Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Muktarovich Ousmanova

Description
Ethiopia forever
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month, 2 weeks ago

በዚህ ቻናል ሀገራዊና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን በፍጥነት ያገኛሉ❗
የውስጥ መስመር👉http://t.me/ayulaw

Last updated 4 days, 16 hours ago

4 days, 21 hours ago
ብሔራዊ ውርደት ነው። የትውልድ ምክነት ነው። …

ብሔራዊ ውርደት ነው። የትውልድ ምክነት ነው። ያሳዝናል

5 days, 14 hours ago
“ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ” በእስር …

“ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ” በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ

የተፈጻሚነት የጊዜ ወሰኑ ባለፈው ሳምንት ካበቃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች፤ “አካልን ነጻ የማውጣት” (habeas corpus) አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ። አቤቱታውን በጠበቆቻቸው በኩል ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ጋዜጠኞች በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ናቸው።

➡️ ጋዜጠኞቹ አቤቱታውን ያቀረቡት፤ የፌደራል ፖሊስ “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር እንዲቆዩ” በማድረጉ መሆኑን ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ አዲሱ ጌታነህ “ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

➡️ ሶስቱ ጋዜጠኞች “ካለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዛቸው”፣ ከተያዙም በኋላ “በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲኖርባቸው” ይህንን መብታቸውን መነፈጋቸውን ጠበቃው ገልጸዋል።

➡️ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ፤ ጋዜጠኞቹ “ከፍርድ ውጭ ተገድደው የተያዙ” መሆናቸውን ይገልጻል።

➡️ የፌደራል ፖሊስ የጋዜጠኞቹን “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር ላይ ማቆየቱ ሕገ ወጥ ተግባር ነው” ሲሉም የጋዜጠኞቹ ጠበቆች በአቤቱታው ላይ አመልክተዋል።

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ 👉 https://ethiopiainsider.com/2024/13301/

@EthiopiaInsiderNews

5 days, 21 hours ago
የጌታቸው ረዳ ጠባቂዎች ተቀየሩ***❗***

የጌታቸው ረዳ ጠባቂዎች ተቀየሩ
የፌዴራል መንግሥቱ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ አዳዲስ ጠባቂዎችን እንደመደበላቸው ዘ-ጆርናሊስት ከታማኝ ምንጮች ሰምቷል።

የጌታቸው ረዳ አጃቢዎች መቀየር በሕወሓት እና ጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል ያለውን የሰፋ ልዩነት ያሳያል ተብሏል።

ምንጮች እንደገለጹት፣ "ነባሩ ሕወሓት" በሚባለው እና እርሳቸው በሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ያለው ልዩነት በፕሬዝዳንቱ ላይ የደህንነት ሥጋት ሳይፈጥር አልቀረም።

የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ በመቀሌ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ በህወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ያለው ልዩነት የፖለቲካ ብቻ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሳምንታት በፊት ከትግራይ ክልል ከመጡ ሰዎች ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ባደረጉት ውይይት ደጋግመው "ጌታቸውን አግዙት፤" ሲሉ ተደምጠዋል።
👉ያልተሰሙ አዳዲስ አለማቀፍና ሀገርአቀፍ ዜናዎችን ለማግኘት ቻናላችንን join አድርጉ👇👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

2 weeks ago
ባለፈው ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ አዲስ …

ባለፈው ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የተገደሉት ሁለት የፋኖ አባላት ቤተሰቦች አስከሬናቸውን ሳያገኙ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ጎንደር ውስጥ መፈጸማቸውን ተናገሩ።

ፖሊስ በአማራ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን አባላት ናቸው ያላቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሽብር ድርጊት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሶባቸው መገደላቸውን መግለጹ ይታወሳል።

የሁለቱ ወጣቶችን ሞት ተከትሎ ወላጆቻቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አስከሬናቸውን አግኝተው ቀብር ለመፈጸም ለፌደራል ፖሊስ እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ መጠበቃቸውን ተናግረዋል።

ዛሬ ግንቦት 26/2016 ዓ.ም. ጎንደር ውስጥ አስከሬኑ በሌለበት በባህላዊ መንገድ በቤተሰብ እና በወዳጆች የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ የተፈጸመው የናሁሰናይ አንዳር ጌ ሲሆን፣ በዚህም ወቅት በርካታ ሕዝብ ታድሞ እንደነበር አንድ የቤተሰብ አባል ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የአቤኔዘር ጋሻው የሽኝት ሥነ ሥርዓትም በተመሳሳይ ቤተሰቡ አስከሬኑ ባላገኘበት ሁኔታ ቀደም ብሎ መከናወኑን የቤተሰቡ አባላት ገልጸዋል።

2 weeks, 1 day ago
***🎉******🎉***እንኳን ደስ አላችሁ የማስታውቂያ ሽያጭ ላይ …

🎉🎉እንኳን ደስ አላችሁ የማስታውቂያ ሽያጭ ላይ ነን ይጎብኙን🎉
በ CMC የተሟላ የመኖርያ መንደር ከ ለሚ ኩራ ፓርክ ፊትለፊት

📌በ ተንጣለለ 23,000 ካሬ ላይ ያረፉ አፓርትመንቶች

❇️ ባለ 1 መኝታ 79.92ካሬ 91.56ካሬ
❇️ ባለ 2 መኝታ 125.4ካሬ 127.44ካሬ
❇️ ባለ 3 መኝታ 169.92ካሬ

የህንፃዉ አገልግሎቶች፥

የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ፣ የደህንነት ካሜራዎች፣ አሳንሰሮች፣ ጀነሬተር፣ ማአከላዊ የቴሌቭዠን መቀበያ፣ የመኪና ቻርጀር፣ ሶላር ሲስትም፣ የእሳት አደጋ መከላከያ፣ የከርሰ ምድር ውሀ፣ የቆሻሻ ማስተላለፊያና ማጠራቀሚያ ስፍራ፣ መዋኛ ገንዳ፣ የቅርጫት ኳስ ሜዳ፣ የልጆች መጫወቻ ቦታ፣ የሩጫና የብስክሌት ቦታ፣ ጂምናዚየም፣ ሰፊ አረንጓዴ አካባቢ፣ ዘመናዊ የገበያ አካባቢ

ለበለጠ መረጃ
what's up - https://wa.me/251945709171

📞 +251945709171
+251915922176

2 weeks, 1 day ago

ከሰሞኑ ከደረሱኝ ጥቆማዎች፣ እኔም ማረጋገጥ ከቻልኳቸው መረጃዎች መሀል፣

  1. በአዲስ አበባ ከተማ ማታ ማታ በስፋት እየተፈፀመ ያለ የቤት ለቤት ፍተሻ አለ። ፍተሻው ለምን ኖረ ሊባል ባይችልም ያለምንም የፍርድ ቤት ትዛዝ ሙሉ ሰፈር መፈተሽ፣ የፀጥታ አካላት ለፍተሻ አንዳንድ ቤቶች ሲገቡ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ መሆኑ እና ከ5 ሺህ ብር በላይ ቤት ውስጥ ሲያገኙ ይዘው እየሄዱ ይገኛል። ህጋዊነቱን በተመለከተ ጥያቄ ተነስቷል።

  2. ከቅርብ ቀናት ወዲህ ወደ ጅማ ከተማ የሚገቡ እቃ የጫኑ ተሽከርካሪዎችን በማስቆም ገንዘብ መቀበል ተጀምሯል። ለምሳሌ ቢራ የጫኑ ተሳቢዎችን የጫኑትን ሳጥን ቆጥረው በአንድ ሳጥን 50 ብር እየተቀበሉ ይገኛል፣ በርካቶችም በዚህ ምክንያት ወደ ጅማ ጉዞ አቁመናል ብለዋል። መንግስት ይህን ያውቀዋል?

  3. ከቀናት በፊት በትምህርት ሚኒስቴር ኦረንቴሽን የተሰጣቸው የግል ትምህርት ቤቶች የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተና ላፕቶፕ ይዘው እንዲመጡ እንደተነገራቸው መረጃ አድርሰውኛል። በርካታ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ካሉበት የኢኮኖሚ ሁኔታ አንፃር ላፕቶፕ መግዛት እንደማይችሉ የተናገሩ ሲሆን አሁን ድረስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሳያውቁ ግራ ተጋብተው እንዳሉ ተናግረዋል።
    Elias Meseret

3 weeks, 1 day ago
Muktarovich Ousmanova
3 weeks, 1 day ago
Muktarovich Ousmanova
3 weeks, 1 day ago
ሰርግ ***💍******❤️***

ሰርግ 💍❤️

በዛሬዋ ዕለተ ሰንበት በመቐለ ከተማ በሥርዓተ ተክሊል ቅዱስ ጋብቻቸውን ለፈጸሙት ለጀግናዋ

  • አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና
  • ለዲያቆን ፍስሐ ኪሮስ

ቅዱስ ጋብቻችው የአብርሃምና የሣራ ይሁን

ርሑስ ጋማ🌹

መልካም ጋብቻ ጀግኒት

❤️❤️❤️🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

2 months, 3 weeks ago
እምጥ ይግቡ ስምጥ የማይታወቅ ደብዛቸው ለቀናት፣ …

እምጥ ይግቡ ስምጥ የማይታወቅ ደብዛቸው ለቀናት፣ ለሳምንታት ብሎም ለወራት የሚጠፋ ሰዎችን ዜና መስማት የተለመደ እየመሰለ ነው። ይህ ክስተት ባለፈው ወር ለሥራ ከቤታቸው የወጡ አንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ላይ ጭምር መድረሱን ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ወንድማቸው ነግረውናል።

DW

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month, 2 weeks ago

በዚህ ቻናል ሀገራዊና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን በፍጥነት ያገኛሉ❗
የውስጥ መስመር👉http://t.me/ayulaw

Last updated 4 days, 16 hours ago