"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

Description
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ አስተምሮ ያላቸውን መርሃግብሮች የሚቀርቡበት ቻናል ነው።

ከነዚህም መካከል

➯ዝክረ ቅዱሳን (የየቀኑን ስንክሳር)፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ መዝሙር፣ የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ PDF፣
ወቅታዊ የኦርቶዶክሳዊ መረጃዎች እና ወ.ዘ.ተ

@AndEmnet Channel
@AndEmnetZeeOrtodoxTewahdo Group
@AmantaanTokko Afaan Oromo
@Yhmeeb Contact 🙏
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 3 weeks, 6 days ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 weeks ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 day, 13 hours ago

5 days, 8 hours ago

#አባ_በትረ_ወንጌል (ስንክሳር)

➯በዚችም ቀን ከአባቶች መምህራን ዐሥራ ስድስተኛ የሆነ በደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት ሆኖ የተሾመ የከበረ አባት አባ በትረ ወንጌል አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ እንደ መላእክት ንጽሕናን የለበሰ ትሕትናን ቅንነትን የሚወድ ነበረ።

➯የምንኵስናንም ልብስ ከለበሰ በኋላ መልካም ገድልን ተጋደለ በክርስቶስ መንጋ ላይም ጠባቂ ሆኖ ተሾመ ከዚያም በኋላ በበጎ እርጅና አረፈ።

➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

#ስንክሳር ግንቦት 20 ቀን

5 days, 8 hours ago

#አባ_አሞንዮስ (ስንክሳር)

➯በዚህች ዕለት የሀገረ ቶና የከበረ አባ አሞንዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ጎልማሳ ሁኖ ሳለ አባ እንጦንዮስ ወደ ምንኩስና ሲጠራው ራእይን አየ። በነቃም ጊዜ ተነሥቶ ወዲያውኑ ወደ አባ ኤስድሮስ ሔደ ከእርሱም አስኬማን ለብሶ እያገለገለውም በእርሱ ዘንድ ኖረ።

➯ከዚህ በኋላም ወደ ደብረ ቶና ተመልሶ ለራሱ በዓትን ሠራ በታላቅ ገድልም ተጠምዶ በቀንም በሌሊትም ተጋደለ። ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ በሴት መነኲሲት አምሳል ወደርሱ መጣ የበዓቱን ደጃፍ በአንኳኳ ጊዜ ከፈተለትና ገባ ቅዱሱም ተነሥተን እንጸልይ አለው ያን ጊዜ ተንኰሉን ገለጠ መልኩም እንደ እሳት ላቦት ሆነ ቅዱሱንም እኔ ታላቅ ጦርነት አመጣብሃለሁ አለው።

➯ከዚህም በኋላ መልኳ ውብ ወደ ሆነ ወደ አንዲት ወጣት ሴት ሰይጣን ሒዶ አነሣሣት። ቅዱስ አሞንዮስን ከእርሷ ጋራ በኃጢአት ልትጥለው ቀጭን ልብሶችን ለብሳ ወደ ርሱ በምሽት ጊዜ ደረሰች።

➯እንዲህም እያለች ደጃፉን አንኳኳች እኔ መጻተኛ ሴት ነኝ መንገድንም ስቼ በምሽት ጊዜ ከዚህ ደረስኩ አራዊትም እንዳይበሉኝ በውጭ አትተውኝ እግዚአብሔርም ስለ እኔ ደም እንዳይመራመርህ።

➯በከፈተላትም ጊዜ የሰይጣን ማጥመጃው እንደ ሆነች የላካትም እርሱ እንደሆነ አወቀ በአምላካውያት መጻሕፍት ቃልም ገሠጻት ለኃጥአን ስለ ተዘጋጀ የሲኦል እሳትም አስገነዘባት ሁለተኛም ለጻድቃን ስለ ተዘጋጀ ፍጹም ተድላ ደስታ ነገራት።

➯ያን ጊዜም የሚላትን ታስተውለው ዘንድ እግዚአብሔር ልቧን ከፈተላት። መልካሙንም ልብስ ከላይዋ አውጥታ ጣለች ከእግሮቹ በታችም ሰገደች ነፍሷንም ያድን ዘንድ በማልቀስ ለመነችው። የጠጉር ልብስም አለበሳት ራስዋንም ተላጭታ በገድል ሁሉ በብዙ ትሩፋትም ተጠመደች በቀንም በሌሊትም ዐሥራ ሁለት ጊዜ የምትጸልይ ሁናለችና በየሁለትና በየሦስት ቀንም ትጾማለች።

➯ሰይጣንም በአፈረ ጊዜ በመነኲሴ ተመስሎ በየአንዳንዱ ገዳም ሁሉ በመግባት እያለቀሰና እያዘነ እንዲህ አላቸው በአባ አሞንዮስ ቤት ሴት አለችና እርሱ ከታላቅ ገድል በኋላ የአንዲትን ሴት ፍቅር ወዶአልና እርሷም በእርሱ ዘንድ በበዓቱ ውስጥ ትኖራለች እነሆ መነኰሳትን አሳፈራቸው አስኪማውንም አጐሳቈለ።

➯የመላእክት አምሳል የሆነ ጻድቁ አባ ዕብሎ ያን ጊዜ ተነሣ አባ ዮሴፍንና አባ ቦሂንም ከእሱ ጋራ ወሰዳቸው። ወደ ቅዱስ አሞንዮስ ገዳም ደብረ ቶና ደረሱ ደጃፉንም በአንኳኩ ጊዜ ያቺ ሴት ወደ እሳቸው ወጣች እርስ በእርሳቸውም ያ መነኲሴ የነገረን ዕውነት ነው ተባባሉ።

➯የከበረ አሞንዮስም ሳድዥ ብሎ ስም አውጥቶላታል ይህም የዋሂት ማለት ነው። ገብተውም ጸሎት አድርገው የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ እስከ ምሽት ተቀመጡ።

➯አባ አሞንዮስም አምባሻ እየጋገረችልን ነውና ተነሡ ሳድዥን እንያት አላቸው። በገቡም ጊዜ በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ቆማ እጆቿም ወደ ሰማይ ተዘርግተው ስትጸልይ አገኙዋት። አይተውም ስለዚህ ድንቅ ሥራ እጅግ አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ከዚህ በኋላም አቅርባላቸው በሉ።

➯በዚያቺም ሌሊት መልአክ ስለ አባ አሞንዮስና ስለ ሳድዥ ገድላቸውን ለአባ ዕብሎ ነገረው ወደዚህም ዛሬ ያደረሳችሁ እግዚአብሔር ነው የሳድዥን ዕረፍት እንድታዩ አላቸው።

➯ሦስት ሰዓትም በሆነ ጊዜ የሚያስጨንቅ የሆድ ዝማ ታመመች በእግዚአብሔርም ፊት አንዲት ስግደትን ሰገደችና በዚያው ነፍሷን ሰጠች መልካም አገናነዝም ገንዘው ቀበሩዋት።

➯አባ አሞንዮስም ትሩፋቷን ይነግራቸው ጀመረ እርሷ በእርሱ ዘንድ 18 ዓመት ስትኖር ከቶ ፊቷን ቀና እንዳላደረገች እርሱም ደግሞ ፊቷን እንዳላያት ምግባቸውም አምባሻና ጨው እንደሆነ። ከጥቂት ቀን በኋላም አባ አሞንዮስ በሰላም አረፈ።

5 days, 8 hours ago

#ዝክረ_ቅዱሳን_ግንቦት_20/፳ (ስንክሳር)

እንኳን ለከበረ ጻድቅ ለኢትዮጵያ ንጉሥ #ለቅዱስ_ካሌብ ለዕረፍቱ፣ ለሀገረ ቶና ለከበረ #ለአባ_አሞንዮስ ለዕረፍቱ፣ ከአባቶች መምህራን ዐሥራ ስድስተኛ ለሆነ በደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት ሆኖ ለተሾመ ለከበረ አባት #ለአባ_በትረ_ወንጌል ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ።

"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"

#ቅዱስ_አፄ_ካሌብ (መናኙ ንጉሠ ኢትዮዽያ)

➯ግንቦት ሃያ በዚህች ቀን የከበረ ጻድቅ የኢትዮጵያ ንጉሥ ካሌብ አረፈ። ይህ ቅዱስ እግዚአብሔርን የሚፈራውና በፍጹም ልቡ የሚወደው ሃይማኖቱም የቀና ነው።

➯በናግራን አገር ያሉ ክርስቲያኖችን አይሁድ እንደሚገድሏቸው በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ መንፈሳዊ ቅናትንም ቀና። ከዚህም በኋላ ተነሣ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ገብቶ በመሠዊያው ፊት ቆመ ዐይኖቹንም ወደ ሰማይ አቅንቶ እንዲህ ብሎ ጸለየ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ሆይ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሚታየውንና የማይታየውን የፈጠርህ መላእክት ሁሉ አእላፈ አእላፋት አንተን የሚያመሰግኑህ ለአንተም የሚገዙ ዐይኖቻቸው ብዙ የሆነ ኪሩቤል ክንፎቻቸው ስድስት የሆነ ሱራፌልም ጽኑዕ ክቡር ልዩ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር በቅዱሳን የሚመሰገን እያሉ ያለማቋረጥ የሚያመሰግኑህ ፣ ብርሃንን እንደ ልብስ የሚጐናጸፍ የክብር ባለቤት ለሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱ እግዚአብሔር ሆይ የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ የጠፉ በጎችን ይመልሳቸው ዘንድ ልጅህን ይኸውም ቃልህ ነው በፈቃድህ የላክኸው አንተ ነህ።

➯ተናጋሪ በግ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳትለይ ከሰማይ የወረድክና ስለ እኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው የሆንክ ከጨለማም ከድንቁርናም አውጥተህ ወደ ብርሃን ወደ ሕይወት ወደ ዕውቀት የመራኸን።

➯አሁንም ከሀዲ ወንጀለኛ ፊንሐስ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች እንደ በጎች በማረድ እንደ ገደላቸው በእሳትም አቃጥሎ የወገኖችህንና የርስትህን ልጆች እንዳጠፋቸው እይ። እነሆ አብ ሆይ እኔ አመንሁብህ በአንድ ልጅህም በሕያው ቅዱስ መንፈስህም በመሠዊያህ ክብርም ተማፅኛለሁ በሃይማኖትህም ጸንቼአለሁ እነሆ ስለ አምልኮትህና ስለ ምእመናን ወንድሞቼ ስለ ቀናሁ በአንድ ልጅህ መስቀል ጠላቶችህን ልዋጋቸው እወጣለሁና ከአለኝታዬ እንዳታሳፍረኝ የማያውቁህም አምላካቸው ወዴት ነው እንዳይሉ።

➯ስለ በደሌና ስለ ኃጢአቴም ጸሎቴን የማትሰማ ልመናዬንም ንቀህ የምትተው ከሆነ በዚሁ ቦታ ብትገድለኝ ይሻለኛል። አቤቱ መሐሪ ይቅር ባይ ርኅሩህ ርስትህ የሆኑ ምእመናንን በከሀድያን ጠላቶችህ እጅ አሳልፈህ አትስጥ። እኛ ወገኖችህና የርስትህ መንጋዎች ስለሆን ለአንተም ምስጋና እናቀርባለን ምስጋና ገንዘብህ ነውና ለዘላለሙ።

➯ከዚህም በኋላ ንጉሥ ካሌብ ከሀገረ መንግሥቱ ወጥቶ ሔደ የናግራንን ሀገር ያጠፉአት አይሁድን ገደላቸው ብዙ ተአምራትም አድርጎ ስለ አደረገለት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ሀገረ መንግሥቱ በታላቅ ክብር በታላቅም ደስታ ተመለሰ።

➯ለእግዚአብሔር ምን ዋጋ እከፍለዋለሁ ለጌትነቱና ፍጹም ለሆነ ገናናነቱ መባ አድርጌ ነፍሴንና ሥጋዬን ከማቀርብለት በቀር አለ። ከዚህም በኋላ ይህን ዓለም ንቆ መንግሥቱንም ትቶ ወጣ ደጋጎች መነኰሳት ወደሚኖሩበት ወደ አባ ጰንጠሌዎን በተራራ ላይ ወደ አለ ገዳም እስከ ደረሰ በእግሩ ሔደ። ወደ ዋሻ ውስጥም ገብቶ ሰውም እንዳያየው የዋሻውን በር ዘግቶ በዚያ ውስጥ ኖረ ከዚያችም ወጥቶ ዳግመኛ ዓለምን እንዳያይ ማለ።

➯ከእርሱ ጋራም ያገባው ዕቃ የለም ከምንጣፍ ከሸክላ ጽዋ ከለበሳት የምንኲስና ልብስ በቀር ምግቡም አምባሻና ጨው የሚጠጣውም ውኃ ነው። የክብር ባለቤት ከሆነ ከእግዚአብሔር ቃል መቃብር መስኮት ላይ ይሰቅልለት ዘንድ የኢየሩሳሌሙን ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስን እየለመነው ዋጋው ብዙ የሆነ የነገሠበትን ዘውድ ላከ።

➯ወደ ዋሻውም ከገባ በኋላ ከማንም ጋራ አልተነጋገረም እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ በፍቅር አንድነት አረፈ።

2 weeks ago

🤑💵 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗶𝗻𝗴 መማር የምትፈልጉ አንድ የሚገርም የ Forex  ቻናል ያውቃሉ

💶  𝗖𝗶𝘁𝘆 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 💶

@City_Forex_Ethiopia ይባላል ።
ተመዝገባችሁ መማር የምትፈልጉ አናግሯቸው እስከ 𝟰𝟬% Discount የሚደርስ ቅናሽ አድርገዋል !

☎️   +251977338586       🇪🇹
☎️   +251977338586       🇪🇹

ይህን ይጫኑት  ይህን  ይጫኑት  ይህን ይጫኑት

👇👇 ይህን ተጭነው መመዝገብ ይችላሉ   !👇👇

█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸

👆 ይህን ይጫኑት  ይህን  ይጫኑት  ይህን ይጫኑት 👆

🇫 🇴 🇷 🇪 🇽    🇹 🇷 🇦 🇩 🇮 🇳 🇬

🇫 🇴 🇷 🇪 🇽    🇹 🇷 🇦 🇩 🇮 🇳 🇬

🎯 𝗔𝗱𝗱 𝗬𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹

👇 ምርጥ ምርጥ ቻናሎችን ከፈረጉ ከስር ያለውን ይጫኑ 👇

2 weeks ago

**በ Online ገንዘብ መስራት ትፈልጋላችሁ?

በኢንተርኔት Dollar መሰብሰብ ይቻላል።
ኑ እንስራ!
👇**
@Nahwork
@Nahwork

2 weeks ago

**በ Online ገንዘብ መስራት ትፈልጋላችሁ?

በኢንተርኔት Dollar መሰብሰብ ይቻላል።
ኑ እንስራ!
👇**
@Nahwork
@Nahwork

3 weeks ago

🤑💵 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗶𝗻𝗴 መማር የምትፈልጉ አንድ የሚገርም የ Forex  ቻናል ያውቃሉ

💶  𝗖𝗶𝘁𝘆 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 💶

@City_Forex_Ethiopia ይባላል ።
ተመዝገባችሁ መማር የምትፈልጉ አናግሯቸው እስከ 𝟰𝟬% Discount የሚደርስ ቅናሽ አድርገዋል !

☎️   +251977338586       🇪🇹
☎️   +251977338586       🇪🇹

ይህን ይጫኑ የ Telegram ቻናላቸውን ለማግኝት  👇👇

https://t.me/City_Forex_Ethiopia
https://t.me/City_Forex_Ethiopia
https://t.me/City_Forex_Ethiopia
https://t.me/City_Forex_Ethiopia

🎯 𝗔𝗱𝗱 𝗬𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹

3 weeks ago

#ዳግም_ትንሣኤ

➯ዳግም ትንሣኤ ሲባል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ሞቶ፣ ተቀብሮ፣ ተነሳ ሳይሆን በድጋሜ ቅዱስ ቶማስ ባለበት ልክ በመጀመሪያ እንደተገለጠላቸው ሆኖ ስለታያቸው ነው።

➯ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአስሩ ሐዋርያት ሲገለጥላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልነበረምና መጥቶ በተገናኛቸው ጊዜ እነሱም ጌታችን እንደተነሳና ተገልጦ ሰላምታ እንደሰጣቸው ሲነግሩት የተቸነከረውን እጁን እና እግሩን በጦር የተወጋ ጎኑን ካላየሁ አላምንም በማለቱ (ዮሐ 20፥25) እንደገና ተገልጦላቸዋል።

➯ቶማስ ይሄንን ሊል የቻለው የተጠራው ትንሣኤ ሙታን የለም ከሚሉት ከማያምኑት ከሰዱቃውያን ወገን ነበርና ነው። አንድም ሌሎች ሐዋርያት ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ አየነው እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብዬ ላስተምር ነው ብሎ ነው። ጌታም የቶማስን ጥርጣሬ ያስወግድለት ዘንድ በተነሳ በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ቶማስ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር ሳለ እንደገና በትንሣኤ እንደታያቸው ሆኖ በዝግ ቤት ገብቶ ሰላምታ ከሰጣቸው በኋላ ሐዋርያው ቶማስን ለይቶ "ቶማስ ቶማስ ና በችንካር የተቸነከሩ እጆቼን እይ እንዲሁም እጅሀን አምጥተሀ በጦር ወደ ተወጋው ጎኔ አግብተሀ ዳሰኝ ያመንክ እንጅ ተጠራጣሪ አትሁን ባለው ጊዜ ቶማስም በችንካር የተቸነከሩ እጆቹን በጦር የተወጋ ጎኑን በእጆቹ በዳሰሰ ጊዜ ከእሳት እንደገባ ጅማት ኩምትርትር ሲል "ጌታዬ አምላኬ" አለ። መዳሰሱን ሲያይ “ጌታዬ”፤ ማቃጠሉን ሲያይ “አምላኬ” አለ አምላክነቱንም መሰከረ፡፡ ጌታም አንተ አይተኽ አምነሃል ነገር ግን" ሳያዩ የሚያምኑ ብፁአን ናቸው"ብሎ ፈውሶታል (ዮሐ. 20፥29)። (እስከ ዛሬም ይህቺ ጌታን የዳሰሰች የቅዱስ ቶማስ እጅ በሕንድ አገር ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ትገኛለች)

➯በሌላ በኩል ዳግም ትንሣኤ የተባለበት በአከባበር፣ በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡ የትንሣኤ ዕለት የሚባለው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ፤ በሙሉ በዚህ ቀን ይባላል፡፡

➯ከዚህም ሌላ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህም “#ፈጸምነ እና #አግብዖተ_ግብር” ይባላል፡፡ "ፈጸምነ" የተባለበት የሰሙነ ትንሣኤን በዓል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው፡፡ "አግብዖተ ግብር" የተባለበትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ" "እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርሁህ" ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው፡፡ (ዮሐ.17፥4)

መልካም በዓል

@AndEmnet

3 weeks ago

#አባ_ዮሐንስ_ሊቀ_ጳጳሳት (ስንክሳር)

➯በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሀያ ዘጠነኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ አረፈ። እርሱም ከእስክንድርያ አገር ነው ከታናሽነቱም በአስቄጥስ በአባ መቃርስ ገዳም መንኲሶ በተጋድሎ ኖረ።

➯ከእርሱ አስቀድሞ የነበረ አባ አትናቴዎስም በአረፈ ጊዜ አዋቂዎች ኤጲስቆጶሳት ሕዝቡም ሁሉ መረጡት። ወስደውም በግድ ተሾም አሉት እርሱ ግን አልፈለገም የክርስቶስን መንጋ እንዳይተው ሌላ ተሹሞ በክርስቶስ መንጋዎች ላይ ጥፋት እንዳያመጣ ብዙ ልመናዎችን ለመኑት አዋቂዎች ኤጲስቆጶሳትና መምህራን ሁሉ አጽንተው ሲለምኑት በአየ ጊዜ ፈራ ይህ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ይሆን ብሎ አሰበ።

➯ከዚህም በኋላ ሊቀ ጵጵስና ሾሙትና በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ ተቀመጠ። ስለ መንጋዎቹም ጥበቃ አሰበ ደግሞ ስለ ትምህርት መጻሕፍትንም ስለ ማንብበ በቀናች ሃይማኖትም የሚያጸናቸው ሆነ ምሁራን ካህናትንም ኤጲስቆጶሳትን አድርጎ ሾማቸው።

➯በዚያ ወራትም ስሙ ዘይኑን የሚባል እግዚአብሔርን የሚፈራ ደግ ንጉሥ ነበረ። ይህንንም ቅዱስ ስለረዳው ሥልጣኑ በሀገሮች ላይ ተዳረሰ የቀናች ሃይማኖትም በግብጽ አገሮች ሁሉ ላይ ተዘረጋች።

➯በዚያም ወራት ስንዴና ወይን ዘይትም የተመሉ ብዙ እንቅቦችን ለአብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት ለፍላጎታቸው ንጉሥ ዘይኑን ላከ። ለዚህም አባት ዘመኑ ሁሉ ጸጥታና ሰላም ሆነ። ጌታችንም በሥራው ሁሉ ተደሰተለት ከዚህም በኋላ በቸርነቱ ጐበኘውና ጥቂት ታመመ በሹመቱም ስምንት ዓመት ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ።

➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

#ስንክሳር ግንቦት 2 እና #ገድለ_አቡነ_መልከ_ጼጼቅ

4 weeks ago

🤑💵 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗶𝗻𝗴 መማር የምትፈልጉ አንድ የሚገርም የ Forex  ቻናል ያውቃሉ

💶  𝗖𝗶𝘁𝘆 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 💶

@CityForexEthiopia ይባላል ።
ተመዝገባችሁ መማር የምትፈልጉ አናግሯቸው እስከ 𝟰𝟬% Discount የሚደርስ ቅናሽ አድርገዋል !

☎️   +251977338586       🇪🇹
☎️   +251977338586       🇪🇹

ይህን ይጫኑ የ Telegram ቻናላቸውን ለማግኝት  👇👇

https://t.me/+haUXQMQqaqFjNDc8
https://t.me/+haUXQMQqaqFjNDc8
https://t.me/+haUXQMQqaqFjNDc8

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

🎯 𝗔𝗱𝗱 𝗬𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 3 weeks, 6 days ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 weeks ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 day, 13 hours ago