Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

Description
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month, 2 weeks ago

በዚህ ቻናል ሀገራዊና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን በፍጥነት ያገኛሉ❗
የውስጥ መስመር👉http://t.me/ayulaw

Last updated 4 days, 16 hours ago

1 month, 3 weeks ago
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
1 month, 3 weeks ago
የጋዛን ፍርስራሽ ለማጽዳት 14 አመታትን ሊፈጅ …

የጋዛን ፍርስራሽ ለማጽዳት 14 አመታትን ሊፈጅ ይችላል‼️

🗣ተመድ

የእስራኤል እና የሀማስ ጦርነትን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው ጥቃት ያልፈነዱ መሳሪያዎችን ጨምሮ ፍርስራሾችን ለማጽዳት 14 አመታት ገደማ ሊፈጅ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

በጦርነቱ አብዛኞቹ የጋዛ ነዋሪዎች ቤት አልባ እና ተፈናቃይ መሆናቸው ተገልጿል።

በጦርነቱ 37 ሚሊዮን ቶን ገደማ ፍርስራሽ መከማቸቱን በተመድ ማይን አክሽን ሰርቪስ (UNMAS) ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ፒህር ሎሀመር በጀኔቫ በሰጡት ጋዜጤዊ መግለጫ ተናግረዋል።

በጋዛ ምን ያህል ያልፈነዱ የጦር መሳሪያዎች መኖራቸውን መገመት እንደማይቻልም ባለሙያው ገልጸዋል።

ጥቅም ላይ ከሚውሉ ተተኳሾች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ከተተኮሱ በኋላ እንደማይፈነዱ ከዚህ ቀደም የተሰሩ ጥናቶች ያመላክታሉ ሲል የዘገበው ዘ ጋርዲያን ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

1 month, 3 weeks ago
መኪና ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ከፈለጉ ያለምንም …

መኪና ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ከፈለጉ ያለምንም ክፍያ
ይህንን የቴሌግራም መተግበሪያ ይቀላቀላሉ።

https://t.me/Poppycarmarket

☎️ 0911248768   👈 ይደውሉልን

1 month, 4 weeks ago
ያለአግባብ ከተወሰደው ብር 96 ነጥብ 3 …

ያለአግባብ ከተወሰደው ብር 96 ነጥብ 3 በመቶው ተመልሷል‼️

🗣የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ባሳለፍነው መጋቢት ወር ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ባጋጠመ ችግር ምክንያት 801 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ያለአግባብ መወሰዱን ባንኩ አስታውሷል፡፡

ከዚሁ የገንዘብ መጠንም እስከ አሁን 96 ነጥብ 3 በመቶ (771 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር) ተመላሽ መደረጉን የባንኩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ቀሪውን ያለአግባብ የተወሰደ ብር የማስመለስ ሥራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተመላከተው፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

1 month, 4 weeks ago
በ41 ዓመቱ ፈጣኑን የማራቶን ሠዓት ያስመዘገበው …

በ41 ዓመቱ ፈጣኑን የማራቶን ሠዓት ያስመዘገበው አትሌት‼️

🗣ቀነኒሳ በቀለ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን በተካሄደው የማራቶን ውድድር ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ከ2019 ወዲህ ፈጣኑን ሠዓት በማስመዝገቡ አድናቆት ተችሮታል፡፡

አትሌት ቀነኒሳ የዛሬውን የለንደን ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡

የዓለም አትሌቲክስም አትሌቱ የገባበት ይህ ሠዓት ከ2019 ወዲህ ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ዘንድ ሲመዘገብ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለጽ አድናቆቱን ገልጿል፡፡

አትሌቱ ባለፈው የፈረንጆቹ ታኅሣስ ወር ላይ በቫሌንሲያ ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ19 ሠከንድ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን በለንደን ማራቶን ደግሞ ይህን ሠዓት በአራት ሰከንድ ዝቅ በማድረግ አሻሽሎታል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

1 month, 4 weeks ago

ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ናቸው‼️

የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ሩጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በውድድሩ ወቅት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም  መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገውና የአዲስ አበባን ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልለው የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ከዚህ ቀደም በርካታ ህዝብ በብዛት የተሳተፈባቸው ተመሳሳይ  ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ያስታወሰው ፖሊስ በመጪው እሁድ  በከተማችን የሚካሔደው የሩጫ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 

የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

መነሻውን ከመስቀል አደባባይ በማድረግ   በለገሃር ፣ ሜክሲኮ አደባባይ ፣ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ፣ ቄራ ፣ ጎተራ ማሳለጫ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ጥላሁን አደባባይ አድርጎ  መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ውድድር  ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ
•  ከመገናኛ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
•  ⁠ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል
•  ⁠ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ አጎና መስቀለኛ
•  ⁠ከጎርጎሪዎስ አደባባይ ወደ ጎተራ
•  ⁠ከጎተራ ሼል ወደ ጎተራ
• ⁠ከማሞ ማቋረጫ ወደ ጎተራ
•  ⁠ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
•  ⁠ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ በረት
•  ⁠ከመካኒሳ አቦ አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
•  ⁠ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
•  ⁠ከልደታ ፀበል ወደ ኤዩ መብራት
•  ⁠ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደኤዩ መብራት
•  ⁠ከኦርቢስ መታጠፊያ/ጮራጋዝ/ መስቀለኛ ወደ ሲጋራ ፋብርካ
•  ⁠ከጠማማ ፎቅ ወደ ጥይት ፋብርካ
•  ⁠ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ወደ ገነት መብራት
•  ⁠ከከፍተኛ ፍ/ቤት /ባልቻ ሆስፒታል/ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
•  ⁠ከአረቄ ፋብርካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
•  ⁠ከሠንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት
•  ⁠ከበድሉ ህንፃ ወደ ቴሌ ባር
•  ⁠ከብሔራዊ ቲያትር መብራት ወደ ለገሃር መብራት
•  ⁠ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት
•  ⁠ከብ/ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
•  ⁠ከኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ  እንደሚሆኑ እና ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድረስ ጎፋ ማዞሪያ ድልድይ ፣ በቅሎ ቤት ድልድይ እና ጥላሁን አደባባይ ድልድይ አካባቢ ለረዥም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍጽም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል፡፡  በየአካባቢው ለተመደቡ የትራፊክ ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት ተባባሪ በመሆን የሚሰጡትን ትዕዛዝ አሽከርካሪዎች  በማክበር የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ አዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

3 months, 4 weeks ago
"ችግሩ ተስተካክሏል" - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ***‼️***

"ችግሩ ተስተካክሏል" - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ‼️

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ ተፈጥሮ የነበረው ችግር መስተካከሉን ገልጿል።

በዚህም ፦በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ በሲቢኢ ብር  ላይ ተቋርጦ የነበረው አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመሩን አመልክቷል። ባንኩ ተፈጥሮ ለነበረው የአገልግሎት መስተጓጎልም ይቅርታ ጠይቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

4 months ago
የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን …

የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ‼️

37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት የበለጠ ለማጠናከር፣ የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ ለማድረግ ግብረ-ኃይሉ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመስራቱ ለተገኘው ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብሏል መግለጫው።

ለጉባኤው የመጡ እንግዶች በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እጀባና ጥበቃ ማድረጉን የገለፀው የጋራ ግብረ-ኃይሉ መሪዎቹም በሰላም ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

በግብረ-ኃይሉ የተሠራው ፀጥታ የማስከበር ተግባር አፍሪካን ሊወክል እና ሊያኮራ የሚችል በመሆኑ ሀገራችን የአፍሪካ ኅብረትን ለማጠናከር ያላትን ሚና እንዲሁም ቁርጠኝነት ያሳየ ነበር ብሏል መግለጫው።

መላው የሀገራችን ሕዝብ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንግዶችን በክብር ከመቀበል ጀምሮ በየሆቴሎቹ ደረጃውን የጠበቀ መስተንግዶ በማድረግ፣ የሚያልፉባቸው መንገዶች ሲዘጉ በትዕግስት ቅድሚያ ሰጥቶ በማሳለፍ, ከፀጥታ ኃይሉ የሚሰጠውን መመሪያ በቅንነት በመቀበል ትብብራቸውንና አጋርነታቸውን በማሳየታቸው, የፀጥታና ደህንነት አመራሮችና አባላትም በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተመሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በመወጣታቸው ጉባኤው ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላምና በስኬት በመጠናቀቁ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

4 months ago

ለሶማሊያ ፕሬዝዳንት ክስ ኢትዮጵያ ምን ምላሽ ሰጠች‼️

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ በራሳቸው እና በልኡካቸው ላይ ደርሷል ስላሉት መጉላላት ላይ የኢትዮያ መንግስት ምለሽ ሰጠ።

37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን፤ የሶማያሊው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃድ ወደ ስብሰባው እንዳይገቡ የመከልከል ሙከራ እንደተደረገባቸው አስተውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ ከስብሰባው መክፈቻ በኋላ በሰጡት መግለጫ፤ በዝግ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ በሚሞክሩበት ጊዜ የኢትዮያ የጽታ ኃይሎች ካረፉበት ሆቴል እንዳይወጡ መንገድ ዘግተው እንደከለከሏቸው ገልጸዋል።“በሌላ ፕሬዝዳንት መኪና ከሆቴል በመውጣት የስብሰባው ስፍራ ብደርስም፤ የፀጥታ አካት እንዳንገባ ክልከላ አድርገውብን ነበር ብለዋል” ፕሬዝዳቱ በመግለጫቸው።

በኋላ ላይ ግን ፕሬዝዳነቱ ወደ ስብሰባው መግታቸው እና በስብሰባው መክፈቻ እንዲሁም የቤተሰብ ፎቶ ላይም ታይተዋል።የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ከሰዓት ላይ በሰጠው መግለጫውም፤ “የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት እና ልኡካቸው ወደ 2024 የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ እንዳይገቡ ያደረገውን ሙከራ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስ በጽኑ ያወግዛል” ብሏል።የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊት የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ደንብን የሚጥቀስ ነው ያለው የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ የአፍሪካ ኅብረትን የቆየ ባህል የሚቃረን በመሆኑ ህብረቱ ጉዳዩን በገለልተኛ ሆኖ እንደሚረምርም ጠይቋል።

አል ዐይ ኒውስ በጉዳዩ ላይ ከምንግስት ኮሙዩኒኬሽን ባገኘው ምላሽ “የኢትዮጵያ መንግሥት ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ለመጡ ሁሉም ሀገራትና መንግስታ መሪዎች ያደረገውን የክብር አቀባበል ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ማድረጉን አስታውቋል።እንደ አስተናጋጅ ሀገር ኢትዮጵያ የሁሉንም ሀገራትና መንግስታት መሪዎችን በቆይታው ደህንነታውን የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበትም አስታውቋል።ነገር ግን የሶማሊያ ፕሬዝዳት ልኡካን በመንግሥት የተመደቡላቸውን የፀጥታ አካላት አንቀበልም ማለታቸውን ነው አል ዐይን ኒውስ ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ያገኘው መግለጫ ያመለክታል።

ከዚህ በላይ ግን የሶማሊያ ልዑክ የደህንነት አባላት የጦር መሳሪያ ታጥቀው ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመግባት ሲሞክሩ በኅብረቱ የፀጥታ አካላት መከልከላቸውን ገልጿል።በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማያው ፕሬዝዳንት እና የልኡካቸውን ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ እንዳላደናቀፈ እንዲሁም ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊዜ እንዳይገቡ እንዳልከለከለ አሳውቋል።ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ አቋም እንዳላትም ነው የመንስት ኮሙዩኒኬሽን መግለጫ የሚያመላክተው።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ባለው የፈረንጆቹ ጥር አንድ ቀን በፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ ምክንያት ቁጣቸውን ያሰሙት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሸክ መሀመድ ትናንት አዲስ አበባ መግታቸው ይታወሳል።የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ የፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ፣ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ሰጥታ በምላሹ 20 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የባህር ጠረፍ በ50 አመት የሊዝ ኪራይ እንድታገኝ የሚያስችል መሆኑ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።

ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አካል አድርጋ የምታያት ሶማሊያ በስምምነቱ ከፍተኛ ቁጣ በማሰማት ከአምባሳደሯን ከኢትዮጵያ መጥራቷም አይታወሳል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በቀረቡበት ወቅት ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የላትም ብለዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

4 months ago

የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6 እስከ የካቲት 11 ቀን 2016 ድረስ ይሰጣል‼️

የ2016 ዓ/ም የአመቱ አጋማሽ የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከነገ ረቡዕ የካቲት 6 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ተልኮልናል ብለው ያጋሩትን የተሻሻለ የፈተና መርሃ ግብር የተመለከተ ሲሆን በዚህ መርሀ ግብር ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እስካ የካቲት 11 /2016 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

በፈተናው የመጀመሪያ ቀን በሺዎች የሚቆጠሩ የጤና ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ተላከልን ብለው አጋርተውት በተመለከትነው ዳታ ከ6 ሺህ በላይ የነርሲንግ፣ ከ1 ሺህ 900 በላይ የፋርማሲ፣ ከ1 ሺህ 700 በላይ የዶክተር ኦፍ ሜዲስን ተማሪዎች በመጀመሪያው ቀን ፈተናቸውን ከሚወስዱት ውስጥና ከፍተኛውን ቁጥር ከሚይዙት የጤና ትምህርት ዘርፍ ውስጥ ይገኙበታል።

ከዚህ ባለፈ በዘንድሮው የመውጫ ፈተና ከፍተኛ ተፈታኝ ከሚጠበቅባቸው የትምህርት ክፍሎች መካከል አካውንቲንግ ከ8 ሺህ በላይ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ ከ3 ሺህ በላይ ፣ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

በአመቱ አጋማሽ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በአጠቃላይ በሺዎች የማቆጠሩ የመጀመሪያ ዙር እንዲሁም ባለፈው ፈተና ውጤት ሳያመጡ የቀሩ የድጋሜ ተፈታኞች የሚወስዱ ይሆናል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ በአጠቃላይ ፈተናው 47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145  ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች ይፈተናሉ።

በሌላ ለኩል ከጥቂት ቀናት በፊት ፤ " በኦንላይን ለሚሰጥ የአንድ ቀን ፈተና በመቶዎች ኪሎ ሜትር ተጉዘን እንድንፈተን ተነገረን " በሚል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን ያሰሙ ተመራቂዎች አሁን ላይ ፈተናውን ባሉበት ከተማ በተቋማቸው እንዲወስዱ ማስተካከያ መደረጉንና ስም ዝርዝራቸውም መውጣቱን ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚል ከባለፈው አመት ጀምሮ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ተግባራዊ እያደረገ ሲሆን ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ (በአመቱ መጨረሻና አጋማሽ) ላይ ይሰጣል።

(ከላይ ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር እንደተላከላቸው የገለፁትን የ2016 የአመቱ አጋማሽ ተሻሻለ የፈተና መርሀ ግብርን አይዘናል)

@Esat_tv1
@Esat_tv1

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month, 2 weeks ago

በዚህ ቻናል ሀገራዊና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን በፍጥነት ያገኛሉ❗
የውስጥ መስመር👉http://t.me/ayulaw

Last updated 4 days, 16 hours ago