Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

የመንፈሳዊ መጻሕፍት ንባብ ቤተሰብ

Description
#የኅብርቱዋናዓላማ

፩.መንፈሳዊ መጻሕፍትን በዓላማ፤በእቅድ እንድናነባቸው፤እንድናስነብባቸው በሕይወታችን ትርጉም እንዲኖራቸው ማድረግ።

፪.ከቤተሰቦቻችን፤ዘመዶቻችን፤ወዳጆቻችን ስላነበብናቸው መጻሕፍት እነሱም ስላነበቡት መጻሕፍት ውይይት የማድረግ ልምድን ማዳበር።
፫.አንባቢ ትውልድ መፍጠር። ለአስተያየትዎ @orthokiha ይጻፉ።
https://t.me/BetMetsahfte
Cross @selam1981
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 3 weeks, 6 days ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 weeks ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 day, 13 hours ago

1 week ago
**37 አልፋ 73**[**@dawitfikr**](https://t.me/dawitfikr) **ይዘዙ።**[**https://t.me/BetMetsahfte**](https://t.me/BetMetsahfte)

37 አልፋ 73@dawitfikr ይዘዙ።https://t.me/BetMetsahfte

1 week, 1 day ago

#Update
የደብረ ሊባኖሱ ከትናንት እስከ ዛሬ 600ሺ ተሰብስበዋል።ዛሬ ፩ሚልዮን እንሞላት ይሆን?
በአማን ነጸረ Tadele Sisay Zekaryas Kiros በርቱልን!

CBE
1000280193667
D/L ABUNE T/HAYMANOT https://t.me/BetMetsahfte

1 week, 2 days ago

አቡነ ተክለሃይማኖት በበረከቱ እቤታችሁ ይግቡ ክፉ አይንካችሁ።

Challengeቹን ተሳክተዋል። ቃል የተገቡም አሉ ከእቅድ በላይ ሁነናል።

ደኅናደሩልን🙏 https://t.me/BetMetsahfte

2 months, 1 week ago
ዛሬ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር በስካይ ላይት …

ዛሬ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር በስካይ ላይት ሆቴል ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕሴቶቻችንን በህዝባችን ሕይወት ላይ እናስርጽ በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የመንፈሳዊ መጻሕፍት ዓውደ ርዕይ /ባዛር ኤግዚቢሽን/እኛንም ያሉንን መንፈሳዊ ምርቶቻችንን ይዘን በድካይ ላይት ሆቴል አባይ አዳራሽ ተገኝተናል እየመጣችሁ እንድትጎበኙን እናሳስባለን።
#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_0912044752_0925421700_ይደውሉ
https://t.me/BetMetsahfte

2 months, 1 week ago
**ኑ መጥታችሁ ጎብኙን!

**ኑ መጥታችሁ ጎብኙን!

እቁብተኞች እንዲሁም አባሎቻችን ይዘንላችሁ እንድንመጣ ምትፈልጉትን መጻሕፍት ቀድማችሁ @dawitfikr እዙዙ!#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_0912044752_0925421700_ይደውሉ!**https://t.me/BetMetsahfte

2 months, 1 week ago
[#ከአዲሱ](?q=%23%E1%8A%A8%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B1) የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ትርጉም …

#ከአዲሱ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ትርጉም በጨረፍታ እናስቃኛችሁ።

እውነትም አፈወርቅ ጥዑም ዘይጥዕም እም መዓር ወሦከር።

#10_የነፍስ_ምግብ_ጉርሻዎች

#የነፍስ_ምግብ አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

አዲሱ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #የነፍስ_ምግብ የተሰኘው መጽሐፍ በገበያ ላይ መዋሉን ምክንያት በማድረግ 10 የነፍስ ምግብ ጉርሻዎችን ከነፍስ ምግብ መጽሐፍ ጋብዘናል፦

#1
"ቃላቶችህ ምንም ያህል ትክክል ቢሆኑም በቁጣ ስትናገር ሁሉንም ነገር ታበላሻለህ።"

#2
"ብል ልብስን እንደሚበላው ሰውንም ቅናት ይበዋል።"

#3
"እግዚአብሔር የሚጠይቀው ጥቂት፣ የሚሰጠው ብዙ ነው"

#4
"እያንዳንዱ ሰው የህይወቱ ሠዓሊ እና ቀራፂ ነው።"

#5
"ባለጠጋ ብዙ ያለው ሳይሆን ብዙ የሚሰጥ ነው።"

#6
“ምሕረት አምላክን ይመስላል ሰይጣንንም ያሳዝነዋል።"

#7
" ኃጢአት ስትሠራ እንጂ ንስሐ ስትገባ አትፈር"

#8
"ለምን በትንንሽ ነገሮች መደሰትን አትማርም - በጣም ብዙ ናቸው።"

#9
"ጸሎት የጭንቀት ሁሉ መሸሸጊያ፣የደስታ መሠረት፣ ከሐዘን መከለያ ናት። "

#10
"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ላይ ባለው ነዳይ ውስጥ ማግኘት ካልቻላችሁ፣ በቤተመቅደስ ውስጥ አታገኙትም።"

እውነትም #የነፍስ_ምግብ የሚያሰኘው ይህ ድንቅ መጽሐፍ ከእንጀራ በፊት አንድ አንድ ጉርሻ ጎረስ ጎረስ እያረጋችሁ እንድትመገቡ ጋብዘናችኋል።

#የመጽሐፉ ርእስ #የነፍስ ምግብ
የጀርባው ዋጋ=450
አርጋኖናዊ ቅናሽ እንደተጠበቀ ነው ይጎብኙን።

ለበለጠ @dawitfikr ይዘዙን። https://t.me/BetMetsahfte
#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_0912044752_0925421700_ይደውሉ

4 months, 1 week ago

ሰኞ - ጥር 13 2016 ዓ.ም

ዘፍጥረት 1-5

በዛሬው እለት ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 እስከ 5 ድረስ እናነባለን። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ እግዚአብሔር በስድስት ቀናት ውስጥ ፍጥረታትን እንዴት እንደፈጠረ፥ በስድስተኛው ቀን አዳምና ሔዋንን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን እንዳረፈ እናነባለን። በገነት ውስጥ አዳም እና ሔዋን እግዚአብሔርን እንዳልታዘዙ፥ በዚህም ምክንያት ከገነት እንደተባረሩም ተጽፎ ይገኛል። በተጨማሪም በልጆቻቸው በአቤል እና በቃየን መካከል ችግር ተፈጥሮ፥ ቃየን ወንድሙ አቤልን እንደገደለው የምናነበውም በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ነው። በምዕራፍ አምስት ላይ ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ያለውን የዘር ግንድ የምናገኝ ሲሆን፥ ይህም ቀጣይ ለምናነባቸው ታሪኮች ያዘጋጀናል። 

የክለሳ ጥያቄዎች

1) እግዚአብሔር በመጀመሪያው ቀን ምን ፈጠረ?

2) እግዚአብሔር የሰው ልጅን የፈጠረው በስንተኛው ቀን ነው?

3) በዘፍጥረት 2 መሠረት፥ አዳም የተፈጠረው እንዴት ነው?

4) እግዚአብሔር በገነት ውስጥ ለአዳም እና ሔዋን የሰጠው ኃላፊነት ምን ነበር?

5) አዳም እና ሔዋን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ የበሉት ምን ነበር?

6) የአዳም እና ሔዋን አለመታዘዝ ምን ውጤት አስከተለ?

7) በዘፍጥረት 4 ላይ የተጠቀሱት የአዳም እና የሔዋን ልጆች እነማን ናቸው?

8) በአቤልና ቃየን መካከል የነበረው ግጭት በምን ተነሳ? ፍጻሜውስ ምን ሆነ?

9) በዘፍጥረት 5 ያለው የዘር ግንድ ዓላማው ምንድር ነው?

10) በዘፍጥረት 5 መጨረሻ ላይ የተጠቀሰው ሰው ማን ነው?

ለውይይት እና ክትትል እንዲመች ከዚህ በኃላ ንባቡን ለመቀጠል የሚከተለውን join አድርጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+3kpzSPDfiVMzYzQ0 https://t.me/BetMetsahfte

4 months, 1 week ago

**ሰላም! በየእለቱ የሚከተለውን ቅድመ ተከተል ይከተሉ፦

1 - ለማንበብ አመቺ ቦታ ተቀምጠው አሳብዎትን ይሰብስቡ።

2 - እግዚአብሔር የቃሉን ምስጢር እንዲገልጥልዎት አጭር ጸሎት ይጸልዩ። ከዚህ ሥር የሠፈረውን የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ጸሎት መጸለይ ይችላሉ፦

“ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።”

3 - በእለቱ ስለሚነበበው ክፍል የቀረበውን አጭር መግለጫ ያንብቡ።

4 - በእለቱ የሚነበበውን ክፍል በተመስጦ ሆነው ያንብቡ።

5 - ያነበቡትን በሚገባ እንደተገነዘቡት ለማረጋገጥ የቀረቡትን ጥያቄዎች ይሞክሩ።**

4 months, 1 week ago
  • የትውውቅ መርሐ ግብር + (ቻሌንጅ/ሞክረኛ)

ከውሃ የወጣ ዓሳ፥ ከአፈር የተነቀለ ተክል፥ ከአየር የተለየ ሰው ሙት መሆኑ እርግጥ ነው። ለክርስቲያን ደግሞ ሞቱ ከእግዚአብሔር መለየት ነው። አንድ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ያለው ግንኙነት ከተቋረጠ፥ በጸሎትም አምላኩን ማነጋገሩን ከተወ የሞቱ ዋዜማ ላይ መሆኑን እንረዳለን። የቫይታሚን እጥረት የሰውነት መቀንጨርን እንደሚያስከትል ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር ቃል ስንለይ መንፈሳዊ ሕይወታችን ይቀነጭራል። ይህ እንዳይሆን መጸለይ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በውስጣችን እንዲያድር ቅዱስ መጽሐፉን በርትተን በጸሎት መንፈስ ማንበብ ይኖርብናል።

ብዙ ጊዜ “ሰው ከእግዚአብሔር ቃል አልገናኝ አለ! ሰው የአምላኩን ቃል አያውቅም!” ወዘተ እየተባለ አስተያየት ሲሰጥ ይስተዋላል። በእርግጥ እውነት ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን ችግሩን እያገዘፉ ከመኖር፥ መፍትሔው ላይ ማተኮሩ ብልህነት ነው። ጨለማውን እያማረሩ መኖር ይቻላል፤ ወይም ደግሞ እንደ አቅማችን ሻማ መለኮስ። ምርጫው እንግዲህ የእኛው ነው።

ይህንን ታሳቢ በማድረግ አንድ ቻሌንጅ/ሞክረኛ አዘጋጅቻለሁ። ይህም ቻሌንጅ መጽሐፍ ቅዱስን ከኦሪት ዘፍጥረት አንስቶ እስከ ዮሐንስ ራእይ ድረስ በስድስት ወር ውስጥ አንብቦ ማጠናቀቅ ነው። በአጭሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚደረግ የትውውቅ መርሐ ግብር ብሎ ማሰብ ይቻላል። መጽሐፍ ቅዱስ ሁሌም አዲስ እንደመሆኑ፥ ሁሌም ትውውቅ ይፈልጋል። “አውቄዋለሁ። ጨርሼዋለሁ።” የሚል ቃል ለመጽሐፍ ቅዱስ አይሠራም። ቤተ-ክርስቲያንንም ለመረዳት ትልቁ ቁልፍ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ እሙን ነው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ እና ብንኖር፥ በዓመት ሁለት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ከጫፍ እስከ ጫፍ ማንበብ እንችላለን ማለት ነው። ንባቡን ሳያውቁ ምስጢሩን መጠየቅ የማይሆን ነውና፥ አስቀድመን ንባቡን ማወቅ ይገባል። ጥልቅ የሆነው የእውቀት ጉዞም የሚነሳው ማንበብ ከመጀመር ነው።

ክርስትና የኅብረት ጉዞ እንደመሆኑ መጠን፥ ይኽም ጉዞ የኅብረት ቢሆን ጥቅሙ ብዙ ነው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህ ጉዞ በነገው እለት ጥር 13 2016 ይጀምርና ሐምሌ 16 2016 ይጠናቀቃል። ይኽንን ጉዞ አብራችሁ ከእኔ ጋር ለመጓዝ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሁሉ፥ በኮሜንት ላይ አሳውቁኝ። የፌስቡክ ቻት ግሩፕ ከፍተን አብረን ጉዞውን እንጀምራለን።

ኑ፥ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አብረን እንጓዝ!!
#ለማንበብ_ፍቃደኛ_የሆናችሁ_ፍላጎታችሁ_በ❤️👏👍 ግለጹ።

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

6 months, 1 week ago

ስለ ኾነ የኾነ ጉደይ ነው እንዲሁም እኛም ወደዚህ ጊዜያዊ ሕይወት የገባነው ከዚያ በላይ ስለ ኾነ ጉዳይ ነው፤ ይኸውም ዘላለማዊ ሕይወት ነው። ወታደር ወደ ቤቱ መመለስን በደስታ እንደሚያስብ ኹሉ፤ ክርስቲያኖችም የሕይወታቸውን መጨረሻና ወደ አባታቸው ዓለም ወደ መንግሥተ ሰማያት መመለሳቸውን ሳያቋርጡ ያስባሉ።" ብሎ በምሳሌ ጥሩ አድርጎ በሕሊናችን ውስጥ የሕይወትን ዓላም በሥዕል መልክ ይቀርጽብናል።
(St. Nicholas of Serbia, Thoughts on Good and Evil)።

ሌላው የሕይወት ዓላማ ምስጋና ነው። ምስጋና ቅዱሳን መላእክትን የምንመስልበት፣ የእግዚአብሔርን ቸርነት የምናደንቅበት፣ ፍቅሩን እያሰብን የምንመሰጥበት የሕይወት ዓላማ ነው። ታላቁ ምስጋና በእያንዳንዳችን ገቢራዊ ሕይወት እግዚአብሔር እንዲታይ የምናደርግበት የየዕለት ሕይወት ያልተቋረጠ ምስጋና ነው። በሰማይ ላይ ፀሐይ እንደሚወጣ በእውነተኛ ክርስቲያን ሰውነትም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ ይወጣል። በብዙ አለማስተዋልና ተስፋ መቍረጥ ተቀጥቅጠው ሊወድቁ ያሉትንም እግዚአብሔር በእውነተኛ ምስጋናችን በኩል ኾኖ ወደ ራሱ ይጠራቸዋል። እውነተኛ የክርስትና ሕይወት ያልተቋረጠ የምስጋና ሕይወት ነው። ስለዚህ በዚህ ውስጥ ያለ ሰው በራሱ ሕይወት ተስፋ የመቍረጥ በሽታን አያኖርም። እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን ይክፈትልን ከክፉ ኹሉም ይጠብቀን አሜን። https://t.me/BetMetsahfte

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 3 weeks, 6 days ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 weeks ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 day, 13 hours ago