Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

አል ሀድራ AL-HADRA Official

Description
ይህ የ አል ሀድራ ጀመአ ትክክለኛው የቴሌግራም ገፅ ነው!!! በዚ ቻናል በጀመአዉ የተሰሩ መንዙማዋች አውዲዮ እና ቪዲዮ ኢስላማዊ ትምህርቶች ቂሷ ቆንጆ ቆንጆ ፎቶዋች በጠቅላላ ምንም አያጡም ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን
አስተያየት ካሎት ከዚ በታች ባለዉ bot ያድርሱን @Alhadrajemeabot

ለዩቲብ https://www.youtube.com/channel/UC0OsBJSQs7foP_sTTVheiyQ
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

2 years, 7 months ago
አል ሀድራ AL-HADRA Official
2 years, 7 months ago
አል ሀድራ AL-HADRA Official
2 years, 7 months ago

#ለመሻይኾቼ_challenge

እንደ ጅረት ዒልማቸዉ ከፈሰሰበት ችግርን በማይፈራ ቸርነት የተራበ ከመገቡበት፣ እንደ አባት ከተወደዱበት፣ እንደ ንጉስ ከተከበሩበት፣ እንደባርያ ጎንበስ ቀና ብለዉ ካቀኑትና አያሌ ደረሳዎችን አስጠልለዉ ዒልም ካስጨበጡበት ሐሪማ እንደዘበት ተፈናቅለው በስደት ላይ ለሚገኙ ለምድር የከበዱ መሻይኾች የሚገባቸውን ያክል ማድረግ ባንችል መልካም ተግባራት ላይ የተሰለፉ እህት ወንድሞች ባመቻቹልን እድል እነዚህን መፅሀፍት እና ቲሸርቶች በመግዛት በትንሹ መደገፍ ግድ ይሆንብናል! ዋጋዎቹ የመነሻ ዋጋ ሲሆኑ ሊላህ ብሎ በውድ ዋጋ የሚገዙትን እናበረታታለን።

እኛ ለመሻይኾቻችን ዉዴታ ስንል ይህን መፀሀፍና ቲሸርት ገዝተናል እናንተስ?

ይህን መልካም አላማ የምትደግፉ መልካሞች ቲሸርትና መፃሀፍቱን ገዝቶ ፎቶ በመነሳት #ለመሻይኾቼ በሚል ቻሌንጅ ይቀላቀሉን።

ገቢዉ ሙሉ ለሙሉ ከሚያቀሩበት ለተፈናቀሉ አሊሞች እና ከቂርአት ገበታቸዉ ተሰናክለዉ ለወደሙ ከ 20 በላይ ሀሪማዋች ማቋቋሚያ የሚዉል ይሆናል።
ቲሸርቶችን በጅምላ ለማዘዝ
0942593113
0937406175
092 138 3587
በፍሬ ለሚፈልጉ
መርካቶ 0925132995
በኒ መስጅድ ኣካባቢ 0922959003
ካራ 0937443544

መፃህፍቶችን ደሞ በዚህ ማግኘት ይችላሉ

Email : Sewnet1st@gmail.com
User names: @Sewnet1st
Phone:
0956561156
0956565556
እንዲሁም ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አጠገብ
በሚገኘው ሴካ ህንፃ ላይ ማግኘት ይችላሉ ለበለጠ መረጃ
0118279077 መደወልና
እንዲሁም በውሥጥ መጠየቅ ይቻላል

2 years, 8 months ago
አል ሀድራ AL-HADRA Official
2 years, 8 months ago
በረሱላችን መዉሊድ ሚስኪኖችን የማልበስ ዘመቻ

በረሱላችን መዉሊድ ሚስኪኖችን የማልበስ ዘመቻ

የጀነትን አረንጓዴ ልብስ መልበስ የሚመኝ ሁሉ የሚሳተፍበት በጎ ተግባር

በአዲስ አበባ ያሉ አብዛሀኛዋቹ ጀመአዋች በማስተባበር የሚሳተፉበት በጎ ስራ

2 years, 11 months ago

#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ሩሑል ዓሚን ለሙሐመዱል ዓሚን!

መላኢካ እኮ ነው አንደኛው ጁንዱ፣
የዓብደላህ ልጅ ሙሐመድ አንዱ!

«ውጁዱን ሞልቶ ፈሰሰ ላዩን!» እንዳሉት አንድ ሆኖ ተኸልቆ ዓለሙን የሞላ፣ አቀማማጩ መላኢካ፣ ኸዳሚ አገልጋዩ ሁሉ በአዘል ቀድሞ የተሾመለት፣ እናቱን አዋላጅ ያላስቸገረ፣ እትብት ቆራጭ ያላስፈለገው፣ ምድርን በኑር የተቀላቀለ፣ እሷም በደስታ የተቀበለችው!

እንደው የልቤ ትልቅነት’ኮ እኔኑ ዓጃኢብ ያሰኘኛል። አሁን ዛሬ ደግሞ በማን ቀናሁ በጂብሪል ዓ.ሰ አዎን በሀዘንም በደስታም ጊዜ ከጎናቸው ባልጠፋው ወዳጃቸው! እንደው ታድሎ!
ደጋጎቹ
ወገበ ቀጭን ትከሻው ሰፊ፣
ምነው በሆንኩኝ የሱ አሳላፊ!
ብለው የተመኙትን እጣ ደጋግሞ አግኝቷል። ገና ከመጀመሪያው «ይሄንን መልእክት ለሙሐመድ አድርስ!» ሲባል እንዴት ፈንጥዞ ይሆን? ሂራ ዋሻ መጥቶ ሲያገኛቸው፣ ያንን ከሚስክና ከአምበር የሚያውድ ጠረን ያለ ከልካይ ሲቀርብ፣ ያንን የሚያሳሳ ዘንፋላ ገላ ጭምቅ እያደረገ "ኢቅራዕ" "ኢቅራዕ" ሲል ምን ተሰምቶት ይሆን? የኔ ነቢ ባዩት ተደናግጠው እዬተንዘፈዘፉ እናታችን ኸዲጃ ጋር ገብተው "ደርቡልኝ!" "ደርቡልኝ!" ካሉ በኋላ መልሶ ሲያገኛቸውስ ምን ብሎ ይሆን? ከሌሎቹ መላኢኮች ሁሉ እሱ ተመርጦ የ‘ሱ ባልንጀራ በመሆኑስ ሌሎቹ መላኢኮች የስስትና የደስታ ቅናት አይቀኑበት ይሆን? እንደው በአጠቃላይ ግን «ሰው የተባለውን አጥፊ ፍጡር ለምን ትፈጥራለህ?» እያሉ ጌታቸውን ሲጠይቁ የነበሩ መላኢኮች ሙሐመድን፣ አሽረፉ ኸልቂሏህን ሲያዩ በጥያቄያቸው አልተፀፀቱ ይሆን? አባቱን አደምን ሲያዩ ከሆኑትም በላይ ነው መቼም የሚሰማቸው!

ወዳጆቻቸው «የጂብሪል ወዳጅ የአላህ ባለሟል!» ይሏቸዋል ስማቸውን ሲያወድሱ። ተወዳጅ መልእክተኞች ናቸው ሁለቱም። እርሳቸው በርሱ ደስ ይላቸዋል፤ እርሱም የርሳቸው ነገር አይሆንለትም። አንድ ቀን የኔ ነቢ ጂብሪልን «ሙሉ ፍጥነትህን ተጠቅመህ ተጉዘህ ታውቃለህን?» ብለው ጠየቁት። የፍጥነቱን ነገር መቼስ በምናውቀው የብርኃን ፍጥነት እንኳን መገመት አንችልም። እሱም «አዎን በአራት አጋጣሚዎች!» አለና አጋጣሚዎቹን መዘርዘር ቀጠለ። «የመጀመሪያው ኢብራሂም ዓ.ሰ በናምሩድ እሳት በተጣሉ ጊዜ ነው። በዛ ጊዜ እሳቱን እንዳቀዘቅዝ ጌትዬ አዘዘኝ። ስገሰግስ በቦታው ደረስኩ። ሁለተኛው አሁንም ነቢ ኢብራሂም ልጁን ኢስማዒልን ሊሰዋ በተዘጋጀበት ጊዜ ነው። አላህም በምትኩ የሚስሰዋውን በግ ይዤ እንድገሰግስ አዘዘኝ። ስከንፍ ደረስኩኝ። ሶስተኛው ጊዜ የዩሱፍ ዓ.ሰ ወንድሞች ዩሱፍን በጉድጓዱ የወረወሩበት ሲሆን ጌታዬ ዩሱፍን እንድታደገው በነገረኝ ፍጥነት በቦታው ደርሼ ከመጎዳቱ በፊት ክንፌን አንተራስኩት።» አለ። አሁን አራተኛው፣ ዋነኛውና የመጨረሻው ቀረ። «ሌላኛው ያረሱለሏህ..»አለ። «ሌላኛው… አንተ በኡሁድ ዘመቻ ጥርስህን የተጎዳህ ጊዜ ነበር። የዛን ጊዜ አሏህ ደምህ መሬት ጠብ ከማለቱ በፊት ደርሼ እንዳቆመው አዘዘኝ። በድንጋጤ ተምዘግዝጌ ደርሼ በክንፌ ላይ አስቀረሁት። ያ ደም በግፍ መሬት ጠብ ቢል ኖሮ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ መሬት ምንም ዓይነት ዛፍም ሆነ አትክልት አታበቅልም ነበር!!»

ያሐቢበሏህ ማበብም ማፍራትም፣ ማብቀልም ማሸትም ባንቱ ነው ወዳጆችዎ የአንቱ አንድ ጠብታ ደም ከሚፈስ መላው ዓለም ቢፈርስ ይመርጣሉ፥ ከውኑም የተፈጠረው ላንቱው ነውና!!

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሑመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዱና ወመውላና ወሸፊዑና ሙሐመድ!💚💚💚
©️ Atiqa Ahmed Ali

2 years, 11 months ago

በአራት ነገሮች እውነተኛ ወንድምነት ይታወቃል:—
❶ ከመተቸቱ በፊት ይቅር ይላል፤
❷ በመጥፎ ከመጠርጠሩ በፊት መልካም ግምትን (ሑስኑዝ‐ዞን‐ን) ያስቀድማል፤
❸ ከጓደኛው ፍቅርን ከመጠየቁ በፊት እራሱ ቀድሞ ይሰጣል፤
❹ እንከን ከማውጣቱ በፊት ምክንያት (ዑዝር) ይፈልጋል።
:
አል‐ኸሊል ኢብኑ አሕመድ

2 years, 11 months ago

ኢማም ዘሀቢይ "ሲየሩ አዕላሚን‐ኑበላእ" በተሰኘው መፅሀፋቸው ከሻፊዒይ ዋና ዋና ተማሪዎች መካከል አንዱ ስለሆኑት ዩኑስ ኢብኑ ዐብዲል‐አዕላ አስ‐ሶደፊይ [ረሒመሁላህ] ይተርካሉ።
:
በትረካው መሀል ዩኑስ ኢብኑ ዐብዲል አዕላ ስለሸይኻቸው [ሻፊዒይ] የተናገሩትን እንዲህ ያቀርቡታል: ‐
«እንደ ሻፊዒይ አዋቂ ሰው አይቼ አላውቅም! አንድ ቀን በአንድ ጉዳይ ላይ ተከራክሬያቸው ተለያየን። ከዚያም በመንገድ ላይ አገኙኝና እንዲህ አሉኝ: ‐ «አቡ ሙሳ ሆይ! በአንድ ጉዳይ ላይ ባንስማማስ ትክክለኛ ወንድማማች መሆን አንችልም እንዴ!»
:
መለያየት ያለ ነው። ችግሩ ለራስ ሙሉ ሐቅን ሰጥቶ ለሌላው ሙሉ ስህተትን በመስጠት ችክ ማለት፣ በሃሳብ የተለየነውን ሁሉ ጠላት አድርጎ ማየት፣ በአንድ ነገር የተለየነውን ሁሉ በሁሉም ነገር ላይ እንደተለየነው ማሰብ ነው!
ኢላሂ! መንገድህን ምራን!
በሃሳብ ብንለያይም ወንድማማቾች ነን!

2 years, 11 months ago
***🌿******🔹***أكثر منها .. فستحتاج لها ***🔹******🌿***

🌿🔹أكثر منها .. فستحتاج لها 🔹🌿
ይህችን ዚክር እናብዛት…ታስፈልገናለችና

ሱብሀን አላህ
አልሀምዱሊላህ
ላኢላሀ ኢለላህ
አላሁ አክበር

HOLY QURAN
🌸 @QURANYEE 🌸

3 years ago
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago