Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

Description
ዲያቆን ፍፁም ከበደ

ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb

facebook Link...
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 2 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 5 days, 7 hours ago

2 days, 17 hours ago

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በይፋ በጀመረው የግንቦት 2016 ዓ/ም ርክበ ካህናት ምልዐተ ጉባኤ ዛሬን ጨምሮ በቀጣይ ቀናት የሚወያይባቸው 21 አጀንዳዎች የሚከተሉት ናቸው፦

  1. የቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ የሥራ ክንውንን በተመለከተ

  2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማትን አስመልክቶ ከቤትና ሕንጻ አስተዳደርና ልማት ድርጅት የቀረበ ሪፖርት በተመለከተ

  3. የሃይማኖት ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ

  4. የገቢዎች ባለሥልጣን የወሰነውን የግብር አከፋፈል ሁኔታ በተመለከተ

  5. አገር አቀፍ የምክክር ኮሚሽንን በተመለከተ

  6. ወደ ውጭ ሀገር ለአገልግሎት የሚላኩ አገልጋዮችን በተመለከተ

  7. የ2017 ዓ.ም በጀት ማጽደቅን በተመለከተ

  8. የስዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅን በተመለከተ

  9. የምግባረ ሠናይ ጠቅላላ ሆስፒታል ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ በተመለከተ

  10. የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አንድነት ገዳም ኅብረት መተዳደሪያ ደንብ በተመለከተ

  11. የጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት ተብሎ የሚጠራበት ስም ቀርቶ የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት አርባ ምንጭ ተብሎ ይጠራልኝ በማለት የቀረበውን ጥያቄ በተመለከተ

  12. የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት ስለ ዚጊቲ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቀረበውን ጥያቄ በተመለከተ

13 ኦሲኤን ቴሌቭዥን አስመልክቶ የቀረበ ጥናት በተመለከተ

14.የብፁዓን አባቶች ዝውውር ጥያቄ በተመለከተ

  1. የእነ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ማመልከቻን በተመለከት

16 ከመሪ እቅድ የሚቀርበውን ዝርዝር የመዋቅር ጥናትና ቻርት በተመለከተ

  1. የመግለጫ አሰጣጥ እና የስብከት ዘዴ ትምህርት አቀራረብን በተመለከተ፣

  2. ሀገራዊ ሰላምን በተመለከተ

  3. የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ግብረ ሰዶማዊነትን በተመለከተ '

20 የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልናና የውስጥ አንድነትን ማጠናከር በተመለከተ

  1. የቋሚ ሲኖዶስ አባላት ምርጫን በተመለከተ

የሚሉት ዋና ዋና የመወያያ አጀንዳዎች ይሆናሉ።

ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን !!

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

2 days, 17 hours ago
ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
3 days, 8 hours ago
  • ምልጃ ለምን ያስፈልጋል +

ለ/ የእግዚአብሔርን ብዙኅ ምሕረት ብዛት / እንድናውቅ ፦

እግዚአብሔር ከበደል በኋላ የሚጸጸት ሰው አለ የማይጸጸትም አለ እንደ በደለ አያውቅምና ። እንደ በደለም እያወቀ ልቡናውን የሚያገዝፍ አለ ። ሰው እንደበደለ በተሰማው በደሉም በቆረቆረው ጊዜ እግዚአብሔርን ይለመናልና ። ሲለምን ግን እግዚአብሔር እንዲሞረው የሚያሳስቡ ከእርሱ የተሻሉትን የሚበልጡትን እግዚአብሔር ደስ የሚያሰኛቸውን ሰዎች በማሳሰብ ነው ። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ምሕረት ተሰፍራ የምትለካ ስላልሆነች ደጋጎቹን ባሰበ ጊዜ ብዙኅ ምሕረቱ ስለሚፈስስ ኃጥአንም ይቅር ይባላሉና ።

#እነ ሙሴ እነዳዊት ስለ እስራኤል ሲለምኑ በደጋጎቹ በኩል አድርገው ነበር ፤ ቅዱሳኑ በአካለ ስጋ ባይኖሩም እንኳን ስለ እነርሱ የሚያደርገው ምሕረቱ በዘመን የማይገታ በመኾኑ ።

"....ዘራቹሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ ይኽችንም የተናገርኳትን ምድር ኹሉ ለዘራቹሁ እሰጣለሁ ለዘለዓለም ይወርሷታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪዎችሆን አብርሃምንና ይሰሐቅን እስራኤልንም አስብ። እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ላያደርግ ስላሰበው ክፍት ራራ። " ዘጸ.32፥13-14  ተብሎ እንደ ተጻፈው በዘመን የማይገታ የእግዚአብሔር ምሕረት በእስራኤል በደል ሳይገደብ በዝቶ የተደረገው ሙሴ አብርሃምን እና ይስሐቅን እስራኤል የተባለ ያዕቆብን አንስቶ ስለ ማለደው ነው ።

ሙሴ የእግዚአብሔር ብዝኅ ምሕረትን በቅዱሳን ስም የሚማለድ መኾኑን ስለ አወቀ አደረገው እንጂ እኔ በቃለሁ አላለም ስለዚህ እግዚአብሔር ምልጃን የፈቀደው በዘመን የማይገታ ምሕረት ያለው መኾኑን አውቀን እንድንጠቀም ነው ። "ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ ለአብርሃም ለዘሩ የዘላለም ምሕረቱን አስቦ እስራኤልን ብላቴናውን ረድቷል ።" ሉቃ 1፥55 እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር በቅዱሳኑ በኩል ዘለዓለማዊ ምሕረትን አድርጓል ። ክብሩ ፣ ገናንነቱ ፣ ጌትነቱ የሚታወቀው በእነርሱ ስም በማለድነው ጊዜ ነው ።

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

1 week, 2 days ago
  • ከክፍ ቀን መውጫ +

  • Sound Recorder +

ከክፍ ቀን መውጫ
ከሞት የሚያድነው
አምላጅነትሽ ለሚተማመነው
አላፈርኩም እኔ ስምሽን ጠርቼ
አዝኜ ብወጣ መጣሁ ደስቼ

አዝ

ልቤ ሰማይ ይሁን ለልጅሽ ዙፍን
አንቺን እንዲያከብር በቀሪው ዘመን
ይሁንልኝ ልቴ የልደቱ ስፍራ
ማረፍያ እንዲሆንሽ ከወለድሽው ጋራ

(#ዲያቆን ፍፁም ከበደ )

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

1 week, 2 days ago

#ምድር ለምለም ሣር ታብቅል አለ ዘፍ 1-11

ምድርን ከማንም ምንም እርዳታን ሳያስፈልጋት በራሷ ታውጣ ማለት ። አንዳንዶች ሰዎች ፀሐይን በምድር ላይ ላለው ምርታማነት ሁሉ ምንጭ እንደሆነች አድርገው ይገነዘባሉ ። እነርሱ እንደሚሉት በምድር እምብርት ውሰጥ ያሉትን ወሳኝ የሆኑ ኃይሎች ወደ ላይ (ወደ ገጸ ምድር ) የሚስበው የፀሐይ ሙቀት ተግባር ነው ።

ነገር ግን ማጌጥ ከፀሐይ መፈጠር በፈት እንደ ነበር ቢያውቁ ። ፀሐይን የሕይወት ምንጭ አድርገው የሚያመልኩ ሰዎች ከስሕተታቸው ይመለሱ ዘንድ የሚከተለው አሳማኝ ምክንያት ነው ። ምድር ከፀሐይ መፈጠር በፈት ያጌጠች መሆኗን በደንብ ቢረዱ ኖሮ ፣ ከፀሐይ መፈጠር በፈት ሣር እና ዕፅዋት መብቀላቸውን ስለሚመለከቱ ለእርሷ ያላቸውን ከመጠን ያለፈ አድናቆት ይቀንሱ ነበር ። (+አፍላጋተ ጥበብ+ "ስለ ስድስቱ ቀን ፍጥረታት ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ እንዳስተማረው" ትርጉም ዲ/ን እንዳለው መለሰ ገጽ 104)

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

እስቲ ይሞክሯት ገባ ብለው ።
ይህቺን ሊንክ 👇

https://t.me/tapswap_mirror_1_bot?start=r_6193689480 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift

1 week, 3 days ago

የሃይማኖት ፍፃሜው ትንሣኤው ነው

የተጻፈ ቢነበብ የተነበበው ቢተረጎም በተተረጎመው ምግባር ቢሠራ የዚህ ሁሉ የሃይማኖት ፍፃሜው ትንሣኤው ነው ። ትንሣኤ ከሌለ ሃይማኖት ሁሉ ከንቱ ነው ። የሃይማኖት የመጨረሻው ዋጋው በትንሣኤ ማክበሩ ነው እንጂ በምድር ማቀማጠሉ አይደለም ። "ወእመሰ ኢትነሥኡ ምውታን ክርስቶስኒ ኢትነሥአ እሙታን ወእመሰ ክርስቶስ ኢትንሥአ እምውታን ከንቱ ሃይማኖትክሙ - ሙታን የማይነሱ ከሆነ ክርስቶስ አልተሣማ ክርስቶስ ካልተሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት" እንዳለ ሐዋርያው (፩ኛ ቆሮ .፲፭-፲፯) ።

ሰው የተፈጠረው ለትንሣኤ ነው ፤ የሚኖረውም ለትንሣኤ ነው ፤ የሚፅናናውም በትንሣኤ ነው ። ጌታም ሥጋውን የበላውን ደሙን የጠጣውን ሰው ስለሚሰጠው ዋጋ ሲናገር እሾመዋለሁ እሸልመዋለሁ ጤና እሰጠዋለሁ ሀብት አድለዋለሁ አላለም ። ይልቁንም "ወበደኃሪት ዕለት አነሥኦ-ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ። እኔም በመጨረሻው ቀን አነሣዋለሁ " (ዮሐ ፮፥፶፬) ። ሌሎች የማያስፈልጉን ሆነው ሳይሆን እነዚያ የፍጡርነት ዋጋ እንጂ የሃይማኖት ዋጋ ስላልሆኑ ነው ። የሃይማኖት ዋጋ በክብር መነሣት ነው (ዮሐ ፭-፳፱) ። (ጸያሔ ፍኖት ርዕሰ ሊቃውንተ አባ ገብረ ኪዳን ገጽ 158-159)

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

2 months, 1 week ago
  • ምልጃ ለምን ያሰፈልጋል +

  • ክፍል ሦስት (3) +

ለመኾኑ ምልጃ ለምን አስፈለገ ? እግዚአብሔር ያለ ሦስተኛ ወገን ሲነግሩት ስለማይሰማ ነውን ? ወይስ የእግዚአብሔር ፍርድ በጠበቃው ችሎት የሚለወጥ ስለኾነ ? ምልጃስ በማጭበርበር ሰነድ በመለወጥ ኃጥኡን ጻድቅ ማድረግ ነውን ? ታድያ ምንድን ነው ምልጃ ? ሰዎች እኛ እግዚአብሔር በቀጥታ ማነጋገር እንችላለን እርሱ ይሰማናል ፤ ስለዚህ ሦስተኛ ወገን አያስፈልግም ይላሉ። በውኑ ምልጃ የሚሹት ወገኖች እግዚአብሔር አይሰማንም ብለው ይኾንን ወይስ ስለ ሌላ ?

ሀ. ድኅነት ሥርዓት ስላለው ?
ለ.የእግዚአብሔርን የምሕረት ብዛት እንድናደንቅ?
ሐ.የእግዚአብሔርን ባለሟሎች ለይተን እንድናቅ ?
መ.ስለ ትሕትና ?

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

2 months, 1 week ago

🎵 የስልክ ጥሪ 🎵

  • የንስሐ ዝማሬ +

  • የጴጥሮስን እንባ +

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

2 months, 1 week ago

🎵 የስልክ ጥሪ 🎵

  • የንስሐ ዝማሬ +

  • በምጓዝበት ተጓዥ +

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

2 months, 2 weeks ago

#በልብህ ብታምን ትድናለህ

"ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔር ከሙታን ለይቶ እንደ አስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ ። በልቡ የሚያምን ይጸድቃልና በአፍ የሚመሰክር ይድናል " ሮሜ 10፥9-10 ። ምን ማለት ? በውኑ መናፍቃን እንደሚሉት ኢየሱስ ጌታ ነው ብቻ በልን የጽድቅን ሥራ ሳትሰራ ትድናለህ ማለት ነውን ? ሌላው በጣም ትኩረት ልንሰጠው የሚገባው ጉዳይ በልቡ የሚያምን ይድናል ማለቱ ምን እንደ ኾነ ማወቅ ነው ።

#ሲብራራ ፦ ኢየሱስ ጌታ እንደ ኾነ በአፍህ ብትመሰክር ማለት "ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ እንደ ኾነ በልብህ ብታምን አንድም የባሕርይ ገዥነቱን ብትቀበል አንድም አብን ጌታ ፈጣሪ ገዢ ጠባቂ አንደምትል ሁሉ እኩል በኾነ መልኩ ወልድንም ብትል ፤ ብለህ ብታምን " ማለት ነው ። በመጽሐፍ ቅዱስ ሰው ኹሉ አብን እንደሚያከብር ወልድንም ያክብር ዘንድ ፍርድን ኹሉ ለወልድም ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው እንኳን አይፈርድም ይላልና ሐዋ 5፥19-25 ።
ይህ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ቀጥሎ እንዲህ የሚል ንባብ አለው ፦ አብ ሙታንን እንደሚያነሳ ሕይወትንም እንደሚሰጥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣል። ይላል። በመኾኑም ይህን ማመን መመስከር ግድ መኾኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል ። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ከልብ አምኖ በአንደበትም መመስከር ተገቢ መኾኑን የሚያስረዳ ነው ። ይህ ከልብ አምነው የሚያቀርቡት ምስክርነት ለሰማዕትነትም ሊያበቃ ይችላል። ብዙ ቅዱሳን ሰማዕታት በአላውያን ነገሥታት ፈት ምንም ሳይፈሩ ስለ ክርስቶስ ጌትነት አምላክነት መስክረው የሰማዕትነትን አክሊል ተቀብለዋልና ። ( ትምህረተ ጽድቅ ገጽ-285፥286

#ይቀጥላል ...

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 2 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 5 days, 7 hours ago