Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

Description
እንኳን ደህና መጡ‼

✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed

✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife

ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 2 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 5 days, 7 hours ago

1 week, 5 days ago
የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን ለነዳጅ ማደያዎች ፍቃድ …

የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን ለነዳጅ ማደያዎች ፍቃድ መስጠትን በጊዚያዊነት አገደ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመላው ሃገሪቱ የነዳጅ ማደያ ፍቃድ ባልተፈለገ አቅጣጫ እየሄደ መሆኑን በማረጋገጡ ባለስልጣኑ ለነዳጅ ማደያዎች የሚሰጠው ፍቃድ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲታገድ ማድረጉ ተሰምቷል።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ👇      
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

1 week, 5 days ago

በውስጥ ለጠየቃችሁኝ ለ10 ወራት በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ አዋጅ ከ18 ቀናት በኋላ ግንቦት 30/2016 ይጠናቀቃል።በቀጣይ ምን እንደሚወሰን አይታወቅም።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ👇      
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

1 week, 5 days ago
Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)
2 weeks, 5 days ago
ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የደረሰችበት የባሕር በር …

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የደረሰችበት የባሕር በር መግባቢያ ስምምነት አተገባበር ወደ ኹለተኛ ምዕራፍ መሸጋገሩን አስታውቃለች።

የመግባቢያ ስምምነቱ አተገባበር ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ባሺ ሐጂ ኦማር፣ በመጀመሪያው ዙር የትግበራ ምዕራፍ፣ ስብሰባዎችን የማካሄድ፣ አማራጭ የባሕር ኃይል ጣቢያ ቦታዎችን የመለየት ሥራዎችና የሕዝብ አስተያየቶችን የማካተት ሥራዎች ሲሠሩ እንደቆዩ መግለጣቸውን የራስ ገዟ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ሶማሊላንድ የመጨረሻውን የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም በምትሄድበት ሂደት ዙሪያ የሚያማክራትን አንድ የእንግሊዝ አማካሪ ኩባንያ መቅጠሯንም ሰብሳቢው መናገራቸውን ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የመግባቢያ ስምምነቱ አተገባበር ምን ደረጃ ላይ እንዳለ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ መረጃ ሰጥቶ አያውቅም።

ሱማሊያ በበኩሏ፣ ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ካልሰረዘች በባሕር በር ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር አልነጋገርም በሚለው አቋሟ እንደጸናች ናት።(ዋዜማ)
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ👇*      
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
*ማስታወቂያና ጥቆማ
👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

2 weeks, 5 days ago

ባለቤቱን ቤት ውስጥ ለ6 ዓመታት ቀብሮ ቤተሰቦቿን አረብ ሀገር ሄዳለች ብሎ ያታለለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ ውስጥ አቶ ደበበ ተሰማ እና ወ/ሮ ዝናሽ ባይሳ የተባሉ ጥንዶች ከ2004 ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ አንድ ልጅ አፍርተው በትዳር አብረው ይኖሩ እንደነበር የሸገር ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ  ከ2004 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ሚስት ወ/ሮ ዥናሽ ወደ አረብ ሀገር ሄዳ ነበር፡፡ ከአረብ ሀገር ስትመለስ አንድ ልጅ ወልደው በመኖር ላይ ሳሉ ከቆይታ በኃላ ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ነው ምሽት ላይ  ሚስት በድጋሚ ኮንትራት ስላላት ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ ሀሳብ ታቀርባለች ባል ግን በዚህ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡

ከሀገር መውጣት  እንደማትችል እና እዚው አብረን መኖር አለብን በማለት በሀሳቧ እንደማይስማማ ያሳውቃታል፤ በሁኔታው ወደ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ውስጥ ይገባሉ  ጭቅጭቁ እና አለመግባባቱም ከሮ ባል አካፋ አንስቶ የሚስቱን ጭንቅላቷን ከመታት በሓላ በህይወት ትኑር አትኑር የሚለውን ሳያረጋግጥ ቤት ውስጥ ጭቃ ለመመረግ የተቆፈረ የአፈር ጉድጓድ ውስጥ ይቀብራታል፡፡

ባል ከሶስት ቀን በሓላም ወደ ቤተሰቦቿ በመሄድ ልጃቸው  ወደ አረብ ሀገር እንደሄደች ይነግራቸዋል፤ ቤተሰቦቿም እንዴት ሳትነግራቸው እንደሄደች ላቀረቡለት ጥያቄ እንዳትሄድ እናንተ ስለከለከላቿት ነው ብሎ ያሳምናቸዋል እነሱም ይቅናት በማለት ጉዳዩን እንደተውት የሸገር ከተማ አስተዳደር የህፃናት እና ሴቶች ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር ረቢሱ ደቻሳ ተናግረዋል  ፡፡

በዚህ ሁኔታ ግን ለ6 ዓመት ያህል ቤተሰቦቿ ስለሷ ምንም አይነት መረጃ ባለማግኘታቸው ተጠራጥረው ባልን ይጠይቁታል ባልም እሱ ጋር እንደምትደውል እና የቤት እና የመኪና መግዣ እስኪሞላላት ወደ ሀገር አልመለስ እንዳለችው ለቤተሰብ ይናገራል፡፡

ቤተሰቦቿም በሁኔታው በድጋሚ ጥርጣሬ ውስጥ ስለገቡ ለፖሊስ ያመለክታሉ። ፖሊስም ጉዳዩን ለማጣራት  ኢምግሬሽን እና ዜግነት ምዝገባ አገልግሎት ያመለከትታል በዚህም ወ/ሮ ዝናሽ ወደ ሀገር ውስጥ መመለሷን እንጂ ከሀገር መውጣቷን የሚያመላክት መረጃ እንደሌለ ለፖሊስ መረጃው ይደርሰዋል፡፡

ፖሊስ በቀጥታ ባለቤቷን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማጥራት ሲጀምር አቶ ደበበ ሚስቱን ለስድስት ዓመታት  ቆፍሮ መቅበሩን እና ቤተሰቧን ሲያታልል እንደነበር  ቃል ይሰጣል በዚህ መሰረትም የግለሰቧ አስክሬንም ተቆፍሮ እንዲወጣ የኦሮሚያ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ክትትል በማድረግ ለጳውሎስ ሆስፒታል ፓቶሎጂስቶች አስክሬኑን እንዲመረምሩ በመደረጉ የአስክሬም ምርመራው ለፖሊስ ይደርሰዋል፡፡

የሸገር ከተማ ፖሊስ እና የገላን ከተማ ፖሊስ ባደረጉት ምርመራ ባል ጥፋተኛ መሆኑ በመረጃ በመረጋገጡ የምርመራ መዝገቡን ለሸገር ከተማ ዓቃቢ ህግ ተልኳል፡፡ ዓቃቢ ህግም በአቶ ደበበ ላይ  ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ መስርቶበት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ተከሳሽ ደበበ ተሰማ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የሸገር ከተማ አስተዳዳር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሸገር ከተማ አስተዳደር የህፃናት እና ሴቶች ጉዳይ ፅ/ቤት ሀላፊ ኮማንደር ረቢሱ ደቻሳ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ነው።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ👇*      
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
*ማስታወቂያና ጥቆማ
👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

2 weeks, 5 days ago

ADVERTISMENT

የዋጋ ማስተካከያ የተደረገባቸው እጣዎች ሽያጭ

የዶ/ር አብዱ፣ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት ማህበር ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ሚያዚያ 28/2016 ባደረገው ስብሰባ ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ የእጣ ሽያጭ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ያደረገ ሲሆን እንደሚከተለው መሆኑን እንገልጻለን።

①. ደሴ ገራዶ ጡንጂት አምባ አደባባይ ላይ የሚገኝ 3 መጋቢ መንገድ ያለው የቅይጥ ንግድ ሳይት፤ ፕላን እየተሠራለት ያለ
👉ባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤት፤ አንድ ሱቅ  እና አንድ የጋራ ገቢ ያለው ፍሎር 170 ሺህ ብር

②. ደሴ ገራዶ አዲሱ ምሪት ጡንጅት አምባ ሳይት፤,ካርታ ጨርሰ፤ፕላን እየተሰራለት ያለ እና የሁለት ወር መዋጮ ያለው
👉ባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤት እና 1 ሱቅ 220 ሺህ ብር
👉በለ 3 መኝታ መኖሪያ ቤት እና 1 ሱቅ በ280 ሺህ ብር

ለበለጠ መረጃ በማህበሩ ስልኮች:—
0937411111 ወይም 0938411111 ይደውሉ
ታማኝነት መገለጫችን ነው።

ዶ/ር አብዱ፣ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት የማልማትና የማከፋፈል ህ/ሽ/ማ

3 weeks, 5 days ago
አቶ በረከት ከሀገር ወጠ***‼***

አቶ በረከት ከሀገር ወጠ

የቀድሞ ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር የነበሩትና ከወራት በፊት ከእስር የተፈቱት አቶ በረከት ስምኦን አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።ዛሬ ሚያዚያ 28/2016 ዳላስ ኤርፖርት በወዳጆቻቸው አቀባበል እንደተደረገላቸው ታውቋል።አቶ በረከት በምን ጉዳይ ከሀገር እንደወጡ ለጊዜው አልታወቀም።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ👇      
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

3 weeks, 5 days ago

Update

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዛሬ ባወጣው መግለጫ "የህወሓት ኃይሎች" ከሱዳን ጦር ጎን በቅጥረኝነት ተሰልፈው ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጋር እየዋጉ ነው መባሉን አስተባብሏል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በትናትናው እለት ባወጣው መግለጫ የህወሓት ኃይሎች ከሱዳን ጦር እና ተባባሪ ሚሊሻዎች ጋር ሆነው እየተዋጉት እንደሆነ ማረጋገጡን መግለጹን ተከትሎ ነው።

የሱዳን ጦርነት ከተጀመረበት ከሚያዝያ 2023 ወዲህ የሱዳን ጦር የውጭ ቅጥረኞችን እርዳታ እየፈለገ ነው የሚል ክስ ያቀረበው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር፣ በጦርነት ወቅት ተገድለው የተገኙ ቅጥረኞችን መመዝገቡን ጠቅሷል።

የህወሓት ኃይሎች ከሱዳን ጦር ጎን ተሰልፈው  እየተዋጉ ነው የሚለውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች "መሰረተቢስ ክስ" በጽኑ እንደሚያወግዝ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደገለፈው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ይህን ክስ ያቀረበው፣ በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያለቁበትን የእርስበርስ ጦርነት አለምአቀፋዊ ይዘት በማለባስ በሱዳን ጦር ላይ ለሚያደርገው ዘመቻ ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው ብሏል።

ህወሓት በሱዳን ጦርነት ውስጥ እየተሳተፈ ነው የሚለው ክስ ከቅዥት ያለፈ አለመሆኑን የገለጸው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ህወሓት የፖለቲካ ፓርቲ በመሆኑ ታጣቂ ክንፍ እንደሌለው በግለጽ የሚታወቅ ነው ማለቱን አል አይን አስነብቧል።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ👇      
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

3 weeks, 5 days ago

ታግታ 150ሺ ዶላር የተጠየቀባት የ2 አመት ህፃን ተገኘች።

ታግታ የተወሰደችውን የ2 ዓመት ከ8 ወር ህፃን የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ጋር ባደረጉት የተቀናጀ ጠንካራ ክትትል በሦስት ቀናት ውስጥ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

የ2 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያላት አቢጊያ ዳንኤል የተባለችው ህፃን የታገተችው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሳርቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተወስዳ ነው።

ቸርነት ጥላሁን የተባለው ግለሰብ ከቤተቡ ጋር በነበረው ቅርበት ህፃን አቢጊያን በተለያዩ ቦታዎች እየወሰደ በማዝናናት እንደ ቤተሰቡ አባል ያጫውታት ነበረ።

ከአምስት ወር በላይ ከቤተሰቡ ጋር በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪነት የነበረው ቅርርብ ወንጀሉን በቀላሉ ለመፈፀም ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረለት ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቡ ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ስዓት ተኩል ገደማ ወደ ህፃኗ ወላጆች መኖሪያ ቤት በመሄድና "እናቷ አምጣት ብላኛለች "ብሎ ለቤት ሰራተኛዋ ከነገረ በሗላ ህፃን አቢጊያ ዳንኤልን ወስዶ በማገት ገንዘብ እንዲሰጠው ከወላጆቿ ጋር ሲደራደር መቆየቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪው 150ሺህ የአሜሪካን ዶላር እንዲሰጠው በመጠየቅ ገንዘቡን ማግኘት ካልቻለ ህፃኗን በህይወት እንደማያገኟት ሲዝት እንደነበረ የህፃን አቢጊያ ወላጅ እናት ለፖሊስ በሰጠችው ቃል አስረድታለች ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ህፃኗን ለማስመለስና ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ቀንና ለሊት ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ በተደረገው ክትትልም ዛሬ ሚያዚያ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አለም ሰላም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተጠርጣሪው ተከራይቶ በሚኖርበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ለሶስት ቀናት ያህል ታግታ የቆየችው ህፃን አቢጊያ ዳንኤል ልትገኝ መቻሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ህፃናት ልጆች ለእንደዚህ አይነት ወንጀል ተጋላጭ እንዳይሆኑ እንዲጠብቋቸው አደራ የተሰጣቸው ግለሰቦችም ሆኑ ሞግዚቶችና ወላጆች ነገሮችን በጥርጣሬ በማጤንና የማረጋገጥ ሃላፊነታቸውን በመወጣት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ👇      
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

1 month ago
188 የእሁድ ገበያዎች…

188 የእሁድ ገበያዎች…

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለትንሳኤ በዓል በ188 የእሁድ ገበያዎች ሰፊ የምርት አቅርቦት እንዲፈጠር በዓሉን ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄደው ገበያ ሳምንቱን ሙሉ እንዲካሄድ መፈቀዱን እወቁልኝ ብሏል።ለሚ ኩራ፣ ኮልፌ እና አቃቂ ቃሊቲ የሚገኙት የግብርና ምርቶች ገበያ ማዕከላት በመደበኛነት የተለያዩ ምርቶች በተመጣጣኝ እያቀረቡ መሆኑንና በግቢያቸው ባዛር ጭምር አዘጋጅተው እንዳሉ ቢሮው አሳውቋል።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 2 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 5 days, 7 hours ago