Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

Description
የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች

Yasin Nuru

"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

"የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም "  

የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7}

This is not official

ለአስተያየት👇👇
@Hasabbbbot

ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇
@yasin_nuru_hadis
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 2 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 5 days, 7 hours ago

1 week ago

“የእናት ሀቅ.. መች ይለቅ!”
(እውነተኛ)-ክፍል ሁለት/መጨረሻ/
ፀሐፊ:አብዱልጀባር ፋሪስ

ታላቅ እህት ሮጣ ወደ ቤቱ ስትደርስ እናት መሬት ላይ ተዘርራለች። አይኗን ማመን አልቻለችም። ...ይሄኔ ኡኡታዋን አቀለጠችው። የአካባቢው ሰው ወደ ቦታው አቤት ሲል ተሰበሰበ። ነገሩ ካለቀ ወዲህ ምን ይፈይድና ነው። ህዝቡ ጉድ እንዲል... ልጅ እናቱን ገድሎ ሬሳዋ ላይ ቆሟል። እህት በልቅሶ እናት ላይ ተደፍታ ታለቅሳለች።

“አ... ወይኔ ሀደኮ, ሲ አጄሴ ሚቲ” እህት በኦሮምኛ እያወራች ትንሰቀሰቃለች። ህዝቡ ለቅሶና ዋይታውን አቀለጠው። በአቅራቢያ ለሚገኘ ፖሊስ ጣብያ ተደውለ። ልጅ በነብስ ግድያ ወንጀል እጅ ከፍንጅ በመያዙ ዘብጢያ ወረደ።

መንደርተኛ ለተራ ሞት እንደሚያለቅስ የታወቀ ነው። በዚች ሚስኪን እናት ሞት ደግሞ ይበልጥ ልባቸው ተሰብሯል። ሀዘናቸውን አሟሟቷ እጥፍ ድርብ አድርጎ፣ ለቅሶው እና ወሬው ሀገር አዳርሶ ነበር።

መቼስ ሬሳን ተሸክመው አይቆዩና.. እናት ልትቀበር በእስልምና ስርዓት መሰረት ሰውነት ተገነዘ። በነጭ አቡጀዲ(ከፈን) ተጠቅልላ ወደ ማይቀረው ቤቷ መጓዟ ነው። በእግሯ ላትሄድ ሸክም አይቀርላትም... ይሄኔ ነው ሀገር አይቶት የማያውቅ ጉድ እንግዳ የገጠማቸው።

የእናት እሬሳ(ጀናዛ) ተገንዞ ከተከፈንበት ቦታ ንቅንቅ አልልም አለ። የሀገሩ ወጣት፣ ወጠምሻ ሊያነሳው ቢሞክር ፍንክች አልልም አለ።

በተቀመጠበት ቦታ እንደ አለት ደርቆ ወደ ላይ ሚያነሳው ጠፋ። የሀገሬው ሰው ጉድ ብሎ... ምን እናድርግ ሲል፣ ከፈሎዎቹ ሼኽ ይጠራና መፍትሄ ያበጅልን ሲሉ ሀሳብ ሰጡ። በአካባቢው ለሚገኙ ሼኾች ጉዳዩ ተነግሮ ወደ ቦታው ፈጥነው ደረሱ። እነሱም ለማንሳት ቢሞክሩ እንቢ አላቸው።

ነገሩን በጥልቀት ሲጠይቁ የእናት አሟሟት ተነገራቸው። መፍትሄ ነው ብለው ያሰቡት እናትን የገደላት ልጅ ከእስር ቤት መጥቶ እንዲያነሳ ነው።

ልጅ ከእስር ቤት ተጠራና በፖሊስ ታጅቦ እቦታው ደረሰ። ከአራቱ የቃሬዛው ቅርንጫፎች አንዱን ይዞ ሎሎች ሶስት ሰዎች ተጨምረው ብድግ ሲያደርጉት፤ እንቢ ብሎ የነበረው እሬሳ ተነሳ። መስጂድ ተወስዳ ተሰገደባት። ሰላቱ እንዳለቀ ከልጅ ጋር ሆነው ወደ መቀበርያ ቦታዋ ወሰዷት።  ችግሩ እንዳለቀ በማሰብ ልጅ ወደ እስር ቤት እንዲመለስ ተደረገ።

የቀብር ቁፋሮው እንዳለቀ... እናትን ወደ ለህድ (የሬሳ መጋደምያ) ቦታ ለማስገባት ቢሞክሩ.. ቢሉ.. እንቢ አላቸው። እናት በድጋሚ መሬት ላይ ደርቃ ቀረች። ልጅ ከእስር ቤት ተመልሶ መጥቶ እናቱን ተሸክሞ ወደ ለህድ እንዲያስገባ ሆነ።

በድጋሚ ልጅ መጥቶ ሬሳውን ሲያነሳው እንደ ቀልድ ብድግ ብሎ ተነሳለት። ይህንን ሁሉ ተዓምር ሀገሬው ቆሞ ይከታተላል። በድጋሚ ልጅ እናቱን ይዞ ወደ ለህድ ውስጥ ሲያስገባ... ሌላ ተዓምር ይመለከቷል። እናቱን ወደ መጋደሚያዋ እንዳስተኛት አስገራሚ ተዓምር ተከሰተ።

ልጅ ጠብቶ ያደገው የእናቱ ጡት ከነበረበት መጠን ጨምሮና ረዝሞ ልጅ ላይ እንደ እባብ ተጠመጠመበት። በነገሩ ነብሱ እስክትወጣ የደነገጠው ልጅ.. ጩኸቱን አቀለጠው። ሰዉ ምን ጉድ ነው ብሎ ሲመለከት ያው ነው። የእናት ጡት እንደ ትልቅ ዘንዶ ልጅ ላይ ተጠምጥሞ ማፈናፈኚያ አሳጥቶታል።

በነገሩ በጣም ደነገጡ። የእናት ሀቅ መሆኑን ሁሉም ተገንዝቦ ነበር። ሆኖም የሞተ አይነሳና ልጅን ከእናቱ ጡት አላቅቀው ለማዳን ቢሞክሩም.. ጭራሽ እንቢ አላቸው። ይሄኔ አዋቂዎቹ የእናት ጡት ይቆረጥ ወይስ ልጅን ከነእናቱ እንድፈነው ብለው ካጤኑ በኋላ አንድ ውሳኔ ላይ ደረሱ።

“የአላህ ውሳኔ እና ተዓምር ነው። ልጅን ለማላቀቅ መሞከር ከንቱ ልፋት በመሆኑ እዛው ከእናቱ ጋር ድፈኑት። ለሰዎችም አላህ ያሳየን ተዓምር ነው” ሲሉ ጉዳዩን ቋጩት። ጨካኙ ነብሰ ገዳይ ልጅ አንቆ ከገደላት እናቱ ጋር በአንድ ጉድጓድ ተቀበረ! ነገሩም በዚህ ተቋጨ።

ወዳጆቼ አሁን ላይ ልጅ እናቱን መግደል፤ አባቱን ማሰቃየት፤ ብሎም ህይወቱን ማጥፋት እየበዛ ይገኛል። ከዚህ በታች ሳይሆን አሳሳቢውም እናትና አባትን አለማክበር.. ትዕዛዛቸውን አለመፈፀምም ሌላው ትልቅ ወንጀል ነው።ወዳጆቼ! ወላጆቻችሁ የእናንተ ጌጥ ብቻ ሳይሆን መነሻችሁም ናቸው።

በነሱ የሚያፍር እና መብታቸውን የማይጠብቅ ከእንደዚህ አይነቱ ውርደት እስከ መጪው አለም ቅጣት ቢጠነቀቅ ይሻለዋል። አደራችሁን በህይወት ላሉት እዝነትና ርህራሄን ሰጥተን፥ ከትዕቢትና ግልምጫ በመቆጠብ ደስተኛ እናድርጋቸው። የሞቱብንን ደግሞ በፀሎታችን ሁሌም ልንዘክራቸውና መሀርታ ልንለምንላቸው ይገባል።

ታሪኩ ፍፁም እውነትኛ ነው። እኔም ለማመን ከብዶኝ ነበር.. ነገር ግን በዘመናችን የተከሰተና ከአካባቢው ሰዎች ምስክር የተሰጠው ነው። መማሪያ ሚፈልግ ይህ በቂና ከበቂም በላይ ነው። እኔ የሰማሁትን ለናንተ በማካፈል ግዴታዬን ተወጣሁ።

@yasin_nuru @yasin_nuru

1 week ago

ሀጅ ለማድረግ ለተነሳችሁ ወንድም እህቶች የሐጅ እና ዑምራን ድንጋጌዎችን ለመማር የሚረዳ ጠቃሚ አፕሊኬሽን ስለሆነ አውርዳችሁ ተጠቀሙበት።

@yasin_nuru @yasin_nuru

1 week, 1 day ago

“የእናት ሀቅ.. መች ይለቅ! ”
(እውነተኛ)-ክፍል አንድ
ፀሀፊ፡አብዱልጀባር ፋሪስ

ይህንን ታሪክ የምጽፍላችሁ በቅርቡ አያቴና እናቴ ካካፈሉኝ ነው። እውነተኛ እና እዚሁ ሀገራችን ውስጥ የተከሰተ ጉድ የሚያስብል ነው።

ታሪኩ በቅርቡ ከአንድ ወይም ሁለት አመት በፊት የተከሰተ ነው። እናት ከልጆቿ ጋር ኑሮዋን መስርታ መኖር ከጀመረች ሰነባብታለች። የመጀመርያ ትሁን ባይነገረኝም ታላቅ ልጇ ትዳር መስርታ መኖር ጀምራለች። ታድያ ታናሹ ወጣት ልጅሆዬ እናቱ ላይ እንደ ልቡ ይደነፋል። በዚህ ስራው እናት ከልብ ትፈራዋለች።

ፍራቻዋ የመነጨው እሱ ለሷ ከሚያሳያት ትዕቢት እንጂ ሌላ አይደለም። ይገርማል የሰው ነገር! ሽንቱን በእጇ ጠርጋ ያሳደገችው እናቱን ግልምጫው አንሶ ሊመታት ይቃጣዋል። ምን ዓይነት ጭንቅላት ነው ይህን ሚቀበለው!!

እናም ከእለታት በአንዱ ቀን ልጅ ለእናቱ የሞባይል ስልኩን ቻርጅ እንድታስደርግለት አስጠንቅቆ ይሰጣታል።

ወቸው ጉድ! እናቱን ይልካል.. እናት በትዕዛዙ መሰረት ገበያ ስትወጣ ስልኩን በጡቶቿ መሃል ቋጥራ ከምትይዘው ብር ጋር አያይዛ ታስቀምጠዋለች። ግብይቷን እንደጨረሰችም የልጇን ስልክ ቻርጅ ለማስደረግ ብትመልከት ከቦታው አጣችው። በድንጋጤ በአካባቢዋ ፈለገች።

ስትባክን ውላ ምንም ልታገኝ ስላልቻለች በፍራቻ ወደ ታላቅ ልጇ ቤት አመራች። 9 ወር በሆዳ ተሸክማው፣ 2 ዓመት ያጠባችውና ተንከባክባ ቆንጥጣ ያሳደገችው ልጁን ትፈራዋለች። የሰው ነገርኮ ጉድ ነው ወዳጆቼ! ግና ልጇ ቤት ደርሳ ችግሩን ነገረቻት። ስልኩ ካስቀመጠችበት መጥፋቱንና ልጅየውም እንደሚገላት አስረድታ አብራት እንድትሄድ ተማፀነቻት። ልጅ ምንም ሳይመስላት “ኧረ እማዬ ምንም አያደርግሽም። ይልቅ እመጣለሁ። ሂጂ” ብላ ከነፍርሃቷ አሰናበተቻት። እናት ሁሉ ነገር ጠቦባታል። ቤት ስትደርስ አንዳች ክፋ ነገር እንደሚገጥማት ጠርጥራለች። ከዚህ ስሜት ጋር ቤት ደረሰች።

ቤት ስትደርስ አንዳች ክፋ ነገር እንደሚገጥማት ጠርጥራለች። ማይደረስ የለምና ከዚህ ስሜት ጋር ቤቷ ደረሰች። ልጅየው ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆኖ ቤት ተቀምጧል። እናት ከበሩ እንደገባች በጥያቄ ጀመራት። “ስልኬን ስጪኝ” ብሎ ከተቀመጠበት ወደሷ ተራመደ።  አንዳች ነገር እንዳይደርስባት የሰጋችው እናት ተርበደበደች። ልጇ ከሚያደርስባት ክፋ ነገር ለማምለጥም እንዲህ ብላ የጠፋውን ስልክ እንደምትክሰው ለማሳመን ንግግር ጀመረች..

“ይሃውልህ የኔ ልጅ! እኛ ቤት ያለችውን ላም ከነ ጥጃዋ ወስደህ መሸጥ ትችላለህ። በምታገኘው ብርም የጠፋብህን ስልክ ትተካለህ። ስልክህ ካስቀመጥኩበት ወድቆ ጠፍቷል” አንዳች ነገር እንዳይደርስባት ትንቀጠቀጣለች። ልጅ ይሄንን ንግግር እየጠበቀ ይመስል እናቱን ዘልሎ አንነቃት። ጎሮሮዋን ይዞ ትንፋሽ እስኪያጥራት አንጠራራት።

ውይይ የሰው ጭካኔ!! እናትን አንቆ ለመግደል ይቃጣል። ሊያውም በተልካሻ ምክንያት። ምናለ እንኳን ስልኩን ልጁን እንኳ ብትደግልበት ባይነካት። እኮ! እናት ናት። እሷ ባትወልደው ከየት አባቱ ይገኝና ነው?!! የጠፋበትን ስልክ ዋጋ እጥፍ የሚሆን ንብረትም "ተክተህ ውስድ" ብላ እየተማፀነችው፤ በእንቢተኝነቱ ፀና። እንዳነቃትም እዛው ገደላት። አዎ! እናቱን አንቆ ገደለ።

ያ አላህ! ለተራ ስልክ ብሎ እሱንም ስልኩንም እንዲገኝ የመጀመርያ ሰበብ የነበረችውን እናቱን ገደለ። በድርጊቱ በጣም ነበር ያዘንኩት። እናቴ ይህንን ስትሰማ በጣም ነበር ያለቀሰችው። የሞተችውን ባታውቃትም፤ ሰው ሊያውም እናት በልጇ ታንቃ ስትሞት መስማት ይዘገንናል። ታላቅ እህት ሮጣ ወደ ቤቱ ስትደርስ እናት መሬት ላይ ተዘርራለች። አይኗን ማመን አልቻለችም። ይሄኔ ኡኡታዋን አቀለጠችው...

ልጁ ምን እንደገጠመው በክፍል ሁለት(በመጨረሻው)ይቀጥላል... እባካችሁ ሼር!! በናንተ ምክንያት ብዙ ሰው የእናቱን ክብር ሊያውቅና ሊረዳ ይችላል። ታሪኩ በጣም አሳዛኝ ነው። በዚህ አላበቃም የልጁ ጉዳይ። በክፍል 2 እንገናኝ። ቸር ቆዩልኝ!!

@yasin_nuru @yasin_nuru

2 weeks, 1 day ago

የጅን ጥቃት በሴቶች ላይ ምልክቶቹ

1.ብቻሽን መሆን የምትፈልጊ ከሆነና ሀሳብሽ በሙሉ ከሰው ለመገለል ከሆነ እራስሽን ጠይቂ፡፡

  1. የወሲብ ፍላጎት ከፍተኛ መሆን እና እራስን መንካት፡፡ በተቃራኒው ከባለቤትሽ ጋር ግንኙነትን እጅግ በጣም መጥላት

3.ምሽትና ቀን ማልቀስ ምክንያቱን በቅጡ በማታውቂው ምክንያቶች እምባ በእምባ መሆን ሆድ መባስ፡፡ ይከፋሻል ምክንያቱን ግን አታውቂውም።

4.ድብርት መሰማት ይህ ድብርት ጥዋት ላይ ይከፋል ሰው ወገግ እያየለለት ሲሄድ ባንቺ ላይ እየጨለመ ይመጣል።

5.የፔሬድ መብዛት፡፡ ፔሬድ ከ5-8 ቀን በኖርማል ሁኔታ ሊፈስ ይችላል ፡፡ በጂን ልክፍት ግን 30 እና 45 ቀን የፔሬድ ደም ሶስት ቀን እረፍት ሊኖር ይችላል፡፡ ይህም እንደ ጥቃቱ ይለያያል፡፡ የጥቃቱ ሃይለኝነት የፔሬዱን ብዛት ይወስናል፡፡ ዝቅተኛ ጥቃት መጠነኛ የፔሬድ መብዛት ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ ከፍተኛ የፔሬድ መብዛት ይኖረዋል፡፡

6.ፍራቻ መሰማት፡፡ ማታ ሲመሽ ከመጠን በላይ መፍራትና የልብ ምት መጨመር፡፡ የሚሞቱ ያክል ፍራቻ መሰማት፡፡ መተንፈስ እንኳ እስኪጨንቅሽ።

7.ለሰው የማይታየው ለሷ ብቻ የሚታያት ምልክቶች መኖር፡፡ እነኛም 100 በ100 ልክ ናቸው፡፡ ከሰፈር ውስጥ ማን እንደሚሞት እንደሚታመም እንዲሁም የሚደረጉ ሁናቴዎች ለርሷ ግልፅ ባለ መልኩ ይታያታል፡፡ ይህ ግን ፈፅሞ በእውነታ ላይ የተመሰረተ ውሸት ነው፡፡ ይህን ሸይጧንም ያመሳስላል፡፡

8.ከጓደኞችሽ ጋር በሆነው ባልሆነው መጣላት ፡፡ ሰላም ማጣት ብሎም ሳምንቱን ሙሉ መጥፎ ወሬዎችን መስማት፡፡ 

9.እጅግ በጣም ተናዳጅ መሆን ሰው ጥሩ እያወራሽ አንቺ ቱግ ማለት። ጥሩ እያሰቡልሽ እንደ ጠላት መቁጠር ሰው አለማመን አደለም ይሁንና እስከመንቀጥቀጥ የሚያደርስ ንዴት።

  1. ውሸታምነት። አዎ እጅግ ሲበዛ ውሸታም ነገር አሳባቂ መሆን ። ውሸቱን ወደሽ አደለም ምትዋሺው የሚያስገድድሽ ነገር አለ።

11.ከልክ ያለፈ ቅናት ምቀኝነት። የምታውቂያቸው ሰዎች ካንቺ በታች ሁነው እንዲንፈራፈሩ ትሻለሽ። የነገራቶች ፈጣሪ ሰው ስላንቺ እንዲያወራ ብቻ ትፈልግያለሽ። ያ ሰው ጥቅም እንዲያገኝ አትፈልጊም ቢያገኝም ካንቺ ካልሆነ ያንገበግብሻል።

  1. ሙእሚኖችን በአሏህ መንገድ ላይ የሚሰሩ ሰዎችን መጥላት ። ይህም ከልብሽ ብትበቀያቸው ደስታሽ ነው። ሲያወሩ ወሬያቸው አይጥምሽም ቢመክሩ ምክራቸው አይዋጥልሽም። ሳታውቂያቸው መጥላት።

  2. ሰላት ላይ መቆም ሞት መስሎ ይታይሻል። ረመዳን ካልመጣ በቀርም ሰላት የለም።

  3. አስመሳይ ገፀ ባህሪ እንዲኖርሽ ያደርጋል። የማትወጂውን መውደድ መምሰል የምትወጂውን ጠይ መምሰል በጥቅሉ የሰውን ህሳቤ ወዳንቺ መጎተት ትፈልግያለሽ። ይህ ከዚህ በፊት የሌለ ባህሪ ነው።

በዚህ ግዜ የሚደረግ ሩቃ እጅግ ጥበብ በተሞላባቸውና አላህን በሚፈሩ ሩቃ ዶክተሮች መካሄድ አለበት፡፡ ምክንያቱም በጅኑ አማካይነት ሁለቱም በመሳሳት ወዳልተፈለገ ወንጀል ሊያመሩ ይችላሉ፡፡ በአላህም እንመካለን በርሱም ከሸይጧን ሸሮች በሙሉ እንጠበቃለን፡፡

@yasin_nuru    @yasin_nuru

2 weeks, 3 days ago

‹ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላህ›
.
🔰🔰በልጁ የውሃ ሽታ ሆኖ መቅረት የተጨነቀው አባት ዐውፍ ኢብኑ ማሊክ
የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ. ዘንድ ሄደና

‹አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ልጄ ማሊክ ካንቱ ጋር በአላህ መንገድ ለዘመቻ ወጥቶ ነበር፡፡ እስካሁን ግን አልተመለሰም፤ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ይንገሩኝ፡፡›

እርሣቸውም ‹ዐውፍ ሆይ! አንተ እና ባለቤትህ ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ የሚለውን ቃል ማለትን አብዙ፡፡› አሉት፡፡ ዐውፍ ወደሚስቱ
ተመለሰ፡፡ ‹ ይህን ያህል ቆይተህ ከአላህ መልዕክተኛ ዘንድምን ይዘህ ይሆን የመጣኸው?› አለችው፡፡

‹ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ› ማለትን እንድናበዛ አዘዙኝ፡፡› አላት፡፡ ‹የአላህ መልዕክተኛ በርግጥም እውነት ተናገሩ› አለች፡፡ ቁጭ ብለው አላህን አወሱ፡፡ ‹ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ እያሉ ዋሉ፡፡ ቀኑ መሸ፡፡ ምሽቱም ገፋ፡፡

በዉድቅቱ ላይ ባልታሰበ ጊዜ በራቸው ተንኳኳ፡፡ ዐውፍ ሊከፍት ተነሳ፡፡ ልጁ ማሊክ ነበር፡፡ በርካታ በጎችን ነድቶ መጥቶ በር ላይ ቆሟል፡፡

አባቱ ጠየቀው፡፡ ‹ምንድነው ይህ የማየው?› አለው፡፡ ልጁም መለሰለት፡፡
‹ጠላቶች ማርከውኝ ወስደው በብረት ሰንሰለት ቀፍድደው አሠሩኝ፡፡

አመሻሽ ላይ ለማምለጥ ብሞክርም እግሬና እጄ የታሰረበትን ብረት መፍታት በጣም ከባድ ሆኖ ስላገኘሁት አልቻልኩም፡፡ ድንገት የሆነ ጊዜ ላይ ቀስ በቀስ ሲላላና ሲላቀቅ አስተዋልኩኝ፡፡

እኔም እግርና እጄን አላቀቅኩኝ፡፡ ሰዎቹ በቦታው ስላልነበሩ ያገኘሁትን በግና ፍየል ሁሉ ነድቼ መጣሁ፡፡› አለው፡፡

ዐውፍ ጠየቀው፡፡ ‹በኛና በጠላት አገር መካከል ያለው መንገድ እሩቅ ነው፡፡ ይህን ሁሉ መንገድ በአንድ ምሸት እንዴት ልትዘልቀው ቻልክ፡፡› ልጅም መለሰ ‹ከሰንሠለቱ ከተፈታሁበት ጊዜ ጀምሮ መላዕክት በክንፎቻቸው እንደተሸከሙኝ ይሠማኝ ነበር፡፡ › አለው፡፡

ዐውፍ የሆነውን ሁሉ ሊነግራቸው ብሎ ወደ አላህ መልዕክተኛ ተመልሶ ሄደ፡፡ ገና ሳይነግራቸው እንዲህ አሉት ‹ ዐውፍ ሆይ አብሽር አላህ ባንተ ጉዳይ
ﻭﻣﻦ ﻳﺘﻖ ﺍﻟﻠﻪ ﻳﺠﻌﻞ ﻟﻪ ﻣﺨﺮﺟﺎ ﻭﻳﺮﺯﻗﻪ ﻣﻦ ﺣﻴﺚ ﻻ ﻳﺤﺘﺴﺐ ﻭﻣﻦ ﻳﺘﻮﻛﻞ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻬﻮ
ﺣﺴﺒﻪ ...
‹ አላህንም የሚፈራ ሰው ለርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡ ካላሰበው በኩልም ሲሳይን ይለግሰዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚመካ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ ...› የሚል የቁርኣን አንቀጽ አውርዷልና፡፡ አሉት፡፡

‹ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላህ › ማለት ‹ብልሃትም ሆነ ጥንካሬ ከአላህ ዉጭ የለም፡፡› ማለት ነው፡፡ ከርሱ ዉጭ ምንም ነን፡፡

እና የላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ›ን ዋጋ እና ጥልቅ ትርጉም በትክክል እንወቅ፡፡

👉 በአስፈላጊ ቦታዎችም ላይ እንጠቀምባት፡፡
እስቲ ደጋግመን እንበላት፡፡ እሷ ጭንቀትን አስወጋጅ፣ የጀነት ዉስጥ ድልብ ሀብት ናትና፡፡

@yasin_nuru @yasin_nuru

2 weeks, 3 days ago

እግዚአብሄር :– እኔ ሰው አይደለሁም።( ሆሴዕ 11:9 )

ኢየሱስ :– እኔ ሰው ነኝ።(ዮሐንስ ወንጌል 8:40 )

( ትንቢተ ሆሴዕ 11:9 ) እኔ እግዚአብሔር አምላክ ነኝ
እንጂ #ሰው_አይደለሁምና

ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሰው ነኝ ይላል

(የዮሐንስ ወንጌል 8:40 ) ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር
የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን #ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ::

ነገር ግን ነገር ግን........
ኢየሱስ ሰው ነኝ አምላክ አይደለሁም እያለ እየተማፀናቹ እናንተ ግን አይ  ኢየሱስ አምላክ ነህ፣ ጌታ ነህ፣ ፈጣሪ ነህ ወዘተ..... ብላችሁ የምታመልኩት ከሆነ ይህን መልዕክት በአንደበቱና በግልፅ  አስቀምጦላቹሃል፣

የማቴዎስ ወንጌል 7 ፣ 21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ #ጌታ_ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥#የሚለኝ_ሁሉ_መንግሥተ_ሰማያት_የሚገባ_አይደለም

22 በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።

23 የዚያን ጊዜም። #ከቶ_አላወቅኋችሁም#እናንተ_ዓመፀኞች፥  #ከእኔ_ራቁ_ብዬ_እመሰክርባቸዋለሁ

ስለዚህ ኢየሱስን ምትወዱት ከሆነ ቃሉንና ምክሩን ስሙ! ከፊቴ ጥፉ አላውቃችሁም እላቹሃለው እያላቹ ነው።

በወንጌል ካላፈሩ እስኪ ሼር አድርጉት
ይህ 100% ከመፅሀፍ ቅዱስ ከ (ወንጌል) ስለወጣ ሁሉም #ክርስቲያን  #ሼር ያድርገው።

📱 “እየሱስ ክርስቶስ እጅግ የተከበረ የፈጣሪ መልእክተኛ”
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
💥1•
“የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የኣብ ነው እንጂ የኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ ወንጌል 14:24)

የማን ነው ኣለ?
••••• የላከኝ የኣብ√

በዚህ ጥቅስ መሰረት ወልድ( እየሱስ) የኣብ መልእክተኛ ነው።

💥 2•
“እኔ ከራሴ ኣንዳች ላደርግ ኣይቻለኝም እንደሰማሁ እፈርዳሎ ፍርዴም ቅን ነው የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን ኣልሻምና”( የዬሐንስ ወንጌል 5:30)

የማን ፈቃድ ኣለ?
••••• የላከኝን√
ማነው የላከው?

እየሱስ ኣምላክ ከሆነ, ኣምላክን የሚልክ ደግሞ ማነው?
ኣምላክ ይልካል ወይስ ይላካል?

💥 3•
“ቃሌን የሚሰማ የላከኝም የሚያምን የዘላለም ሂወት ኣለው”( የዬሐንስ ወንጌል 5:24)

ማንን የሚያምን ኣለ?
••••••• የላከኝን√
ማነው የላከው?

💥 4•
“ኢየሱስም ጮኸ እንዲህም ኣለ በኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ ወንጌል 12:44)

በኢየሱስ ማመን በማን ማመን ነው?
•••••• በላከው√
ማነው የላከው?

💥 5•
“እኔ ከራሴ ኣልተናገርሁምና ነገር ግን የላከኝ ኣብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ”( የዬሐንስ ወንጌል 12:49)

እዚህ ላይ ደግሞ ” የላከኝ ኣብ” በማለት የኣብ መልእክተኛ መሆኑን በግልፅ ተናግርዋል።

💥6•
“የላከኝ እውነተኛ ነው”( የዬሐንስ ወንጌል 8:26)

ኢየሱስን የላከ እውነተኛው ማነው?

💥 7•
“የላከኝም ኣብ ሰለኔ ይመሰክራል”( የዬሐንስ ወንጌል 8:18)

ማን ኣለ?
••••• የላከኝ ኣብ√

💥8•
“ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም ኣላቸው ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ 7:16)

ትምህርቱ ከማን ነው?•••••ከላከው√
ማነው የላከው?

💥 9•
“እኔም በራሴ ኣልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው”( የዬሐንስ ወንጌል 7:28)

ኢየሱስን የላከ የማይታወቅ እውነተኛው ማነው?

💥 10•
“እኔንም የጣለ የላከኝም ይጥላል”( ሉቃስ ወንጌል 10:16)

የላከኝን? ማነው የላከው?

💥11•
“ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር ኣልተላክሁም ኣለ”( ማቴዎስ 15:34)

ወደ እስራኤል መልእክተኛ ኣድርጎ የላከው ማነው?

💥12•
“ኣንተም እንደላክኸኝ ኣመኑ”( የዬሐንስ ወንጌል 17:8)

ማነው የላከው?

💥13•
“ይህ የማደርገው ስራ ኣብ እንደላከኝ ስለኔ ይመሰክራልና”( የዬሐንስ ወንጌል 5:36)

ኣብ እንደላከኝ በማለት መልእክተኛ መሆኑን በግልፅ ይናገራል።

💥14•
“የላከኝ ኣብም እርሱ ስለኔ መስክሮዋል”( የዬሐንስ ወንጌል 5:37)

ምን ያደረገኝ ኣብ?
•••••••• የላከኝ√

💥15•
“እኔ ከእግዚኣብሄር ወጥቼ መጥቻለሁና እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ ኣልመጣሁም”( የዬሐንስ ወንጌል 8:42)

ከእግዚኣብሄር የተላከ መልእክተኛ መሆኑን ይነግረናል።

💥16•
“ባሪያ ከጌታው ኣይበልጥም መልእክተኛም ከላከው ኣይበልጥም”
( የዬሐንስ ወንጌል 13:16)
መልእክተኛው ማነው? ላኪውስ ማነው?

💥17•
“ኣብ እንደላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኃለሁኝ”( የዬሐንስ ወንጌል 20:21)

ኣብ እንደላከኝ በማለት የኣብ መልእክተኛ እንደሆነ በግልፅ ነግሮናል።

@yasin_nuru @yasin_nuru

2 months, 2 weeks ago

አስተማሪና መሳጭ ታሪክ!

በስዑዲ የሚኖር አንድ የመኒ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያጋጠመውን ታሪክ እንዲህ ይተርከዋል፡፡
ከፊሌ የዘካ ገንዘብ ሊያከፋፍል ፈልጎ ከሱ ጋር ወጣሁ፡፡ የድሃ መንደሮች ወዳሉባቸው ጠረፍ አካባቢ ሄድን፡፡ የዘካው ገንዘቦች በፖስታ የታሸጉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ፖስታ በውስጡ 5000 ሪያል ይዟል፡፡ ከአንዱ መንደር ወጥተን የጂዳን-ጂዛን መስመር ስንይዝ አንድ የ70 አመት አካባቢ ሽማግሌ አገኘን፡፡ ሽማግሌው ብርቱና ጤናማ ነው፡፡ ጎዳናውን ይዞ ይጓዛል፡፡
ወዳጄ “ይሄ ደግሞ በዚህ ሰዓት በዚህ በረሃ ምን ይሰራል?” አለኝ፡፡

ሹፌሩ “ህገ ወጥ የመኒ ነው” አለ፡፡
ካጠገቡ ደርሰን ቆምንና ሰላም አልነው፡፡
“ከየት ነው ወንድም?”
“ከየመን”
“የት ነው የምትሄደው?”
“የአላህን ቤት ናፍቄያለሁ”
“ህጋዊ ነህ?”
“አይደለሁም”
“ለምን ህጋዊ አልሆንክም?”
“ለዋስትና 2000 ሪያል ማስያዝ ይጠበቅብኛል፡፡ እኔ ያለኝ 200 ብቻ ነው፡፡ በመቶዋ ተሳፈርኩባት፡፡ የቀረኝ መቶ ብቻ ነው” አለ፡፡
“እሺ አጎቴ! በጉዞ ላይ ምን ያክል ሆነህ?” አለው ጓደኛየ፡፡
“ስድስት ቀን!”
“እየፆምክ አይደለም?”
“አይ ፆመኛ ነኝ፡፡”
“ጥሩ፡፡ አንተ ከ 5 በላይ የፍተሸ ኬላዎችን አልፈሃል፡፡ እንዴት ነበር የምታልፋቸው?” ሲለው
“ከሱ በስተቀር እውነተኛ አምላክ በሌለው አላህ እምላለሁ! የማልፈው በነሱው ዘንድ ነው፡፡ ግን አንድም ያናገረኝ የለም!!” አለ፡፡
“ለስራ ነው አመጣጥህ?”
“በጭራሽ ወላሂ! እኔ የአላህን ቤት ናፍቄ ነው የመጣሁት፡፡ ዑምራ ማድረግ ነው የምፈልገው፡፡ ወደ መካ ነው የምጓዘው፡፡”
“በአስፋልት ላይ ስትጓዝ ተዘዋዋሪ ዘቦች /ፓትሮል/ አልያዙህም?”

“ከግማሽ ሰዓት በፊት በ 50 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ ይዘውኝ ነበር፡፡ እዚህ ከመድረሴ አንድ ኪ. ሜ. ቀደም ብሎ ድረስ እነሱ ናቸው ያመጡኝ፡፡ የት እንደምሄድ ሲይቁኝ በአላህ ምየ የአላህን ቤት እንደምፈልግ ስነግራቸው ለቀቁኝ” አለ፡፡
“ሱብሓነላህ! ጭራሽ እስከዚህ ቦታ በፍጥነት እንዲያደርሱህ አላህ ፓትሮሎችን አመቻቸልህ” አልኩኝ በውስጤ፡፡

ወዳጄ ሁለት ፖስታዎችን እየሰጠው “እነዚህን ያዝ፡፡ ዘካ ነው” አለው፡፡
እየተቀበለ “ጀዛኩሙላህ ኸይር” አለ፡፡
በፖስታዎቹ ያለው ገንዘብ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ አያውቅም፡፡
“የሰዑዲን ብር ታውቃለህ?” አልኩት፡፡
“አዎ!” አለ፡፡
“ጥሩ፡፡ ፖስታውን ክፈትና እንዳይጠፋብህ ገንዘቡን በቀበቶህ (በሒዛምህ) ውስጥ ደብቅ” አልኩት፡፡
ሲከፍተው 10 ሺህ ሪያል!!
“ይህ ሁሉ ለኔ ነው?” አለ፡፡
“አዎ ላንተ ነው” አልነው፡፡
ከመኪናው ላይ ወደቀ፡፡ እራሱን ሳተ፡፡ ከመኪናው ወርደን በላዩ ላይ ውሃ መርጨት ያዝን፡፡ “ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው? ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው?” እያለ መጮህ ያዘ፡፡ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ቀጠለ፡፡

ወዳጄ፡ “ከኛ ጋር ትንሽ ወደ ፊት እንውሰደው” አለ፡፡ ከኛ ጋር መኪና ላይ ወጣ፡፡ ትንሽ ሲረጋጋ ጠየቅኩት፡

“ምንድን ነው ይህ ሁሉ ለቅሶ?” አልኩት፡፡
“እኔ የመን ውስጥ ከቤቴ ጎን ቦታ አለችኝ፡፡ ለአላህ ሰጥቻታለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቦቼ በሷ ላይ በጭቃና በድንጋይ አድርገን መስጅድ ገንብተንባታል፡፡ ግንባታው ቢጠናቀቅም ምንጣፍና ጥቂት ነገሮች ቀርተውት ነበር፡፡ ለዚህ መስጂድ እንዴት ምንጣፍ እንደማገኝ ተቀምጬ አስብ ነበር” አለ፡፡

ይህን ሲል የእውነት ሁላችንም አለቀስን፡፡ “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው ዱንያ እንዳለች ትመጣለታለች” የሚለውና “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃቱን ከልቡ ውስጥ ያደርግለታል፡፡ ነገሩንም ይሰበስብለታል፡፡ ዱንያ በግዷ ወደሱ ትመጣለች፡፡ አሳቡ ዱንያ የሆነ ደግሞ አላህ ድህነቱን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል፡፡ ነገሩንም ይበትንበታል፡፡ ከዱንያም የተወሰነለት ብቻ እንጂ አይመጣለትም” የሚለው የነብዩ ﷺ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡

በዚህን ጊዜ ወዳጄን ለሰውየው እንዲጨምረው ጠየቅኩት፡፡ ተጨማሪ 2 እሽግ ፖስታ ሰጠው፡፡ በድምሩ 20 ሺ ሪያል አገኘ ሰውየው፡፡ ሰውየው ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እያለቀሰ ያጉተመትምና ዱዓ ያደርግ ነበር፡፡

“በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ልክ ወፍን እንደሚረዝቀው ይረዝቃችሁ ነበር፡፡ ተርባ ወጥታ ጠግባ ትመለሳለች” የሚለው የነብዩ ﷺ ሐዲሥ መጣብኝ፡፡

@yasin_nuru  <>  @yasin_nuru         

2 months, 2 weeks ago

አንድ ቀን እንዲህ ሆነ…
ረሱል ሰ,አ,ወ ቢላልን ጠርተው ያ ቢላል አሰላቱ ጃሚአ ብለህ ህዝቤን ሰብስብልኝ አሉት ያኔ ቢላል ረ,ዐ ወዲያውኑ አሰላቱ ጃሚአ ብሎ ህዝቡን ሰበሰበ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ወደ ሚንበር ላይ ወጡና እሚገርም ቁጥባ ማድረግ ጀመሩ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ይጠይቃሉ ሰሀባወች ይመልሳሉ ።
.
ረሱል ሰ,ዐ,ወ የእኔ ነብይነት ለእናንተ እንዴት ነበር ???
በደንብ አስተምሬአችሆለሁን ?
ሀቃችሁን ሁሉ ተወጥቻለሁ ወይን? ብለው ጠየቁ።
.
ሰሀባወችም አንቱማ በጣም ረሂም አባት ነበሩ እንዲሁም መካሪ ወንድም እናት ነውት እኮ ለእኛ አሎቸው በሉ እንግዲያውስ በአላህ ይዧችሆለሁ ምናለልባት የበደልኩት ሰው ካለ ነገ አኼራ ላይ እንዳይጠይቀኝ ዛሬ ላይ ይኸው የበደልኩት ካለ ንብረቱን የወሰድኩበት ሰውም ካለ የመታሁት ዛሬ ነውና እድሉ ይምጣ እና ይበቀለኝ ብለው አሉ።
.
ሁሉም ፀጥ አሉ ማንም አልተነሳም አሁንም ለ2ኛ ጊዜ ደገሙና በአላህ ይሁንበት የበደልኩት ይምጣና ይበቀለኝ ይሄው አለሁ ሁሉም ፀጥ አሉ።
.
ለ3ኛ ጊዜ ደገሙና ያመእሸረል ሙስሊሚን አስኪ ማነው እኔን መበቀል እሚፈልግ ትላንት በእኔ የተከፋ አለን? በአላህ ይሁንባችሁ ይኸው እኔ እዚህ አለሁ የበደልኩት ሰው ይምጣና ይበቀለኝ ሲሉ ይህኔ በእድሜ የገፋው ኡካሻ የሚባሉ ሰሀባ ተነሱና ፊዳከ ቢአቢ ወኡሚ ወላሂ ያረሱለላህ በአላህ ይሁንባችሁ አያልክ ደጋግመው ባይጋብዙ
ኖሮ ወላሂ እኔ ለእዚህ ጉዳይ እምቆም አልነበርኩም ።
በእርግጥ አንድ ቀን ከእርስዎ በደል ደርሶብኛል ፊዳክ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ☞ ከእለታት አንድ ቀን አንቱ ጋር ጦርነት ላይ አላህ ማሸነፍን አድሎን ሰጥቶን ወደየቤታችን ልንመለስ እያልን ሳለን ያንቱ ግመል ከእኔ ግመል አጠገብ ለአጠገብ ሆነው ነበር።
እናም እኔ የእግረዎትን ጡንቻ ለመሳብ ከግመሌ ወረድኩ ወደ እግረዎ ዝቅ ስል በእጅዎ የያዙትን አለንጋ ዝቅ ሲያደርጉ ወገቤን እስከ ሆዴ
ጭምር መቱኝ ሆን ብለው ነው የመቱኝ ወይስ አለንጋውን ከፍ ለማድረግ አላቸው?
☞ረሱል ሰ,ዐ,ወ አሉ ኧረ አውቄ እማ ከመምታት አላህ ይጠብቀኝ አላወኩም አሉት ።
.
እና አሁን ምን ትፈልጋለክ ሲሉት እኔማ እምፈልገው የመቱብኝ ቦታ መምታት ነው አላቸው ለረሱል (ሰዐወ)
☞ረሱል ሰ,ዐ,ወ ቢላልን ጠሩትና ያ ቢላል በል ከፋጡማ ረ,ዐ ቤት ሂድና አለንጋዋን አምጣ ብለው አሉት።
.
ቢላልም ሄዶ ያ ፋጡማ ቢንት ረሱል ሰ,ዐ,ወ
ረሱል ሰ,ዐ,ወ አንቺ ጋር ያስቀመጡትን አለንጋ ላኪ ብለውሸል አላት።
ያ ቢላል ዛሬ የሀጅ ቀን ወይም የዘመቻ ቀን አይደለም ምን ሊያደርጉት ነው አለችው።
ቢላልም ቀጠለና ያ ፋጢማ አልሰማሽም እንዴ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ የደረሰባቸውን የተባሉትን አልሰማሽምን?
.
ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ከዚህ አለም አየሞቱ ወደ እዛኛው አለም እየተሸጋገሩ እኮ ነው ። ያ ፋጡማ አልሰማሽም እንዴ መሄዴ ነው እና በቀል ካላችሁ ተበቀሉኝ አሉ እኮ ታዳ ማነው ነብዩን እሚመታ እሳቸውን እሚገርፍ?
ያ ቢላል ማነው ሀሰን እና ሁሴንን ውሰድ እና በረሱል ቦታ ይገረፉው እነሱ እያሉ ረሱል ሰ,ዐ,ወ አይገረፉውም አለች አለንጋውን ለረሱል ሰ,ዐ,ወ ወስዶ ሰጣቸው።
.
እሳቸውም ተቀበሉና ያ ኦካሻ በል ወገቤም ሆዴም የሄው ምታኝ አሉት ኦካሻም ሊመታቸው ተነሳ ያኔ አቡበከር ረ,ዐ ቆሙ ኡመርም ረ,ዐ ተነሱ ያ ኦካሻ እኛ እያለን ረሱልን እንዳትነካብን አሉ ።
.
ይሄው እኛ ቆመናል እኛን ግረፍ አሉት ።
እሳቸውን እንዳትመታብን ያ ኦካሻ እያሉ የማፀኑት ጀመር።
ረሱል ሰ,ዐ,ወ እንቢ ያ አቡበከር እንቢ ያ ኡመር አላህ ሱ,ወ ለእኔ ያላችሁን ቦታ አውቋል አይቷል ወዶታል እና ተቀመጡ አሉ ።
ምታኝ ያ ኦካሻ ሲሉት አልይ ኢብን አቡጣሊብ ረ,ዐ ተነሳና ያው እኔን እንደፈለክ ወገቤም ሆዴም አደራ ብየሀለሁ ረሱልን እንዳትነካብኝ እኔን እንደፈለክ አርገኝ አለ።
ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ አልይ አላህ ያንተንም ለእኔ ያለህን ቦታ ወዶታል ቁጭ በል አሉት ።
.
የዛኔ የፋጡማና አሊ ረ,ዐ ልጆች ሀሰንና ሁሴን ተነሱ እና ያ ኦካሻ የረሱል ሰ,ዐ,ወ የልጅ ልጆች መሆናችንን አታውቅምን ነብዩን እንዳትነካ እኔን እኔን ግረፍ አማና ያ ኦካሻ እያሉ የማፀኑ ጀመር ።
ይህኔ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ ቁረተል እዩኒና አይደለም ተቀመጡ አሎቸው።
.
☞ያ ኦካሻ እምትመታኝ ከሆነ ምታኝ አሉት።
ያረሱለላህ እርስወ እኮ የመቱኝ ሆዴ ክፍት ሆኖ ነው እንዴት አድርጌ ከእነ ልብስዎ ልምታወት ይህኔ የኸው ሆዴ በለው ገለጡለትና ምታኝ አሉት ።
.
ይህኔ ሰሀባዎች በእንባ ተራጩ ። ያ ኦካሻ አይከብድህም አታፍርም ነብዩን ልትመታ ነው? እያሉ ይጮሀሉ ።
.
የነብዩ ሰ,ዐ,ወ ሆድ በሚያይ ሰአት በሚገርም ሁኔታ ፊዳከ ቢአቢ
ወኡሚ ፊዳከ ቢአቢ ወኡሚ እያለ ይስማቸው እየላሳች ይጮሀል ።
ይህኔ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ ኦካሻ ወይ ምታ ወይ አፉው በል አሉት።
አላህ የውመል ቂያማ አፉዉ እንዲለኝ አፉው ብየዎታለሁ እኔ እኮ ልመታወት ፈልጌ አይደለም ቆዳየ ከቆዳወ ጋር አንዲላተም እንዲገናኝ ብየ ነው።
.
ረሱል ሰ,ዐ,ወ ተናገሩ ጀነት ውስጥ የእኔ ጎደኛ የሆነን ሰው ማየት እሚፈልግ ካለ ወደ እዚህ ሽማግሌ ይይ አሉ። እንዳለ ሰሀባዎች የኡካሻን ግንባር እየሳሙ የረፊቅል አእላ ባለቤት እያሉ ያለቅሳሉ ኦካሻም ያለቅሳል
ሰሀባዎች ይህን ያህል ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ያፈቅሮቸው ነበር ።
እኛስ?

@yasin_nuru  <>  @yasin_nuru       

2 months, 2 weeks ago

🌟ህፃኑ ከእናቱ እና ከአንዲት እንስት ጋ ሁኖ ሳያየው የሞተበትን የአባቱን ቀብር ለመዘየር የዐረቢያ በረኃዎችን እያቆራረጠ ይጓዛል።

ናፍቆትን የቋጠሩ የህፃኑ አይኖች የአባቱን ቀብር ተመልክተው ከህፃን አንጀት የሚንጠፋጠፉ የእዝነት ስሜቶችን ቋጥሮ ወደ መጣበት በረኃውን እያቆረረጠ ሊመለስ ጉዞውን አብረው ጀመሩት።

እልም ባለው በረኃ፣ ደራሽ በሌለበት እና የጮኺ ሰሚ ባማይታይበት የአሸዋ ውቅያኖስ ላይ ህፃን እናቱ በጠና ታመመችበት።

እናት የቲም ልጇን ከበረኃ ላይ ሁና በእዝነት ተመለከተችው፣ ወደራሷ ጠጋ አድርጋ አቀፈችውም፣ ከጉንጯ እንባዎች እየፈሰሱ የተሰናባች አሳሳምም ልጇን ስማ እስከ ወድያኛው አሸለበች።

ከጎኑ አንዲት እንስት ብቻዋን ቀረች፤ የ 6 አመት ህፃኑ አባት እና እናቱ ለበረኃ ሲያይ ሁነው በማይራራው በረኃ ባይተዋር ሆነ።

አብራው የቀረችው እንስት ህፃኑን ጠርታው ከሚያቃጥለው የበረኃ አሸዋ በትናንሽ እጆቹ ለእናቱ ማረፍያ የሚሆን ቀብር ቆፍሮ እንዲያግዛት አዘዘችው።

እንስት ከልብሷ ቀንሳ ሟቿን ገነዘች። በህፃን ጣቶች ተቆፍሮ በተዘጋጀላት የማረፍያ ስፍራ እናት አፀደ ገላዋ አረፈ። አፈር ተመልሶ እናት ከቀብር በታች ቀረች።

ህፃን የቀበራትን እናት ትቶ ጎዞ ሲጀምር ከትናንሽ አይኖቹ የሚፈሱትን እንባዎች በአዋራማ እጆቹ እየጠራረገ ከእንስቲቱ ጎዞን ቀጠለ።

ያላየውን አባቱን ቀብር ልይ ብሎ ወጥቶ ያያትን እናቱን በበረኃ ቀብሮ ሲመለስ ህፃን ልቡ ተሸበረ። ባይተዋርነት ወረረው።

ሰዎች ሆይ! እስቲ ፍረዱ፤ ከዚህ በላይ ሀዘን አለ?
እስቲ ተናገሩ የዚህ ብላቴና ልብ ይህን ሁሉ ህመም ይቋቋማል?

ይህ አሳዛኝ ብላቴና ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?
«ነብያችሁ ሙሀመድ ዐሰወ ነው።»
ያ በልጅነቱ የባይተዋርነትን ህመም ሲቀለብ አድጎ፤ በጉልምስና ዕድሜው በኛ የመዳን ጉዳይ የጭንቀትን ምሬት በልቅሶ ሲጋት የኖረው ሙሀመድ ሰዐወ ነው!!!

"ረመዳን ገጥሞት ሳይጠቀምበት ምህረት ሳያገኝ የሄደበት ሰው በአፍጢሙ ጀሀነም ይደፋ!"፡ ጂብሪል(ዐሰ)፤ አሚን በል ሲላቸው
ነብዩ(ሰዐወ) "አሚን"ብለዋል! ጠንቀቅ እንበል አደራ!!

@yasin_nuru  <>  @yasin_nuru       

2 months, 3 weeks ago

ኢናሊላሂ ወኢና አሊይሂ ራጂዑን😳😳

ፔንጤዎች እንደ ሙስሊም ሆነው ምን እንደሚያረጉ ተመልከቱ😭😭

"በመሲህ ኢሳ የጀነትን መንገድ አገኘን እያሉ ነው ያልቀሩ ሙስሊሞችን ለማሳሳት"

@yasin_nuru @yasin_nuru

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 2 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 5 days, 7 hours ago