Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

Description
ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 4 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month, 2 weeks ago

በዚህ ቻናል ሀገራዊና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን በፍጥነት ያገኛሉ❗
የውስጥ መስመር👉http://t.me/ayulaw

Last updated 3 days, 15 hours ago

1 month, 1 week ago

“ሶስት ጁምዓዎችን ያለ በቂ ምክንያት የተወ ከሙናፊቆች ተደርጎ ይመዘገባል።”

ረሱል ﷺ

1 month, 1 week ago

ባለፉት 29 ዓመታት የህገ-መንግስቱን ግልጽ ድንጋጌዎች ሆንብሎ ያለአግባብ በመተርጐም ሙስሊሙ ማህበረሰብ በልዩነት ሲጠቃባቸው የነበሩና ማህበረሰቡም ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያቀርብባቸው የነበሩ መመሪያዎችና አሰራሮች መወገድ ሲገባቸው በዚህ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ በድጋሚ ተካተው መገኘታቸው በህዝብ ዘንድ ከወዲሁ እየፈጠረ ያለው ከፍተኛ የስጋት ስሜት ለወደፊቱም ከሀገር ደህንነትና ሰላም አንፃር የሚያመጣውን ውጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣

አዋጁ በብስለትና በስክነት ታይቶ ተጨባጭ የሆኑ የጥናት ውጤቶች ተንፀባርቀውበት፣ ከገዳቢነት ይልቅ መብት ማስከበርን መርሁ ያደረገ አዋጅ እንዲሆን እንደገና እንዲከለስና ተጨማሪ ሰፊ ጊዜ ተወስዶበት እንዲወጣ ያለንን አቋምና ስጋት እየገለፅን ም/ቤታችን ከዚህ አንፃር የሙስሊሙን ማህበረሰብ ፍላጎትና መብት እንዲሁም በረቂቅ አዋጁ ላይ ቢካተቱ የሚላቸውን ገንቢ ሀሳቦች በዝርዝር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የሚያቀርብ መሆኑን እያሳወቀ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ረቂቅ አዋጁ እንደ ተቋም በፅሁፍ እንዲደርሰን ለመጠየቅ እንወዳለን፡፡
“ከሰላምታ ጋር”

1 month, 1 week ago

የሃይማኖት ጉዳይን አስመልክቶ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የም/ቤታችንን አቋም ስለማሳወቅ፤
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 🔴🔴🔴🔴🔴

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሀ ሃይማኖት መገኛ ሆና ሳለ ለዘመናት የሃይማኖቶች እኩልነትና የሐገር ባለቤትነት ጉዳይ ከሙስሊሙ አንፃር ሳይረጋገጥ በመኖሩ እስልምና እንደ ሃይማኖት ሙስሊሙ ማህበረሰብም እንደ ዜጋ ከፍ ያለ ዋጋ ሲከፍሉ ኖረዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ህዝበ ሙስሊሙ ከንጉሳዊው የአስተዳደር ዘመን ጀምሮ መንግሰትና ሃይማኖት የተለያዩ እንዲሆኑና የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት እንዲከበር መራር ትግል ሲያደርግ ቆይቷል።

ከዚህም በመነሳት ሙስሊሙ በታላቁ የኢትዮጲያ ህዝባዊ አብዮት ዋነኛ ተሳታፊ ነበር። አብዮቱ ካስገኛቸው ድሎች አንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ መንግስትና የሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸው የተደነገገበት የደርግ ዘመን 1979 ህገ መንግሰት ተጠቃሽ ነው። ይሁን እንጂ መብቱ በህገመንግሰት ይካተት እንጂ በተግባር ስራ ላይ ሳይውል ጭቆናው ቀጥሎ ቆይቷል። በአንፃራዊነት በ1983 የነበረውን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ የመንግስትና የሃይማኖት መለያየት በ1987 ፀድቆ እስከ አሁንም በስራ ላይ የሚገኘው የኢፊዴሪ ህገ-መንግስት በግልፅ በመቀመጡ ከቀድሞ የተሻለ ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
ነገር ግን ህገ-መንግስቱ ውስጥ በመርህ ደረጃ የተቀመጡትን የመንግሰትና ሐይማኖት መለያየት እንዲሁም የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት መብቶችና መሰረታዊ መርሆዎችና ድንጋጌዎች ለማስፈፀም የሚውሉ ዝርዝር ህጎች ሳይወጡ በመቆየቱ ምክንያት መብቶቹን በምሉዕነት መጠቀም አልተቻለም። ይባስ ብሎም አንዳንድ ተቋማት ህገመንግሰታዊ የሆነውን የመንግሰትና ሃይማኖት መለያየት መርህ ያልተገባ ትርጉም በመስጠት ለአድሏዊ አሰራር ሲያዉሉት ተስተውለዋል። አንዳንድ ተቋማትም የህገ-መንግስቱን ግልፅ ድንጋጌዎች የሚቃረኑ፤እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ኢላማ ያደረጉ ደንቦች፤መመሪያዎችንና አሰራሮችን በመዘርጋት ህዝባችን ላይ ጥቃቶችና በደሎች ሲያደርሱበት በስፋት ተስተውለዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብም በተለያዩ ጊዜያት እነዚህ በደሎችና ጥቃቶች በዘላቂነት ሊያስቆሙለት የሚያስችሉና ህገ መንግስተዊ መብቱን በምሉዕነት እንዲገለገልባቸው የሚያስችሉ ዝርዝር ህጎች በአግባቡ እንዲወጡና ስርዓት ያለው ወጥ አሰራር እንዲኖር ሲወተውቱ ቆይተዋል፡፡

ከዚህም በመነሳት የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህገመንግስታዊውን የመንግስትና ሃይማኖት መለያየት መርህን እንዲሁም የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነትን በዝርዝር ለማስፈፀም አዋጅ መውጣቱን በመርህ ደረጃ ይደግፈዋል። ይሁን እንጂ ከአዋጁ ረቂቅ ዝግጅት ጀምሮ ህጉን ለማውጣት እየተኬደበት ያለው ሂደትና ፤የረቂቅ አዋጁ ይዘትን አስመልክቶ ከሰሞኑ እየተስተዋለ ያለውን የህዝበ ሙስሊሙን ፍላጎትና ስጋት በእጅጉ ይጋራል።

ምክር ቤታችን መንግስት ሊያወጣው ያሰበው ረቂቅ አዋጅ እንደ ሙስሊም ማህበረሰብ ወኪልነቱ እንደዚ ያሉ መመሪያዎች ባለመኖራቸው የተነሳ በሙስሊሙ ላይ ይደርሱ የነበሩትን ያልተማከሉ ነገር ግን የተቀናጁ የሚመስሉ ጥቃቶችን በወጥነት ያስቆማል ብሎ ስለሚያምን ለአዋጁ ያለውን ድጋፍ ከወዲሁ መግለፅ ይፈልጋል። በአዋጁ ላይ ያሉንን አስተያየቶችና ስጋቶች የምንገልፀውም የመንግስትን ፍላጎት ወይም አላማ በመጥፎ በመረዳት ሳይሆን በሀገራችን የህግና የአዋጆች መውጣት ታሪክ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎችና ጥቅሞች የማይገናዘቡበት የቆየ አሰራር በመኖሩ አንዳንድ ለኛ ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን አንድም ባለማወቅ ወይን ደግሞ በግለሰቦች የተለየ ፍላጎት የተነሳ ቸል ሲባሉ እና ሙስሊሙን ተጎጂ ሲያደርጉ በመኖራችን ስጋት ስላለን መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን።

ይህ የአማኞች ሀገር በምትባለው ሀገራችን ሊወጣ እየተዘጋጀ የሚገኘው አዋጅም የሃይማኖትን እኩልነት፣ የመንግስትና የሃይማኖትን መለያየት በተለያዩ ጊዜያት በሙስሊሙ ማህበረሰብ በተለይም ደግሞ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሚገኙ ሙስሊም ሰራተኞችና ባለስልጣናት ላይ ይደርስ የነበረውን ግልጽ የሆነ ተቋማዊና ግለሰባዊ የሆነ የበደልና የጥቃት ተግባራትን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀርፍ መሆን እንዳለበት ም/ቤታችን ያምናል፡፡

ከዚህ አንፃር በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ እየተነሱ ካሉ የህዝባችን ሃሳቦች በመነሳት ምክር ቤታችን በተወሰነ መልኩ ለማጣራት ባደረገው ጥረት ረቂቅ አዋጁ እነዚህን ነባር ችግሮች ከመቅረፍ ይልቅ የሚያባብሱና ተጨማሪ ችግሮችን የሚያስከትሉ አንዳንድ ድንጋጌዎች እንዳሉበት ለመገንዘብ ችሏል።

በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በተደረገው ውይይት መሠረት ሰፋ ያለ የሙስሊሙን መብት የሚመለከቱ ጉዳዮችን በዝርዝር የሚያቀርብ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ጠቅላይ ምክር ቤታችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ጉዳዮች ላይ ያለውን ጥብቅ አቋምና ስጋት ለማቅረብ ይወዳል፡-

  1. ምንም እንኳን ህግ መውጣቱ የምንፈልገውና የቆየ የህዝባችን ጥያቄ ቢሆንም የእምነታችንን የተለዩ የአምልኮ ባህሪያት ግምት ውስጥ ሳያስገባ በስመ እኩልነት ብቻ ከሌሎች ሃይማኖቶች የአምልኮ ስርዓት ጋር በማነፃፀር እዚህም እዚያም ከልክለናል በሚል የተሳሳተ መነሻ የተቀረፀው እንዲሁም በእምነታችን የአምልኮ ስርዓት ውስጥ በመግባት አንድ ሙስሊም በእምነቱ የታዘዘውን የአምልኮ ተግባር እንዴት ማከናወን እንዳለበት እሰከመምረጥ ድረስ ገደብ ለመጣል በሚሞክሩ አናቅፅ የተሞላ ረቂቅ አዋጅ መሆኑ ተገቢ ስላልሆነ ፣

  2. የሃይማኖትና የአማኞች ሃገር ናት የምትባለውን ሃገራችንን ሃይማኖታዊ እሴቶች ከማጎልበትና ሃይማኖቶችን ለሃገራዊ አንድነትና እድገት በአዎንታዊነት ከመጠቀም ይልቅ የሀገራችንን ተጨባጭ ባለማገናዘብና ወደጐን በመተው እምነቶችን በበማዳከም ለሃገር ከሚያበረክቱት ገንቢ አስተዋፅኦ የማግለል ባህሪ ያለው በመሆኑ ፣

  3. ሃገራችን ህብረ ብሄራዊ የፌዴራል ስርዓት የምትከተል እንደመሆንዋ በተለያዩ ክልሎች በመሬት ላይ ያለውን እውነታ በፍፁም ከግምት ውስጥ ያልከተተና ተፈፃሚነት የሌለው ህግ እንዳይሆን የሚያሰጋ በመሆኑ፣

  4. ረቂቅ አዋጁ በመሠረቱ አንድ ህግ ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚወጣበትን መርህ በመጣስ በህገ መንግስቱ የተረጋገጠውን የእምነት መብትና ነፃነትን ከማስፈፀም ይልቅ መገደብ ላይ በማተኮር የአለም አቀፍ ህጐችንና ህገ መንግስታችንን የሚቃንኑ ሀሳቦች ያሉበት በመሆኑ ፣

  5. የመንግሰትና ሃይማኖት መለያየት መርህ ዋና አስኳል የሆነውን የመንግስትን በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ የመግባት ሁኔታ ከመገደብ ይልቅ፤ያለአግባብ መንግሰት በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ መግባትን የሚያበረታታና መንግስት የሀይማኖቶች ተቆጣጠሪ የማድረግ ባህሪ ያለው በመሆኑ ፣

  6. ሕገመንግስታዊውን የሃይማኖት ነፃነትን ከማስከበር አንፃር የእምነታችንን ልዩ የአምልኮ ባህሪያት በመረዳት ለዚያ የሚመች ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ይልቅ አምልኮዎችን መከልከል ላይ ማተኮሩ፣

ለምሳሌ፡- በት/ት ቤቶች እና በመንግስት ተቋማት አካባቢ ሙስሊሙ ግዴታ የሆነበትን ሰላትና የሴቶች አለባበስ ሁኔታ የመከልከልን ባህሪያት የተሞላ መሆኑ ፣

  1. የመንግስትና የሃይማኖትን መለያየት አስመልክቶ ለረቂቅ አዋጁ ግብዓት ተደርገው የነበሩ ጥናቶችን ውጤትና ምክረ ሃሳቦች ወደጐን በመተው ህግ አርቃቂዎቹ አካላት በተቃራኒው ለመሄድ የመረጡበት አግባብ ትክክል አለመሆኑ ፣
2 months, 3 weeks ago

“ነገር አዋሳጅ ጀነት አይገባም።”

ረሱል (ﷺ)

2 months, 3 weeks ago

“እጁ አመድ አፋሽ ይሁን ሰውዬው ረመዳን በሱ ላይ ገብቶበት ወንጀሉ ሳይማርለት በፊት ረመዳኑ የወጣበት።”

ረሱል (ﷺ)

2 months, 3 weeks ago

“Rabbiin gabricha isaatif waan gaari wayta fedheef arraba isaa Nabi Muhammad ﷺ irratti salawaata akka buusu laaffisaaf.”

(Ibnu Al-jawzii)
صلوا عليه…

3 months ago

«አንዳችሁ ፆመኛ በሆናችሁበት ቀን አፀያፊ ንግግር አይናገር። አይጩህም። ከተሰደበ ወይም ከተጋደሉት "እኔ ፆመኛ ነኝ ፣ እኔ ፆመኛ ነኝ" ይበል።»

ነቢዩ (ﷺ)

3 months ago

Ergamaan Rabbii(‎ﷺ) akkana jedhaniiran:–

«Namni tokko maatii ofiitif yaade baasin inni baasu akka sadaqaatti lakkaahamaaf.»

3 months ago

የትንሳኤ ቀን እኔ ዘንድ በላጩ በኔ ላይ ብዙ ሰለዋትን ያወረደ ነው።

ረሱል ﷺ

3 months, 1 week ago

📌 ረመዳን ሙባረክ!

የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የረመዳን ወር ነገ ሰኞ march 11 እንደሚጀምር ታውቋል።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 4 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month, 2 weeks ago

በዚህ ቻናል ሀገራዊና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን በፍጥነት ያገኛሉ❗
የውስጥ መስመር👉http://t.me/ayulaw

Last updated 3 days, 15 hours ago