القناة الرسمية والموثقة لـ أخبار وزارة التربية العراقية.
أخبار حصرية كل مايخص وزارة التربية العراقية.
تابع جديدنا لمشاهدة احدث الاخبار.
سيتم نقل احدث الاخبار العاجلة.
رابط مشاركة القناة :
https://t.me/DX_75
Last updated 1 year, 3 months ago
القناة الرسمية لشبكة ملازمنا كل مايحتاجه الطالب.
((ملاحظة : لايوجد لدينا اي حساب تواصل على تلكرام ولا نقوم بنشر اعلانات في القناة))
Last updated 2 days, 5 hours ago
ከዐሥር በኋላ ዚክር በሸይኽ ዐዲል ይቀላቀሉ።
https://t.me/Noor_Musela?livestream
ሳምንታዊ ደርስ ለሴቶች በሸይኽ ዐዲል https://t.me/Noor_Musela/4444
የሕይወት ሚዛን
የምንኖርባትን አጭር የዱንያ ዓለም በትዕግስትና በእርጋታ ካልተረዳናት ከዐለሙ በሰፋው ውስብስብ ጥልቀቷ ውስጥ እንድንዘፈቅ ታደርገናለች።
የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዚህች ዐለም መከራ እንድንሻገር በርካታ መንገዶችን አድርገውልናል። የርሳቸውን ብርሃናማ ንግግሮች ለመረዳት ጥልቅ እምነት ቢያሻንም ንግግሮቻቸውን ደጋግሞ በማውራትና በማዳመጥ ልባችን ውስጥ ለመጻፍ ጥረት እናደርጋለን። ይህ በራሱ ዚክር ሲኾን በሌላኛው ዕይታ ደግሞ ሕክምና ነው።
የሚቀጥሉት አራት ሐዲሶች ለተረጋጋ ሕይወታችን መሠረቶች ናቸው።
አንደኛ፦ ምላስን ከክፉ ንግግር መቆጠብ
« በአላህና በመጨረሻው ዘመን ያመነ ሰው መልካም ንግግር ይናገር ወይም ዝም ይበል።» (ሐዲስ)
ክፉ ንግግሮች ከአንደበታችን ከሚወጡ ዝምታችን የተሻለ እንደኾነ የሚመክረን ሐዲስ ነው። ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚያዙት በዝምታቸው ሳይኾን በንግግሮቻቸው ነውና!
ሁለተኛ፦ ከማያስፈልጉ ነገሮች መራቅ
የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
« አንድ ሰው የማይመለከተውን ነገር መተዉ ከእስልምናው ማማር ነው።»
ያለንበት ጊዜ በማንፈልጋቸው በርካታ ጥፋቶች በግዴታ የምንነከርበት ነው። ይህ በመኾኑም በቀጥታ የማይመለከቱንን ነገሮች ከመስራት፣ ከማድመጥና፣ ከመናገር መቆጠብ እምነትን እንደሚያጠናክርና ንጽሕናን እንደሚያፋፋ መገንዘብ ተገቢ ነው።
ሦስተኛ፦ ራስን መቆጣጠር (ከቁጣ መጠበቅ)
አንድ ሰው የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲመክራቸው ጠይቋቸው ደጋግመው "አትቆጣ" አሉት።
ይህ የሚያሳየው ቁጣ የአዕምሮን ሚዛን የሚያዛባ ፍትሕን የሚያሳጣ ግለሰቦች ላይ ውስጣዊ ጉዳትን የሚያስከትል ከባድ ነገር መኾኑን ነው።
አራት፦ ንጹሕ ልቦና መያዝ
የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
« ለራሳችሁ የወደዳችሁትን ለሌሎች እስካልወደዳችሁ ድረስ አላመናችሁም።»
ራሳችን ላይ ቢኾን የምንወደውን ነገር ሌሎች ላይ እንዲኾን መመኘት፣ ራሳችን ላይ እንዳይደረግ የምንጠላውን ሌሎች ላይ እንዳይደረግ ማሰብ የአማኝ ባሕርይ ነው። የእምነትም መለኪያ ነው። በዚህች ቅጽበታዊ ዐለም ተታለን ሰዎችን በልብም ኾነ በአካል ከመጉዳት መታቀብ ጥልቅ ከሆነ ከኢማን መንገድ መሸለም ነው።
አላህ ያስረዳን 🤲
« ልክ ያለፈ ጉጉት የሰውዬውን ዋጋ ያጎድለዋል፤ በሲሳዩ ላይ የሚጨምረውም አንዲትም ነገር የለም።»
ኢማም ዐሊይ (ከረመላሁ ወጅሀሁ)
የተጻፈልንን እንኑር ... ያለንን ዛሬ፣ የተለገሰንን ዐፊያና ጸጋ እናጣጥም፣ የጎደለንና ያጣነው እንዳይጎዳን ከአላህ ጋር እናስተሳስረው፣ የውስጥ ደህንነትን ከሚሸረሽር ጭንቀትና አላስፈላጊ ውጥረት ለማረፍ እንጣር።
ዛሬ ካልኖርን ነገ ውጤታማ አይደለንም። የምናከማቻቸው ቁሳቁሶች እኛን ሰው አያደርጉንም። እኛ ሰው ከሆንን ግን ችግር አይጎዳንም፤ ሐብትም ወሰን እንድናልፍ አያነሳሳንም። ሰው ለመኾን ከሚያግዙን ነገሮች ውስጥ አንዱ ልክ ካለፈ ጉጉት ራስን ማቀብና ማመስገን አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።
ጌታዬ ሆይ! በሕመሜ ውስጥ ስለፈጠርክልኝ እምባና ፈገግታ፤ በእረፍቴ ውስጥ ስላደረግክልኝ ደስታና እምባ ምስጋና ይገባህ።
አልሐምዱሊላህ ♥
በተለምዶ ሰዎች ንጋት ላይ ከእንቅልፋቸው እንደነቁ በፍጥነት ወደ ሶሻል ሚድያ የመግባት ልምድ አዳብረዋል። ማታም እንዲሁ ከሚዲያው በረጅሙ ሳይነቁ ወደ መኝታ ይሄዳሉ። ይህ ሳይታሰብ ብዙዎቻችን የተዘፈቅንበት ጎጂ ተግባር ሆኗል።
አንዳንድ ቦታዎች ከመግባታችን በፊት ብዙ የምናደርጋቸው ጥንቀቄዎች አሉ አይደል?! እንደው በትንሹ እነርሱን ማድረግ አይገባንም?! ሰዎች ለጉዳት በሚጋለጡበት ቦታ በጥንቃቄ ለማለፍ ከብዙ ፍርሀት ጋር አስፈላጊ ዝግጅት ያደርጋሉ። ሰዎች በሚበዙባቸው፣ ባለጌዎችና አላዋቂዎች በሚበዙበት ሰፈር አንዲት ሙስሊም ሴት ለማለፍ ስትሳቀቅና ዕቃዋ እንዳይሰረቅ ሰዎች እንዳይለክፏት የምታደርገውን ጥንቃቄ እናውቀዋለን አይደል? ይህ ሰውኛ ነው።
ሶሻል ሚድያ ላይ ከመግባታችን በፊት እንዲህ አይነት ጥንቃቄዎች ያስፈልጉናል። የሚወራውን ሁሉ ላለማየት፣ የምንለብሰውን፣ የምናስተላልፈውን፣ የምንናገረውን መለየትም ተገቢ ነው። ቦታው በብዙ ተናካሽ መንፈሶች ስለተከበበ በቂ መንፈሳዊ ስንቅ ሳንይዝም ለማስተማር ተገቢ አይደለም ሁላ የሚል የግል እምነት አዳብሬያለሁ።
በአጭሩ ጠዋት ከአዝካር ወይም ከቁርኣን በፊት ዘሎ ሚድያ ላይ መግባት በለሊት ገበያ ላይ እንደመግባት ነው የምቆጥረው። ገበያ ላይ ሰው ሳይገባ መግባት ይጠላል ለምን? ቦታው ላይ ቀድመው ሰይጣናት ይሰፍሩበታልና። የገበያ ቦታዎች ላይ ያሉ ሰይጣናት ሰዎች እንዲያታልሉና በረከት እንዲነሳ የሚያደርጉ ናቸው።
በምንሰራው፣ በምንናገረው፣ በሐረካት ሰከናት ላይ በረከት ከፈለግን ከቁርኣን በዐቅማችን ልክ እንቅረብ። የቀራችሁ ለመረዳት ጣሩ፣ የተረዳችሁ የበለጠ ለመኖር ጣሩበት፣ የሐፈዛችሁ እንዲሁ የመልእክቶቹን ጥልቀት ለማጤን ልፉበት፣ ምንም ያልቀራችሁ ተማሩ፣ ምንም ያልቻላችሁ በጥሩ ኒያ አዳምጡት በርሱም ታከሙበት ሁሉም ቁርኣን ላይ የሚደረግ ልፋት በረካ አለው።
« ልፋቱን ኹሉ በቁርኣን መንገድ ላይ ያፈሰሰ፤ በሕይወቱ ጉዳይ ላይ ኹሉ በረከት ይፈስለታል።» ይላሉ የቁርኣን ሰዎች
ቁርኣን ውስጥን የሚያጠግብ ዝናብ ነው፣ ነፍሶችን የሚያለዝብ፣ መንገድ የሚመራ፣ ታላቅ መድሐኒት ነው።
በገራን የቁርኣን ወይም የዚክር መንገድ ለልባችን ሳንሰጥ ወደ ሶሻል ሚድያ ዘው ብለን አንግባ፤ ማታም ከሶሻል ሚድያ ስንወጣ እንዲሁ በቀና መንፈስ ላይ እንዲኾን ከመጣር ጋር መልፋት ተገቢ ነው ለማለት ያህል ነው።
አላህ ከክፉው ኹሉ ይጠብቀና ♥
አንዳንድ መልካም ነገሮች ሸህዋ ሲኾኑ ኒያን በማደስ ማቃናት ያስፈልጋል። ቅርብ ሰአት አንድ መስጂድ ውዱእ እያደረግኩ ነው። አንድ ሰው መጣና ከኋላዬ ባልተገባ ድምጽ "ቀንስ ቀንሰ" ብሎ አደናገጠኝ ለራሴ ውሃው አልወርድ ብሎኛል። ሰብር አደርግኩና ምን ልቀንስ ድምጽ ነው አልሁ በልቤ ከዚያም ትቼው ገባሁ። ሰውዬውም ዝም አለ። ትዕዛዙን በበጎ ጎን ባየውም ኺድማ ሻህዋ ሲኾንበት ነው የታየኝ። አንዳንድ አምልኮዎች፣ ዳዕዋዎች፣ ኸይር የተባሉ ሥራዎች ኹሉ ኒያ የሚያስፈልጋቸው መሰል ችግሮችን ለመርታት ነው። አንድ ሰው የሰዎችን ሐቅ ቀርጥፎ እየበላ ሐጅ ቢሄድና ስለሐጅ ጠቀሜታ ቢያወራ ሐጁ ሻህዋ ነው ወይስ ዒባዳ? መስጂድ እየተመላለስን እውነት መናገር ካቃተን?! በሕይወታችን ውስጥ ሲድቅ (ጄኒዩኒቲ) ከራቀን የምንሰራቸው መልካም የሚባሉ ኢስላማዊ ነገሮች የሚወልዱት ሌላ የሻህዋ ችግር አለ ማለትን ያስይዛል። ይህን አደገኛ በሽታ ማከም የምንችለው ሻህዋን በሚጨምረው በመታየትና ከሰዎች ምስክር በመፈለግ ሳይኾን ኒያን በማቃናት ነው። የምናደርገውን ነገር ቆም ብሎ በመፈተሽ በሥራችን የአላህን ፊት በመፈለግና ለእርሱ ስንል እውነት ላይ መቆማችንን ደጋግሞ በማስታወስ ነው። ይህን ለማድረግ እርሱ ከረዘቀን "ለአላህ ብሎ ከመጥፋት" እንድናለን።
ያስረዳና ሰላም እደሩ ♥
በውድቅት ለሊት በመንቃት ከአላህ ጋር ተገልሎ መቆየት ፣ ከፈጅር በኋላ ጥቂት ደቂቃዎች ታግሶ ሳይተኙ መቀማመጥ፣ ከዐሥር በኃላ ባለው ወቅት ስለ መንፈሳዊ ነገሮች ማስተንተንና ወይም ዎክ (በጥቂቱ እርምጃ) ማድረግ ከዚያም ከመግሪብ እስከ ኢሻ በመስጂድ ወይም በቤት ውስጥ ከቁርኣን ጋር መቆየት አራቶቹ ምርጥ ወቅቶች ናቸው።
ሰይዲ ሸይኽ ሳሊሕ ጃዕፈሪይ እንዲህ ይላሉ፦ « ሰላት ከሚጠላና ከመጥፎ ነገሮች ትከለክላለች።»
ብዙ ሰዎች ይህን አንቀጽ ይዘው “እከሌ እየሰገደ ይህን መጥፎ ነገር ያደርጋል?!" ይላሉ
እነዚህ ሰዎች በዚህ ቃላቸው ከአንቀጹ የተረዱት ነገር የሚሰግድ ሰው በፍጹም መጥፎ ነገር ጋር አለመድረሱን ነው። ጉዳዩን ስንመለከተው ግን እንደሰዉ ይለያያል።
ሰላት ለአንዳንድ ሰዎች ወንጀሉ ላይ ከመውደቁ በፊት ይከለክለዋል። ለዚህኛው ሰው ሰላቱ ከወንጀል ይከለክለዋል በሚለው ይተረጎማል።
ለአንዳንድ ሰው ደግሞ ሰላት ደግሞ ወንጀሉ ከተፈጸመ በኋላ ወደ ንሰሐና ጸፀት እንዲገባ ያደርገዋል።
የመጀመሪያው፦ የዘውታሪዎች ሰላት ሲባል ሁለተኛው ደግሞ የመንገደኞች ሰላት ይባላል። (አላህ ንሰሐቸውን ይቀበላል ተብሎ ይከጀላል።)
የሐዲስና የቁርኣን ትርጉሞችን ቀደምት ካለፉ የዒልምን ሰንሰለት ጠብቀው ካቆዩ ዐሪፎች ለመረዳት መሞከር የእምነቱን ስፋት እንይበታለን። ይህ ካልሆነ ማንም ሰው ከኪሱ እንደሚያወጣው ገንዘብ አንቀጾችንና ሐዲሶቹን በፈለገው ስሜት ሊቃኘው ይችላል። በተለይም የአላህ ቃል የኾነውን ቁርኣን በዘፈቀደ ስሜትን ተከትሎ በአእምሮ ሚዛን ብቻ ለመዳሰስ መሞከር ከውስጥ ረባኒያን ያጠፋል፣ ሰዎች ላይም በር ይዘጋልና መጠንቀቅ ያሻል።
ከላይ የተተነው ሐሳብ በጥቅሉ ሰዎች ወንጀል ሲሰሩ በደፈናው የሚታየው ወንጀል ላይ ይዘወትራሉ ማለት እንዳልሆነ እንድንማር ነው። ሌላው ማናችንም ብንኾን ከወንጀል ማምለጥ አለመቻላችንን ይጠቁማል። የምንሰራው አምልኮ ለወንጀል ከጠበቀን በሚፈለገው እርከን ላይ ነን ማለት ነው። አምልኮው ጠበቀኝ ከወንጀል ጸዳሁ የሚል ስሜት ከመጣብን ወይም የሌሎች ሰዎች ወንጀል ላይ ከተጠመድን ሌላ ከባድ ወንጀል ላይ እየቆምን ነውና መላልሶ ማሰብ ደግ ነው።
ሰይድና አባ በክር ሲዲቅ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦ « አላህ ከባባድ ወንጀሎችን ይምራል ተስፋ አትቁረጡ፤ ትናንሽ ወንጀሎችን ደግሞ ይቀጣል እንዳትታለሉ።»
ሸርህ ቡኻሪ ለኢብን በጣል (19/267) ?
አላህ ምህረቱን ይለግሰና ♥
القناة الرسمية والموثقة لـ أخبار وزارة التربية العراقية.
أخبار حصرية كل مايخص وزارة التربية العراقية.
تابع جديدنا لمشاهدة احدث الاخبار.
سيتم نقل احدث الاخبار العاجلة.
رابط مشاركة القناة :
https://t.me/DX_75
Last updated 1 year, 3 months ago
القناة الرسمية لشبكة ملازمنا كل مايحتاجه الطالب.
((ملاحظة : لايوجد لدينا اي حساب تواصل على تلكرام ولا نقوم بنشر اعلانات في القناة))
Last updated 2 days, 5 hours ago