Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Doctor Alle 8809/ዶክተር አለ 8809

Description
ጤናዎን ያብዛሎ
8809 ዶክተር አለ
መተኪያ ስለሌለው ጤናዎ የሀኪም መፍትሄ የሚያገኙበት የጥሪ ማዕከል 8809 ዶክተር አለ
- አካላዎ ህመም -
- የውስጥ ደዌ
- የስነልቦና ችግር
- እንዲሁም የሚያስፈልግዎ ህክምና የት ሆስፒታል እንደሚሰጥ እንጠቁምዎታለን፡፡
- የውጪ ሀገር ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ባለን ዓለምአቀፍ ኔትዎርክ ሁሉን ያሟላ
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 3 weeks, 6 days ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 weeks ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 day, 13 hours ago

2 weeks, 6 days ago
3 weeks, 4 days ago

✍️ #የስንፈተ #ወሲብ #መድሐኒት #የጎንዬሽ #ጉዳት

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

👉👉 #የስንፈተ ወሲብ ችግር በዋናነት ወደ ብልት የሚደርሰዉ የደም ዝዉዉር እና የነርቭ ስርአት ላይ ተፅእኖ ሲፈጠር ፤በሆርሞን መዛባት እንዲሁም የጡንቻ መዛል ሲኖር ሊከሰት ይችላል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ያለ ባለሙያ ምክር እና ትዛዝ የተለያዩ መድሃኒቶችን ሲያዘወትሩ ይስተዋላል የነዚህን መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት

👉👉 በሚዋጥ በሚቀቡ ወይም በሌሎች መንገድ የተቀመሙ መዳኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት

🔵 የራስ ምታት
🔵 የደም ግፈት መቀነስ
🔵 የጡንቻ ህመም
🔵 የጀርባ ህመም
🔵 ማዞር እስከ ራስ መሳት የሚያስከትል ሊሆን ይችላል
🔵 የአይን ብዥታ
🔵 የሰውነት መቅላት (መቆጣት)
🔵 የአፍንጫ ማፈን
🔵 ብልት አካባቢ ጤናማ ያልሆነ እብጠት
🔵ብልት አካባቢ ኢንፌክሽን

👉👉 #በጣም #ያልተለመዱ #ወጣ #ያሉ #የጎንዮሽ #ጉዳቶች

🔵 የብልት ከ 4 ሰአት በላይ መነሳት ይህም በብልት አካባቢ ያሉ የደም ስሮች እስከ መበጠስ ሊያደርስ ይችላል
🔵 የእይታ መጣት (አይነ ስውርነት)
🔵 የመስማት ችግር
🔵 ድንገተኛ ሞት

👉👉 ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮች የስንፈተ ወሲብ መዳኒቶች ሙሉ ለሙሉ ከስሩ ችግሩን የማፈታ አይደለም በተጨማሪም ሌሎች ህመሞች ያለባቸው ሰዎች ይህን መዳኒት መውሰድ ፈፅሞ አይችሉም እስከ ሞት የሚያደርስ ውስብስብ ችግሮችን ይዞ ይመጣል፡፡

1 month, 1 week ago
3 months, 1 week ago

✍️ እውቁ ፀሐፊ ፓውሎ ኪሊዮ እዲህ ይላል፤

✍️ ሰዎች እንዲረዱህ ከመጠን በላይ አትድከም ሰዎች እንደሆኑ የሚሰሙት መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ነውና።

✍️ አንድቀን ከእንቅልፍህ ስትነቃ ጊዜህ አልቆ ልታገኘው ትችላለህ፤ ስለዚህ ልታደርገው የምትፈልገውን ነገር አሁኑኑ አድርገው።

✍️ ስኬታማ ለመሆን ከፈለክ አንድ ሕግ አክብር ፈጽሞ ራስህን አትዋሽ።

✍️ የህይወት ምስጢሩ ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው።

✍️ ሕልምህ እንዳይሳካ የሚያደርግ አንድ መጥፎ ነገር አለ "አይሳካልኝም" የሚል ፍርሃት።

✍️ በዓለም ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ሊገባው የሚችለው ቋንቋ አለ "ፍቅር "!

✍️ ስትሸነፍ አይደለም የተሸነፍከው በቃኝ ብለህ ስታቆም እንጂ!

✍️ ምንም ምክንያት ከማያሻቸው ነገሮች አንዱ ማፍቀር ነው።

✍️ አንድ ነገር አስታውስ ልብህ ያለበት ቦታ ሀብትህም ተቀምጧል።

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤

3 months, 2 weeks ago

#በተደጋጋሚ #በሆድ #ጥገኛ #ትላትል #እጠቃለሁ #ምን #ይሻላል?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
#የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በየትኛዉም የእድሜ ክልል የሚከሰቱ ሲሆኑ በዋናነት ክብ እና ጠፍጣፋ በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ወደ ሰዉነት የሚገቡት በቆዳ፣ በአፍንጫ እና በአፍ በኩል በእንቁላል መልኩ ሲሆን ወደ ሰዉነታችን ከገቡ በኃላ በአንጀታችን ላይ ይራባሉ፡፡
#ለሆድ #ጥገኛ #ትላትል #መንስኤዎች
🔹 በንፅህና ያልተዘጋጁ ምግቦችን መመገብ
🔹 የተበከለ ዉሃ
🔹 በደንብ ያልበሰለ ምግብ መመገብ
🔹 በባዶ እግር መሄድ
🔹 የግል ንፅህና አለመጠበቅ
🔹 የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ
🔹 በጥገኛ ትላትሎች ከተያዙ የቤት እንስሳ ጋር መኖር
#ምልክቶች
🔹 የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ
🔹 የምግብ ፍላጎት መቀነስ/መጨመር
🔹 ማቅለሽለሽና ማስመለስ
🔹 የሆድ ህመም/ቁርጠት
🔹 በሰገራ ላይ የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን መታየት
🔹 የሆድ መነፋት እና ጋዝ መብዛት
🔹 በፊንጢጣ ወይም ብልት ዙሪያ ማሳከክ
#የሆድ #ጥገኛ #ትላትሎችን #መከላከል #መንገዶች
🔹 ፍራፍሬዎች ከመመገብ በፊት በደንብ ማጠብ
🔹 ከመመገብ በፊት ምግብን በደንብ ማብሰል
🔹 ፈልቶ የቀዘቀዘ ወይም የተጣራ ዉሃ መጠቀም
🔹 ንፅህና መጠበቅ
🔹 ከመመገብ በፊት፣ ምግብ በሚያበስሉበት ወቅትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅን በዉሃና ሳሙና መታጠብ፤ እንዲሁም የቤት እንስሳዎችን ከነኩ በኋላ እጅን በደንብ መታጠብ፡፡
🔹 በባዶ እግር አለመሔድ እና ንጽህናዉ በተጠበቀ/በታከመ ገንዳ ዉስጥ መዋኘት
#ህክምና
🔹ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች መኖራቸዉ በሰገራ ምርመራ ከተረጋጋጠ በኋላ ለተገኘዉ የትላትል አይነት መድሐኒት እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡
👉 👉 የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በአግባቡ ካልታከመ እና አመጋገብ ካላስተካከልን ከፍተኛ የአንጀት ጉዳት ያስከትላል፡፡

3 months, 2 weeks ago

Follow my tic toc page

4 months, 3 weeks ago
5 months ago

✍️#ካሮትና አቮካዶን ጨምሮ ለአይናችን ጤና እና የእይታ ጥራት የሚረዱ ምግቦች

ለዓይን ጥራት ከፍተኛ ጥቅም አለው በሚል ለምግብነት ከሚውሉት ውስጥ ካሮት ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ ብዙዎቻችን እናውቃለን።
ተመራማሪዎች ከሰሞኑ ባወጡት የጥናት ውጤት ደግሞ ከካሮት በተጨማሪ አትክትሎችን ጨምሮ በርካታ ምግቦች የአይናችንን የእይታ ጥራት እና ጤና ለመጠበቅ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል።

የዓይንን ጤንነት እና የእይታ ጥራት ለመጠበቅ የሚረዱ ምግቦችም፦

1.አቮካዶ
አቮካዶ ሉተን እና ዠያንቲን የተባሉ አንቲ ኦክሲደንት ንጥረ ነገሮችን በውስጡ የያዘ በመሆኑ በብርሃን ምክንያት በዓይናችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት የመከላከል አቅሙ ከፍ ያለ ነው ተብሏል።

በፈረንሳይ የተሰራ ጥናት እንዳመለከተው፥ ዠያንቲን የተባለው አንቲ ኦክሲደንት በዕድሜ ምክንያት የሚከሰት የእይታ ችግር፣ በደም ግፊት፣ ለከፍተኛ የብርሃን ጨረር በመጋለጥ እና በአመጋገብ ችግር በዓይናችን ላይ የሚከሰተውን የጤና ችግር ይከላከላል።
በተጨማሪም አቮካዶ ቫይታሚን ሲ በውስጡ በመያዙ አይናችን ጤነኛ ሆኖ አንዲቆይ እንደሚረዳም ነው ጥናቱ ያመለከተው።

2.እንቁላል
እንቁላል የዓይናችንን ጤና በመጠበቅ በኩል ያለው ጠቀሜታም ከፍተኛ መሆኑ ይነገርለታል።
የቫይታሚን ኤ ምንጭ የሆነው እንቁላል ለዓይን ጤንነት ጠቃሚ ነው የተባለ ሲሆን፥ ልክ አንደ አቮካዶ የእንቁላል አስኳልም ዠያንቲን የተባለው አንቲ ኦክሲደንት በውስጡ በመያዙ በብርሃን ጨረር ምክንያት በዓይን ላይ የሚከሰትን ጉዳት ለመከላከል ይረዳል።

3.ካሮት
ካሮት የዓይናችንን የእይታ ጥራት እንደሚጨምር ከዚህ በፊት ሲነገር የነበረ ሲሆን ፥ በዚህኛው ጥናት ማረጋገጫ ማግኘቱም ተነግሯል።

በቫይታሚን ኤ የበለፀገው ካሮት ቤታ ካሮቲን የተባለ ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ የዓይናችን የእይታ ጥራት ከፍ ያለ እንዲሆን እንደሚያደርገው ጥናቱ አመልክቷል።
በጥናቱ ላይ እንደተመለከተው ቫይታሚን ኤ፣ ቤታ ካሮቲን፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ኤ፣ ዚንክ እና ኮፐር ንጥረ ነገሮችን የሚወስዱ ሰዎች ከአድሜ ጋር ተያይዞ ለሚከሰት የዓይን ችግር የመጋለጥ እድላቸው 25 በመቶ የቀነሰ መሆኑ ተረጋግጧል።

4.አረንጓዴ ሻይ
አረንጓዴ ሻይ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት የሚነገርነት ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ የሰውነትን ክብደት ለመቀነስና የአእምሮን የመስራት አቅም መጨመር ተጠቃሽ ሲሆኑ፥ ከዚህ በተጨማሪም ለዓይናችን ጤንነት ጠቃሚ መሆኑ ተነግሯል።
በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ ያሉት እንደ ቫይታሚን ሲ፣ ሉተን እና ዠያንቲን የተባሉ አንቲ ኦክሲደንቶች ካንሰርን፣ የልብ ህመምን እና የዓይን በሽታን ለመከላከል እንደሚረዱ ጥናቱ አመልክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የሚገኘው ገሎካትቺን የተባለ ንጥረ ነገር ለዓይን ጤንነት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑንም ነው ጥናቱ ያመለከተው።

5 months, 3 weeks ago
6 months, 3 weeks ago

✍️#የጡንቻ #ህመም #ምልክቶች
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
#በቅንነት #ሼር #ያድርጉ
#ድንገት ሰውነትን ሽምቅቅ የሚያደርግ ስሜት አጋጥሞት ያውቃል ወይም ከፍሎ የሰውነት ክፈሎትን በተለይም ጡንቻዎች አካባቢ የህመም ስሜት አስተውለው ያውቃሉ እንግዲያውስ ቀጥሎ የቀረበው ጽሁፍ መልስ ይሆኖታል ይከታተሉን፡-
#ምልክቶች
🔵 የሰውነት ህመም ስሜት
🔵 ሰውነትን እንደተፈለገ ማንቀሳቀስ አለመቻል
🔵 ቁርጥማት
🔵 ብርድ ብርድ ማለት ይጠቀሳሉ፡፡
#መንስኤዎቹ
🔵 ከባድ ስራዎችን ማዘውተር
🔵 ረፍት አለማድረግ
🔵 የመውደቅ ወይም የመመታት አደጋ
🔵 የታይሮይድ ሆርሞን ችግር
🔵 ለኮሌስትሮል ማስተካከያ ተብለው የሚወሰዱ መድሀኒቶች
🔵 የጡንቻ መቆጣት
🔵 የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ሳያሟሙቁ መጀመር
🔵 በሰውነት ውስጥ የፖታሲየም ንጥረ-ነገር እጥረት መከሰት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
#በቤት #ውስጥ #ሊያደርጓቸው #የሚችሉት #መፍትሄዎች
🔵 ረፍት ማድረግ
🔵 የህመም ማስታገሻ መድሀኒቶችን መውሰድ
🔵 የታመመው ጡንቻ ላይ በበረዶ መያዝ ነገር ግን 3 ቀን ካለፈው ለብ ያለ ውሀን መጠቀም
🔵 ሰውነትን ለማሳሳብ መሞከር
🔵 ከባድ ስራዎችን ማቆም
🔵 የዮጋ እንቅስቃሴዎችን መስራት ይጠቀሳሉ፡፡

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 3 weeks, 6 days ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 weeks ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 day, 13 hours ago