Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Minber TV

Description
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!

ይከታተሉ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ!

#ሚንበር_ቲቪን ለማግኘት

📡 በኢትዮሳት ይከታተሉ:– 👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 30000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 3 weeks, 6 days ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 weeks ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 day, 13 hours ago

2 days, 14 hours ago
ኤንዶኔዢያ በርካታ ሙስሊም ዜጎች ካሏቸው የአለም …

ኤንዶኔዢያ በርካታ ሙስሊም ዜጎች ካሏቸው የአለም ሐገራት መሓል ናት ። በሀይማኖታዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ አንቱ የሚሰኙ ጎበዞችም አፍርታለች ። ዛሬ በምናወሳው ስብዕና በኩል በቤተሰብ የተወራረሰውን አንቱታም ተርከናል ።

ዛሬ ምሽት ከ02፡00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#ክብር_ይወራረሳል
#እነሆ_ኸበር

ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 22 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 22 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

2 days, 15 hours ago

ወደ እስልምና ስትመጣ የምትወደው እየሱስን አጣኸው?

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/7ovpHi1J2SU 🔗

#እየሱስ #ዒሳ #ሂዳያ
#የኔ_መንገድ

ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 22 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 22 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

3 days, 13 hours ago

ፊሊፒንስ የሐላል ቱሪዝም ገበያውን ልትቀላቀል መሆኑን አስታወቀች

ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 21 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 21 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

የደቡብ ምሥራቅ እስያዋ ሀገር ፊሊፒንስ፣ በሀገሯ በሚገኝ ትልቁ የባህር ዳርቻ ውስጥ የሐላል ቱሪዝም አማራጮችን ለማቅረብ እየሠራች እንደምትገኝ አስታወቀች፡፡ ሀገሪቱ የሐላል ቱሪዝም አማራጮችን ለማስጀመር ዕቅድ የያዘችው በትልቁ የባህር ዳርቻዋ ስር በሚገኘው ቦራኬይ ሪዞርት ውስጥ መሆኑን ይፋ አድርጋለች፡፡

ፈሊፒንስ የሐላል ቱሪዝም የምታስጀምርበት ቦራኬይ ሪዞርት የሚገኝት የባህር ዳርቻ ሥመ ገናና ከሆኑ የዓለማችን የቱሪዝም መዳረሻዎች ውስጥ አንደኛው ነው፡፡

25 በመቶ የቱሪዝም ገቢዋን ባህር ዳርቻዎቿን ከሚጎበኙ ቱሪስቶች የምታገኘው ፈሊፒንስ፣ በቀጣይ ሙስሊም ጎብኚዎችን በይበልጥ ለመሳብ እየተንቀሳቀሰች መሆኑንም ገልጻለች፡፡ የሀገሪቱ ቱሪዝም መስሪያ ቤት ባለሥልጣን የሆኑት ክሪስቲና ፈራስኮም ይህንኑ የፊሊፒንስን ዕቅድ ለመገናኛ ብዙኃን አረጋግጠዋል፡፡ ፍራስኮ በቦራኬይ ሪዞርት በቅርቡ የሐላል ቱሪዝም አማራጮችን ለማስጀመር በመስሪያ ቤታቸው እና በሪዞርቱ መካከል ውይይት እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡

የሐላል ቱሪዝም ለማስጀመር እየሠራች መሆኑን ያሳወቀችው ፊሊፒንስ፣ ካላት 12 ሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ የሙስሊም ዜጎች ቁጥር 10 በመቶ ነው፡፡ ሀገሪቱ እ.አ.አ የ2024 አዲስ ዓመት ከገባ ወዲህ ባሉት አምስት ወራት ውስጥ ብቻ 2 ሚሊዮን ጎብኚዎችን አስተናግዳለች፡፡ ፊሊፒንስ ከጎብኚዎቿ መካከል ከሙስሊም ሀገራት የሚነሱት 10 በመቶ ጭማሪ ማሳየታቸውን ገልጻለች፡፡

የሐላል ቱሪዝም አቅርቦት በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ የሚገኘው ሐላል ኢንዱስትሪ አንደኛው ዘርፍ ነው፡፡ ሰባት ዘርፎችን የሚያቅፈው ይህ ኢንዱስትሪ፤ በሥሩ ምግብን ጨምሮ እስላማዊ ፋይናንስ፣ ሐላል ምግብ፣ ሐላል ፋሽን፣ ሐላል ሚዲያ እና መዝናኛ፣ የመድኃኒት እና ሐላል መዋቢያዎችን ያካትታል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

1 week, 2 days ago

ልዩ “ኸበር” - የሳዑዲ ዐረቢያ የሐጅ ሽር ጉድ በመጨረሻው ሰዓት

ከመላው ዓለም ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ወደ ሀገሯ ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁትን ከሁለት ሚሊዮን የሚልቁ ምዕመናንን መቀበል የጀመረችው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ የአላህ እንግዶች ከቤት የወጡበትን ውጥን እንዲሞሉ ሽር ጉድ ማለቷን ቀጥላለች፡፡ ሳዑዲ እንግዶችን መቀበል የጀመረችው ግንቦት 1/2016 ነበር፡፡ እስካሁን ከተቀበለቻቸው ውስጥ ከእኛዋ ኢትዮጵያ የተነሱ ምዕመናን ይገኙበታል፡፡ 12 ሺሕ ኢትዮጵያውያን እስከ ሰኔ 2/2016 ድረስ ሳዑዲ ዐረቢያ ተጠናቀው ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በርግጥ ሳዑዲ ዐረቢያ ሑጃጆችን መቀበል ጀምራም ቢሆን ለዑምራ እና ሌላ ጉዳይ (ለምሣሌ ለጉብኝት) በተለይ መካ ከተማ የሚጓዙ የሀገሯን ሰዎችም ሆነ እንግዶችን ስታስገባ ቆይታለች፡፡ ሆኖም ከዛሬ ሐሙስ ግንቦት 15/2016 አንስቶ ለሐጅ ካልሆነ በስተቀር የከተማዋን በር መቆለፏን እወቁት ብላለች፡፡ በዚህም ወደ ቅድስቲቱ መካ ከተማ የሚያስገቡ የፍተሻ ጣቢያዎች፣ ከሑጃጅ ውጪ ሌላ ሰው ወደ ውስጥ እንዳይዘልቅ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ሳዑዲ ዐረቢያ ከሚቀጥለው ሳምንት ግንቦት 25/2016 ጀምሮ ደግሞ፣ በድንገት ያለ ሐጅ ቪዛ ወደ መካ ከተማ ዘልቆ ያገኘችውን ግለሰብ እንዲሁ አትለቀውም፤ 10 ሺሕ ሪያል መቀጮ እንደምታስከፍለው ቀድማ አሳውቃለች፡፡ ቅጣቱ በዚህ ብቻ ላይቆም ይችላል፤ ከተደጋገመ ከምድሯ ያስባርራል፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ ወደ ሐጅ ቀናት ስትቃረብ፣ ከሐጅ ቪዛ ውጪ የያዙ ምዕመናንን ወደ መካ እንዳይገቡ ከማገድ ጎን ለጎን ሐጅ መድረሱን ጠቋሚ የሆነውን የካዕባን ልብስ ከፍ አድርጋለች፡፡ ሳዑዲ በየዓመቱ የሐጅ ቀናት ሲቃረቡ ይህን የምታደርገው በጥንቃቄ ነው፡፡ ዘንድሮም ኪስዋውን ከመሬት ከፍ ለማድረግ 36 ባለሞያዎችን ከአስር “ክሬን” ጋር መድባለች፡፡ ባለሞያዎቹ ልብሱን ከፍ አድርገው በአራቱም ማዕዘን በነጭ የጥጥ ጨርቅ እንዲሸፈን (ኢህራም) አድርገውታል፡፡

ኢህራም የተደረገው ኪስዋ በየዓመቱ የሚቀየር ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚጀምረው በዙልሒጃ ወር 9ኛው ቀን ይቀየር የነበረ ቢሆንም በቅርብ ጊዜያት በአዲሱ ዓመት መግቢያ ሙሐረም ወር የመጀመሪያው ምሽት እንዲቀየር ተወስኗል፡፡

ኪስዋ የዓለማችን ውዱ ልብስ ነው፡፡ የልብሱ ክብደት 850 ኪሎ ግራም ሲመዝን፣ ወጪው ደግሞ 6.5 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል፡፡ ኪስዋ ሲዘጋጅ ቢያንስ 200 ባለሞያዎች ይሳተፋሉ፡፡ የኪስዋ 670 ኪሎ የሚመዝነው ጥቁር ሀር ነው፡፡ በዚህ ሀር ላይ ለሚጻፉ የቁርኣን አንቀፆች 120 ኪሎ 21 ካራት ወርቅ እንዲሁም 100 ኪሎ ግራም ብር ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

በድረ ገጽ ተጨማሪ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=8121

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

1 week, 2 days ago
ልዩ “ኸበር” - የሳዑዲ ዐረቢያ የሐጅ …

ልዩ “ኸበር” - የሳዑዲ ዐረቢያ የሐጅ ሽር ጉድ በመጨረሻው ሰዓት

1 week, 2 days ago

የሀገሪቱን “የአብሮነት እሴት” የማስገንዘብ አላማ አለው የተባለ ጉባዔ በኮምቦልቻ ከተማ ሊካሄድ ነው

ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 15 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 15 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

በአማራ ክልል ውስጥ የምትገኘው ኮምቦልቻ ከተማ፣ የሀገሪቱን የአብሮነት እሴት የማስገንዘብ አላማ አለው የተባለ ጉባዔ የፊታችን እሑድ ታስተናግዳለች ተባለ፡፡ “አንድነታችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ጉባዔ ላይ ከመላው ሀገሪቱ የሚጓዙ እንግዶች እንደሚሳተፉበት ተገልጧል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሣን ጨምሮ የጉባዔው አዘጋጅ ኮሚቴ ትናንት ረቡዕ ግንቦት 14/2016 በሰጡት መግለጫ ይህንኑ ገልጸዋል፡፡ ሸይኽ ሐሚድ ሙሣ ሀገር አቀፍ ጉባዔው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት “የበላይ ጠባቂነት” እንደሚካሄድ የገለጹ ሲሆን፣ አዘጋጁ ደግሞ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

አዘጋጆቹ በመግለጫቸው ላይ ጉባዔው ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች “በአንድነት ተሰባስበው የሚኖሩባትና ታላቅ የአብሮነት እሴትን ይዛ የኖረች ሀገር የመሆኗን ፋይዳ” ለአዲሱ ትውልድ የማስገንዘብ ዓላማ አለው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በጂማ ከተማ የተካሄደው ጉባዔ ተከታይ መሆኑ በተነገረለት ጉባዔ ላይ፣ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የሚጓዙ ዓሊሞች እና ዱዓቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ለሁለት ቀናት ይቆያል የተባለው ሀገር አቀፍ የሰላም፣ የአብሮነትና የወንድማማችነት ጉባዔ ላይ ከእንግዶች በተጨማሪ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ አዲስ አበባ እና ድሬደዋን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንቶች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በመግለጫ ላይ ተገልጧል፡፡

የዚህን ዜና ዝርዝር በድረ ገጽ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://minbertv.com/?p=8112

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

2 weeks, 3 days ago

በኢትዮጵያ “የቤተሰብ ቀን” ለሁለተኛ ጊዜ ተከብሮ ዋለ

ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 7 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 7 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

በኢትዮጵያ የቤተሰብ ቀን በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ተከብሮ ዋለ። ቀኑ ለሁለተኛ ጊዜ ሲከበር “መተሳሰብ እንደ ቤተሰብ፣ ለሀገርና ለማኅበረሰብ” በሚል መሪ ቃል ነው።

በዓሉ በተከበረበት መድረክ ላይ የቤተሰብን ሁለገብ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ ለማሳደግ፣ ዕውቅና ለመስጠት እና ሁሉም ቤተሰብ፤ ለቤተሰብ አባላት ምሥጋና እና ክብር የሚሰጥበትን ዕድል ለመፍጠር በማለም መሆኑ ተገልጿል።

ቤተሰብ ትውልድን የመተካት፣ የልጆችን ሰብዕና የመቅረፅ፣ የሀገር ኢኮኖሚን የማሳደግ፣ ለቤተሰብ አባላት ዋስትና የመሆን ትልቅ ሚና ስላለው፣ ቤተሰብ ደኅንነቱ ሊጠበቅ እና ተገቢውን ክብር እንዲሁም ጥበቃ ሊያገኝ እንደሚገባም ክብረ በዓሉ በተሰናዳበት መድረክ አፅንኦት ተሰጥቶበታል።

በዛሬው መድረክ ላይ የተናገሩት በሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ሕፃናት ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ ዓለሚቱ ዑመድ፣  ቤተሰብ የራሱን እና የአባላቱን ደኅንነት በመጠበቅ ለጤናማ ሀገር እና ማኅበረሰብ ምሥረታ መተኪያ የሌለው መሆኑን አብራርተዋል።

ሚኒስትር ዲኤታዋ በመልካም ሥነ ልቡና፣ በአካላዊ ጤንነት እና በኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይረጋገጣል ላሉት የቤተሰብ አባላት ደኅንነት መጠበቅ፣ ቤተሰብ እንደ ተቋም ቀዳሚ ድርሻ እንደሚወስድ አስታውሰዋል።

የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የዛሬውን በዓል ባከበረበት ወቅት ሁሉንም ቤተሰብ አባላት ተጠቃሚ ያደርጋል ያለውን ለአንድ ዓመት የሚቆይ ዕቅድ ይፋ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የተከበረው የቤተሰብ ቀን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ ተከብሮ አልፏል።

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

2 weeks, 3 days ago
Minber TV
2 weeks, 3 days ago

ልዩ “ኸበር” - 76 ዓመታት ያስቆጠረው መቅሰፍት

ጣሪቅ አቡ አዙም ከሚገኝበት ጋዛ ለዓለም ይድረስ ብሎ ዛሬ ማለዳ ባሠራጨው ዘገባ፣ እስራኤል በፍልስጤም ንጹሐን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት በአየር እና በመሬት መቀጠሏን ይገልጻል፡፡ ጋዜጠኛው የአልጀዚራ ባልደረባ ነው፡፡ ጣሪቅ በተለይ ባለፉት ሰባት ወራት እስራኤል በንጹሐን ላይ ቦምብ ስታዘንብ እግር በእግር እየተከተለ ሲዘግብ ቆይቷል፡፡ ሕፃናት እና እናቶችን ጨምሮ ንጹሐን ሲረግፉ ዐይቷል፡፡ ውሎ አዳራቸውን፣ ሕልማቸውንም ጭምር የሚያጋሩት ወዳጆቹም በሞት ሲወሰዱ በአቅመ ቢስነት ሸኝቷል፡፡ የእስራኤል ቦምብ የሞያ ባልንጀሮቹንም ነጥቆታል፡፡

ጣሪቅ አቡ አዙም የዕለት ተዕለት ውሏቸውን የሚዘግብላቸው ፍልስጤማዊያን ሰቆቃ የጀመረው እ.አ.አ ከ76 ዓመት በፊት በዛሬው ቀን ሜይ 15/1948 ነበር፡፡ በእስራኤል መሬታቸው በወረራ ተይዞ ጥቃት የሚፈራረቅባቸው ፍልስጤማዊያን፣ ይህን ቀን መቅሰፍት (“ነክበህ”) ብለው ይጠሩታል፡፡ በየዓመቱም ይታሰባል፡፡

በዚህ ወቅት አይሁዳዊያን በፍልስጤማዊያን ላይ ጦርነት ከፍተው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ቀያቸውን ጥለው እንዲሸሹ አድርገዋል፡፡ የቀጠለው ጥቃት የፍልስጤማዊያንን የሰባት ዐስርት ዓመታት ኑሮ ተቆጣጥሮት ሕይወታቸውን በሰቆቃ ሞልቶታል፡፡

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ፍልስጤማዊያን በመሬታቸው ላይ ለመንቀሳቀስ ጭምር ፍቃድ ሰጪው ሌላ ሆኗል፡፡ እስራኤል በተለይ ከ1995 ወዲህ በወረራ የያዘችውን ዌስት ባንክን በሦስት ሸንሽና በ700 ሺሕ ሠፋሪዎች ሞልታ ፍልስጤማዊያን በአንድ አካባቢ እንዲወሰኑ አድርጋለች፡፡ በዌስት ባንክ እስራኤል የራሷን ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ስታሠፍር ከዐስር ሺሕ በላይ የፍልስጤማዊያን ግንባታዎችን አውድማ ነው፡፡

መሬታቸው ባዕድ የተወረረባቸው ፍልስጤማዊያን፣ ወደ ሥራ ሊሄዱ ሲሉ የይለፍ ፍቃድ ለማግኘት በማለዳ መሰለፋቸውም የዕለት ውሏቸው አካል ከሆነ ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ እስራኤል የፍልስጤማዊያኑ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ጥላ ሥማቸው በሥራ ፈትነት ከዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ ሆኗል፡፡

እስራኤል የፍልስጤማዊያኑን ሰቆቃ የምታበረታው የንግድ እንቅስቃሴንም በማፈን ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ፍልስጤም ከአጎራባች ዐረብ ሀገራት ጋር የንግድ ግንኙነቷ ተቆርጧል፡፡ የወጪ እና ገቢ ንግዷም በእስራኤል በኩል እንዲያልፍ ጉልበተኛ ተሹሞበታል፡፡

እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ የጣለችው ገደብ ወደ ቴክኖሎጂም የሚሻገር ነው፡፡ እስራኤል ለራሷ 5ጂ ኔትወርክ ስትጠቀም፣ ፍልስጤማዊኑ በ3ጂ ኔትወርክ እንዲወሰኑ ተደርገዋል፡፡ እስራኤል በገደብ የምትለቀውን ኔትወርክ ፍልስጤማዊያኑን ለመሰለል ጥቅም ላይ የምታውለው ነው፡፡ ፍልስጤማዊን የኔትወርክ ብቻ ሳይሆን የውሃ እና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ላይ ገደብ ተጥሎባቸዋል፡፡

ለ76 ዓመታት በወረራ በያዘችው መሬት ላይ የተሾመችው እስራኤል፣ ከጥቅምት 2024 ወዲህ በንጹሐን ላይ የምትሰነዝረውን ሰብዓዊነት የጎደለው ጥቃት በመጠን አስፋፍታ ቢያንስ 35 ሺሕ ሰዎችን ገድላለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺሕ የሚሆኑት ሕፃናት ናቸው፡፡ ፍልስጤማዊያኑ መቅሰፍት ሲሉ የሚጠሩትን የዛሬውን ቀን ሲያስቡ፣ በዓመታት ሰቆቃ ውስጥ ከአጠገባቸው የተለዩዋቸውን እያስታወሱ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
(ይህ ጥንቅር በዋነኝነት የተወሰደው ከአልጀዚራ ነው፡፡)

2 months, 2 weeks ago
إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ …

إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُونَ 
እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡
(አል-ፉሲለት፤ 30)

#መወሰኛይቱ
ኑን የቁርኣን መድረክ 10
እሁድ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ል
በሚሊኒየም አዳራሸ

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 3 weeks, 6 days ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 weeks ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 day, 13 hours ago