Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
It is all about mood!
ሙድ በምን ይስተካከላል?
የሰው ስሜት ተለዋዋጭ ነው። በሚሰማው፣ በሚያየው ላይ ተመርኩዞ የሰው ስሜት ይቀያየራል። ስሜት በሚበላና በሚጠጣም ይቀያየራል።
ታድያ ሙድ በብዙ ነገር ይስተካከላል። በጸሎት፣ በስፖርት፣ በሥራ፣ በዝማሬ፣ በሙዚቃ፣ በንባብ በመሳሰሉት ሙድ ይስተካከላል።
"በሥራ በፍቅር ግን ለመነሳት
ቆስቋሽ ይፈልጋል የሰው ልጅ እንደሳት "
ብሏል ዕውቁ የበረከተ መርገም ገጣሚ ኃይሉ ገብረ ዮሓንስ (ገሞራው)። ነፍስ ይማር!
ቡና ይሁን ቢራ የሚጠጣው ሙድ ለማስተካከል እንጂ ለስካር አይደለም። ስትጠጣ ሙድ ከማስተካከል አትለፍ። ስትበላሞ የረሃብ ሙድ ከማስተካከል አትለፍ።
ሙድህ ሲደወክ ጸልክይ፣ ዘምር፣ ሙዚቃ ስማ ወይም አንብብ ወይም አሪፍ ፊልም መርጠህ እይ አለያም ከወዳጆች ጋር ተጫወት።
ላወቀበት ሙድን ማስተካከል ቀላል ነው።
ሙድህን ነቃ ነቃ አድርገህ ለማስተካከል ምን ታደርጋለህ?
አሪፍ ሙድ ማስተካከያ ግን የተስተካከለውን ሙድ ረጅም ጊዜ ካንተ ጋር የሚያቆይ ነው።
እና እንዲህ ዓይነት ሙድ ማስተካከያ አለህ ወይ?
ካለህ/ካለሽ ምንድን ነው?
It is all about mood. Control your holiday vibe by controlling your mood.
Get
የዛሬው ደግሞ ልዩ ነው!
ዛሬ ማለዳ 10:35 (4:35 a.m.) ላይ ከእንቅልፍ የቀሰቀሰኝ የመሬት ንቅናቄ ጠንከር ያለና ቆይታውም ረዘም ያለ ነበር።
ስነቃ የመብራት ጌጦቹ ሁሉ እየተነቃነቁ ነው። መሬቷ "ተነሱ!" እያለች ነው።
እንደገናም 11:53 ላይ ተደግሟል።
ይሄ ነገር ድግግሞሹ በዝቷል፣ ጠንከርም ብሏል። ቤቱም ድምጽ አሰምቷል። እንግዲህ መዘጋጀት ነው።
Inefficiency | ብክነት
በብዙ ቦታ ብክነት ተንሰራፍቷል።
ብክነታችን 2/3 ያህል ይገመታል። 67% ብክነት!
ከሀገራችን ዋና ችግሮች አንዱ አባካኝነት ነው። በሀገራችን ጊዜ ይባክናል፣ ገንዘብ ይባክናል፣ ጉልበት ይባክናል፣ ጥሬ-ዕቃ ይባክናል፣ ከሁሉ በላይ ሰው ይባክናል።
ብክነት ማለት ውጤቱ ከግብዓቱ ሲነጻጸር የውጤቱ አንሶ መገኘት ነው። ብክነት ማለት በ1:00 ሰዓት ውስጥ 12 ደንበኛ ማስተናገድ ሲገባህ 4 ብቻ ማስተናገድ ማለት ነው። ይህ የ67% ብክነት ነው።
በታክስ በኩል ያለውን ብክነት ደግሞ እንይ። ጥቅል ደሞዝህ 100,000 ብር ቢሆን 34,338 ብር ያህል ታክስ ትከፍላለህ፣ 7000 ብር ደግሞ ለጡረታ ትከፍላለህ። እጅህ ላይ የሚገባው ደሞዝ 59,660 ብር ያህል ነው። ከዚህ ላይ ደግሞ እቃ ስትገዛ 15% ለVAT ስለምትከፍል 9,000 ብሩ ያንተ አይደለም። በዚህ ስሌት ሲታይ ያንተ ትክክለኛ ለዕቃ ወይም አገልግሎት የምታወጣው ገቢ 50,000 ብር ያህል ነው። የደሞዝህ 50% ብቻ ነው ውጤትን ጥቅም ያለው። ሌላው የታክስ አረፋ ነው። ብክነት ነው።
እያንዳንዱ ደሞዝተኛ ሌላ የራሱን ያህል ደሞዝተኛ ተሸክሟል ማለት ነው። ትልልቁ ደሞዝተኛማ ከአንድ በላይ ትንንሽ ደሞዝተኛ ተሸክሞ እየሮጠ ነው። ይሄ ትልቅ ብክነት ነው፣ አድካሚ ነው፣ ሊቀየር የተገባው ነው። ከዚህ ላይ 10% አስራት ማውጣትን ስትጨምርበት የደሞዝህ ብክነት 60% ይደርሳል። ከዚያ ላይ ማዕድ ማጋራት፣ መዋጮ፣ ቅጣት ስትጨምር 33% ደሞዝህ ነው ጥቅም ላይ የሚውለው። ሌላው 67% ብክነት ነው።
በንጉሡ ዘመን ሢሶ አራሽ የሚባል ነበር አሉ። አርሶ ካገባው ላይ ሢሶውን (33%) ለራሱ አስቀርቶ ሌላውን ለባላባቱ ይሰጥ ነበር። ይህንን ለማስቀረት ነበር አብዮት የፈነዳው ይባላል። ድንቄም አብዮት!
አሁን ህዝቤ ሢሶ አራሽ ዓይነት ነው። ከደሞዙ 67% ያህሉን የሚወስደው ባላባቱ ነው። መንግስታችን እንደ ባላባት ሆኗል። ለዚያውም ጨካኝ ባላባት!
የፋብሪካዎች ዓቅም አጠቃቀም ወርዶ ወርዶ 33% ያህል ነው። ይሄ መቼም አስደንጋጭ ነው። የቻይናዎች የአቅም አጠቃቀም ወደ 100% የተጠጋ ነው።
ሰው ተሰልፎ ስታይ የጊዜ ብክነት እንዳለ ተረዳ። ይህንን ለማሻሻል ምን እያደረግህ ነው? መፍትሔ የሌለው ችግር የለም። ችግሩ አስቦ መሥራት አለመቻል ላይ ነው።
የተራ ጥበቃ ሰልፍ በገቢዎች ቢሮ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ በኢሚግሬሽን፣ በኢትዮ ቴሌኮም፣ በትራንስፖርት፣ ... ጎልቶ የሚታይ ነው። በዚህ ዘመን ብዙ ሰው የተሰለፈበት ወረፋ ማየት የተቋሙን ድንዙዝነት ማሳያ ነው። በዚህ ዘመን ወረፋ ጥበቃ ብርቅ ሊሆን ይገባ ነበር።
እንዴት ብንደነዝዝ ነው በዚህ ዘመን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በየቀኑ በተራ ጥበቃ ሰልፍ የምናስጠብቀው? እንዲህ ያለ መ/ቤት ውስጥ ያሉ ኃላፊዎችን በድንዛዜ ሰበብ ከሥራ ማሰናበት ያስፈልግ ነበር። ችግሩ ሁሉም አንድ ሆኖ ነው።
ፍጥነት ያጣ፣ የተኛ፣ የተንቀረፈፈ፣ የደነዘዘ አገር ላይ ነን። እንዲህ ሲሆን በፈጣኖቹ ለመዳጥ ተዘጋጅተናል።
ግብጽ ሱዊዝ ካናልን ለማስፋት በምን ያህል በጀት እና ጊዜ እንዳጠናቀቀች ታሪኳን ፈትሽ። እኛ የህዳሴውን ግድብ ዛሬም ሳናጠናቅቅ ገንዘብ እንለምንበታለን። What a crisis!
ደንዝዘናል! ባክነናል!
We need Velocity!
አፋር፣ ሶማሊ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ በሥራ ላይ ናቸው። ምርት እያመረቱ ነው።
አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ ውዝግብ ላይ ናቸው። ምርት ቀንሷል፣ የረሃብ አደጋም አንዣብቧል።
ደቡብ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ገና መልክ አልያዙም። አዲስ ጎጆ ወጪ ናቸው።
ሐረሪ ቀዝቅዛለች። የኛ ነች የሚሉም መጥተውባታል። የፖለቲካ አቅሟ ተዳክሟል። ቱርክ ካላነሳት በቀር እንጃላት።
ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ድምጽ አጥፍተዋል።
ሲዳማ ራሱን ጠልፎና አሳስሮ ቁጭ ብሏል። መግቢያና መውጫውን ጠፍሮ ዘግቶ ሐዘን ተቀምጧል።
አሁን የስበት ማዕከሉና ማቅለጫው ያለው አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ላይ ነው። ሁሉም መንገዶችና ትኩረቶች ወደ እነዚህ የአስተዳደር ክልሎች የሆኑ ይመስላል።
በእነዚህ ሁሉ ቦታዎች ያሉት ዋና ዋና ተጽዕኖ ፈጣሪ ኃይሎች እነማን ናቸው?
If you take care of the top line, you can control the bottom line ያለው ማን ነበር?
ሲስተም ይኑርህ!
ትልልቅ ነገሮች በስርዓት የሚመሩ ናቸው። ስርዓት የስኬት መሠረት ነው። ስርዓት የረብሻ ጠላት ነው።
የመሬትና የፀሓይ ግንኙነት ስርዓት አለው። የወቅቶች መፈራረቅ ስርዓት አለው። መሽቶ የመንጋት ጉዳይ ስርዓት አለው።
ሰውነትህም ስርዓት አለው። የአተነፋፈስ ስርዓት አለህ፣ የደም ዝውውር ስርዓት አለህ፣ የነርቭ ስርዓት አለህ፣ የምግብ አፈጫጭና አሰለቃቀጥ ስርዓት አለህ።
መንግስትም፣ ቤተሰብም፣ ዓለምም ሁሉም የሚተዳደሩት በስርዓት ነው።
ሲስተም (ስርዓት) የሌለው ጉዳይ ለችግር የተጋለጠ ነው። ለዚህ ነው ባንኮች ስርዓት ለሌለው ንግድ ለማበደር ዳተኛ የሚሆኑት።
ስርዓት ካለህ ሠራተኞች ይታዘዙሃል፣ አለቆች ያከብሩሃል፣ ባንክ ያበድርሃል፣ ደንበኞች ይጎርፉልሃል።
ስርዓት ግን ምንድን ነው?
ስርዓት አንድ የታወቀን ዓላማ ለመፈጸም በታወቀ መልኩ በተከታታይነት የሚከወን የተለያዩ አካላት ተናብበውና ተጣጥመው በተቀናበረ መልኩ የሚከውኑት ተግባር ነው።
የተለያዩ አካላት ካልተጣጣሙ፣ ካልተናበቡ የስርዓት ችግር አለ። የታወቀ ዓላማ ከሌለ ስርዓት አለ ለማለት አይቻልም። የተለያዩ አካላት ተግባራቸውን የሚፈጽሙበት መንገድ የታወቀ ካልሆነ፣ ተከታታይነት ከሌለው የስርዓት ችግር አለ።
አሁን የመንግስታችን አሠራር ከዚህ አንጻር ሲቃኝ ምን ይመስላል? ስርዓት አለው ወይ? ውሃ ክፍሉ እና የመንገድ ባለስልጣኑ አይናበቡም። የታክስ ቢሮው ባልተገመተና በማይታወቅ መልኩ የታክስ ተመኑን እንዳሻው ይቀያይራል። የትራፊክ ፖሊሶቹ መንገድ ማስተናበር ትተው ከአቅጣጫህ ውጪ ጠርተው ያጋጩህና መንገድ ያስዘጉሃል። ጉድ እኮ ነው!
በ4:00 ሰዓት በረራ ዱባይ ሂድልኝና ጉድ ተመልከትልኛ! በዱባይ ፖሊሶቹን ችግር ካልተፈጠረ በስተቀር አታያቸውም። በየቦታው "ና ተፈተሽ!" የሚልህ የለም። ያለስጋት ከተማውን ስትዞር ብትውል ጫፍህ ላይ የሚደርስ የለም። ዕቃ ርካሽ ነው፣ ሀገር ሰላም ነው። ያ ሁሉ ደግሞ ታክስ ሳትከፍል እየኖርህ ነው።
በዱባይ "ታክስ መክፈል የዜግነት ግዴታ ነው" የሚል የቀልድ መፈክር የለም። በዱባይ ከደሞዝህ ላይ ታክስ አይቆረጥም። እንዲያውም በዜግነትህ የሚሰጡህ ብዙ ጥቅሞች አሉ።
ዱባይ ከተባበሩት ዐረብ ኤመሬቶች አንዷ ነች።
በቅርቡ የዱባይ እና የአቡዳቢ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ የሚል ወሬ ሽው እያለ ነው። ከእነ ሲስተማቸው ከመጡልን እሰየው ነው። በመጀመሪያ ግን የገቢዎች ቢሮ ሲስተምን ቢለውጡልን ጥሩ ነው።
እንዲያውም ለምን የእኛ የገቢዎች ቢሮ በዱባይ ሰዎች ለምን አይመራም? እስኪ ከምርጫው በፊት ለ1 ዓመት ቢሞከር ጥሩ አይመስላችሁም?
አጼ ቴዎድሮስ ጆን ቤል እና ፕላውዴን የሚባሉ አማካሪዎች ነበራቸው። አጼ ዮሓንስ እንኳ ምክር የሚሰሙ አይመስሉም። አጼ ምንሊክ አልፍሬድ ኢልግ የተባለ የስዊዝ አማካሪ ሰው ነበራቸው። ጃ ምክር በምክር ናቸው። በደርግ ዘመንስ የጦር አማካሪ ከውጭ ሀገር ስናስመጣ ከርመን የለ?
እናም የገቢዎች፣ የኢንዱስትሪ፣ የንግድ፣ የቱሪዝም፣ የሰላም፣ የትራንስፖርት ሚ/ር መ/ቤቶች ከዱባይ አማካሪ ቢያስመጡ ጠቃሚና ዜጋውን የሚያሳርፍ ስርዓት ይዘረጉልናል ብዬ አምናለሁ።
እኔ ራሴ ለዚህ ሀሳቤ ሊከፈለኝ አይገባም? 🤔
ግዴለም እንዲህ ዝብርቅርቅ ባለ አካሄድ ሩቅ አንጓዝም። የሚሻለው አማካሪ መያዝ ነው።
አማካሪ ይዘን እድገት በሚያመጣ ስርዓት በሰላም ታክስ ሳንከፍል መኖር ይሻለናል። ይህ ደግሞ ቀልድ አይደለም። ይቻላል!
ይህን የመሰለ መሬት፣ ውሃና አየር ይዘን ስንራብ ያሳፍራል።
ችግራችን የሁነኛ ስርዓት እጦት ነው።
ስርዓት የሌለው ህዝብ ምግብ ሳያጣ እርስ በርሱ ይባላል። ስርዓት የሌለው ህዝብ በመሬት ይጣላል። ስርዓት የሌለው ህዝብ በወንዝ ይጣላል። እኛ አሁን የቀረን በአየር፣ በፀሓይ እና በጨረቃ መጣላት ነው።
ግዴለም የዓለም ህዝብን በሰላም የሚያኖሩትን ዱባዮች ጥሩልንና አማካሪ አድርጋችሁ ያዙልን። ታድያ ስሟቸው።
ታክስ ዜሮ ሲሆን ያኔ ዱባዮቹ እንደመጡ እናውቃለን። የቱሪዝም ገቢ ሲጨምር ያኔ ዱባዮቹ እንደመጡ እናውቃለን። የውጭ ሀገር ነጋዴ ሲበዛ ያኔ ዱባዮቹ እንደመጡ እናውቃለን። ፋብሪካ ሲበዛ እና የዕቃ ዋጋ ሲረክስ እና የሥራ ዕድል ሲጨምር ኬንያውያን ለሥራ በሀገራችን ሲርመሰመሱ ያኔ ዱባዮቹ እንደመጡ እናውቃለን።
ዱባዮቹ በምን ይበልጡናል? ዱባዮቹ ስርዓት ያውቃሉ። ከምንም ተነስተው ትልቅ ነገር ይፈጥራሉ። ወደ ውጤት የሚያምዘገዝግ ሀሳብ አላቸው!
እነርሱ ባይሆኑ ኖሮ ፀሓይ፣ አሸዋ እና ባህርን ማን ሀብት አድርጎ በንግድ፣ ትራንስፖርት እና ቱሪዝም ከፍ ያለ ገቢ ያገኝ ነበር?
በነገራችን ላይ የኤመሬትስ አየር መንገድ ከእኛ አየር መንገድ በ5 እጥፍ የላቀ ዓመታዊ ገቢ አለው።
ዝ! ዱባዮቹን ጥሩልንማ።
አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ውጤት ያመጣል!
የኢትዮጵያ ንግድ የአሜሪካ ዓይነት አይደለም፤ የቻይናም ዓይነት አይደለም፤ የህንድም ዓይነት አይደለም።
በየሀገራቱ ያሉት ማህበረሰቦች ያላቸው የኢኮኖሚ እድገት ደረጃ እና የፍላጎት ደረጃ የተለያየ ነው።
አብርሃም ማስሎው የተባለው ሳይኮሎጂስት ስለ ሰው ፍላጎትና ደረጃዎች በፒራሚድ መልክ ካስቀመጠ ቆየ። የሰው ፍላጎት ከታች ሲሞላ ወዳላይ ያድጋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ገና ታች ነው። መብላት፣ መጠጣት፣ መጠለያ ማግኘት፣ መልበስ እና መጋባት ላይ ነው። ይህንን ከተረዳህ የሚያዋጣህን ቢዝነስ መምረጥ ከባድ አይደለም።
ምግብ ቤት፣ መጠጥ ቤት፣ ሪል እስቴት፣ ማሳጅ ቤት፣ የውበት ሳሎን፣ ልብስ ቤት፣ የሙሽራ ልብስ መሸጫ፣ የሰርግ አዳራሽ፣ የሠርግ መኪና ኪራይ፣ የፎቶና ቪዲዮ ስቱድዮ፣ የሠርግ Event ማኔጅመንት ዓይነት ናቸው።
ይህንን ተሻግረህ ለSelf Actualization የሚሆን ቢዝነስ ውስጥ ገብተህ ገበያ ጠፋ አትበል። እዚያም ቢሆን ጥቂት ቢሆኑም ሰዎቹ አሉና ፈልገህ ገበያህን ፍጠር።
የቢዝነስ ዘርፍ ምርጫ ከብዙ አንግል የሚታይ ነው።
ለዚህ ነው ዶሮ አርባ የምንልህ!
እስኪ ሰው ከሚባላ ምግብ ይብላ! እስኪ አመራርጦ ይብላ! ቆሎ ይሁን ዳቦ፣ ድንች ይሁን ስጋ አማርጦ እንዲበላ ተጠበብ። አጣፍጥለት፣ ዋጋ አርክስለት።
ዶሮ አርባ! የዶሮ ስጋ አርክስ፣ የመኖ ዋጋ አርክስ፣ ስጋ አርክስ፣ ወተት አርክስ፣ ዳቦ አርክስ። ይህንን ለማድረግ ግን ብዙ ሥራ አለው። Work on the value chain.
ለዚህ መንገዱን ልናሳይህ ልናማክርህ አለንልህ።
ሰሞኑን ፀሓይ እያለ ለምን ይበርደናል? ለምንስ ከሌላው ጊዜ በተለየ ከንፈራችን ይደርቃል?
የሰሞኑ ደረቅ ነፋስ ከወደ ሳይቤርያ የመጣ ነው አሉ። እኔ 'ምለው እነዚያ የሰሜን ተራሮች ይህንን መከላከል አይችሉም ማለት ነው? ቁመና ብቻ!
የብርድ ዓይነት 2 ነው። አንደኛው በመቀት መጠን መቀነስ የሚመጣ ብርድ ነው። ይህ ዓይነቱ ብርድ በክረምት የሚታየው ዓይነት ብርድ ነው። ይህ ብርድ ከንፈር አይሰነጣጥቅም። ምክንያቱም አየሩ እርጥብ ስለሆነ ርጥበታችንን ስለማይወስድብን ነው።
ፀሓይ እያለች የሚበርደው እና ከንፈር የሚሰነጣጥቀው የሰሞኑ ዓይነት ብርድ ግን በአየር ውስጥ ያለው የእርጥበት መጠን ሲቀንስ የሚፈጠር ብርድ ነው። ይህ ብርድ በሚከሰትበት ጊዜ ደመና የለም፣ ንፋሱም የበዛ ነው። አየር ውስጥ ያለውን እርጥበት እና ደመና እንደ ሙቀት ማፈኛ ቁጠረው። የአየር እርጥበት Humidity ይባላል። ይህ በRH የሚለካው የሙቀት መጠን ሲቀንስ አየሩ የሰውነትህን ርጥበት ይሰርቅሃል። ርጥበቱ ከሰውነትህ ሙቀት ይዞ ስለሚሄድ ይበርድሃል፣ ቆዳህም ይደርቃል።
በዚህ ጊዜ የከንፈርህንና የእጆችህን ርጥበት ለመጠበቅም ቻፕስቲክ ወይም ቅባት ተቀባ፣ ውሃም ቶሎ ቶሎ ጠጣ!
የወር የአስቤዛ ወጪዎ ስንት ነው?
ለእንድ ባልና ሚስት ከ4 ልጆች ጋር ያለው ከቤት ኪራይ፣ የትምህርት ቤት ክፍያ እና ትራንስፖርት ውጪ ያለው የወር የአስቤዛ ወጪ ምን ያህል ነው?
ይህ የብዙ ሰው የወቅቱ ጥያቄ ነው። በዚህ ዘመን inflation proof መሆን የቻለ ሰው ጥቂት ነው።
በእርግጥ የየሰዉ አኗኗር ይለያያል። ቢሆንም ግን የወር የአስቤዛ ወጪን ማወቅ ለBenchmark ይረዳል።
ከ2,000 ብር እስከ 80,000 ብር ድረስ ያለ ልዩነት ሰምቻለሁ። ልብ በሉ! ይህ ወጪ የመኖሪያ ቤት ኪራይ፣ የትምህርት ቤት ክፍያ እና የትራንስፖርት ወጪን ሳይሸፍን ነው።
በ2,000 ብር ይኖራል ያሉኝን ያህል ያስገረመኝ የሚኒስትሮች ጥቅል ደሞዝ ከ20,000 ብር በታች ነው መባሉን ስሰማ ነው። አንድ ሚኒስትር ደኤታ ታክስ ተቆርጦ እጁ ላይ የሚደርሰው 12,000 ብር አይሞላም አሉ። እውነት ደሞዛቸው እንዲያ ነው ወይ? በስንት ብር ጤፍ ይገዛሉ? ዘይቱስ? ሽንኩርቱስ? ምስር፣ ሽሮና በርበሬውስ? ቡና እና ስኳሩስ? ሱፍ ልብሱስ በምን ይገዛል? አጃኢብ ነው እኮ?
ለማንኛውም የወር አስቤዛ ወጪዎ ስንት ነው?
_
ማብራሪያ ያለው አስተያየት ይመረጣል።
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад