Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

እንማር

Description
@Enmare1988

እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯 መፅሀፎች
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
የተለያዩ PDF መፅሐፍት እንደፍላጎቶ አሉ
    ለ  አስተያየት And promotion ካሎት👇👇   

@Kiya988

https://youtube.com/channel/UCr7-LDddhyqtFUCH0OHhM2Q
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month, 2 weeks ago

በዚህ ቻናል ሀገራዊና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን በፍጥነት ያገኛሉ❗
የውስጥ መስመር👉http://t.me/ayulaw

Last updated 4 days, 16 hours ago

2 weeks, 3 days ago

**ከመጣችበት ታክሲ ወርዳ ልትሻገር ግራ ቀኟን ስትማትር በራሪ መኪናዎቹ አስፈሯት። አንዱ ሲመጣ ይሂድ ብላ ስትጠብቅ... ሌላ ሲመጣ አሁንም ስትጠብቅ... ደቂቃዎች ነጎዱ የመኪናዎቹ ብዛት ደግሞ አልፈው የሚያባሩ አይመስሉም።

"እስከ ስንት ሰዓት እዚህ ተገትሬ ልውል ነው?!" ብላ በሆዷ እያጉረመረመች ፊቷ ያለውን አስፋልት ስታየው ከሶስት ሰፋፊ እርምጃዎች አይበልጥም። እንደምንም ራሷን አደፋፍራ ሮጥ ሮጥ ብላ ተሻገረችና ዞራ በግርምት አስፋልቱን ራሷን እየነቀነቀች ተመለከተችው።

የራሷን ህይወት መሰላት... ግቧ ላይ እንደማተኮር ችግሮቿ ላይ ስትመሰጥ ግቧን ለመምታት ብዙ ዘመን አቃጠለች። ምናልባትም ትኩረቷን ሰብስባ አላማዋ ላይ ብቻ ብታተኩር ኖሮ ያን ያህል ርቆ አይታያትም ነበረ ማለት ነው።

"መገናኛ መገናኛ" የሚል ታክሲ ሲጣራ ስትሰማ ባነነች ደግሞ አሁንም በራሷ አመለካከት ስትመሰጥ ወደፊቷ መባከን ስለሌበት ዳይ! ወደቀጣዩ ታክሲ...

nani**

https://t.me/justhoughtsss

Telegram

Thoughts

ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው እና እናንተስ ጎራ አትሉም? Since: Dec-10-2022 discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk

**ከመጣችበት ታክሲ ወርዳ ልትሻገር ግራ ቀኟን ስትማትር በራሪ መኪናዎቹ አስፈሯት። አንዱ ሲመጣ ይሂድ ብላ ስትጠብቅ... ሌላ ሲመጣ አሁንም ስትጠብቅ... ደቂቃዎች …
2 weeks, 3 days ago
እንማር
2 weeks, 4 days ago

✔️**ሰውዬው ስራ አጥ ነው
ከአንድ ድርጅት ዘንድ ሄዶ "ተላላኪም ቢሆን ቅጠሩኝ" ብሎ ይማፀናል

የድርጅቱ ቀጣሪ "ኢሜይልህን ስጠኝ እና ፎርም እልክልሃለሁ: እሱን ሞልተህ ይዘህ ትመጣለህ" ይለዋል

"ጌታዬ! እኔ ዘመናዊ ስልክ እና ኮምፒውተር የለኝም :ኢሜይልም አልጠቀምም:: ስራው ግን በጣም ያስፈልገኛል" ብሎ ይማፀናል

"ኢሜይል እንኳ ሳይኖርህ ነው እንዴ ስራ የምትጠይቀው!" ብሎ በግልምጫ ያሰናብተዋል*✔️*ሰውዬው ወደ መንደሩ ተመለሰ
ስራ የማግኘት ተስፋው ሲደበዝዝ እጁ ላይ በሚገኘው ብር እንቁላል ቀቅሎ አካባቢው ለሚገኙ ተማሪዎች ማቅረብ ጀመረ: ትንሽ ቆይቶ ትርፉን በማጠራቀም ሌሎች ምግቦችን ጨመረ

እንዲህ እንዲህ እያለ ለትላልቅ ተቋማት እና ዩኒቨርስቲዎች ምግብ የሚያቀርብ ስኬታማ ሰው ሆነ

*✔️****ከአመታት በኃላ ላፈራው ንብረት ኢንሹራንስ ለመግባት ወደ አንድ ድርጅት ጎራ ብሎ ጉዳዩን አስረዳ

"የሚሞላ ፎርም ስላለ ኢሜይልህን ስጠኝ!" አለችው አስተናባሪዋ

"ኢሜይል የለኝም እመቤቴ"

"ኢሜይል ሳይኖርህ እንዲህ ስኬታማ የምግብ ኢንዱስትሪ ከገነባህ ኢሜይል ቢኖርህ ደግሞ ምን ልትሆን ትችል እንደነበር ታውቀዋለህ?"

ሰውዬው መለሰ

👇🏾

"አዎ አውቀዋለሁ: ተላላኪ ነበር የምሆነው"

ሰዎች በሚለጥፉባችሁ ስያሜ እና ስለ እናንተ ባላቸው አመለካከት አትገደቡ !!

❤️🙌🏼**

3 weeks, 3 days ago
እንማር
3 weeks, 4 days ago

**እያወራን ነው ከባሌ ጋር ። እሱ አልጋው ላይ ጋደም ብሏል አልጋው ጠርዝ ላይ ቢጃማዬን ለብሼ ቀሚሴን እስከጉልበቴ ገልቤ በእጄ የቆነጠርኩትን ግሪሲሊን ጉልበቴን፣ ጭኔን ፣ ቁርጭምጭሚቴን ... እየቀባባሁ ነው።

ከላይ ነጭ ፓካውንት፣ ከስር ቱታ ለብሶ አንዴ ስልኩን አንዴ TVውን ያያል። Televisionኑ የትዝታ ዘፈን ያስመለክታል። ዘፈኑ የድሮ ቢሆንም በአዲስ ክሊፕ አዲስ ቆንጆ ድምፅ ያለው ልጅ እየዘፈነው ነው ።

🎼🎼🎼🎼

ሞት አደላድሎኝ አፈር ካልተጫነኝ
ቃሌን አላጥፈውም ካንቺ ጋር ነዋሪ ነኝ
ውበትሽ ኩራዜ ይበራል ከቤቴ
ጠረንሽ ፈውሴ ነው የፍቅር እመቤቴ
ሞት አደላድሎኝ አፈር ካልተጫነኝ ቃሌን አላጥፈውም 🎶🎶

"ክሊፑ ላይ ያለችው ልጅ የድሮ እጮኛዬን ትመስላለች።" አለ ፈገግ እያለ አፈጋገጉ እንደናፈቀችው አይነት ነው ።

ስቀብጥ ይሁን ስጃጃል፣ ወይም የጎጆ እና የትዳር ቀመር ስላልገባኝ የድሮ ፍቅረኛው ስላላት ልጅ ጠየኩት ።

ትክዝ እንደማለት አለና ሲያፈጥበት ከነበረው የሙዚቃ ክሊፕ አይኑን ነቅሎ ሲነካካው የነበረውን ስልክ አስቀመጠው ።

"እወዳት ነበር በጣም ። ስትናፍቀኝ ብንጣላም እኔ ካላሁበት ብትርቅ ፣ አላገኝህም ብትልም የትም ሄጄ አያት ነበር ...ስታኮርፈኝ የበለጠ ማግኘት እፈልግ ነበር...።" ሳቅ ነገር አለ ።

"እሷ ላይ ከቻቻ ነበርኩ ! ቀልድ ትችላለች ፣ ኩርፊያዋም፣ አሳሳሟም፣ አደናነሷ ፣ አስተቃቀፏ፣ ግልፅነቷን እወደው ነበር .... ደስስ ትላለች" ደማቅ ፈገግታ ፈገግ አለና "ናይል እኮ እብድ ነገር ነች " አለ ።

"አለ ኣ ደስ የምትል እብድ : ብዙ ደስ የሚሉ ነገሮች አሳልፈናል... " እያለ እየተመሳሰጠ ያለ ይሉኝታ አብራራልኝ ።

የእሷን እሩብ ያህል እንደማይወደኝ አይነት ነው ሁኔታው ። ላየሁት.. ላሳየኝ ማረጋገጫ ይሰጠኛል፣

ከትላንት ዛሬ አይበልጥም?

ለምኖ ላገባት ለልጆቹ እናት ይሄ ይነገራል ? ፣ የልጆች እናትስ እኔ የጠየኩትን ትጠይቃለች? ፣

የተጠየቀ ነው በሃላፊነት መመለስ ያለበት ? ወይስ ጠያቂው ነው ተጠያቂ ??

ስንት ጥልፍልፍ መንገድ አብረን መጣን አይደል? ፣ስንት የሃሳብ ዳገት ተጓዝን አይደል ?፣ የተሸከምነው የወጣነው የወረድነው የግዜ መዓት ትንሽ ይሉኝታ እንኳን እንዴት አልወለደበትም ?፣

ለጎጇችን ብዙ ገንዘብ ስለሚያመጣ ነው?፣ ዘመዶቿ አቅም የላቸውም ቢከፋት አትሄድም ብሎ ነው?፣ ወልዳለች ፈላጊ የላትም ብሎ ነው ?፣ ስለማይወደኝ ስለሚሰማኝ ስሜት ግድ ስለሌለው ነው ?፣

አይውደደኝ እንዴት አያከብረኝም ?፣

እውነት የሆነ ሁሉ ይነገራል ?፣ ሳይሰክር ሳንጣላ ሳላናድደው እንደዚህ ግዴለሽ እንዴት ይሆናል ?!፣
ይሉኝታና ብስለት ካልከለለን ልባችን ያባውን፣ ያደረግነውን ሁሉ ፣ የተሰማንን ሁሉ ቢወራ መች ኑሮ ፡ጎጆ ይመሰረታል?

ብቻ አመመኝ ...አለመወደድ በመላ አካሌ ተርመሰመሰ ማምለጫ የሌለው ህመም ተላወሰኝ ... እንደዋዛ የማይተው ሰው ሲወጋ ህመሙ ይለያል !!

የተሰማኝ ህመም እንዳልታመን ፣ እንዳልወደው፣ እንዳልጠነነቅለት ሊያደርገኝ የገፋኝ መሰለኝ ።

የቱ ጋ ነው የወጋኝ ?!

ቁስሉ ያልታየ ህመም ለመታከም ምቹ አይደለም !!

የመርሄ ወላጅ አባት ፍቅሬ እንደሆነ አላወቀልኝም** !!

3 weeks, 4 days ago

✅️⇲⇲  ✘ የታላላቅ ሰዎች እውነተኛ ታሪክ ✘ ⇲⇲
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐

❈ ደራሲ ፦ Unknown
❈ ትርጉም ፦ ሰለሞን ሀይለማርያም
❈ ይዘት ፦ ታሪክ

➠➠➠➠ ሼር ያድርጉ!! ➠➠➠➠

✅️✅️@Enmare1988
✅️@Enmare1988
═══════ •『 ♡ 』• ═══════

1 month ago

ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል

የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

1 month ago

🪽

መረሳት ትልቅ ቅጣት ነው እንት`ረሳኝ እድል ሰጠዋት❤️

1 month ago

**በጨለማ ተከበብን አይነት ስሜት ሲያጠቃን አይዞን ላላችሁን ፣ ለህልማችን መሳካት በአቅማቹ አለን ለምትሉ ። ስንወድቅ ብለን ነበር ለማትሉ ።

ችርስ

ደስታችን ለሚያስቦርቃቹ ፣ ማዘናችን ግድ የሚሰጣቹ ፣ ስናጠፋ ጥፋታችን ላይ ክችች ለማትሉ ።

በየደቂቃው ለማትመዝኑን ። ሃሳባችን ከቁብ ለምትቆጥሩ ፣ መውደዳችን ለሚገባቹ ። ተናዶ ነው ፤መስሎት ነው ፤ተሳስቶ ነው እያላቹ ላለፋችሁን

ኑሮ እንዳይሰለቸን ላደረጋችሁን ። አሻግረን እንድናይ ጥሩ እንድንሆን ለገፋችሁን ። ስትፀልዩ ስለምታስቡን ። አሪፍ ነገር ስታዩ ስለምታስታውሱን ።

ችርስ

ውለታቹ አለብን እናመሰግናለንም **

3 months ago

**Sister ነበር ያሳደገችኝ።

አራት ወይ አምስት አመት እያለሁ ነበር ወላጆቻችን ወደ ሞት የሄዱብን ። ሁለት ብቻ ነበር የወለዱት : እኔን እና እህቴን ። ስምንት አመት ትበልጠኝ ነበር ። መቼ ወደ አባትነት ፣ መቼ ወደ እናትነት እንደተቀየረች አላውቅም ።

ቤታችን ውስጥ አባትና እናት የሚወጣውን ሃላፊነት ተሸከመች ። ሸክሙ አላስጠናትም መሰለኝ ትምህርት አልገፋችም። አስረኛ ክፍል  የሙያ ውጤት መቶላት ነበር፤ እሱንም ተወችው ።*✅️*አልምልም : ከማልኩ ኤልዱ ትሙት እላለሁ በቃ ። ምድር ላይ ሞት መጥቶ ቻው ማለት የምትፈልገው ሰው ብባል፣ ዘመድ ጥራ ብባል ፣ አንደኛ ማን ያስብልሃል ብባል ፣ የማን ወዝ እና ህልም አልፎብሃል ብባል መልሴ ኤልዳና የሚል ብቻ  ነው ።

ተሰብስበን ህልም ስንናገር ኤልዳና ህልሟ እኔ ነበርኩ ። እንደዚህ ሰው ይወደዳል እንዴ? እንደዚህ በፍቃድ ህልም ይሰዋል ? የሆነ ቀን ከስራ ስመጣ ኤልዳ ታማ ጠበቀችኝ ። ክሊኒክ ወሰድኳት ቀላል አይደለም ብለው ሪፈር ላኩን ።

ፊቷ ችፍፍፍ ፣ ቁስልስል አለ ። ቀኝ እግሯ እምቢ  አልራመድ አለ ፣ ምግብ አልበላ አላት ። ብዙ ቦታ ሄድን መፍትሄ  አጣን ።

ኢ- አማኝ ነበርኩ ፤ እንዲ አደረክብኝ ብዬ የምጠይቀው ፣ እንዲ አድርግልኝ ብዬ የምለምነው አካል  የለም ።  ነፍስ ካወኩ እንዲ ሀዘን ተጣብቶኝ አያውቅም ። የመኖር ፍላጎት እና ህልሜ ከሰመ። ህመሟን አለምደው አልኩ ። ሃኪሞች ተስፋ የላችሁም አሉን ።

የሆነ ቀን አስራ አንድ ሰዓት ለሊት ቀስቅሳኝ
"በዓታ ማርያም ሶስት ቀን ፀበል ተጠመቂ  ትድኛለሽ ተባልኩ" አለችኝ ።  ማመን የማይደክማት ልጅ ፤ መሞኘት የማይሰለቻት ልጅ ።
"እሺ እንሂድ" አልኳት ።**አማራጭ የሌለው ሰው ምንም አይፈላሰፍም። እንኳን ቤተክርስቲያን ስምጥ ሸለቆ እሄዳለሁ ። በርግጥ እኔ ከ 'Bible'  የ  Sigmund Freud - 'The Future of an Illusion' የተሻለ ያሳምነኛል።

ግን፤ ኤልዱ እድናለሁ ካለች የት አልሄድም ??

ሄድኩ : ተጠበለች ወደቤት መጣን ። እሷ በህልሟ፣ እሷ በበኣታ ፣እሷ በፀበል ያላት እምነት ትልቅ ነበር እና ውጤት ጠበቀች በርግጥ እኔ የምጠብቀው ነገር የለም ።*✅️*በነጋታው ጠዋት ፊቷ ለውጥ ያለው መስሎኝ ነበር እሷ አረጋገጠችልኝ ። በሁለተኛው ቀን ሄድን "እግሬ  ቀለለኝ" እያለች ነበር ። የዛ ቀን በነጋታው "እግሬ ሰራ " አለች ።

የሆነ ነገር ማለት ፈልጌ ነበር ደስታ፣ እምባ አላናግር አለኝ እና ዝም አልኩ።  ሶስተኛ ቀን ተጠመቀች ፊቷ፣ እግሯ ፣የምግብ ፍላጎቷ እንደነበረ ሆነ ።

ሶስተኛ ቀን እሷ ተጠምቃ ስትጨርስ "ወደቤት እንሂድ ወይ?"  አለችኝ።**"እኔ ልጠመቅ እና እንሄዳለን" አልኳት። ስትድን ደስ ያላትን ያህል ደስ አላት። ሆድ ብሶኝ ነበር ፣ደስ ብሎኝ ነበር ፣ ማመን አቅቶኝ ነበር። እያለቀስኩ እያመሰገንኩ እየተደሰትኩ ተጠመኩ  አመንኩ ።

ሄሌ ሉያ
©  Adhanom Mitiku**

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month, 2 weeks ago

በዚህ ቻናል ሀገራዊና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን በፍጥነት ያገኛሉ❗
የውስጥ መስመር👉http://t.me/ayulaw

Last updated 4 days, 16 hours ago