«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

Description
وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ
{{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}
      [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ]
በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!!
http://t.me/Abdurhman_oumer
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 2 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 2 months ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 1 month, 1 week ago

5 days, 18 hours ago

በዲን ላይ ቀጥ ማለት

🎙በሸይኽ ዓብዱል ሐሚድ حَفِظَهُ الله

🗓 ዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 18 ቀን 2016 E.C የወራቤ ዩኒቨርስቲ ሰለፍይ ጀመዓዎች ባዘጋጁት የ 𝙬𝙚𝙡𝙡 𝙜𝙤 ፕሮግራም ላይ የቀረበ ሙሐደራ!
https://t.me/Abdurhman_oumer/8298

5 days, 18 hours ago

ሙመይዓዎች ከየት እስከየት

🎙 በኡስታዝ ባህሩ ተካ حَفِظَهُ الله
🗓 ዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 18 ቀን 2016 E.C የወራቤ ዩኒቨርስቲ ሰለፍይ ጀመዓዎች ባዘጋጁት የ 𝙬𝙚𝙡𝙡 𝙜𝙤 ፕሮግራም ላይ የቀረበ ሙሐደራ!
https://t.me/Abdurhman_oumer/8297

6 days, 17 hours ago

وكذلك في عصرنا مثلا الشيخ عبد المحسن العباد دافع عن أبي الحسن المأربي فلم يلتفت العلماء إلى دفاعه واعتذروا له بأنه لم يعرف حاله كما عرفه الشيخ ربيع المدخلي الذي صنّف عددا من الكتب في الرد على أبي الحسن فوقف علماء السنة كالشيخ أحمد النجمي وزيد المدخلي وعبيد الجابري ومحمد بن هادي ومحمد بازمول ومشايخ اليمن وغيرهم مع الشيخ ربيع لأن معه الحجة والبرهان هذا هو الحق الذي يرضي الله عز وجل.
وأما المميعة فيستغلون مثل هذا الخلاف للدفاع عن أهل البدع ولا يهمهم معرفة صاحب الحق والوقوف معه كما كان عليه السلف ولهذا قلت مرارا (المميعة سرطان المنهج السلفي).
وأما اشتراط الإجماع في التبديع فمما أحدثه المميعة للدفاع عن أهل البدع فلا تجد ذلك في الكتب المؤلفة في الجرح والتعديل خلال أربعة عشر قرنا.
ومن أراد التوسع فليرجع إلى كتاب( الجامع لشبهات المميعة ودحضها) فقد بينت زيف شبهات المميعة بكلام علماء الجرح والتعديل السابقين واللاحقين.
والله الموفق.

2 months, 1 week ago

-      #የጎዳና_ኢፍጣር_!!

ረመዳን ማብቂያ፣ ሃያ"ዎቹ ሲደርስ፣
የጎዳና ኢፍጧር፣ የፍክክር ድግስ፣
የቢድዓ ሰዎች፣ አምጥተዋል አዲስ፣
ባልታዘዙት ነገር፣ ሱናን ለማደፍረስ፣
ጭቅጭቅ ለማስፋት፣ ግጭት ለመቀስቀስ፣
ከመከበር ይልቅ፣ ውጭ ወቶ ለመርከስ፣
ሱና እንዳያብቃቃ፣ ይሄን ዲን ለማፍረስ፣
ነግቶ ያዘልቃሉ፣ ፋሽን በመጠንሰስ!!
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
አህባሽና ሱፍይ፣ በመውሊድ ሲያምታቱ፣
ኢኽዋንና ጄሌው፣ ስልጣን ወንበር ሞቱ፣
ልታይ ልታይ ይላል፣ ወጥቶ በየ-አስፓልቱ፣
ሰልፍ ሰልፍ እያለ፣ ነበረ ጩኸቱ፣
ሌላ አጀንዳ አገኘ፣ በዛው በአይነቱ፣
ወጥቶ መታየት ነው፣ ሀደፉ ምኞቱ!!

- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ፋሽኑ ያብቃበት፣ ድራሹን ያጥፋልን፣
ከእምድር አስወገዶ፣ ጭራሽ ይገላግለን፣
ከስሜት ሰዎች ጋር፣ ሳያነታርከን፣
ዘንድሮ አይመጣብን፣ በጥሩ ያፁመን!!
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ሴት ወንዱን አውጥቶ፣ በአንድ ማስተያየት፣
በፎቶ ቀርፆ፣ ይባስ ማሰራጨት፣
ለካፊር መዝናኛ፣ ሴት ልጅን ማምቻቸት፣
ስንቱ ይጠቀሳል፣ የቢድዓ ውጤት፣
የጎዳና ኢፍጣር፣ ብዙ ጉድ አበት!!

- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ጃሂል አላዋቂ፣ ምን አለበት ይላል፣
የተራበው ሁሉ፣ ድሃው"ም ይበላል፣
ይሄን ምክንያት ይዞ፣ ሳያውቅ ያራግባል፣
የሱናን መሠረት፣ መች ለይቶ ያውቃል፣
መረጃው ምንዲን ነው፣ መች ይጠይቃል፣
የመጣውን ሁሉ፣ አምኖ ያካሂዳል!!
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
የዲን አስተምሮት፣ ምን ቢያንስም ቢገዝፍ፣
ነብዩ አላስቀሩም፣ አብራርተዋል በገፍ፣
የጎዳና ኢፍጣር፣ ይሄ አዲሱ ፍልስፍ፣
መልካም ቢሆን ኖሮ፣ በኢስላም ቢደገፍ፣
እነዚያ ሰሀቦች፣ የነበሩ ቅልጡፍ፣
ይቀድሙ ነበረ፣ ለመልካም መጣደፍ፣
ከነሱ ለመሆን፣ አብሮ ለመሰለፍ፣
የሰሩት ይሰራል፣ የለም የሚታለፍ፣
የተውት ይተዋል፣ ይህ ነው የሚያፀይፍ!!

- - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ሚስኪን እንደ ማብላት፣ በማዘጋጃው ብር፣
በየ ቤቱ ገብቶ፣ መርዳት ለሚቸገር፣
አስቤዛ ቢያሟሉ፣ ደብቀው በሚስጥር፣
እንደት ትርፋማ ነው፣ ለሚያስብ ለቀብር፣
አለበለዚያ ግን፣ ይህ የታይታ ነገር፣
ምንም አይፈይድም፣ የአንድ ቀን ግርግር፣
የጋጋታ ሥራ፣ የጎዳና ኢፍጣር!!

አብዱረህማን ዑመር
ረመዳን 12/ 1444 ሂጅራህ
የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
https://t.me/Abdurhman_oumer/4398
https://t.me/Abdurhman_oumer/4398

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

የዲን አስተምሮት፣ ምን ቢያንስም ቢገዝፍ፣ ነብዩ አላስቀሩም፣ አብራርተዋል በገፍ፣ የጎዳና ኢፍጣር፣ ይሄ አዲሱ ፍልስፍ፣ መልካም ቢሆን ኖሮ፣ በኢስላም ቢደገፍ፣ እነዚያ ሰሀቦች፣ የነበሩ ቅልጡፍ፣ ይቀድሙ ነበረ፣ ለመልካም መጣደፍ፣ ከነሱ ለመሆን አብሮ ለመሰለፍ፣ የሰሩት ይሰራል፣ የለም የሚታለፍ፣ የተውት ይተዋል፣ ይህ ነው የሚያፀይፍ!! ሙሉ ግጥሙን ለማንበብ ***👇*** https://t.me/Abdurhman\_oumer/4398

- [**#የጎዳና\_ኢፍጣር\_!!**](https://t.me/Abdurhman_oumer/4397)
2 months, 1 week ago
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር
2 months, 1 week ago

🚫 የአልከሶ ጉድ

➧ አልከሶ በስልጤ ዞን የሚገኝ አነስተኛ የቀበሌ ከተማ ሲሆን እንደ አብዛኛዎች የሀገራችን ክፍሎች ከአላህ ውጪ የሚመለክ በሕይወት የሌለ የሸይኽ ቀብር ያለበት ቦታ ነው። እዚ ቦታ ላይ የአልከሶ ሸይኽ (አልከስዬ) እና ሌሎች ወደ ስድስት አካባቢ የሚጠጉ ቀብሮች ይመለካሉ።

➽ እነዚህ ቀብሮች አብዛኞቹ በግንብ የተገነባ ቤት (ዶሪሕ) ያለባቸው ሲሆን የተወሰኑት በጭቃ የተሰሩ ናቸው። በተለይ የአልከስዬ ቀብርን የልጅ ልጅ ነው የሚባለው አቶ ነስሮ ከሪያድ መጥቶ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚጎርፉ ሰዎች የሚያመጡትን ስለትና ቤዛ የመሰብሰቡን ሀላፊነት ከተረከበ በኋላ በልዩ ሁኔታ ያስጌጠውና የቀብር አምላኪዎቹን ልብ በሚስብ ሁኔታ እንዳስዋበው ይነገራል

↪️ ይህን ቀብር ለማምለክ የሚመጡ ሰዎች ወደ ግቢው የሚገቡት በባዶ እግራቸው ሲሆን ቀብሩ አካባቢ ሲደርሱ አብዛኞቹ ፍፁም በሆነ የተዋረደ ስሜት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ተዋርደው ተናንሰው ያዩናል በሚል ስሜት ኮሽታ ሳያሰሚ ወደ ቀብሩ ይጠጋሉ። ከዛም ተበርክከው፣ ተደፍተውና ስጁድ ያደርጋሉ በዚህ ሁኔታ በሁለመናቸው ወድቀው ችግራቸውን ፍላጎታቸውን የደረሰባቸውን መከራና ጭንቅ ተናግረው እንዲፈርጁዋቸው ከጭንቅ እንዲያወጡዋቸው እንዲያሽሩዋቸው እንዲያከብሩዋቸውና ዘር እንዲሰጡዋቸው በእንባ እየታጠቡ ከለመኑ በኋላ ተነስተው ጠዋፍ ያደርጋሉ

➼ በአብዛኛው እንዲህ አይነቱ የኩፍር ተግባር የሚፈፀመው በመውሊድ ጊዜ ነው። የዚህ አይነቱ ሽርክና ኩፍር በአይነቱ የሚሰራበት አልከሶ በየአመቱ መውሊድ ሲደርስ ከየቦታው በሚጎርፉ ሰዎች ይጨናነቃል። ፖሊስና የፀጥታ ሰዎች ቢዚ ይሆናሉ።

➲ በመውሊዱ ጊዜ ከሚሰሩ የኢስላምን ገፅታ ከሚያጠለሹ ተግባራት ውስጥ አንዱ "ቹፒሳ" የሚባለው የአልከሶ መውሊድ ጭፈራ ነው። የዚህ አይነቱ ጭፈራ በተለያየ ግሩፕ የሚከናወን ሲሆን ዘፋኞቹ ገሪባ የሚባሉ ሙሪዶች ናቸው።

➜ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ራሱን ሴት አድርጎ ሻሽ አስሮ በሴቶች መካከል ሆኖ ነው ሴቶችን የሚያስጨፍረው ተራ ጭፈራ ቢሆን ይቀል ነበር እነዚያ ሴቶች ሁሉ ከአላህ ውጪ ላለ አካል እንዲሰግዱና ሩኩዕ እንዲያረጉ የሚደረግበት ነው። ከአጅ ነብይ ወንድ ጋር መጨፈራቸው እንዳይገርምህ ይህ በጣም ቀላሉ ነው ምናልባት በስሜት ሲቀልጡ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም

➝ በዚህ ቀን በዝሙት የሚወለደው ልጅ ወልይ ነው ሊባልና ከህፃንነቱ ጀምሮ ሊመለክ ይችላል። የዚህ አይነት ሽርክና ኩፍር ቢዳዓና ዘግናኝ ወንጀል የሚሰራበት አልከሶ ማህበረሰቡ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ሙስሊም ነው።

➔ ውስጥን የሚያደማውና የሚዘገንነው ይህን ከአላህ ውጭ የሚመለክና ዘግናኝ የአምልኮ ቦታ ያለበት አልከሶ ላይ ሸይኽ ነስሮና ኢማዱዲን የሚባሉ የዲን መሪ ተብዬዎች መኖራቸው ነው መኖራቸው ብቻ ሳይሆን በአልከሶ ከተማ በሚገኙ መስጂዶች ላይ ስለ አልከሶ ሽርክና ኩፍር በዝርዝር እንዳይነገር መከልከላቸውም ነው ኢማዱ ኡስታዝ ነው ነስሮ ሸይኽ ነው ኩቱቡ ሲታ ያስቀራል ይባላል

➛ የሚገርመው ኢማዱ የሚባለው በመውሊዱ ጊዜ የሚያደርገው ዳዕዋ ለመውሊድ የሚመጣው ሰው መኪና እንዳይገጨው ምን መደረግ እንዳለበት ነው።

➞ እነዚህ ሁለቱ የዲን መሪ የሚባሉት አካላት ማህበረሰቡን በቁጥጥራቸው አድርገው እነሱ ከሚሉት ነገር እንዳይወጣ አስተማማኝ ስራ ሰርተዋል። አይደለም ተራው ሰው አብዛኛውን የመንግስት አመራርን ጭምር በኔት ወርካቸው ውስጥ በማስገባት ሶስት የከተማ ሽማግሌዎች ብለው በሰየሙዋቸው የእነርሱን መመሪያ በሚያስፈፅሙ ሰዎች አማካይነት ነው ከተማዋ የምትመራው

➪ አላህ በየጊዜው እንዲህ አይነቱን ሽርክና ኩፍር የሚዋጉ እሱ ብቻ እንዲመለክ ሰዎች ፍጡርን ከማምለክ አላህን ወደ ማምለክ የሚጣሩ ይፈጥራልና አልከሶ ላይም ይህ የኩፍርና የሽርክ ተግባር ኢስላምን አይወክልም ብለው የተውሒድ ዳዕዋ ለማህበረሰቡ ለማድረስ የተነሱ ወንድሞች አሉ

➩ ይሁን እንጂ እነዚህን ወንድሞች በእንጭጩ ለማስቀረትና ሰዉ በቀብር አምላኪነቱ እንዲቀጥል ለማድረግ በእስር ከሀገር በማባረርና የወጣቶቹን ቤተሰቦች ከማህበራዊ ኑሮ በማስወጣት የማይሰሩት ነገር የለም ነገር ግን እነዚህ ወጣቶች ይህ ሁሉ ሳይበግራቸው ባገኙት አጋጣሚ የተውሒድን ብርሃን ጮራ ወደ ሰዎች እንዲደርስ በማድረጋቸው ብዙ ሰዎችን ከዚህ ሽርክ ለማውጣት ችለዋል

➵ እነዚህ ይህ ሽርክና ኩፍር አይወክለንም ኢስላምንም አይወክልም ያሉ ሙስሊሞች በዚህ ረመዳን አንድ የተተወ መስጂድ ጠርገውና አስተካክለው ፈርድ ሶላትና ተራዊሕ መስገድ ይጀምራሉ ብዙም ሳይቆዩ ከተማውን በኔት ወርክ በሚመሩት ሸይኽ ነስሮና ኢማዱ ዲን ትእዛዝ ሽማግሌዎችና የፖሊስ አባላት መስጂዱ እንዲዘጋና እንዲወጡ ይደረጋሉ እሺ ውጪ እንድንሰግድ ይፈቀድልን ሲሉ የፖሊስ አባላቱ ውጪ መስገድ ትችላላችሁ ይሏቸዋል። መስገድ ይጀምራሉ። ብዙም አልቆየም የኔት ወርኩ አካል የሆነ የተደራጀ የዱርዬ ቡድን እንደ ገጀራና ፌሮ የመሳሰሉ ድምፅ አልባ መሳሬያ በመያዝ ለቀው እንዲሄዱ ያደርጋል

➺ በዚህን ጊዜ በከተማው ውስጥ የዚህ አይነቱ ሽርክና ኩፍር ኢስላምን የነብዩን ዲን አይወክልም ብለው የጠሉ አንድ እናት መጋዘናቸውን ለወጣቶቹ ሰጥተው ቁርኣን እንዲቀራበት አድርገው ነበርና ለረመዳን እንዲሰግዱበት አስፈቅደዋቸው እዛ መስገድ ጀመሩ። ብዙም አልቆዩም የኔት ወርኩ አካል የሆነው የሽማግሌ ቡድን አሁንም አይቻልም ከበላይ እንደማይቻል ተነግሮናል በማለት አቁሙ ይላሉ። የበላይ የሚባሉት ኢማዱና ነስሮ ናቸው

➻ እነዚህ ሽርክና ኩፍር አንቀበልም የኛ እምነት አይደለም ያሉ ሙስሊሞች መብታቸው የሚጠይቁበት አጡ። በሚቀጥለው ቀን የዱርዬው ቡድን መጋዘኑን ሰብሮ በመግባት ለሶላት የተነጠፈውን ምንጣፍና የተካፈለበትን መጋረጃ እንዲሁም ቁርኣኖችን ሰብስቦ ይዞ በመሄድ ምንጣፍና መጋረጃውን ገበያ መሀል በማቃጠል ቁርኣኑን የት እንዳደረሰው አይታወቅም።

➛ ይህ ነገር ከተከሰተ በኋላ የከተማው የፀጥታ ሀላፊ የመስጂዶች ኮሚቴ ቦርድና እነዚህን ወንድሞች ሰብስቦ ካነጋገረ በኋላ በራሳቸው መድረሳም ሆነ መስጂድ ካላቸው መማርም ሆነ መስገድ ይችላሉ ብሎ የወሰነ ቢሆንም የዱርዬ ቡድኑ ለህግ የማይገዛ በመሆነ በተሰጣቸው መጋዘን መስገድ አልቻሉም። አቅም ያላቸው ወጣቶች ከከተማው አንድ ኪሎሜትር ወጣ ብሎ በያዙት ቦታ ላይ እየሰገዱ ሲሆን ሴቶችና አዛውንቶች በረመዳን ቁጭ ብለው ነው ያሉት።

➻ በጣም የሚገርመው ከሀገራችን የኢኽዋን መሪዎች አንዱ የሆነው ካሚል ሸምሱና ግበረአበሮቹ ከዚህ በፊት በዚህ መውሊድ ላይ ተገኝተው ነው ከኛ ምን ትፈልጋላችሁ ምን እናድርግ ያሉዋቸው።

➼ አሁን የድሮዎቹና አዲሶቹ ኢኽዋኖች ከሱፍይና አሕባሽ ጋር ሆነው የሚመሩት መጅሊስ የአልከሶ ሙስሊሞችን መብት ማስከበር አልቻልም። ይልቁንም አዲስ መጤ ሰለፍዮች ናቸው በሚል ሊያጠፉዋቸው ለሚሰሩት ሽፋን ይሰጣሉ።

➧ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያላችሁ የአልከሶ ተወላጅ የነብዩን ዲን ሶሐቦች ዋካ የከፈሉለትን ኢስላም የምትወዱ የሆናችሁ የእነዚህን ወንድሞች እንባ ጥረጉ። አለን በሉ መብታቸው እንዲጠበቅ ቁርኣንና ሐዲስ ሩሕ ኖሯቸው በስራ ላይ እንዲውሉ አድርጉ ኢማዱንና ነስሮን አትወክሉንም በሉዋቸው። የተውሒድ ባንዲራ በአልከሶ ምድር ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርጉ።

➔ በየቦታው ያላችሁ ሰለፍዮች አላህ አልከሶና የመሳሰሉ ቦታወች ላይ ሽርክን አርክሶ ተውሒድን አንገሶ እንዲያሳየን ዱዓእ እያደረጋችሁ ከወንድሞቻችን ጎን እንድትቆሙ አደራ እላለሁ።

https://t.me/bahruteka

4 months, 1 week ago

ለዛም ነው
👇
قال الإمام أحمد رحمه الله تعالى:
((قبور أهل السنة من أهل الكبائر روضة ، وقبور أهل البدعة من الزهاد حفرة ، فسّـاق أهل السنــة أوليـاء الله ، وزهــاد أهل البدع أعداء الله)).اهـ
📚 طبقات الحنابلة (1/184)
አላህ ይዘንላቸው ኢማም አህመድ  የሚከተለውን ብለዋል፡-
  {{የአህሉ ሱና መቃብሮች ከትላልቅ ወንጀሎች ባለቤቶች (ቢሆኑ እንኳ ከጀነት ጨፌ የሆኑ) ጨፌ  ናቸው፣ የቢድዓ ሰዎች መቃብሮች ደግሞ፤ ከዛሂዶች (ቢሆኑ እንኳ ከእሳት ጉድጓድ የሆኑ) ጉድጓዶች ናቸው። የሱና ሰዎች ሥነ ምግባር የጎደላቸው ቢሆኑኳ የአላህ ወዳጆች ናቸው። የቢድዓ ሰዎች ዛሂዶች ቢሆኑ እንኳ የአላህ ጠላቶች ናቸው))
📚 ጦበቃቱል ሀናቢላህ (1/184)

➻ወንጀልህ በዝቶ መልካም ሥራህ ካነሰ ሰለፎች (ደጋግ ቀደምቶች) የሚሉትን አድርግ
‏ﻗﺎﻝ اﻟﻔُﻀَﻴﻞ ﺑﻦ ﻋﻴﺎﺽ:
"ﺇﺫا ﻋﻠﻢ اﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ ﻣﻦ اﻟﺮﺟﻞ ﺃﻧﻪ ﻣُﺒﻐِﺾٌ ﻟﺼﺎﺣﺐ ‎ﺑﺪﻋﺔ ﻏﻔﺮ ﻟﻪ ﻭﺇﻥ ﻗﻞَّ ﻋﻤﻠُﻪ"
شرح السنة للبربهاري(1/138)

ታላቁ ዛሂድ (በጣም አላህን ፈሪ በመሆኑ የሚታወቀው) የቀደምት ዓሊም ፉዶይል ኢብኑ ዒያድ እንድህ ይላል
{{አንድ ሠው መልካም ሥራው እንኳ ትንሽ ብትሆንበት ነገር ግን የቢድዓ ባለቤትን የሚጠላ ከሆነ  ይችን ተግባሩን አላህ ስለሚያውቅለት ወንጀሉን ይምርለታል}}

➻ ደጋግ ቀደምቶች የፈለገ አላህን ፈሪ ቢመስል ሙብተዲዕ ከሆነ ፈጽሞ ቦታ አይሰጡትም።

قال الإمام البربهاري رحمه الله تعالى: وإذا رأيت الرجل مجتهدا في العبادة متقشفا محترقا بالعبادة صاحب هوى فلا تجالسه ولا تقعد معه ولا تسمع كلامه ‏ولا تمشي معه في طريق، فإني لا آمن أن تستحلي طريقته فتهلك معه"
[شرح السنة:١٢٤]
አላህ ይዘንላቸው ታላቁ የቀደምት ሊቅ ኢማሙ አል በርበሀሪ እንዲህ ይላሉ፦
{{በዒባዳው ላይ ታጋይና በጣም የናጠ፣ ለጋሽም ዛሂድም የሆነን (ግን) የሥሜት ተከታይ (የቢድዓ ሰው) ካየህ ከሱ ጋር አትቀማመጥ፣ ንግግሩን አትስማ፣ በመንገድም ከሱ ጋር አትሂድ፣ (ምክንያቱም) ያለበትን የጥመት መንገድ #አቅልለህ ታየውና ከሱ ጋር ትጠፋለህ ብየ እፈራልሃለሁ}} (ሸርሁ ሱና 123)

4 months, 1 week ago

መተናነስ ከዓሊሞች እንማር!

ወሳኝ ሙሃዶራ

ርእስ:- የእውቀትና የአዋቂዎች ደረጃ!!

🕌በቂልጦ ከተማ ጥቅምት 19/2015 የተደረገ

🎙 الشيخ حسين بن محمد بن عبد الله السلطي الإثيوبي

🎙በመተናነስ ጥግ የሚታወቁት ታላቁ ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ)

በአላህ ፈቃድ ተጨማሪ ጥቆማዎችን ለማግኘት
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6774

4 months, 1 week ago

https://t.me/HussinAssilty/29

Telegram

قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد

4 months, 2 weeks ago

አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ የተከበራችሁ ሰለፍዮች በዚህ ቻናል በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል የተባለው ወድ የሆነው የጉራጌው ፕሮግራም ላይ ድንገተኛ የግል ጉዳይ ያጋጠመኝ በመሆኑ ላልገኝ እችላለሁ!! ሆኖም ግን ከደረስኩ በተቻለኝ እሞክራለሁ!!

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 2 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 2 months ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 1 month, 1 week ago