ፬፵፮ ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል

ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር  አያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩ እነ ነቢዩ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለተፈጸመበት ይህ ጾም የነቢያት ጾም ይባላል የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ስለሆነም ጾመ ስብከት ይባላል

የጾሙ መጨረሻ መፍቻ በዓለ ልደት ስለሆነ ጾመ ልደትም ይባላል

🌺 በድጋሚ እንኳን ለጾመ ነቢያት  በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።

ጾም: በፍትሐ ነገስት ዘንድ ጾምሰ ተከልኦተብእሲ እመብልእ በጊዜ እውቅ ፣
ጾም ማለት በታወቀ ዕለት በታወቀ ሰዓት ከምግብ መከልከል ነው ተብሎ ተተርጉሟል።
በመጽሐፈ መነኮሳት ደግሞስለእግዚአብሔር ብለን የምንተዋቸውን ነገሮች በሙሉ ሊያካትት ሊያጠቃልል የሚችል ነገር ነውና ጾም ማለት መተው መከልከል ማለት ነው ። ብለው ይተረጉሙታል። የምግብ ብቻ ሳይሆን ሰውነታችንን ለእግዚአብሔር ከመገዛት ለጽድቅ ሼል ከመትጋት ከሚከለከሉ ነገሮች ሁሉ መከልከል  ነው።
👍በልማደ መነኮሳት ከእንቅልፍ መከልከልም ጾም ተብሎ ተቆጥሯል።
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ኩኑ እንከ ከመ ብእሲ ጠቢብ ዘይጸውም ወይጼሊ፣  እንደሚጾም እንደሚጸልይ ሰው ጠቢባን ሁኑ።
በዚህ አስተምህሮ መሠረት ምዕመናን እንደ ጠቢባን ነቢያት ሐዋርያት ጾምን ገንዘብ በማድረግ ሊመላለሱ እንደሚገባ ያስተምራል።
👉የጾም አጀማመር
ከመብል በፊት የጀመርነው ጾምን ነው።
ሰው በሕይወቱ ብዙ ጊዜ መጾም እንጅ  ብዙ ጊዜ መብላት አይስማማውም ።
ለሰው ልጅ ለባሕዩው የሚስማማው ጾም ነው።
👉ለአዳም ከተሰጡት የመጀመሪያ ትዕዛዛት መካከል ጾም ይገኝበታል። መልካምና ክፉውን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን የሞት ሞትን ትሞታለህ ዘፍ ፪፥፲፯ የሚለው ትዕዛዝ ደግሞ የጾም ሕግ መሆኑን ሊቃውንት ይተረጉማሉ።
ይሕ ጾም መጀመሪው ህዳር፲፭ ሲሆን ፋሲካው በዓለ ልደት ወይም በዓለ ጌና ነው።ለዚህ ጾም መሠረቱ አዳም ነው።በሐሙስ ዕለት ለሚለው ቃል ኪዳን የበቃበት ጾም ነው።
በመጀመሪያ የጾመው አዳም በመሆኑ ፆመ አዳም ተብሎ ይጠራል።ነገር ግን በመጽሐፍ ጽፎ ያስተላለፈው ሙሴ በመሆኑ ጾመ ሙሴ ተብሎም ይጠራል። ዘዳ፱፥፱ ጾመ ነቢያት መባሉ በየዘመኑ የተነሱ ነቢያት ክርስቶስ የሚመጣበትን ለማወቅ ይጾሙት ስለነበረ ነው።ቀዳ.ነገ ፲፱፥፰ ዳን ፲፥፫ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ይህን ጾም ከጾሙት መካከል የመጨረሻ የጾመችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ጌታ ፀንሸ ስወልድ ዝም ብየ እወልደዋለሁን?ብላ ነው የጾመችው ።
ሊቃውንቱ ወለተ ነቢያት ብለው የሚጠሯት ድንግል እመቤታችን የነቢያት ሱባኤ ሊፈጸም የመጣዉን ጌታ እንደፀነሰች ታውቃለች ከአባቶቿ ነቢያት ጋር በሱባኤ ተባበረች።
በዘመነ ወንጌል ደግሞ ሐዋርያት ጹመውታል።
አምላካችን ጾሙን የበረከት፣ የረድኤት ፣የድኅነት

ጾሙን የሰላም ያደርግልን ዘንድ የአምላካችን መልካም ፍቃድ ይሁንልን ከነብያቱ ረድኤት በረከት ያሳድርብን መልካም ጾም መልካም እለተ ቀዳሚት ሰንበት🙏

🪻ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።

https://t.me/zena_tewahido

1 week, 5 days ago
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ …

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ስንክሳር ኅዳር 13

እንኩዋን ለ99ኙ ነገደ መላእክት "ቅዱስ አስከናፍር" እና "ቅዱስ ጢሞቴዎስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

አእላፍ መላእክት

እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጉዋል::

+መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-

1.አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2.ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ)
3.ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ)
4.ኃይላት (አለቃቸው ሚካኤል)
5.አርባብ (አለቃቸው ገብርኤል)

6.መናብርት (አለቃቸው ሩፋኤል)
7.ስልጣናት (አለቃቸው ሱርያል)
8.መኩዋንንት (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9.ሊቃናት (አለቃቸው ሰላታኤል)
10.መላእክት (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::

+ከእነዚህም አጋእዝት: ኪሩቤል ሱራፌልና ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው:: አርባብ: መናብርትና ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው:: መኩዋንንት: ሊቃናትና መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::

+መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::

+ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::

+ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::

ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ (ዘካ. 1:12)
ምሥጢርን ይገልጣሉ (ዳን. 9:21)
ይረዳሉ (ኢያ. 5:13)
እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ (መዝ. 90:11)
ያድናሉ (መዝ. 33:7)
ስግደት ይገባቸዋል (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ. 25:31)
በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::

+"+ አእላፍ +"+

=>ይህ ዕለት በሊቃውንት አንደበት "አእላፍ" እየተባለ ይጠራል:: በሃይማኖት: በተልእኮትና በምስጋና የሚኖሩ 99ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከበሩበት ቀን ነው:: ምንም እንኩዋን የጐንደሩን ፊት ሚካኤልን ጨምሮ በአንዳንድ አድባራት ታቦቱ ቢኖርም ሲያነግሡ ተመልክቼ አላውቅም::

+ሊቃውንቱ በማሕሌት: ካህናቱም በቅዳሴ እንደሚያከብሯቸው ግን ይታወቃል:: ሕዳር 13 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ13 ወርሃዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::

+ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳን መላእክትን በስምና በማዕረግ እንደሚነግረን ሁሉ በማሕበር (በትዕይንት) አገልግሎታቸውም ይነግረናል:: ለምሳሌ:-

ያዕቆብ= በረዥም መሰላል ሲወጡና ሲወርዱ ተመልክቷል:: (ዘፍ. 28:12)
ኤልሳዕ ለግያዝ አሳይቶታል:: (2ነገ. 6:17)
ዳንኤል ተመልክቷል:: (ዳን. 7:10)
በልደት ጊዜ በዝማሬ መገለጣቸውን ቅዱስ ሉቃስ ጽፏል:: (ሉቃ. 2:13)
*ዮሐንስ በራዕዩ አይቷቸዋል:: (ራዕይ. 5:11)

+ከዚህም በላይ በብዙ የመጻሕፍት ክፍል ተጠቅሰዋል:: ቅዱሳን መላእክተ ብርሃን: መንፈሳውያን: ሰባሕያን: መዘምራን: መተንብላን (አማላጆች) ተብለውም ይጠራሉና ያስቡን ዘንድ ልናስባቸው ይገባል::

+"+ ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ +"+

=>የዚህ ቅዱስ ሰው ሕይወት ታሪክ ደስ የሚያሰኝና የሚያስተምር ነው:: ቅዱሱ የገዳም ሰው አይደለም:: በሮም ከተማ እጅግ ሃብታም: ባለ ትዳር: የአንድ ልጅ አባትና የከተማዋ መስፍን ነው:: ይህ ሰው በጣም ደግና አብርሃማዊ ነው::

+ከጧት እስከ ማታ ነዳያንን ሲቀበልና ሲጋብዝ ነበር የሚውለው:: ነገር ግን አንድና ብቸኛ ልጁ መጻጉዕ (ድውይ) ሆነበት:: ለ35 ዓመታትም ከአልጋ ላይ ተጣብቆ ይኖር ነበር:: ቅዱስ አስከናፍር ግን ፈጣሪውን ያማርር: ደግነቱን ይቀንስ ዘንድ አልሞከረም:: አሁንም ነዳያኑን ማጥገቡን: እንግዳ መቀበሉን ቀጠለ እንጂ::

+በዚያ ወራት ደግሞ በሮም ግዛት ቁዋንጃ የሚቆርጡ: ሰው እየገደሉ የሚዘርፉ 13 ሽፍቶች ነበሩ:: ስለ ቅዱስ አስከናፍር ደግነት ሰምተው ገድለው ይዘርፉት ዘንድ ተማከሩ:: የሠራዊት አለቃ በመሆኑ በማታለል ሔዱ::

+መነኮሳትን ይወዳልና 13ቱም ልብሰ መነኮሳትን ለብሰው: ሰይፎቻቸውን ደብቀው: ከበሩ ደርሰው: "የእግዚአብሔር እንግዶች ነን: አሳድረን" አሉት:: ቅዱስ አስከናፍር ድምጻቸውን ሲሰማ ደነገጠ::

+ብቅ ብሎ አያቸውና "ጌታየ! ምንም ኃጢአተኛ ብሆን አንድ ቀን ወደ ባሪያህ እንደምትመጣ አምን ነበር" ሲል በደስታ ተናገረ:: እንዲህ ያለው ሽፍቶቹ 13 በመሆናቸው ጌታ 12ቱን ሐዋርያት አስከትሎ የመጣ መስሎት ነው::

+ወዲያውም ወደ ቤቱ አስገብቶ እግራቸውን አጠባቸው:: የእግራቸውን እጣቢ ወስዶም በልጁ ላይ አፈሰሰበት:: ድንገትም ለ35 ዓመታት አልጋ ላይ ተጣብቆ የኖረው ልጅ አፈፍ ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳ::

በዚህ ጊዜ ቅዱስ አስከናፍር ለ13ቱ ሽፍቶች በግንባሩ ሰገደ:: ሽፍቶቹ ግን ነገሩ ግራ ቢገባቸው ደነገጡ::

+ጌታ 12ቱን ሐዋርያት አስከትሎ መምጣቱን የሰሙ የሃገሩ ሰዎችም እየመጡ ይሰግዱላቸው ገቡ:: በዚህ ጊዜ ሽፍቶቹ ልብሳቸውን አውልቀው እውነቱን ተናገሩ:: "እኛ ሽፍቶች ነን:: የመጣነውም ልንገልህ ነው:: አምላክ ግን ባንተ ደግነት ይህንን ሁሉ ሠራ:: አሁንም እባክህ ትገድለን ዘንድ ሰይፋችንን ውሰድ" አሉት::

+እርሱ ግን "ንስሃ ግቡ እንጂ መሞት የለባችሁም" ብሎ: ስንቅ ሰጥቶ አሰናበታቸው:: 13ቱ ሽፍቶችም ጥቂት ምሥሮችን ይዘው ወደ ተራራ ወጡ:: ምስሩን በመሬት ላይ በትነው ማታ ብቻ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት ተጋደሉ:: በዚህች ቀንም 13ቱም በሰማዕትነት የክብር አክሊልን ተቀዳጁ:: ቅዱስ አስከናፍርም በተቀደሰ ሕይወቱ ተግቶ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::

+"+ ቅዱስ ጢሞቴዎስ +"+

=>ይህ ቅዱስ አባት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በዘመነ ሰማዕታት የነበረ የእንጽና (ግብጽ) ክርስቲያን ነው:: በጐ ሕይወቱን የወደዱ አበው በወቅቱ የከተማዋ ዻዻስ: የሕዝቡም እረኛ እንዲሆን መርጠው ሾሙት::

+ጊዜው የመከራ በመሆኑ ከትንሽ ጊዜ በሁዋላ የከተማው መኮንን ክርስቲያኖችን ይገድል ገባ:: ቅዱስ ጢሞቴዎስንም "ክርስትናህን ካልካድክ" በሚል አሠረው:: ጧት ጧት እያወጣም ደሙ እስኪፈስ ድረስ ይገርፈው ነበር:: ደቀ መዛሙርቱንም አንድ አንድ እያለ ፈጀበት::

+ቅዱሱ ግን በትእግስት ሁሉን ቻለ:: በዚህ መካከል ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ነጻ ወጣ:: ያን ጊዜም ሕዝቡን ሰብስቦ ጸሎትን አደረገ:: "ጌታ ሆይ! ይህንን መኮንን እባክህ ማርልኝ? ያደረገው ነገር ሁሉ ባለ ማወቅ ነውና
https://t.me/zena_tewahido

1 week, 5 days ago

……………………………………………………………………… #ህዳር_የቅዱስ_ሚካኤልን_ክብረ_በዓል#ለምንድን_ነው_የምናከብረው**??
………………………………………………………………………
የሥሙ ትርጓሜ መኑ ከመ አምላክ (ማን እንደ እግዚአብሔር  ማለት ነዉ)
መጋቢ ብሉይ እየተባለም ይጠራል
ህዳር 12 የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓላት ከሚከበሩበት ቀናቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዚህ ዕለት ለምን እንደምናከብር እና በዕለቱ ምን ምን የተደረገበት ዕለት እንደሆነ እንመለከታለን።

(1) => በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል
ህዳር 12 በዚህ እለት መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመበት እለት ነው፡፡

(2) => ቅዱስ ዱራታዎስ ቴዋብለት(ቴውብስታ) ቤት የተገለጠበት እና ቤታቸውን የባረከበት ዕለት ነው።

እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዋብለት ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያረጉ ነበር፡፡ ከዚህምወ በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ በዚህም የተነሳ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን አጡ፡፡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስን ወደ በጎች እንዲሔድና በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ አዘዘው፤ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሔዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ አዘዘው፡፡ መልአኩም ወደ ቤት ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አስጠነቀቀው፡፡ ወደ ባለ ስንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በእርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ፡፡

ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ፤ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደው አደረገ፡፡ የተራቡ ድሆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው ዱራታዎስንም የዓሳውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፤ በሰነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሳው ሆድ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዋብስታን እንዲህ አላቸው፡፡ ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሳውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ፤ እግዚአብሔር አስባችኋልና በጎ ሥራችሁን መስዋዕታችሁን ምጽዋዕታችሁን በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፡፡ በኋላኛውም መንግስት ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል፡፡›› ብሎ ባርኳቸው ከእንርሱ ተሰወረ።

(3) => የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በባህር ሲጓዙ የተጨነቁትን የተራዳበት ዕለት ነው።

በአንድ ዘመን ብዙ ሰዎች ከግብፅ አውራጃ መጥተው ወደ ባሕር ማዶ ሄዱ፡፡ ከባሕሩም በደረሱ ጊዜ በመርከብ ላይ ተሳፍረው ከየብሱ ጥቂት በራቁና ወደ ባሕሩ መካከል በደረሱ ጊዜ ጽኑ ነፋስ ተነሳባቸው ለመስጠም እስኪ ደርሱ ድረስ፡፡
የማዕበሉ ሞገድ እየጨመረ እየጸና ከፍ አለ፡፡ ታላቅም ማዕበል መጥቶ ሊገለብጣቸው ደረሰ፡፡ ፍጹም ጥፋትና ክፉ ሞት እንደ መጣባቸው ባዩ ጊዜ ጽኑ ሐዘን ያዛቸው፡፡ የሚያድናቸው የሚያጽናናቸው አጥተው ተስፋ ቆረጡ፡፡ ያን ጊዜ እንዲህ ብለው ጮኹ፡፡ ‹‹የመላእክት አለቃቸው ግሩም ገናና የምትሆን ሚካኤል ሆይ የተአምራትና የይቅርታ መልአክ ነህና፡፡ ልዑል ቸርነቱን የሚገልጥብህ መልአክ ሆይ! እግዚአብሔር ፍቅሩን የሚያስታውቅብህ መልአክ ሆይ ወደኛ ተመልከት እርዳን፡፡ የተጨነቅን እኛን አድነን፡፡ ከመጣብን ሞትና ጥፋት እንድን ዘንድ ስለኛ ወደ ፈጣሪህ ወደ ፈጣሪያችን ወደ እግዚአብሔር ለምንልን፡፡ አሁን የሞት መጋረጃ ዓይናችንን ሸፍኖታልና፡፡ ፍጹም የጥፋት ጥላንም አይተናታልና›› ብለው በፍጹም ልቦናቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡ በመርከብ ውስጥ ያሉት ሁሉ ጽኑ ለቅሶ እያለቀሱ መራራ እንባ እያፈሰሱ ጮኹ፡፡
ከባሕር ጽኑ ማዕበል ከሞት ያድናቸው ዘንድ ያን ጊዜ በዚያች ሰዓት እግዚአብሔር የልቦናቸውን ሐዘንና ልመናቸውን ሰማቸው፡፡ ያን ጊዜም ይገዳቸው ዘንድ ቸር መልአኩን ሚካኤልን ላከላቸው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወረደ መርከቡን በእጁ ይዞ ሳበው፡፡ በመርከቡ ውስጥ ያሉትንም ወደ የብስ አወጣቸው፡፡ በደኅናቸው ተሻገሩ፤ ክፉ ነገር ጥቂትስ ስንኳ ፈጽሞ አላገኛቸውም፡፡

(4 ) => እስራኤልን ከግብፅ እየመራ ወደ ሀገራቸው ያስገባበት ዕለት የሚታሰብበት እለት ነው
ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጡትን ሕዝብ እግዚአብሔር ቀኑን በደመና ዓምድ ሌሊቱን ደግሞ በብርሃን ዓምድ መርቷቸዋል እስራኤል ዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው መና ከሰማይ ያወረደላቸው ተአምራትን ያደረገላቸው ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ርስታቸው የመራቸው በደመና መጋረጃ የጋረዳቸውበክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይ የተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው።

ስለዚህም እኛ የተዋህዶ ልጆች ህዳር 12 ቀን በየዓመቱ በማኅሌት እና በቅዳሴ የምናከብረው በዓለ ሹመቱን በማሰብ ቴዎብስታ ዱራታዎስ ያደረገው ታምረ እና በባህር የተጨነቁትን ያዳነበትን እና ሌሎችም በቀኑ የተደረጉትን ለመዘከርና ለማሰብ ነው።

በተጨማሪም ከገናናው መልዓክ ከቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከቱን ለማግኘት ነው።

የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ሚካኤል ምልጃና ፀሎት ከሁላችን ጋር ይሁን በዓሉም የሠላም የፍቅር ያድርግልን። አሜን

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
     ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
     ።።።።። #ወለመስቀሉ -ክቡር።።።።።።**

1 week, 5 days ago
🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤
1 week, 5 days ago
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ …

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ስንክሳር ኅዳር 12

ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት

ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::

+ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::

+በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል:: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)

+ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::

+"+ ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ +"+

=>ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን እንደ ረዳው ታስተምራለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በመጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 5 ላይ እንደ ተጻፈው ቅዱሱ መልአክ ለኢያሱ ተገልጦለታል:: እሥራኤልን በምድረ በዳ የመራ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ሲያርፍ ታላቅ ሐዘንና ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር::

+እግዚአብሔር ግን ኢያሱን አስነስቶ አረጋግቷቸዋል:: ቅዱስ ሚካኤል 40ውን ዘመን እሥራኤልን ደመና ጋርዶ: መና አውርዶ: ክንፉን ዘርግቶ: ጠላትን መክቶ ከሙሴ ጋ እንደ መራቸው ከኢያሱ ጋርም ይሆን ዘንድ ከሰማይ ወረደ::

+በኢያሪኮ አካባቢም የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በግርማ ለኢያሱ ታየው:: ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ "አንተ ከእኛ ወገን ነህን? ወይስ ከጠላቶቻችን?" ሲል ጠየቀው:: ቅዱስ ሚካኤልም መልሶ "እረዳህ ዘንድ እነሆ የሠራዊት አለቃ ሆኜ ተሹሜ መጥተቻለሁ" አለው::

+ያን ጊዜ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ በግንባሩ ተደፍቶ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰገደለት:: ቅዱሱ መልአክም አክሎ "ፍታሕ ቶታነ አሳዕኒከ እም እገሪከ: እስመ ምድር እንተ ትከይዳ ቅድስት ይዕቲ - የረገጥካት ምድር የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ" አለው::

+ኢያሱም የተባለውን አደረገ:: ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን "ለመላእክት የጸጋ (የአክብሮ) ስግደት ይገባል: በቅዱሳኑ ፊትም ጫማ ተለብሶ አይቆምም" የምትለው:: ያ መሬት ሊቀ መላእክት ቢቆምበት ተቀድሷል:: ዛሬም ቤቱ በታነጸበት: ታቦቱ በተቀረጸበት ቦታ ሁሉ ቅዱሱ መልአክ አለና ጫማን አውልቆ: ባጭሩ ታጥቆ መግባት ይገባል::

+ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከኢያሱ ጋር ሆኖ አማሌቅን ጨምሮ የእሥራኤልን ጠላት አጥፍቷል:: ጥቅመ ኢያሪኮን (ቅጥሩን) አፍርሷል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: በገባኦን ፀሐይን: በቆላተ ኤሎምም ጨረቃን ሲያቆም ከእርሱ ጋር ሆኖ ረድቶታል::

+"+ ዱራታኦስና ቴዎብስታ +"+

=>ቅዱሳኑ ዱራታኦስ (ዶርታኦስ) እና ቴዎብስታ (ቴዎብስትያ) የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ናቸውና በዚህች ዕለት ይታሰባሉ:: በድርሳነ ሚካኤልና በመጽሐፈ ስንክሳር ተጽፎ እንደምናገኘው 2ቱ ቅዱሳን በተቀደሰ ትዳር ተወስነው: ሕጉን ትዕዛዙን ፈጽመው: ለነዳያን ራርተው: ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለው የሚኖሩ ነበሩ::

+ይልቁኑ ግን የጌታችን: የእመቤታችንን እና የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ያለማስታጐል ያደርጉ ነበር:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ሐብት ንብረታቸው አልቆ ተቸገሩ:: ግን የጨነቃቸው መቸገራቸው ሳይሆን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ሊያቆሙ መሆናቸው ነው::

+አማራጭ ሲያጡ ተቀምጠው ተመካከሩ:: የቅዱሱ መልአክ ዝክር ከሚቀር ልብሳቸውን (ያውም የክብር ልብሳቸውን) ሊሸጡ ተስማሙ:: በዚህ መሰረት ቅዱስ ዱራታኦስ ወደ ገበያ ሲሔድ ወዳጁ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወረደለት::

+መንገድ ላይም የጦር መኮንን ሃገረ ገዢ መስሎ ተገናኝቶ አጫወተው:: ችግሩን ጠይቆም መፍትሔውን ነገረው:: "እኔ እዋስሃለሁና ለበዓል የሚያስፈልጉህን ነገሮች ሁሉ ገዝተህ አሰናዳ" አለው::

+"እኔ ወደ ቤትህ መጥቼ ስለምስተናገድ አንድ አሣ አምጥተህ አቆየኝ:: እኔ ሳልመጣ ግን አትረደው" አለው:: ቅዱስ ዱራታኦስ የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ ወደ ቤቱ ሲሔድ ድንቅ ነገርን ተመለከተ:: ሚስቱ ቅድስት ቴዎብስታ በቤቱ መካከል ሁና ቤቱ በበረከት ሞልቷል::

+ማሩ: ቅቤው: እሕሉ ሁሉ በየሥፍራው ሞልቷል:: ባልና ሚስቱ ደስ ብሏቸው:: ነዳያንን ሲያበሉ: እንግዳ ሲቀበሉ ዋሉ:: በሁዋላ ያ መኮንን (ቅዱስ ሚካኤል) በቤታቸው መጥቶ ተስተናገደ::

+በእርሱ ትዕዛዝ የአሣው ራስ (ሆድ) ሲከፈት በውስጡ 300 ዲናር ወርቅ (እንቁ) ተገኘ:: ቅዱሳኑ ይህን ተመልክተው ሲደነግጡ ቅዱስ ሚካኤል ክንፉን ዘርግቶ ራሱን ገለጸላቸው:: ደንግጠው በግንባራቸው ተደፉ::

+እርሱ ግን "በተገኘው ሃብት እዳችሁን ክፈሉ:: ከዚህ በሁዋላ ግን በምድር አትቸገሩም:: በሰማይም ክፍላችሁ ከእኔ ጋር ነው" ብሎ ባርኩዋቸው ወደ ሰማይ ዐረገ:: እነርሱም በሐሴትና በበጐ ምግባር ኖረው ዐርፈዋል:: ለርስቱም በቅተዋል::

+"+ ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ +"+

=>የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ::
በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ::
በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ::
በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ::
ምጽዋትን ያዘወተረ::
*አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
¤አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::

+"+ አፄ በእደ ማርያም +"+

=>"በዕደ ማርያም" ማለት "በማርያም እጅ" እንደ ማለት ነው:: እኒህ ሰው የኢትዮዽያ ንጉሥ ሲሆኑ የነገሡትም በ1460 ዓ/ም ነው:: ደጉ አባታቸው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሲያርፉ በመንግስቱ ተተክተው ሃገራችንን አስተዳድረዋል:: ድርሰት ደርሰዋል:: አብያተ መቃድስ አንጸዋል::

+በተለይ ለቅኔ ትምሕርት ማበብ ልዩ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ይነገራል:: ልክ በነገሡ በ10 ዓመታቸው ግን መንግስተ ምድር በቃኝ ብለው በምናኔ በርሃ ገብተዋል:: በዙፋናቸውም አፄ እስክንድር ተተክተዋል:: ጻድቁ ንጉሥ ግን ቅዱስ ሚካኤልን ይወዱት ነበርና በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን በክንፈ ሚካኤል ከክፉው ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም አይለየን::

=>ኅዳር 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ
3.ቅዱሳን ዱራታኦስና ቴዎብስታ
4.አፄ በዕደ ማርያም ጻድቅ
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
6.ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ
7.አባ ፊላታዎስ ሊቀ ዻዻሳት

https://t.me/zena_tewahido

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago