ኢማን 🌙тυℬℰ™🌙

Description
<< `በጊዜያቱ እምላለሁ ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው ፤ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ፥ በእውነትም አደራ የተባባሉት ፥ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።` >>
ሱረቱል ዐስር፦(1፥3)

For comment an& cross
▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
@Alhamdulilah25
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 2 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 5 days, 7 hours ago

1 day, 11 hours ago

✍️ለታቦት አምላኪዎች⁉️

ታቦቱ፦
ሰው ጠርቦ ይሰራዋል፤ የፈለገው ስያሜ ይሰጠዋል፤ የፈለገው ቦታ ያስቀምጠዋል፤ ሲፈልግ ይሸከመዋል፤ ሲፈልግ ያስቀምጠዋል፤ ሲፈልግ ያጥበዋል፤ ሲፈልግ ይቀባዋል፤ ተሸክሞ እየወሰደውም "አልሄድ አለ" እያለ ይጃጃላል።

ከዚህ ሁሉ በኋላ "ባመልከው ይጠቅመኛል ብተወው ይጎዳኛል" ብሎ ይሰግድለታል፤ ይስመዋል።
አይደል እንዴ

የገብርኤል ታቦት ማን ጠርቦ ማን ቀርፆ ነው የሰራው {የሰው ልጅ}

የመድሀኔዐለም ታቦት ማን ነው ጠርቦ ማን ቀርፆ ነው የሰራው {የሰው ልጅ}
.
.
.
ማን ነው ወደ ወንዝ ወስዶ የሚጠምቃቸው {የሰው ልጅ}

ከታቦቶቹ አንዱ ታቦት ወንዝ ጥላችሁት ብትሄዱ ተነስቶ መምጣት ይችላል
የሚችል ከሆነ ለምን ተሸክማችሁ ወስዳችሁ ተሸክማችሁ ትመልሱታላቹስለ ማይችል ነው

ተሸክማችሁ ስትወስዱት ለምሳሌ የሚካዔል ታቦት  ለምን "አልሄድ አለ" ትላላችሁ

ሰው ነው የተሸከመው። የሚወስደውም የሚያስቀምጠውም ሰው ነው አይደል እንዴ

እሺ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ እንዴት እያሰባችሁ ነው እነዚህ ክንውኖቻቸው ሁሉ በሰው እጅ የሆኑ ቁሶችን አምላክ አድርጋችሁ የምቲዙት

ይህ እኮ ልክ አንድ መኪና ሰው ይሰራዋል፤ ይቀባዋል፤ ስያሜ ይሰጠዋል፤ ወደ ፈለገበት ይወሰደዋል፤ በፈለገ ጊዜ ያጥበዋል።

የናንተም ታቦቶች ክንውን ከዚህ የተለየ ነገር የለውም።

እና ቆም ብሎ ማሰብ የሚባል ነገር የለም ወይ

እንዴት ተብሎ ነው ሰማያትና ምድር በውስጣቸው እስካሉ ነገሮች፤ ፀሀይና ጨረቃ .... በአጠቃላይ የምናውቃቸውና የማናውቃቸው ነገሮች የፈጠረው ብቸኛው አንድ ፈጣሪ መገዛት ትታችሁ እነዚህ በሰው እጅ ተዘጋጅተው የተቀመጡ ግዑዝ ነገሮችን የምትገዙት

NB: መበሻሸቅና መሰዳደብ ባህሪያችንም ፍላጎታችንም አይደለም።

ፍላጎታችን=> ፍጡር ፍጡርን ከማምለክ ወጥቶ ፈጣሪን እንዲያመልክ መጣራት ነው‼️

📖📖📖📖📖📖📖📖
እስልምና ብቸኛው መፍትሄ ነው‼️
📖📖📖📖📖📖📖📖

@sineislam
@sineislam

2 days, 8 hours ago

🍃 #ወንድሜ_ጥሩ_ትዳር_እንድኖርህ_ትሻለህን ?

አወን ከሆነ መልስህ ፦ ኢማም አህመድ ኢብኑ ሀንበል አላህ ይዘንላቸውና ልጃቸው ሲያገባ የለገሱትን ምክር ላካፍልህ ነውና ለኔ ብለህ ስማ !!
.
#ልጀ #ሆይ እነዚህን አስር ነገሮች ለባለቤትህ ለመፈጸም ካልቻልክ በትዳር ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል ምክሬን ምክሬን ጠበቅ አድርገህ ለመያዝ ሞክር ፦.......
.
⭐️ #ሴት #ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት !
.
⭐️ #ሴት #ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ፍቅርህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል !
.
⭐️ #ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር !
.
⭐️ #ሴቶችን መልካም ንግግር ውብ ገጽታ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንድኖሩህ ጥረት አድርግ !
.
⭐️ #ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያክል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው ቤቷ ስትሆን ዙፍኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያክል ክብር ይሰማታል በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባትን ነገር እንዳትፈጽም ከንግስና ዙፍኗ ላይም ልታወርዳት አትሞክር ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ ልታደርግ ይገባል !
.
⭐️ #ሴት የቱን ያክል ብትወድህም ቤተሰቦቿን ማጣት አትፈልግም አንተን ከቤተሰቦቿ በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር ይህን ማድረግ ፍጻሜው የማያምር ጠላትነት ሊያመጣብህ ይችላልና !
.

⭐️ #ሴት ከጎንህ ጠማማ ዐጥንት መፈጠሯን አትዘንጋ ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን እወቅ ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለሁ እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ ስብራቷ ፍች ነው ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠምም መንገድ አትክፈትላት መካከለኛ ሰው ሁንላት !
.
⭐️ #ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች ስትናደድ ያደረክላትን ነገር ልትክድ ትችል ይሆናል ነገር ግን እንድህ አደረገች በማለት ብቻ አትጥላት ይህን ባህሪዋን ባትወድላት ሌሎች የሚያስደስቱህ ብዙ ባህሪያት እንዳላት አትዘንጋ !
.
⭐️ #ሴት አካላዊ ድካምና ልቦናዊ ጫና ሊያድርባት ይችላል በዝህ ወቅት አላሁ ሱ.ወ የግደታ አምልኮወችን ሶላትና ጾም ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል በነዚህ ጊዜ እዘንላት ትእዛዝ አታብዛባት !
.
⭐️ #ሴት አንተ ዘንድ ያለች የፍቅር ምርኮኛህ መሆኗን አትዘንጋ ምርኮኛህን ደግሞ በጥሩ ሁኔታ መያዝ ይጠበቅብሀል እዘንላት በድክመቷ የምትፈጽመውን ስህተት ይዘህ ከመጨቃጨቅ ይልቅ አውፍ ብለህ ከጥፍቷ እንድትስተካከል አድርግ ምርጥ የህይወት አጋርህ ትሆናለችና ።
.
💐💐አላህ ሁላችንንም ሷሊህ የትዳር አጋር ይወፍቀን Amiiiiiiiiiiiiiiiiin በሏ
.
ልብ ያለው ልብ ይበል !!!!!!!
.
👏ይህ ውብ ትምህርት ሌሎች ወንድሞች ጋር ይደርስ ዘንድ አንብበው ሲጨርሱ ሸር ያርጉት

@sineislam
@sineislam

4 days, 10 hours ago

#ውድ_ምክር_ለውድ_እህቴ

ሙዚቃና በሃራም መንገድ ወንዶች ጋር የምትደዋወሉ ክብረ ንፅህናችሁንና ማንነታችሁን አርክሳችሁ በየ ሚዲያውና በየቴሌቪጅኑ በየ ቲክቶኩ... መስኮት የምትወጡ በከንቱ ስሜታ ላይ ላላችሁ
ወደዳችሁም ጠላችሁም የሆነ ቀን ትሞታላችሁ ከጀናዛ አልጋ ላይ ትተኛላችሁ በፍላጎታችሁ ሳይሆን በግዳችሁ!

አስተውይ እህቴ ከጀናዛ አልጋ ላይ ስተኝ ብቻሽን ነው ጓደኛም ሆነ ሌላ ወዳጅሽ አይከተልሽም ታዲያ ያኔ ለአላህ ምን ልትይው ነው?
አላህ የምትሰሪውን እንደሚከታተልሽ እያወቅሽ ግን ከአላህ ይልቅ የሰዎች ሃቅ ያስበለጥሽ እህቴ ያኔ ለአላህ ምን ልትይው ይሆን!?
የሆነ ቀን በድንገት ቀንሽ ይደርስና ከጀናዛ አልጋ ላይ ትታጠቢያለሽ ግን አስተውለሽ ታውቂያለሽ ከዛ አልጋ ላይ ተኝተሽ ታጥበሽ በነጠላ ጨርቆች ብቻ ነው ተገንዘሽ ወደ ቀብርሽ የምትገቢው
አላህ ያዘነላቸው እህቶች ብቻ ሲቀሩ ብዙዎች በዚህ ሰአት በሰርግ ሰአታቸው ሰውነታቸውን እየተገላለጡ ነው ሚገኙት
ረሱላችን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)እንደተናገሩት ከኡመቶቸ ብዙ ሴቶችን ጀሃነም ውስጥ ያየኋቸው በእርቃን ልብስ የሚገላለጡ ነው ብለዋል።
ያ አላህ! ውድ እህቴ ለመሆኑ የጀሃነም እሳት ከዱንያዋ እሳት በምን ያክል እጥፍ እንደምትበልጥ አውቀሽ ይሆን?
   አላህ ሆይ ጠብቀን ከእሳት!

በአላህ  ይሁንብኝ ራሳችሁን የምትገላለጡ እህቶች አስቡት በዱንያ አንድም ቀን በስርዓት ሳትሸፈኑ ነገ ሞታችሁ በጀናዛ አልጋ ላይ በነጠላ ጨርቅ ተገንዛችሁ ቀብር ከመግባታችሁ በፉት ራሳችሁን ብትሸፍኑ አይሻልም?

አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ በአንድ ዛፍ ላይ ያሉ ቅጠሎች ከዛፉ ላይ ከረገፉ የግንዱ መጨረሻ ምን እንደሚሆን ታውቃላችሁ? ተቆርጦ እሳት ላይ ይማገዳል አይደል?
ልክ አንደዛው አንዲት ሴት ራሷን ከገላለጠች ቁጥብነቷን ከራሷ ላይ ከገፈፈችውና በማይረባ ብጥቅጥቅ ልብስ ራሷን ከገላለጠች መጨረሻዋ የዛ ግንድ ነው ሚሆነው።
  በአላህ ይሁንብኝ የሴት ልጅ ቁጥብነቷ(ሃያዋ)ለአላህ ያላት እውነተኛ ታማኝነትና ኢማኗ ነው።
    እባክሽን እህቴ ወደ አላህ ተመለሺ

በዚህ ባለንበት ዘመን ሰርጎች የጭፈራ ፕሮግራሞችና መሰል የፊትና መድረኮች የበዙበት ግዜ ላይ ነው ያለነው
አላህ ያዘነላቸው እህቶች ሲቀሩ ብዙዎች በዚህ ፊትና ላይ ወድቀዋል

በአላህ ይሁንብኝ ውድ እህቴ ብዙ ሙሸራዎች አሉ በሰርግ ቀናቸው የሰርግ ልብስ ከመልበሳቸው በፊት ከፈን አድርገው ወደ ቀብር የገቡ ውድ እህቶቸ ለዚች ዱንያ አትጨናነቁላት ይህች ዱንያ ረጅም መስላ የምትታያችሁ ካላችሁ አትሳሳቱ በጣም አጭር ናት።

ሌላው መልዕክቴ ደግሞ አይናችሁን የምትቀነደቡና ሰውነታችሁን ለባዳ ወንዶች የምትገላለጡ እህቶች
ዋ! አላህ ከረገማቸው ሴቶች መካከል ተቀንዳቢዎችንና የሚገላለጡ ሴቶችን ነው ተጠንቀቁ

በተጨማሪም የሴቶች የውበት ሳሎን የምትሰሩ እህቶች ከኔ በበለጠ እናንተ በደምብ ነው ምታውቁት ገንዘብ ለማግኘት ብቻ ሲባል ምን ያክል ሸሪአን ያልጠበቁ አላህን የሚያስከፉ ነገሮች በነዚህ ቤቶች እንደሚሰሩ ታውቃላችሁ።  በነዚህ የሴቶች ውበት ሳሎን የምትሰሩ እህቶቼ አደራችሁን ይቅርባችሁ እንጂ ሃራም ነገር አትብሉ አላህን ለምኑት ሃላል የሆነ ስራ ይሰጣችኋል።

ሌላው ፊታችሁንና ሰውነታችሁን ወይም ኒቃብ ለብሳችሁ  አላህን የሚያስቆጣ ስራ የምትሰሩ እህቶቸ ሆይ ተጠንቀቁ አላህ ያያችኋል ስንት ሴቶች ናቸው ማንነታቸውን ሸፍነው በየ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሃራም ነገሮችን የሚሰሩ ውድ እህቴ በሶሻል ሚዲያ ላይ ለወንደሞችሽ ፊትና ከመሆን ተቆጠቢ አይ አልሰማም የምትይ ከሆነ አላህን እያስቆጣሽ ስለሆነ  ምን አልባት መጨረሻሽ ሊበላሽብሽ ይችላል።

ውድ እህቴ የዋህ አትሁኚ ሶሻል ሚዲያ ላይ ማንነታቸውን ደብቀው የሰው አውሬ የሆኑ ወንዶች አሉ ምንም ሌላ አላማና ግብ የሌላቸው ዋናው አላማቸው ሴቶችን ብቻ ለስሜታቸው መጠቀም የሚፈልጉ ወጣቶች አሉ ተጠንቀቁ ከነዚህ ወጣቶች እጅ ላይ እንዳትወድቁ
ውድ እህቴ ይህ ምክሬ ከልቤ ወንድማዊ ነው በደምብ ተጠቀሙበት አላህን ፍሩ በአላህ ይሁንብኝ አላህ(ሰብሃነ ወተዓላ)ይሄን ሁሉ ጤንነት ሰጦሽ እሱን የምታስቂጪው ከሆነ በደቂቃ ውስጥ ወደ ሞት አልጋ ላይ እንድትተኝ ያደርግሻል የአላህ ቅጣት ከባድ ነው። ወደ አላህ ተመለሺ ከመሞትሽ በፊት

ሴቷ ሒጃቧን በአግባቡ ከለበሰች ይህም የሚያስተላልፈው የራሱ መልዕክት አለው፡፡ ይኸውም «እኔ ላንተ የተከለከልኩ ነኝ የሚል ይሆናል፡፡
አዎ! ሴቶች ሒጃባቸውን በአግባቡ ከለበሱ ጨዋ እንደሆኑ ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ በባለጌዎችም አይደፈሩም፡፡ በመሠረቱ ሒጃብ ማለት አማኝ ሴቶች ለአስገዳጅ ነገሮች ከቤቶቻቸው ሲወጡ ሰውነታቸውን የሚሸፍኑባቸው ልብሶች ናቸው፡፡ 

በተቃራኒውም ተቀባብታ ከንፈሯን ሊፒስቲክ አጥግባ፣ ጡቶቿን አሹላ፣ ደረቷ ከፍታ፣ ዓይኖቿን ተኳኩላ፣ ፀጉሯን እያሳየሽ፣እጆቿንና እግሮቿን ገላልጣ ሱሪ ለብሳ፣ ሰውነቷን አጣብቃ፣ አጭር ጉርድ ለብሳ ከቤት የምትወጣ ሴት አለባበሷ የሚያስተላልፈው መልዕክት ሰውነቴ ለናንተ የስሜት መውጫ ለዚና የቀረበ ነው እኔን ለማግኜት ብዙ ልፋት አይጠይቅም ቅረቡኝና አላህን እንመፅ የሚል መልዕክት ነው ሚያስተላልፈው ምክንያቱም አላህን አትብቃ ብትይዝና ወንዶችን ለመፈተን ባታስብ እንደዚህ አላህን አምፃ ከቤት ባልወጣች ነበር። እና ዋናው አላማቸው ይሄ ነው ወንዶችን ለማጥመድ የታሰበ ነው  በዚህ ምንገድ ያላችሁ እህቶች አላህን ፍሩ የአላህን ቅጣት ፈርታችሁ ወደ አላህ ተመለሱ

አላህ ስታምጭው ዝም የሚልሽ ታጋሽ ስለሆነና እድል እየሰጠሽ ነው እንጂ እንዳመፅሽው አንቺን መቅጣት ይችላል ግን ይታገሳል እና ውድ እህቴ ታጋሽነቱ አያዘናጋሽ ሞት ስለማይቀር ሁሌ ያን እድል ላታገኝው ትችያለሽ።

በመጨረሻም እናንተ እራሳችሁን ንፁህ አድርጋችሁ አላህ ያዘዛችሁን እየተገበራችሁ ራሳችሁን ቁጥብ አድርጋችሁ የአላህን ውድ ሃገር የምትጠባበቁ አብሽሩ  ፈተናው ቢበዛባችሁም መጨረሻችሁ ግን በምንም የማይገመት ትልቅ ወደሆነው ጀነት ነው! ኢንሻ አላህ።

ወንጀል ላይ የምትገኙ እህቶቸ ወደ አላህ ተመለሱ ወላሂ አላህ ወደሱ ተመላሾችን ይቀበላል እንዲሁም ወንጀላችሁን በመልካም አጅር ይቀይርላችኋል ታዲያ ምን ትጠብቃላችሁ።

በዱዓችሁ አትርሱኝ

ወሰለላሁ አላ ነብይና ሙሃመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ አጅመዒን

መልዕክቱን ለአላህ ብላችሁ ሼር አድርጉት
የአንድ ሰው ወደ አላህ የመመለስ ሰበብ መሆን ትልቅ ነገር ነው ወደ አላህ ለተመለሱትም ለፅናታቸው ሰበብ ይሆናቸዋል በአላህ ፍቃድ።

@sineislam
@sineislam

1 week, 2 days ago

🔞አሳዛኝ ታሪክ ነው።

ሴትየዋ ልትወልድ ኦፕራሲዮን ክፍል አስገቧት ና ቆንጅዬ ወንድ ልጅም ተገላገለች። ልክ ልጇን እንደተገላገለች እሷ ግን አረፈች።ባልየው በጣም አዘነ በራሱ ህፃኑን ተንከበክቦ ማሳደግ ስለማይችልም ህፃኑን
ለአክስቱ አስረከቦ ለ7 ወራት መራራ የሀዘን ግዚያትን ካሳለፈ በኋላ ሌላ ምስት አገባ። ከአዲሷ ሚስቱም አሏህ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ልጅለሶሰጠው።

ከ3 አመታት በፊት ለአክስቱ ሰጥቶ የነበረውንም የመጀመሪያ ልጁን ከራሱ ጋ ሊያኖረው አመጣው። ያን ግዜ የአዲሷ ምስቱ ሁኔታ ተቀየረ።ይሄን 4 አመት ማይሞላው ጨቅላ ህፃን ትበድለው ጀመር። ያለ ርህራሄ በተደጋጋሚ ያለጥፋቱ ትቀጣዋለች።

ጭንቀቷ ሁሉ ለራሷ ልጆች እንጂ  ደንታም
የላትም።ምግብም ከልጆችዋ ለይታው ለብቻው ነበር ምትሰጠው። የሆነ ቀን እች ሴት ቤተሰቦችዋን እራሷ ቤት እራት ግብዣ ትጣራቸዋለች።

የተለያዩ የምግብ አይነቶች ተዘጋጅተውም ነበር እናም ይሄ እድሜው 4 ማይሞላው ጨቅላ (የሙት ልጅ) ከነዚህ ምግቦች ሊቀምስ እጁን ሲዘረጋ በጣም ትጮህበትና እያመናጨቀችው ከቤት ይዛው ትወጣለች።

ወደ በረንዳ አውጥታው እንግዳ እስኪወጣ ድረስ ከበረንዳ ንቅንቅ እንዳይል ታስጠነቅቀውና ቁራሽ ዳቦ በጁ አስይዛ እዛው
በረንዳ አስቀመጠችው።

ሌሊቱ በጣም ይበርድ ነበር አይደለም ለህፃን ለአዋቂ ከባድ ነበር።ብርዱም በጣም በረታበት ቤት ገብቶ እንዳይተኛ የ አባቱ ሚስት አስጠንቅቃዋለች። ህፃኑም በገዛ ቤቱ ባዳ ሆኖ የሰጠችውን ቁራሽ ዳቦ እየበላ እዛው ተጣጥፎ እንቅልፍ ወሰደው።

ሰዐቱም ረፈደ እንግዳውም ወጣ ሴትዮዋም በረንዳ ያለውንልጅ ረስታው ልጆችዋን ይዛ መኝታ ክፍሏ ገባች። ሰዓቱ ረፍዷል ባል ከስራ አርፍዶ ገባ።

እራት ላቅርብልህ ስትለው ውጭ እንደበላ ነግሯት ልጁ የት እንዳለ ሲጠይቃት "መኝታ ክፍሉ ተኝቷል" አለችው በዛ ብርድ በረንዳ እንደጣለችው ረስታ.. ሰውየውም ተኛ።
ወዲያው የቀድሞ ሚስቱ በህልሙ መጣችበት እና.... "ልጅህን ድረስለት" አለችው።

ሰውየውም ከእንቅልፉ ደንግጦ ተነሳና ልጁ የት ነው ብሎ ሚስቱን ሲጠይቃት..
"አልጋው ላይ ተኝቷል አልኩህ እኮ" አለችው።
ሰውየውም ድጋሚ ተኛ።

ሟች ሚስቱ ድጋሚ በህልሙ መጣች።
"ልጅህን ድረስለት" አለችው። ሰውየው ከመጀመሪያው በጣም ደንግጦ ከእንቅልፉ ነቃ።

"ልጄ የት ነው ያለው?" ብሎ ድጋሚ ጠየቃት ሴትየዋም "ምንድነው ዝም ብለህክፍሉ ምትጨናነቀው ልጁ ተኝቷል አንተም በቃ ዝም ብለህ ተኛ" ትለዋለች።

ሰውየውም ለሶስተኛ ግዜ ተመልሶ ተኛ።እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረገው በህልሙ የቀድሞ ሚስቱ ከመጀመሪያው ለየት ባለ ሁኔታ ፊቷን ቀይራ መጣችና..."በቃ ተወው ልጁ እኔ ጋ መጥቷል" ስትለው በድጋሚ ሰውየው ከእንቅልፉ ነቃ።

ልጁ የሚያድርበትም ክፍል በፍጥነት ሲሄድ ልጁ የለም። በድንጋጤ ልጁን ይፈልገው ጀመር... ሁሉም ክፍል ፈልጎ አጣው ድንገት የበረንዳውን በር ሲከፍት... ልጁ በረንዳ ላይ ነው ከብርዱ ብዛት ሰውነቱ ደርቋል።

ጭንቅላቱን በሁለት እግሮቹ መሀል እስገብቶ.... ሴትየዋ ከሰጠችው ቁራሽ ዳቦ ግማሿን በልቶ ግማሹ አጠገቡ ወድቋል።

አባቱ ሲያንቀሳቅሰው ምንም የለም ቀና ሲያረገው ልጁ ግን እችን አለም ተሰናብቷል።ያለ እናት እቅፍ ያደገው ልጅ የእናቱ እቅፍ ናፍቆት ከናፈቃት እናቱም ተገናኝቷል...

# ኢና_ሊላሂ_ወኢና_ኢለይሂ_ራጂዑን

በራሳቹ ልጅ ለይ እንዲደርስ ማትፈልጉትን በሰው ልጅ ለይ እንዲደርስ አትፍቀዱ።

@sineislam
@sineislam

1 week, 3 days ago

"ከእለታት አንዲት ቀን ትመጣለች ያህቺ ቀን ደግሞ ዱኒያን ምንሰናበትባት ወደ እውነተኛው ሀገራችን ምንሸጋገርባት ቀን ነች"! (አዎ እንሞታለን)!

እንዴት በውሸት ሀገር ተታለን እውነተኛው ሀገራችንን ችላ እንላለን ግን??

እስከመቼ በገፍላ ሂጃብ ታጥረን እንኖራለን?
  አላህ ሆይ እዝነትህን እንከጀላለን፣ቅጣትህንም እንፈራለን እንደኛ ስራ ሳይሆን እንዳአንተ እዝነት ያማረ መመለስን ወደ አንተ መልሰን ከአንተ ሚያርቁ ነገሮችን አርቅልን አንተን ለማመፅ ደካሞች አድርገን ትክክለኛ የሆነ ፍርሃትን ምንፈራህ አድርገን

@sineislam
@sineislam

1 week, 4 days ago

ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ?
🌹🌹🌹  💎💎   🌹🌹🌹  

💚 በእናቱ ሆድ ውስጥ እያለ ወላጅ አባቱን በሞት ተነጠቀ።

💛 የስድስት ዓመት ህፃን እያለ ወላጅ እናቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ?

❤️ የስምንት ዓመት ህፃን እያለ በፍቅር ተንከባክበው ያሳደጉት አያቱን አይቀሬ የሆነው ሞት ወሰዳቸው።

💚 እንደ አይን ብሌናቸው የሚሳሱለት አጎቱ እና በማራኪ ስብዕናው ተረታ የትዳር አጋሩ ለመሆን የበቃቸው ውድ ባለቤቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ከአይኑ ተሰወሩ። ለህይወቱ ወሳኝ የነበሩትን ምሰሶዎች ሞት ነጠቀው። ያ ፈታኝ ጊዜ «የሀዘን ዓመት» የሚል ስያሜ ተሰጠው። 

ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ??

💛 በምድር ላይ ከሁለት ዓመታት ዕድሜ በላይ ያልቆዩ ሁለት ህጻናት ወንድ ልጆቹን በማለዳ ሞት ቀጠፋቸው። በህፃናቱ ፈገግታ ደምቆ የነበረው ቤት የሀዘን ጥላ አጠላበት።

❤️ ከእርሱ ህልፈት በኋላ በስድስተኛው ወር በሞት ከተከተለችው ተናፋቂ ልጁ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ልጆቹ በህይወት እያለ ወደ መጪው ዓለም ተጓዙ።

ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ?

💚 የአባቱ ጥሪት የነበሩት አጎቱ ተገደሉ። መገደል ብቻም ሳይሆን የሰው ልጅ ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ጭራቃዊ ተግባር በአካላቸው ላይ ተፈፀመ። አንዲት እንስት አስክሬኑን በሰንጢ አስቀድዳ ጉበቱን በላችው። የዚህ ሰው ሀዘን ከሚገመተው በላይ በረታ።

💛 ጧኢፍ ነዋሪዎቿን በነቂስ አውጥታ የስድብ እና የድንጋይ ናዳ እንዲወርድበት ፈቀደች። ምድር ከሰውነቱ የሚፈሰውን ደም መጠጠች። ታሪክ ክስተቱን በደማቅ ገጹ አስፍሮ ለትውልድ አስተላለፈ።

ጧኢፍ መስክሪ ለዚያ አርበኛ
ለሰላሙ አባት ለዓለም ሁነኛ
ነዋሪዎችሽ የሰሩት ግፍ
በሙሐመድ ላይ ባንቺው ደጃፍ
መላ አካሉን አሰቃዩት
ሰላም ባመጣ በደም ሸኙት
ያሆደ ባሻ ይቅር አላቸው
ሊጠፉ ደርሰው ደረሰላቸው

ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ??

❤️ በአንድ ታላቅ ዘመቻ የፈት ጥርሱ ተሸረፈ። ብርሃናማ ፊቱ በደም ተለወሰ። 

💚 ግንባሩን ከመሬት አዋዶ ከፈጣሪው ጋር በለሆሳስ ሲያወራ የመካ ቂሎች በትከሻዎቹ መሃል የግመል አንጀት እና ደም ሲያፈሱበት ግንባሩን ከመሬት ለአፍታ አላነሳም ነበር።

ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ?

💛 በመተት እና ድግምት ሲያሰቃኙት፣ በመርዝ የተለወሰ ምግብ ሲሱጠት፣ ከሚናፍቅው የትውልድ ቀዬ ሲባረር «ይቅር ባይነት» የዘውትር ስንቁ ነበር ።

❤️ ይህን ሁሉ ስቃይ በተሸከመ አካልና መንፈሱ ታግዞ እግሮቹ አስከሚያብጡ ድረስ ሌሊቱን ሙሉ በመቆም አመስጋኝ ባሪያ ለመሆን ከአምላኩ ጋር ያወጋል። 

እናት ለልጇ በትምህርቱ ዓለም ብቻ የከፈለችውን መስዋዕትነት ብንፈትሽ አንድ ነገር ይከስትልናል። ለአብራኳ ክፋይ ከልጅነት እስከ ወጣትነት የዕድሜ ዘመኑ የዋለችው ውለታ መለኪያ የለውም። ከማዋዕለ-ህፃናት እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ይዘልቅ ዘንድ በትንሹ 23 ዓመታትን የፈጀ ጥረት ታደርጋለች። የእናት እያንዳንዱ የህይወት ምዕራፍ በአደገኛ ምጥ የተሞላ ነው። አንተን ከወለደችበት ምጥ ባሻገር ሌላ ስፍር ቁጥር የለሽ የህይወት ምጥ አለ።

ይህን ከግንዛቤ ካስገባችሁ 

ውስን በሆኑ 23 ዓመታት ውስጥ ብቻ የሰውን ልጅ ከፍጡራን ባርነት አላቆ አላህን ወደማምለክ ነፃነት ያሻጋገረ ፣ ከጠባብ ዓለማዊ ህይወት አውጥቶ ወደ ሰፊው የመንፈስ ዓለም ያመጠቀ ፣ ከምድራዊ እምነቶችና ስርዓቶች ጭቆና አላቆ ለኢስላም ፍትህ ያበቃ ፈርጡ የሰው ልጅ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم) ውለታ ምን ያህል የከበደ መሆኑን ትገነዘባለህ። 

ልቦቻችን ውሃ እንዳጣ የዓረቢያ ምድረ በዳ ስንጥቅ በዝቶባቸዋልና ፈለግህን በመከተል በፍቅርህ ይረሰርሱ ዘንድ አላህ ያግዘን  !!!

@sineislam
@sineislam

2 weeks, 2 days ago

እግዚአብሄር :– እኔ ሰው አይደለሁም።( ሆሴዕ 11:9 )

ኢየሱስ :– እኔ ሰው ነኝ።(ዮሐንስ ወንጌል 8:40 )

( ትንቢተ ሆሴዕ 11:9 ) እኔ እግዚአብሔር አምላክ ነኝ
እንጂ #ሰው_አይደለሁምና

ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሰው ነኝ ይላል

(የዮሐንስ ወንጌል 8:40 ) ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር
የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን #ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ::

ነገር ግን ነገር ግን........
ኢየሱስ ሰው ነኝ አምላክ አይደለሁም እያለ እየተማፀናቹ እናንተ ግን አይ  ኢየሱስ አምላክ ነህ፣ ጌታ ነህ፣ ፈጣሪ ነህ ወዘተ..... ብላችሁ የምታመልኩት ከሆነ ይህን መልዕክት በአንደበቱና በግልፅ  አስቀምጦላቹሃል፣

የማቴዎስ ወንጌል 7 ፣ 21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ #ጌታ_ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥#የሚለኝ_ሁሉ_መንግሥተ_ሰማያት_የሚገባ_አይደለም

22 በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።

23 የዚያን ጊዜም። #ከቶ_አላወቅኋችሁም#እናንተ_ዓመፀኞች፥  #ከእኔ_ራቁ_ብዬ_እመሰክርባቸዋለሁ

ስለዚህ ኢየሱስን ምትወዱት ከሆነ ቃሉንና ምክሩን ስሙ! ከፊቴ ጥፉ አላውቃችሁም እላቹሃለው እያላቹ ነው።

በወንጌል ካላፈሩ እስኪ ሼር አድርጉት
ይህ 100% ከመፅሀፍ ቅዱስ ከ (ወንጌል) ስለወጣ ሁሉም #ክርስቲያን  #ሼር ያድርገው።

📱 “እየሱስ ክርስቶስ እጅግ የተከበረ የፈጣሪ መልእክተኛ”
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
💥1•
“የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የኣብ ነው እንጂ የኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ ወንጌል 14:24)

የማን ነው ኣለ?
••••• የላከኝ የኣብ√

በዚህ ጥቅስ መሰረት ወልድ( እየሱስ) የኣብ መልእክተኛ ነው።

💥 2•
“እኔ ከራሴ ኣንዳች ላደርግ ኣይቻለኝም እንደሰማሁ እፈርዳሎ ፍርዴም ቅን ነው የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን ኣልሻምና”( የዬሐንስ ወንጌል 5:30)

የማን ፈቃድ ኣለ?
••••• የላከኝን√
ማነው የላከው?

እየሱስ ኣምላክ ከሆነ, ኣምላክን የሚልክ ደግሞ ማነው?
ኣምላክ ይልካል ወይስ ይላካል?

💥 3•
“ቃሌን የሚሰማ የላከኝም የሚያምን የዘላለም ሂወት ኣለው”( የዬሐንስ ወንጌል 5:24)

ማንን የሚያምን ኣለ?
••••••• የላከኝን√
ማነው የላከው?

💥 4•
“ኢየሱስም ጮኸ እንዲህም ኣለ በኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ ወንጌል 12:44)

በኢየሱስ ማመን በማን ማመን ነው?
•••••• በላከው√
ማነው የላከው?

💥 5•
“እኔ ከራሴ ኣልተናገርሁምና ነገር ግን የላከኝ ኣብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ”( የዬሐንስ ወንጌል 12:49)

እዚህ ላይ ደግሞ ” የላከኝ ኣብ” በማለት የኣብ መልእክተኛ መሆኑን በግልፅ ተናግርዋል።

💥6•
“የላከኝ እውነተኛ ነው”( የዬሐንስ ወንጌል 8:26)

ኢየሱስን የላከ እውነተኛው ማነው?

💥 7•
“የላከኝም ኣብ ሰለኔ ይመሰክራል”( የዬሐንስ ወንጌል 8:18)

ማን ኣለ?
••••• የላከኝ ኣብ√

💥8•
“ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም ኣላቸው ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ 7:16)

ትምህርቱ ከማን ነው?•••••ከላከው√
ማነው የላከው?

💥 9•
“እኔም በራሴ ኣልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው”( የዬሐንስ ወንጌል 7:28)

ኢየሱስን የላከ የማይታወቅ እውነተኛው ማነው?

💥 10•
“እኔንም የጣለ የላከኝም ይጥላል”( ሉቃስ ወንጌል 10:16)

የላከኝን? ማነው የላከው?

💥11•
“ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር ኣልተላክሁም ኣለ”( ማቴዎስ 15:34)

ወደ እስራኤል መልእክተኛ ኣድርጎ የላከው ማነው?

💥12•
“ኣንተም እንደላክኸኝ ኣመኑ”( የዬሐንስ ወንጌል 17:8)

ማነው የላከው?

💥13•
“ይህ የማደርገው ስራ ኣብ እንደላከኝ ስለኔ ይመሰክራልና”( የዬሐንስ ወንጌል 5:36)

ኣብ እንደላከኝ በማለት መልእክተኛ መሆኑን በግልፅ ይናገራል።

💥14•
“የላከኝ ኣብም እርሱ ስለኔ መስክሮዋል”( የዬሐንስ ወንጌል 5:37)

ምን ያደረገኝ ኣብ?
•••••••• የላከኝ√

💥15•
“እኔ ከእግዚኣብሄር ወጥቼ መጥቻለሁና እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ ኣልመጣሁም”( የዬሐንስ ወንጌል 8:42)

ከእግዚኣብሄር የተላከ መልእክተኛ መሆኑን ይነግረናል።

💥16•
“ባሪያ ከጌታው ኣይበልጥም መልእክተኛም ከላከው ኣይበልጥም”
( የዬሐንስ ወንጌል 13:16)
መልእክተኛው ማነው? ላኪውስ ማነው?

💥17•
“ኣብ እንደላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኃለሁኝ”( የዬሐንስ ወንጌል 20:21)

ኣብ እንደላከኝ በማለት የኣብ መልእክተኛ እንደሆነ በግልፅ ነግሮናል።

@sineislam
@sineislam

2 weeks, 3 days ago

‹ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላህ›
.
🔰🔰በልጁ የውሃ ሽታ ሆኖ መቅረት የተጨነቀው አባት ዐውፍ ኢብኑ ማሊክ
የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ. ዘንድ ሄደና

‹አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ልጄ ማሊክ ካንቱ ጋር በአላህ መንገድ ለዘመቻ ወጥቶ ነበር፡፡ እስካሁን ግን አልተመለሰም፤ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ይንገሩኝ፡፡›

እርሣቸውም ‹ዐውፍ ሆይ! አንተ እና ባለቤትህ ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ የሚለውን ቃል ማለትን አብዙ፡፡› አሉት፡፡ ዐውፍ ወደሚስቱ
ተመለሰ፡፡ ‹ ይህን ያህል ቆይተህ ከአላህ መልዕክተኛ ዘንድምን ይዘህ ይሆን የመጣኸው?› አለችው፡፡

‹ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ› ማለትን እንድናበዛ አዘዙኝ፡፡› አላት፡፡ ‹የአላህ መልዕክተኛ በርግጥም እውነት ተናገሩ› አለች፡፡ ቁጭ ብለው አላህን አወሱ፡፡ ‹ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ እያሉ ዋሉ፡፡ ቀኑ መሸ፡፡ ምሽቱም ገፋ፡፡

በዉድቅቱ ላይ ባልታሰበ ጊዜ በራቸው ተንኳኳ፡፡ ዐውፍ ሊከፍት ተነሳ፡፡ ልጁ ማሊክ ነበር፡፡ በርካታ በጎችን ነድቶ መጥቶ በር ላይ ቆሟል፡፡

አባቱ ጠየቀው፡፡ ‹ምንድነው ይህ የማየው?› አለው፡፡ ልጁም መለሰለት፡፡
‹ጠላቶች ማርከውኝ ወስደው በብረት ሰንሰለት ቀፍድደው አሠሩኝ፡፡

አመሻሽ ላይ ለማምለጥ ብሞክርም እግሬና እጄ የታሰረበትን ብረት መፍታት በጣም ከባድ ሆኖ ስላገኘሁት አልቻልኩም፡፡ ድንገት የሆነ ጊዜ ላይ ቀስ በቀስ ሲላላና ሲላቀቅ አስተዋልኩኝ፡፡

እኔም እግርና እጄን አላቀቅኩኝ፡፡ ሰዎቹ በቦታው ስላልነበሩ ያገኘሁትን በግና ፍየል ሁሉ ነድቼ መጣሁ፡፡› አለው፡፡

ዐውፍ ጠየቀው፡፡ ‹በኛና በጠላት አገር መካከል ያለው መንገድ እሩቅ ነው፡፡ ይህን ሁሉ መንገድ በአንድ ምሸት እንዴት ልትዘልቀው ቻልክ፡፡› ልጅም መለሰ ‹ከሰንሠለቱ ከተፈታሁበት ጊዜ ጀምሮ መላዕክት በክንፎቻቸው እንደተሸከሙኝ ይሠማኝ ነበር፡፡ › አለው፡፡

ዐውፍ የሆነውን ሁሉ ሊነግራቸው ብሎ ወደ አላህ መልዕክተኛ ተመልሶ ሄደ፡፡ ገና ሳይነግራቸው እንዲህ አሉት ‹ ዐውፍ ሆይ አብሽር አላህ ባንተ ጉዳይ
ﻭﻣﻦ ﻳﺘﻖ ﺍﻟﻠﻪ ﻳﺠﻌﻞ ﻟﻪ ﻣﺨﺮﺟﺎ ﻭﻳﺮﺯﻗﻪ ﻣﻦ ﺣﻴﺚ ﻻ ﻳﺤﺘﺴﺐ ﻭﻣﻦ ﻳﺘﻮﻛﻞ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻬﻮ
ﺣﺴﺒﻪ ...
‹ አላህንም የሚፈራ ሰው ለርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡ ካላሰበው በኩልም ሲሳይን ይለግሰዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚመካ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ ...› የሚል የቁርኣን አንቀጽ አውርዷልና፡፡ አሉት፡፡

‹ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላህ › ማለት ‹ብልሃትም ሆነ ጥንካሬ ከአላህ ዉጭ የለም፡፡› ማለት ነው፡፡ ከርሱ ዉጭ ምንም ነን፡፡

እና የላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ›ን ዋጋ እና ጥልቅ ትርጉም በትክክል እንወቅ፡፡

👉 በአስፈላጊ ቦታዎችም ላይ እንጠቀምባት፡፡
እስቲ ደጋግመን እንበላት፡፡ እሷ ጭንቀትን አስወጋጅ፣ የጀነት ዉስጥ ድልብ ሀብት ናትና፡፡

@sineislam
@sineislam

2 weeks, 3 days ago

ክብር ለሴቶች
.
1⃣. ባል በሚስቱ ላይ ከወሰለተ ቅጣቱ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ መወገር ነው፡፡

2⃣. 2ኛ ሚስት አግብቶ እኩል ካላስተዳደር የትንሳኤ ቀን ወደ ጎን ተጣሞ ይቀሰቀሳል፡፡

3⃣.ጥሎሽ ይህን ያህል እሠጣታለሁ ብሎ ቃል ገብቶ ካልሠጠ እሱ ሌባ ነው፡፡

4⃣. የፈታት አንደሆነ ከሠጣት ነገር ዉስጥ አንዳችም ነገር መውሰድ የለበትም፡፡ አሳፋሪ ነው አትውሰዱ ይላል ቁርኣን፡፡

5⃣. የዉርስ መብቷን የማይሠጣት ከሆነ የአላህን ድንበር ተላለፈ፡፡ የአላህን ድንበር የሚተላለፍ ራሱን ምንኛ በደለ!፡፡

6⃣ ሴትን ልጅ በመምታት ይሁን በሌላ ነገር ያዋረዳትና ዝቅ ያደረጋት እሱ የተዋረደ ነው፡፡

7⃣. ከአራትወር በላይ ጥሏት የጠፋ እንደሆነ የመለያየት መብት አላት፡፡

8⃣. እንደ እናቱ ሊያያት አይገባም፤ ጀርባውን መስጠትና ፍራሹን መለየትም የለበትም፡፡

9⃣. ‹አልቀርብሽም አንቺ ለኔ እንደ እናቴ ነሽ› ካላት በኋላ ቃሉን ማጠፍ ከሳበ ለቅጣቱ ስልሳ ቀናትን መፆም ይኖርበታል፡፡

🔟. የጠላት እንደሆነም ይታገስ፡፡ በጠሉት ነገር ዉስጥ ብዙ መልካም ነገር ሊኖር ይችላልና ይላል ቁርአን ፡፡

1⃣1⃣. አንደኛውን ባህሪዋን ቢጠላ ሌላውን ይውደድላት፡፡ ሰው ሆኖ ሙሉ የለምና፡፡

1⃣2⃣ የፈታት እንደሆነም መልካምነቷን አይርሳ፡፡ ትዝታ አያረጅም፡፡ ምንም እንኳ የሆነ ጊዜ ጥሩ ትንፋሽ ተለዋውጠዋልና፡፡

1⃣3⃣. በፍቺ ከተለያዩ ልጆቿን አይከልክላት፡፡ ቀለባቸውንም በትክክል ይስጣት ፡፡

1⃣4⃣. ሴት ልጅ በሀብት ንብረቷ ሙሉ ባለመብት ናት፡፡ መፀወተች፣ ነገደችበት መብቷ ነው፡፡ በሷ ገንዘብ ባሏ አያገባውም፡፡

1⃣5⃣ ድንበር ያለፈባት ሰው በተመሳሳይ መልኩ መቀጣት ይኖርበታል፡፡

1⃣6⃣. ባሏን የምትታዘዘው በመልካም ነገር ያዘዛት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ፈጣሪን በማመፅ ፍጡርን መታዘዝ የለም፡፡

1⃣7⃣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የበኑ ቀይኑቃዕ ጎሣዎች ላይ የዘመቱት በሴት ልጅ ክብር ምክንያት ነው፡፡

1⃣8⃣. ከሷ መከላከል የመስዋእትነት ደረጃ አለው፡፡

1⃣9⃣. ኸሊፋ አል-ሙዕተሲም ዐሙሪያ ድረስ ጦራቸውን ያዘመቱት ስለሷ መነካት እልህ ብለህ ነው፡፡ (ይህን ታሪክ ፈልጋችሁ አንብቡ፡፡)

2⃣0⃣. በዉሸት በዝሙት የወነጀላት የሰማኒያ ጅራፍ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡

2⃣1⃣. እሷን ማስተማር ግዴታ ነው፡፡ በመልካም ሁኔታ ማሳድግ የጀነት መግቢያ መንገድ ነው፡፡

2⃣2⃣ ከእናቶች እግር ሥር አትነሱ፡፡ ጀነት በእግራቸው ሥር ነውና፡፡

2⃣3⃣. እናት ከአባት በሦስት ደረጃዎች የበለጠች ናት፡፡

አል-ዐሪፊ እንደፃፉት… ራሳችሁ በድላችሁ፣ መብቶቻቸውን ሰርቃችሁ እስልምና ሴቶችን ይበድላል አትበሉ።💞💞💞

@sineislam
@sineislam

3 weeks, 2 days ago

🥀የሰብር ውጤት ሁሌም ቆንጆ ነው
አላህ እንድትጠብቅ የምያደርግህ ከሆነ
ምናልባት ከምትጠብቀው በላይ ልሰጥህ
ይፈልግ ይሆናል::

@sineislam

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 2 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 5 days, 7 hours ago