ሂዳያ መልቲሚዲያ | ʜɪᴅᴀʏᴀ ᴍᴜʟᴛɪᴍᴇᴅɪᴀ

Description
- አንዳንድ ማስታወሻና ምክሮች
- ዳዕዋዎች እና ፈታዋዎች
- ምርጥ ግጥሞች
- አጫጭር የዳዕዋ ቪድዮዎች
- የተለያዩ ደርሶችና ታሪኮች
-ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞች የሚጋሩበት የሆነ ቻናል ነው።

Join እና Share በማድረግ አጋርነታችሁን ግለፁ!!
🔘በተጨማሪም የዩቱብ ቻናላችን ይቀላቀሉ!
https://www.youtube.com/@hidaya_multi

🗳ለአስተያየት @annafiabot ይጠቀሙ!
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago

1 month ago
1 month, 1 week ago
1 month, 1 week ago
1 month, 1 week ago

ልባችን አዝኗል ፤አላህ የተሻለ ይተካላችሁ! !

ከመርካቶ የበለጠ ብዙ ወንጀል የሚሰራበት: አላህ የሚታመፅበት ቦታ ሞልቷል።
አላህ ለምን እንዳመጣው እሱ ብቻ ነው የሚያውቀው።
የሰው እጅ ካለበት፤ የፖለቲካ ፍላጎት ካለበት፤ አድራጊዎቹ ለፍትህ ሊቀርቡ ይገባል ።
በዚህ አይነቱ ጊዜ ሁሉም በአንድነት ሊቆም ይገባል።
ሁሉም ነገር ቦታና ጊዜ አለው።
መርካቶ ውስጥ አንድ ሰው ስለ በደለህ ሁሉንም
አንድ ላይ መፈረጅ ልክ አይደለም።
ለሰው የሚያዝኑ ደሀ የሚረዱ ስንቶች አሉ።
መርካቶ የሁሉም እንደመሆኑ እድገቱም ጉዳቱም የሁሉም ነው ።
አላህ የተጎዳውን ሁሉ ይካስ
አላህ ከመጀመሪያው የተሻለ ያድርግላችሁ

ኡ/ስ አብዱልዋሲእ ሼኽ ነስሮ

📢 :- @menhajadama
ᴄʜᴀɴɴᴇʟ

1 month, 2 weeks ago
ሂዳያ መልቲሚዲያ | ʜɪᴅᴀʏᴀ ᴍᴜʟᴛɪᴍᴇᴅɪᴀ
1 month, 2 weeks ago

📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث الثلاثون

وعن أبي ثعلبة الخشني - جرثوم بن ناشر، رضي الله عنه، عن رسول الله ﷺ قال: «إن الله فرص فرائض؛ فلا تضيعوها، وحد حدودا؛ فلا تعتدوها، وحرم أشياء؛ فلا تنتهكوها،  وسكت عن أشياء؛ رحمة لكم غير نسيان؛ فلا تبحث عنها». حديث حسن رواه دارقطني وغيره.

📗ሀዲስ ቁጥር 30

ከአቢ ሰእለበተ አል ሁሸኒይ - ጁርሱም ኢብኑ ናሺር አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንደተወራው; የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል; ❝አላህ ግዴታ ነገሮችን ደንግጉዋል እንዳታጎድሉዋቸው: ድንበርንም አስቀምጧል እንዳትተላለፉ: አንዳንድ ነገሮችን ሀራም አድርጉዋል እንዳትፈፅሙት: አንዳንድ ነገሮች ላይ ዝም ብሉዋል; ይህም ረስቶት ሳይሆን ለናንተ በማዘን ነውና እንዳትፈላፈሉ::❞ ብለዋል::

ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል ሀዲሱ ሀሰን ነው ተብሏል።

📌ማስታወሻ

- ሀዲሱ ዶኢፍ ነው:: ነገር ግን ውስጡ ያለው መልእክት ቁርአን እና ሌሎች ሀዲሶች የሚደግፉት በመሆኑ ይሰራበታል::
والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 እሁድ | ጥቅምት 10/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ

1 month, 2 weeks ago

📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث التاسع والعشرون

وعن معاذ بن جبل رضي الله عنه قال: قلت؛ يا رسول الله! أخبرني بعمل يدخلني الجنة ويباعدني من النار؛ قال: «لقد سألت عن عظيم؛ وإنه ليسير على من يسره الله عليه؛ تعبد الله ولا تشرك به شيئا؛ وتقيم الصلاة، وتؤتي الزكاة، وتصوم رمضان،وتحج البيت». ثم قال: «ألا أدلك على أبواب الخير؟ الصوم جنة، والصدقة تطفئ الخطيئة كما يطفئ الماء النار، وصلاة الرجل في جوف الليل» ثم تلا {تتجافى جنوبهم عن المضاجع يدعون ربهم خوفا وطمعا}  حتى بلغ {يعملون} ثم قال: «ألا أخبرك برأس الأمر وعموده وذروة سنامه؟» قلت: بلى يا رسول الله! قال: «رأس الأمر الإسلام، وعموده الصلاة، وذروة سنامه الجهاد». ثم قال: «ألا أخبرك بملاك ذلك كله؟» قلت بلى يا رسول الله! فأخذ بلسانه، وقال: «كف عليك هذا». قلت: يا نبي الله! وإنا لمؤاخذون بما نتكلم به؟ قال: «ثكلتك أمك. وهل يكب الناس على وجوههم - أو قال: على مناخرهم؛ إلا حصائد ألسنهم».رواه الترمذي وقال: حديث حسن صحيح

📕ሀዲስ ቁጥር 29

ሙኣዝ ኢብኑ ጀበል አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንዲህ ብሏል; አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ጀነት የሚያስገባኝን እና ከጀሀነም የሚያርቀኝን ስራ ንገረኝ አልኩዋቸው:: እሳቸውም;

❝ትልቅ ነገር ነው የጠየከው: (ይህ ነገር) አላህ ላገራለት ሰው ቀላል ነው::
አላህን በብቸኝነት ትገዛዋለክ: በሱ ላይ ማንንም ሳታጋራ: ሰላትን ቀጥ አድርገክ ትሰግዳለክ: ዘካን ትሰጣለክ: ረመዳንን ትፆማለክ: ሃጅ ታደርጋለክ::❞
አሉኝ::
ከዛም; ❝የመልካም ስራ በሮችን አላመላክትክምን? ፆም ጋሻ ነው: ሰደቃ ወንጀልን ታጠፋለች ውሀ እሳትን እንደሚያጠፋው: የለሊት መሀል ላይ የሚሰገድ ሰላትም እንደዛው:: ❞ አሉና; {ጎናቸው ከመተኛ የሚላቀቅ የሆኑ(ለሊት ለሰላት መነሳታቸውን} የሚለውን የቁርአን አንቀፅ {በሚሰሩት ስራ አማካኝነት} እስከሚለው ድረስ ቀሩ:: ከዛም ❝የነገሮች ዋናውን: ምሰሶውን እና የላይኛው ሻኛውን አልነግርክምን?❞ አሉኝ:: እኔም; እንዴታ! ንገሩኝ እንጂ አንቱ የአላህ መልእክተኛ! አልኩዋቸው ❝ የነገሮች ሁሉ ዋናው; ኢስላም ነው: ምሰሶው ሰላት ነው: የላይኛው ሻኛው; በአላህ መንገድ መዋጋት ነው::❞ አሉኝ:: ከዛም ❝የነዚህን ሁሉ መቆጣጠሪያ አልነግርክምን?❞ አሉኝ:: እኔም; እንዴታ! ንገሩኝ እንጂ አንቱ የአላህ መልእክተኛ! አልኩዋቸው:: ምላሳቸውን በእጃቸው ያዝ አደረጉና; ❝ይሄንን ጠብቅ!❞ 👅 አሉኝ:: አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ በምንናገረው ነገር ሁሉ እንጠየቃለን እንዴ??? አልኩዋቸው:: ❝እናትህ ትጣክና! ሰዎች በፊታቸው/ በአፍጢማቸው (ጀሀነም) የሚወረወሩት ምላሳቸው ባጨደችው እንጂ ሌላ በምን ሆነና?!❞ አሉ::

ቲርሚዚይ ዘግበውታል:: ሀዲሱንም ሀሰንም ሶሂህም ነው ብለዋል::

📌ማስታወሻ

- ፆም ጋሻ ነው ማለት; በዱንያ ከወንጀል በአሄራ ከእሳት ምትጠበቅበት ማለት ነው::
- ጂሀድ የላይኛው ሻኛ ነው ሲባል; የእስልምና ጠላቶች ሙስሊሞችን ለማዋረድ ሲዘምቱ ኢስላም የበላይ መሆኑን የምናሳይበት ነው ማለት ነው::
- እናትክ ትጣክና የሚለው አ.ነገር; እንዴት ይሄ ይጠፋካል? ለማለት እንጂ ቀጥታ ትርጉሙ አይደለም የተፈለገበት::
*🧷*ከሀዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍የሰሃቦችን የእውቀት ጥልቀት; የጠየቁት ጥያቄ የሰውን ልጅ መዳረሻ የያዘ መሆኑ

📍ጀነትም መግባትም ሆነ ከጀሀነም መራቅ የፈለገ ሰው ምንጩን የነቢዩ ሱና ማድረግ እንዳለበት

📍ጥያቄ የሚጠይቅን ሰው ማበረታታት እንዳለብን; ትልቅ ጥያቄ ነው የጠየከው በማለታቸው

📍ሙኣዝ የጠየቀውን ጥያቄ ትልቅነት

📍መልካም ስራን ለመስራት አመላክተኝ ላለን ሰው ቀለል አርገን መንገር እንዳለብን; ቀላል ነው በማለታቸው፤
ቀላል የሚሆነው ግን በአላህ እገዛ እንደሆነ; አላህ ላገራለት ሰው በማለታቸው

📍5ቱ የእስልምና ማእዘናት ጀነት እንደሚያስገቡና ከጀሀነም እንደሚያርቁ

📍ወደ መልካም ነገር አመላካች የሆነ ሰው እሱ የሚያውቀውን ነገር ባይጠየቅም ማስተላለፍ እንዳለበት

📍የፆምን የሰደቃ እና ለሊት ሰላት መስገድ ያለውን ደረጃ

📍ተውሂድ የነገሮች ሁሉ ዋና መሆኑን

📍ሰላት የዲን ምሰሶ መሆኑን

📍ጂሀድ አንዱ እስልምና ከፍ የሚልበት ተግባር መሆኑን

📍የምላስ አደገኝነት እና እሱዋን መቆጣጠር እንደሚገባ

📍አንድ ሰው ምክር ወይም እውቀት ልጨምርልክ ሲባል እሺ ማለት

📍የምንመክረውን ሰው ምክር ለመቀበል ዝግጁና ፈቃደኛ መሆኑን መጠየቅ**

والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ጁሙዓ | ጥቅምት 8/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ

1 month, 2 weeks ago
1 month, 2 weeks ago
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago