"ቃለ እግዚአብሔር "

Description
"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

1 day, 23 hours ago

#ከሐልዮ_ኃጢአት_መጠበቅ

ሰይጣን ነቅዓ ሐልዮን መጠበቅ ላልቻለ ወጣት በቀጣይ እርሱን የሚወጋበት ኹለተኛው ጦር ሐልዮ ኃጢአት ነው። “የሐልዮ ኃጢኣት ምን ትጎዳለች?” እያለ እንዲያስብ ያደርገዋል። በሐልዮ ኃጢአት ያዝለዋል። ይኸውም ደቂቀ ሴት ደቂቀ ቃኤልን ከመስማት አልፈው እንዲመለከቷቸው በማድረግ በዝሙት ፍላጻ እንደነደፋቸው ነው። ስለዚህ የተለያዩ ነገሮችን እንዲመለከት ያደርገዋል። ለምሳሌ ራስን በራስ ስለ ማጎሳቆል፣ ወይም ስለ ምስለ ሩካቤ፣ ወይም ስለሚያውቃት ሴት በዝሙት ሕሊና እንዲያስብ ያደርገዋል። ጓደኞቹ የተናገሩትን ነገር ወይም በመጽሔት ያነበበውን ወይም በተለያየ መንገድ ሲወራ የሰማውን “ይህ ምን ያረክሳል?” እያለ በሕሊናው እንዲያመላልሰው ያደርገዋል።

እንደዚህ በሚኾንበት ጊዜ በየትኛውም ቀን ቢሰግድ ፆሩ ይመለስለታል። አንድ ወንድሜ እንደ ነገረኝ፡ እንደዚህ ያለ ፆር ሲመጣበት በሩካቤ አካሉ አከባቢ ካለው ፀጕር የተወሰነውን ይነጫል። በጣም ያማል። በዚያ ሰዓትም ከፆሩ ይልቅ ሕመሙ ስለሚበልጥ ፆሩን ከማሰብ ይመለሳል። ሕሊናው አድርገኝ አድርገኝ ብሎ እንዳይገፋፋው፣ ነጉዶ የመጣውን ፆሩን በተግባር ለመፈጸም ሰይጣንን እንዳይታዘዘው ያደርገዋል። እንደ ነደ እሳት የሚያቃጥለውን የፍትወትን ፆር እንዳያስነሣበት ይከልለዋል።

የሐልዮ ኃጢኣት በተነሣ ጊዜ "ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ” እንደ ተባለው፥ ለዚህ ከሚዳርጉን ነገሮች (ቦታ፣ ኹኔታ) መራቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። “ይህ አሳብ የእኔ አይደለም” ብሎ ለመሸሽም የሐልዮ ኃጢአት የምታመጣውን መከራ የሚነግረን መምህር ወይም አበ ነፍስ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው (2ኛ ጢሞ.2፥22)። መካሪ መምህር ሳናገኝ ቀርተን ካዋልናትና ካሳደርናት ለሰይጣነ ፍትወት እጅ እንደ መስጠትና ወድቀን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ገቢር ልናልፍ እንችላለንና። ከክፉ አሳብ መራቁ ብቻውን በቂ አይደለም። ክቡር ዳዊት “ከክፉ ሽሽ” ካለ በኋላ በዚያ ሳያቆም ጨምሮ “መልካምንም አድርግ" ይላልና (መዝ.33፥14)። እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ናቸው። ስለዚህ አንዲት ሴት ጥሩ ልብሷን ተሸላልማ ተጊያጊጣ እየተኩነሰነሰች ስትሔድ አይቶ ፈላስፋው ዲዮጋንስ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች "ከዚች ክፉ ወጥመድ ሽሹ" እንዳላቸው ሸሽቶ ወደ በጎ ሥራ ፊትን ማዞር ይገባል። ከወደቁ በኋላ ከመጠበብ ሳይወድቁ መጠንቀቅ ይሻላልና።

በሌላ መልኩ ደግሞ ተፈጥሮ ስለኾነ እነዚያ ስሜቶች ለምን መጡ ማለት አይቻልም። ስሜቶቹን ግን መቀደስ ስለሚቻል ከክፉ ሸሽቶ መልካም በማድረግ መቀደስ ይቻላል። አንድ ፈረስን የሚጋልብ ሰው፥ ፈረሱ ወደ ገደል ቢያመራ ጋላቢው የሚያደርገው ልጓሙን ማጥበቅ ብቻ አይደለም፤ ፈረሱ በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድም ይመራዋል እንጂ። ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ሲመጡብን ከመራቅ ባሻገር ወዲያው መንፈሳዊ ተግባር ማከናወንም አስፈላጊ ነው። ጸሎት ሊኾን ይችላል፤ ስግደት ሊኾን ይችላል፤ መጽሐፍ ማንበብ ሊኾን ይችላል፣ መንፈሳዊ አባት ጋር መደወል ሊኾን ይችላል።

ከበረኻ አባቶች ከተሰጡት ምክሮች አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦“ሌላ እኁም ከሰይጣነ ዝሙት ጋር ይጋደል ነበር። በሌሊት ተነሥቶም ከአረጋውያኑ ወደ አንዱ መጥቶ ስለ ሕሊናው ነገረው። አረጋዊውም ይታገሥ ዘንድ መከረው። በዚህ መንገድ እገዛ አግኝቶም ወደ በዓቱ ተመለሰ። ለኹለተኛ ጊዜም ወደ አረጋዊው መጥቶም እርዳታ አግኝቶ ወደ በዓቱ ተመለሰ። ውጊያው ለሦስተኛ ጊዜ ሲመጣበትም እንደገና  በሌሊት ወደዚያ አረጋዊ ሔደ። አረጋዊውም ወጣቱን አላሳዘነውም፤ እንደሚጠቅመው መክሮ ዘክሮ ነገረው እንጂ፤ እንዲህ ሲል፡- ምንም ዕድል እንዳትሰጠው። ሰይጣነ ዝሙት በፈተነህ በማናቸውም ሰዓት ወደ እኔ ና። ከዚያም ታጋልጠዋለህ። ስታጋልጠው ሸሽቶ ይሔዳል። ሰይጣነ ዝሙት እነዚህን አሳቦች የሚደብቃቸውንና የማይገልጣቸውን ሰው ያህል የሚፈትነው የለምና።" ያ እኁም በዚያች ሌሊት እርዳታ ፈልጎ ዓሥራ አንድ ጊዜ ወደ አረጋዊው እየተመላለሰ አሳቦቹን ተቃወማቸው። አረጋዊውም ሰይጣነ ዝሙቱ ከእርሱ እንደ ራቀ ነገረው። ነገር ግን ወደ በዓቱ በተመለሰ ጊዜ ውጊያው እንደ ገና መጣበት። ከብዙ ጊዜ ምልልስ በኋላም ያ እኁ አረጋዊውን:- አባ! ቸርነትህ ይደረግልኝ፡ እንዴት አድርጌ መኖር እንዳለብኝ ምከረኝ አለው። አረጋዊውም፡- ልጄ ፥ በርታ! እግዚአብሔር ፈቃዱ ከኾነ የእኔ ሕሊና ወደ አንተ ይመጣል። ከዚያም በኋላ ንጹሕ ሕሊና ይዘህ ትሔዳለህ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ አትፈተንም' አለው። ይህን ብሎ ሲጨርስም እግዚአብሔር ሰይጣነ ዝሙቱን እስከ ወዲያኛው ከዚያ እኁ አራቀለት።”

ስለዚህ ሰይጣነ ዝሙት መጥቶ ሲያሳስበን ወይም በሌላ መንገድ ያየነውንና የሰማነውን በሕሊናችን እንድናመላልሰው በሚፈልግበት ጊዜ ምንም ሳንሰለችና ዕድል ሳንሰጥ ወደ አበ ነፍሳችን መሮጥ እንዳለብን ያስረዳል። አበ ነፍሶችም በትዕግሥት ልጆቻቸውን የመርዳት መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው። ወላጆቻችንም ሊያግዙን ይችላሉ።

የሐልዮ ኃጢአት በእኛ ላይ እንዲነግሥ ከሚያደርጉ ነገሮች ኣንዱ ለብቻና ሥራ ፈት መኾን ነው። ሥራ ፈትተን ለብቻችን ስንኾን ሰይጣን መጥቶ ያንን ኃጢአት በደንብ እንድናስብበት፣ ተግብረው ተግበረው ይለናል። ልክ ለሔዋን በለስን የምታስጎመጅ አድርጎ እንዳሳያት፥ በእኛም የማስተዋል ሕሊናችንን አጣምሞ ከዚያ ኃጢአት ስለምናገኘው ደስታ ያሳስበናል። “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀድዶ ይሰፋል” የተባለው መነኰሴ ሥራ ላለመፍታትና ከሓልዮ ኃጢኣት ለመራቅ ሲል ይህን ስለሚያደርግ ነው። ስለዚህ ዝም ብለን መቀመጥ አይገባንም። ይልቅስ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመሳተፍ፣ ሌሎች በጎ ሥራዎችንም በመሥራት እንጠመድ።

በዚህ ከተጎዱት ሰዎች መካከል አንዱ ነቢዩ ዳዊት ነው። ነቢዩ ዳዊት ወጣት ኾኖ በጎችን በሚጠብቅበት፣ ለሳኦል ጋሻ ጃግሬው ኾኖ በገና እየደረደረ በሚያገለግልበት፣ ሳኦል በምቀኝነት ተነሥቶበት በሚያሳድደው፣ ወደ ንግሥናው መጥቶ መንግሥቱ እስከ ተደላደለ ጊዜ ድረስ በዝሙት አልወደቀም ነበር። መንግሥቱ ተደላድሎ ከተመሠረተ፣ ክብሩ ከጨመረ በኋላ ግን ሥራ ፈትቶ በሰገነት ላይ ሲመላለስ የኦሪዮን ሚስት ቤርሳቤህን ስትታጠብ ተመለከታት። ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ፡- “ሰውነት ሥራ ሲፈታ፥ ሕሊናም ሥራ ይፈታል” እንዳለው፥ ንጉሥ ዳዊት ሥራ ፈትቶ ስለ ነበረም በቀላሉ በነቅዓ ሐልዮ ሳያበቃ ስለ እርሷ በማሰብ ወደ ሐልዮ ኃጢኣት ገባ። ስለዚህም “መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፣ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ" (2ኛ ሳሙ.11፥4)።

በመኾኑም ራሳችንን ሰይጣን ወደ ሕሊናችን የሚያስገባውን የሐልዮ ኃጢአትን ከላይ በጠቀስናቸው መንገዶች በማራቅ፥ ንጽሕናችንን ጠብቀን ከሴት ከወንድ ርቀን እስከ ጋብቻ ድረስ መጽናት ይኖርብናል።

አንዳንድ ጊዜ በሕልማችን ሩካቤ ስንፈጽም ልናይ እንችላለን። በዚህ ጊዜ እኛ ራሳችን ቀን ላይ ያሰብነው አሳብ አለመኾኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በቀን ያሰብነው ሌሊት ቀጥሎ ከኾነ ከአበ ነፍስ ጋር ተነጋግሮ አሳቡን ማራቅ፣ ከዚያ ውጭ ግን ወጣቶች በመኾናችንና “ፒቱታሪ” የተባለው ዕጢ የዘር ፈሳሽ ማመንጨቱና አንዳንድ ጊዜ በራሱ ተስፈንጥሮ ስለሚወጣ በዚህ መነሻነት ወደ ሌላ ኣሳብ እንዳንሔድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

(ገብረ እግዚአብሔር ኪደ  ከተጻፈው #ትንሿ_ቤተክርስቲያን መጽሐፍ - ገጽ 161-163)

1 week, 1 day ago

ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት (ሁለተኛ መነሳት)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል።

ሁለተኛ ለምን ተገለጠ?

👉 ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን

የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል።

ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል ።ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ።ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች)እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች ።እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ።

👉 ሰንበትን ሊያጸናልን

የአይሁድ ሰንበት፣እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም(ቅዳሜ)ናት ።በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ከሙታን መካከል የተነሳባት፣አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት(ዳግማይ ትንሳኤ)፣መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች ።ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች ።ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት ።እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን)የምናሳልፈው ማለት አይደለም ።እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ

👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል ።በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ።
"ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ"
(ዮሐ20:29)

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
    ...............ይቆየን...........

1 week, 3 days ago

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

ዓርብ :-ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል።

በዚህ እለት ቤተ ክርሰቲያን በክርስቶስ ደም መመስረቷ ይነገራል።ክርስቶስ ስለ እርሷ እራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አጽንቶ በትንሳኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል የቤተክርስቲያን እራሷ መሰረቷ ክርስቶስ መሆኑን በስፋት እና በምልዐት ይሰበካል።

1 week, 4 days ago
1 week, 4 days ago

ሐሙስ -  [ አዳም ሐሙስ ]

አዳም ማለት ትርጉሙ

፩ኛ.  የሰው ሁሉ አባት ፣ የሥጋው ተፈጥሮ ከአፈር ከመሬት ስለሆነ አዳም መባልን ከአዳም ወስዷል፡፡ [ ዘፍ ፪፥፲፤ ፲፱፥፳፯ ]

፪ኛ.  አዳም ማለት እንሰሳዊና መልአካዊ ሁለት ባሕርያት ስላሉት በሥጋው መዋቲ፣ ድኩም፣ ፈራሽ፣ በስባሽ፤ በነፍሱ ነባቢ፣ ልባዊ፣ ሕያው፣ ባለ አእምሮ ይባላል፡፡ [ዘፍ ፪፥፯]

፫ኛ. አዳም በ፮ኛ ቀን መጀመሪያ ከምድር የፈለቀ የሰው ሁሉ ምንጭ ስለሆነ፤ በዘር በሩካቤ ከእርሱ እየተቀዳ ሞትና መቃብር የሚጠጡት ምድራዊ ሰው ሁሉ በእርሱ ስም በምንጩ ስም አዳም አዳሜ ይባላል፡፡ [ዘፍ ፫፥፲፱]

ስለዚህም አዳም የመጀመሪያ ሰውና የሰው ሁሉ አባት ነው፤ በ፮ኛው ቀን የተፈጠረ የሰው ሁሉ ምንጭ ስለሆነ የሰው ዘር ሁሉ ከእርሱ ተገኝቷል፡፡

በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው የተስፋ ቃል ስለመፈጸሙ፤ [ዘፍ. ፫÷፲፭]  አዳም ከነልጆቹ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻ ስለመውጣቱ ይታሰብበታል፡፡

ክርስቶስ በተነሳበት በአምስተኛው ቀን ሐሙስ  አዳም ይባላል፤ ጌታችን አዳምን ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ  አድንሃለሁ ብሎ  ቃል ገብቶለት  እንደነበር በቀሌምንጦስ ተጽፏል፡፡

አዳምና ሔዋን በገነት ፯ ዓመት ከቆዩ በኋላ ትእዛዙን በመተላለፋቸው ከኤደን ገነት አስወጣቸው [ ኩፋ.፬፥፲፮፤ዘፍ.፫፥፳፫ ]«ብዙ ተባዙ» ያለው ቃል እንዳይቀር በምድር ላይ ወርደው ልጆችን ወለዱ ይላል፡፡

የተወለዱትም ልጆችም በቁጥር ፷ እንደሆኑ [ ፩መቃ. ፳፰፥፮] የተወለዱት ልጆች ደጎችና ክፉዎች እንደ ነበሩ በአቤልና በቃየል ታውቋል። [ ዘፍ. ፬፥፰]።

አዳም በዚህ ዓለም ፱፻፴ ዓመት ኑሮ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ፵፻፭፻፸ ሚያዚያ ፮ ዐርፏል፡፡

1 week, 5 days ago

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን  

ክርስቶሰ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኅይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም  *   እም ይእዜሰ
ኮነ 
*   ፍሥሐ ወሰላም  

"የትንሣኤው ምሥጢር"

⚜️ረቡዕ  ⚜️⚜️⚜️ አልአዛር ⚜️⚜️⚜️

"ጌታዬ አምላኬ" (ዮሐ፳:፳፰)

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቅደላዊት ቀጥሎ በዝግ ቤት ሳሉ ከሐዋርያው ከቶማስ ውጭ አንድ ጊዜ ተገልጦላቸው ነበር ፡፡ የሐዋርያውን የቶማስን ጥያቄ ሊመልስ ፤ እምነት ያሳድግ እና አምላክነቱን ይገልጥ ዘንድ ለሁለተኛ ጊዜ ከስምንት ቀን በኋላ ተገልጦላቸኋል፡፡ "ከስምነት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ፡፡ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ ፤ በመካከላቸውም ቆሞ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው፡፡ ከዚያም በኋላ ቶማስን ፡- ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው ፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው፡፡ ቶማስም ፡- ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት፡፡ ኢየሱስም ፡- ስለ አየኸኝ አምነሃል ፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡" እንዲል፡፡ (ዮሐ፳፡፳፮-፳፱)

ሐዋርያው ቶማስ አምላኬ ጌታዬ ያለበት ምክንያት በዋናነት ጣቱን ወደ ጎኑ ባስገባት ጊዜ ከእሳት እንደገባ ጅማት ሆናለችና መዳሰሱን ሲያይ ጌታዬ አለ ፤ ማቃጠሉን ሲያይ ደግሞ አምላኬ አለ፡፡ ገቦ መለኮትን የዳሰሰች እጅ በሕያውነት ትኖራለች፡፡ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር ከመንበር ላይ ነው የምትኖር በዓመት በዓመት በእመቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች ዓመት አገልግሎ ያርፋል ፤ በዓመቱ ሊያጥኑ ሲገቡ ትይዛቸዋለች እንዲህ እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡(ወንጌል ቅዱስ ገጽ፮፻፬)

ሳናይ ልናምን እንደሚገባ እና ማመናችን ብፁአንም አንደሚያሰኘን ከገለጠለት በኋላ ቁጥር ፴ ላይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ(በሌሎች ወንጌላት እና በተአምረ ኢየሱስ የተጻፉ) ብዙ ታምራትን እንዳደረገ ይህ ግን እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ (የባሕርይ አምላክ ነው) ብሎ ለማመን እንደተጻፈ ገልጦልናል፡፡ (ዮሐ፳፡፴፩)

የሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሊቅ የነበሩት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ስለ አምላካችን ስለ ኢየሱስ ክርሰቶስ ባሕርይ በጥልቀት ለካቶሊኩ መነኩሴ ዶክተር አባ አየለ በመለሱበት መጽሐፍ ስለ አምላክነቱ በግልጽ በአንድ ኃርፍተ ነገር ጽፈውልናል፡- "ክርስቶስ ፍጹም ሰው የሆነ ፍጹም አምላክ ነው"(መድሎተ አሚን ገጽ ፻፴፬) 

"የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት "

የሰው ልጆች በተለይ ቅዱሳን አማልክት ዘበጸጋ ይባላሉ ፤ ሙሴ በፈርዖን ላይ አምላክነትን ቢሾም በጸጋ ነው ፤ እናንተን አማልክት ናችሁ አልኋችሁ ግን ትሞታላችሁ የተባሉት እግዚአብሔር የመረጣቸው ቅዱሳኑን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት ግን የባሕርይው ነው፡፡ እኛ ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች ብንባል በጸጋ ነው ፤ እርሱ ግን እግዚአብሔር ልጅ ሲባል በባሕርይ ልጅነት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የገለጠ የእውነት ምሥክር ነው፡፡

፩. አምላክነቱ በፈጣሪነቱ ተገልጧል፡፡ (ዘፍ፩፡፩ እና ዮሐ፩፡፫)

፪. አምላክነቱ በሥራው ተገልጧል፡፡ (ዮሐ፭፡፴፮)

፫. አምላክነቱ በትምህርቱ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፯፡፳፱) 

፬. አምላክነቱ በፈዋሽነቱ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፬፡፴፮)

፭. አምላክነቱ ኃጢአትን በማስተስረይ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፭፡፳) 

፮. አምላክነቱ ሙታንን በማስነሳቱ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፯፡፲፯) 

፯. አምላክነቱ በመድኃኒትነቱ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፰፡፩) 

፰. አምላክነቱ ዲያብሎስን በመሻሩ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፰፡፲፮) 

፱. አምላክነቱ ሁሉን በማሸነፉ ተገልጧል፡፡ (ዮሐ፲፯፡፪) 

፲. አምላክነቱ ሁሉን በመግዛቱ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፰፡፳፮) 

፲፩. አምላክነቱ ሞትን ድል በመንሳቱ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፯፡፲፬) 

፲፪. አምላክነቱ በሁሉ አዋቂነቱ ተገልጧል፡፡ (ዮሐ፩፡፵፰) 

፲፫. አምላክነቱ በሁሉ ቦታ በመኖር ተገልጧል፡፡ (ማቴ፲፰፡፳) 

፲፬. አምላክነቱ ሁሉን በማዳኑ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፲፰፡፲፩) 

፲፫. አምላክነቱ በሁሉ ቦታ በመኖር ተገልጧል፡፡ (ማቴ፲፰፡፳) 

፲፮. አምላክነቱ በእግዚአብሔርነቱ ተገልጧል፡፡ (ሐዋ፳፡፳፰) 

በአጠቃላይ ይህቺ ዕለት ቶማስ በመባሏ ለእነዚህ ሁሉ የትንሣኤው ምሥጢር ሕያው ምስክር ትሆን ዘንድ አባቶቻችን እንድናስባት አደረጉን፡፡

ወዳጆቼ በዋናነት ይህች ቅድስት ዕለት ወይም ሠሉስ የሐዋርያው ቶማስ በአምላካችን ፍቅር መማረክ ፤ ትንሣኤውን ማመኑ ፤ ሳያዩ የሚያምኑ ክርስቲያኖች የሚያገኙትን ብፅዕና ፤ የአምላካችን ተአምራቶችም ሆኑ ትምህርቶች በዚህ መጽሐፍ ብቻ የተጻፉት ብቻ እንዳልሆኑ ፤ ከሁሉ በላይ ኢየሱስ ክርስቶስን የባህርይ አምላክ ብሎ ማመን የተገባ እና መጽሐፍትም የተጻፉበት ዓላማ መሆኑን እንማራለን፡፡

⚜️⚜️⚜️፫. ረቡዕ አልዓዛር ይባላል ⚜️⚜️⚜️

በዚህች ዕለት አምላካችን ትንሣኤ እና ሕይወት መሆኑን በተግባር በታላቅ ተአምራቱ ማሳየቱን የምናስብበት በመሆኑ ስያሜው አልዓዛር ተብሏል፡፡

የአራት ቀን ሬሳን ሕይወት ይዘራበት ዘንድ የፍቅር አምላካችን በሞት በሚፈልጉት በጠላቶቹ ሰፈር ተመላለሰ ፤ የደቀ መዛሙርቱን ክልከላ አልሰማም ፤ የመንገዱ ርቀት አላዘለውም ግን በፍቅር ስለ ፍቅር ሰው ሁሉ ተስፋ የቆረጠበትን ወዳጁ አለዓዛርን ከሞት ሊያስነሳ ወደ ቢታኒያ በፍቅር ተጓዘ ፤ እውነት ነው ሞት ለታወጀብን ለእኛ ለመመላለሱ ምሳሌ ነው ፤ ሞት ድል ያላደረገው የትንሣኤውን ጌታ አምላካችንን በእውነት እንደተነሳ እንድናስብ ቤተክርስቲያን በዚህ ዕለት በአልዓዛር አንጻር ትንሣኤ እና ሕይወት እርሱ እንደሆነ ታስተምረናለች፡፡ ይቆየን ...
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

2 weeks, 2 days ago

ምናልባት ቤተክርስቲያን ድረስ መውስድ ሚከብዳችሁ ከሆነ
በ0961050205 ደውሉልን እና መጥተን ካላቹበት እንወስዳለን።

2 weeks, 4 days ago

የያዘውን በትር ከእጁ ተቀብለው ራሱን መቱት፤ ነገር ግን የሾኽ አክሊልን በመቀዳጀቱ በምድራችን ላይ የበቀሉትን አሜከላና እሾኽ ርግማንን አጠፋልን፤ ራሱንም በዘንግ በመመታቱ የታላቁን እ ባብ

ሰባቱን ራሶቹን ዐሥሩን
ቀንዶቹን
አጠፋልን) በማለት አስተምረዋል፡፡
ክብር ይግባውና ንጹሐ ባሕርይ ጌታችንን አይሁድ መስቀሉን አሸክመው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ከወሰዱት በኋላ ኹለት ወንበዴዎችን በቀኝና በግራ ጌታችንን በመኻከል አድርገው ሰቅለውታል (ማቴ ፳፯፥፴፰፤ ማር ፲፭፥፳፯፤ ሉቃ ፳፪፥፴፫፤ ዮሐ ፲፱፥፲፰)፡፡ ክፉዎች አይሁድ ይኽነን ያደረጉበት ምክንያት በክፋት ነው ይኸውም በቀኝ የሚመጡ ሰዎች በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው ይኽ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ወንበዴ ነው ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን ይኽስ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ በግራ የሚመጡ ሰዎች በግራ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው ይኽ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ወንበዴ ነው ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን ይኽስ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ ዳግመኛም አነገሥንኽ ብለውታልና ቀኛዝማች ግራዝማች ሾምንልኽ ለማለት ለመዘበት ነው በተጨማሪም ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕ ፶፫፥፲፪ ላይ “ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና” የሚለው ትንቢቱን ሊፈጽም ሲኾን ምስጢሩ ግን በዕለተ ምጽአት እኛን ኃጥኣንን በግራ ጻድቃንን በቀኝ ታቆማለኽ ሲያሰኛቸው ነበር (ማቴ ፳፭፥፴፫፤ ራእ ፩፥፯)፡፡
ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ውስጥ የኸኑት ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳና በርዜዳ ስለዚኽ ነገር ሲገልጹ “ወሰቀልዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል እንዘ ገጹ መንገለ ምሥራቅ ወእዴሁ ዘየማን መንገለ ደቡብ ወእዴሁ ዘፀጋም መንገለ ሰሜን…” (ጌታችን ኢየሱስንም በዕንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉት፤ ፊቱን ወደ ምሥራቅ ቀኝ እጁን ወደ ደቡብ፤ ግራ እጁን ወደ ሰሜን አድርገው ሰቀሉት…ከርሱም ጋር ኹለቱን ወንበዴዎች አንዱን በቀኝ አንዱን በግራው በመኻከላቸው ጌታችን ኢየሱስን አድርገው ሰቀሉ፤ ሕዝቡም ርሱም እንደነርሱ ወንበዴ ነው ይሉት ዘንድ ሰቀሉት፤ ርሱ ግን ወድዶ ከወንበዴዎች ጋር በዕንጨት መስቀል ተሰቀለ፤ ልዑላን መላእክት ፈርተው በፊቱ ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ የሚያደርጉለት ርሱ በሚሰቅሉት ፊት ራሱን ዝቅ አደረገ (ፊልጵ ፪፥፲፤ ራእ ፬፥፲-፲፩)፤
በከሃሊነቱ ሰማይና ምድርን ያጸና ከግርማውም የተነሣ ሰማያትና ምድር የሚንቀጠቀጡለትን ርሱን ደካማ ዕንጨት ተሸከመው (ምሳ ፴፥፬፤ ኢሳ ፵፪፥፭)፤ ርሱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ከራሱ ያስታርቀን ዘንድ ከሰማይ ዝቅ ብሎ ከምድር ከፍ ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ርሱም ስለእኛ በሥጋው በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ከኀጢአታችን ይለየን ዘንድ በቸርነቱ ያድነን ዘንድ ተሰቀለ (፩ጴጥ ፪፥፳፬)፤ ርሱ ግን ሰማያትን ይቀድስ ዘንድ በአየር ያሉ አጋንንትን ያወርዳቸው ዘንድ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ሙሴ አርዌ ብርትን በገዳም እንደ ሰቀለው ርሱም በዕንጨት ላይ ተሰቀለ ፤ በርሱ ያመነ ኹሉ ይድናል እንጂ እንዳይጐዳ የክብር ባለቤት ርሱ ግን ስለ እኛ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ (ዮሐ ፫፥፲፬-፲፭)፤ አውቀውስ ቢኾን የክብር ባለቤት ጌታን ባልሰቀሉት ነበር (፩ቆሮ ፪፥፰)፤ ሰማይ ዙፋኑ ሲኾን ምድርም በእግሮቹ የተረገጠች ስትኾን ስለኛ በዕንጨት ተሰቀለ (ኢሳ ፷፮፥፩)፤ ርሱ ግን ተጠብቆለት ስላለ ስለ ደስታው የመስቀልን መከራ ንቆ አቃልሎ ተቀበለ ኀፍረትንም ናቃት፤ ለተሰቀለው ለርሱ የማይሰግድ ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይኹን (ፊልጵ ፪፥፰-፲፩)፤ ርሱ ግን ስለ ዓለሙ ደኅንነት በማእዝነ ምድር ወደ ላይ ወደ ታች ወደ ግራ ወደ ቀኝ ኾኖ እንደ መጋረጃ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ፤ እኛን ከጻድቃን ጋራ አንድ ያደርገን ዘንድ ርሱ ከበደለኞች ጋር ተቈጠረ) በማለት በስፋት የነገረ ስቅለቱን ምስጢር አስተምረዋል፡፡
በመስቀል ሲሰቀልም በቀኙ የተሰቀለው ጥጦስ በግራ የተሰቀለው ዳክርስ ይባላል፤ በቀኝ የተሰቀለው ጥጦስ ፀሓይ ስትጨልም፣ ጨረቃ ደም ስትኾን፣ ከዋክብት ከብርሃናቸው ሲራቈቱ፣ ድንጋዮች ሲሠነጠቁ፣ መቃብራት ሲከፈቱ፣ ሙታን ሲነሡ፣ የምኩራቡ መጋረጃ ወደ ኹለት ወደ ሦስት ሲቀደድ ሰባቱ ተአምራት ሲደረጉ አይቶ አምላክነቱን ተረድቶ ወደ ርሱ ሲለምን በግራ የተሰቀለው ወንበዴ ሰምቶ “አንተስ ክርስቶስ አይደለኽምን? ራስኽንም እኛንም አድን” ይል ዠመር (ሉቃ ፳፫፥፴፱)፡፡
ያን ጊዜ በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ጌታችን ለቤዛ ዓለም የተሰቀለ እውነተኛ የባሕርይ አምላክነቱን ስለተረዳ በግራ የተሰቀለውን “አንተ እንደዚኽ ባለ ፍርድ ሳለኽ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን? ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይኽ ግን ምንም ክፋት አላደረገም” ብሎ ከገሠጸው በኋላ ኀጢአት ሳይኖርበት የተሰቀለውን ንጹሐ ባሕርይ አምላኩን “ተዘከረኒ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ” (ጌታ ሆይ በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ አስበኝ) እያለ ሲለምነው ጌታችንም “እውነት እልኻለኊ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኾናለኽ” ብሎት ደመ ማኅተሙን ሰጥቶታልና ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በዚኽ መጽሐፉ ላይ፡- “ምስጋና ለአንተ ይገባል፤ የሞትን ፃዕረኝነት (ችንካር) ትሽር ዘንድ ክፋትን የሠራኽ ሳትኾን (ሳትሠራ) በኹለት ሽፍቶች (ወንበዶች) መኻከል የተቸነከርኽ እውነተኛ ኢየሱስ ምስጋና ለአንተ ይገባል” በማለት ንጹሐ ባሕርይ አምላኩን አመስግኗል (ሉቃ ፳፫፥፴፱-፵፫)፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ . . . .

2 weeks, 4 days ago

ይኽ የጌታችን ትሕትና ብዙዎችን አስደንቋል፤ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንትም በቅዳሴያቸው ላይ “በይእቲ ሌሊት አኀዝዎ ወጸቢሖ ረበናተ አይሁድ ወሊቃነ ካህናት ምስለ ጲላጦስ መስፍን ወነበሩ ዐውደ ለኰ
ንኖቱ…” (በዚያች ሌ
ሊት ያዙት.
በነጋም ጊዜ የአይሁድ መምህሮችና የካህናት አለቆች ከገዢው ከጲላጦስ ጋራ ሊፈርዱበት በዐደባባይ ተቀመጡ፤ እንደ ሌባ የኋሊት አሰሩት እንደ የዋህ በግ በፍቅር ተከተላቸው፤ ሊፈርዱበት በዐደባባይ ተቀመጡ፤ የመላእክት ሰራዊት በመፍራት የሚቆሙለትን በፊታቸው አቆሙት፤ ክፉ ባሪያ ርሱን ያልበደለውን ፊቱን በጥፊ ይመታው ዘንድ እጁን አጸና፤ የመላእክት አለቆች በፍጹም ድንጋፄ ለሚሰግዱለት ለርሱ በትዕቢት ይሰግዱ ዘንድ አጐነበሱለት) በማለት ዐርብ ጠዋት አይሁድ ጌታን ወደ ፍርድ ዐደባባይ እንዴት እንዳቀረቡት በስፋት አስተምረዋል፡፡
ጌታ ከመወለዱ አንድ ሺሕ ዓመት አስቀድሞ ጌታችን በንጉሥ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፰ ላይ “ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” በማለት ያናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ጭፍሮች ጌታን ከሰቀሉት በኋላ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ኾኖ በአራት ሲከፋፍሉት ከላይ ዠምሮ ወጥ ኾኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ ያልነበረው እጀ ጠባቡን ደግሞ በመውሰድ ርስ በርሳቸው ለማን እንዲኾን በርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባለዋል፤ ይኽቺውም ቀሚሱ ሰብአ ሰገል ያመጡለት ሲያድግ የምታድግ ዐሥራ ኹለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የነበረችው ሴት የተፈወሰችበት ገባሪተ ተአምራት ነበረች (ማቴ ፪፥፲፩፤ ፱፥፳)፡፡
አይሁድ ይኽነን ማድረጋቸው ለጊዜው “ኹለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል” (ማቴ ፭፥፵) በማለት ኹለት ልብስ አታኑሩ በማለት የሚያስተምረው የርሱ ልብስ ለአራት ቤት ጭፍራ በቃ ለማለት ለመዘበት ሲኾን ፍጻሜው ግን ልብስ የወንጌል ምሳሌ አራት ዕጣ መጣጣላቸው ወንጌል አራት ወገን ኹና ለመጻፏ፤ አለመቅደዳቸው በምስጢር አንድ የመኾኗ፤ አንድም አራቱ ኹሉ ባንዲቱ ዕጣ መጣጣላቸው ወንጌል አራት ክፍል ስትኾን አንድ ሕግ ለመኾኗ ምሳሌ፤ አንድም “አንቅደድ” ማለታቸው ትስብእቱን ከመለኮቱ ሳንለይ እንመን ሲያሰኛቸው ነው በማለት መተርጒማነ ሐዲስ ያመሰጥራሉ (ማቴ ፳፯፥፴፭፤ ማር ፲፭፥፳፬፤ ሉቃ ፳፫፥፴፬፤ ዮሐ ፲፱፥፳፫)፡፡
ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የሚኾን ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ፣ በርዜዳ የሚባሉት በጻፉት የጌታን ሕማማቱን በሚናገረው መጽሐፍ ላይ ይኽነን ሲገልጹ “ወእምዝ አዕተቱ አልባሲሁ ወአልበስዎ ሜላተ ልብስ…” (ከዚያም ልብሶቹን ገፍፈው የመንግሥት ልብስ የሚኾን ነጭ ሐር የካህናት ልብስ የሚኾን ቀይ ሐር ሕብራቸው ቀይና ጥቁር የሚኾን ልብስ አለበሱት፤ የአጣቢ ሳሙና ማንጻት የማይቻለው እንደ መብረቅ የሚያንጸባርቅ እንደ በረድ የኾነ ነጭ ልብስ የሚለብስ ሲኾን፤ ለኪሩቤል የመብረቅ ልብስን ለሱራፌል ግርማ ያለው ልብስን የሚያለብሳቸው ርሱን እንደዚኽ በምድር በመዘባበት ቀይ ሐርና ነጭ ልብስ አለበሱት) በማለት አስተምረዋል፡፡
ልዑል አምላክ ዘመኑ ሲፈጸም ስለሚቀበላቸው ሕማማተ መስቀል አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፮ ላይ “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዙኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፤ ዐጥንቶቼ ኹሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም” በማለት ውሻ ከአፉ ያወጣውን መልሶ ለምግብነት እንዲፈልገው፤ አይሁድም ኦሪትን እለፊ ካላት በኋላ ሲሠሯት በመገኘታቸው በውሻ መስሎ ትንቢት ያናገረባቸው ሲኾን፤ ዳግመኛም ከ፯፻ ዓመት አስቀድሞ በነቢዩ በኢሳይያስም ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ዠርባዬን ለግርፋት ጕንጬንም ለጥፊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም” በማለት ያናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ጌታችንን አይሁድ ገርፈውታል፡፡
አንድም ንጹሐ ባሕርይ ጌታችን መገረፉ ዲያብሎስ የአዳምን ዘባነ ልቡና እየገረፈ ወደ ሲኦል አውርዶት ነበርና ለርሱ ሊክስለት ሲኾን ዳግመኛም በጌታ ላይ አይሁድ የግፍ ድርብ አድርገውበታል በሀገራቸው የሚሰቀል አይገረፍም ነበር በተጨማሪም በኦሪት ልምድ ከአርባ አትርፎ መግረፍ የተከለከለ ሲኾን እነርሱ ግን ፴፱ ጊዜ ከገረፉ በኋላ ቊጥር ተሳሳትን እያሉ ሥጋው ዐልቆ ዐጥንቱ እንደ በረድ ነጭ እስከሚኾን ድረስ ፮ሺሕ ከ፮፻፷፮ ግርፋትን ገርፈው እንደ ብራና ወደዚያና ወደዚኽ ወጥረው ሲሰቅሉት ዐጥንቱ ታይቶ የሚቈጠር ኹኗል፡፡
ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የሚኾን ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ፣ በርዜዳ የሚባሉት በጻፉት የጌታን ሕማማቱን በሚናገረው መጽሐፍ ላይ ይኽነኑ ሲያብራሩ
“ወእምድኅረ አሠርዎ ቀሠፍዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ጲላጦስ ወአርባዕቱ ሐራ በሐብል ወበአስዋጥ መጠነ ፷፻ ወ፮፻፷፮ … ”
(ጌታችን ኢየሱስንም ካሠሩት በኋላ አራት ቤት ጭፍሮችና ጲላጦስ በገመድና ባለንጋ ፮ሺሕ ከ፮፻፷፮ ጊዜ ገረፉት፤ ዐምስት እልፍ ነው የሚሉም አሉ፤ የግርፋቱን ቊጥር እያሳሳቱ ገርፈውታልና፤ የሚሞት እንዳይገረፍ የማይሞት እንዲገረፍ እያወቁ፤ በግፍ ገርፈው በግፍ ገደሉት የተገረፈባቸውም አለንጋና ገመድ በደም ታለሉ፤ ከግርፋቱም ጽናት የተነሣ ሥጋው ኹሉ ዐለቀ፤ ሺሕ ከ፮፻ ከሚኾኑ ቊስሎቹም ወገን ዐጥንቶች ታዩ፤ ጥቁርና ሰማይ የሚመስሉ ቊስሎቹ ግን ሺሕ አንድ መቶ ከዘጠና ናቸው፤ የማይገረፍ አምላክ በዚኽ ሥጋ ተገረፈ፤ ጲላጦስ እጁን ከታጠበ በኋላ ጌታችንን የገረፈው በዦሮ ለሚሰማው በዐይን ለሚያየው ሰው ዕጹብ ድንቅ ነው፤ በመገረፉም አይሁድን ደስ አሰኛቸው፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን በመገረፉ ሰው ኹሉ ከተገረፈባት ኀጢአት ፍዳ አዳነን፤ ስለ ልጆቹና ስለ አዳም መገረፍን መታሠርን ከፍሏልና) በማለት ለኹላችን ካሳ ስለተገረፈው ግርፋት አስተምረዋል፡፡
በነቢዩ ኢሳይያስ ላይ ጌታ ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ዠርባዬን ለግርፋት ጕንጬንም ለጥፊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም” ብሎ ያናገረው ሊደርስ ሊፈጸም ክብር ይግባውና በአምላካችን ፊት ላይ አይሁድ ምራቃቸውን ተፍተውበታል፤ ዳግመኛም ዲያብሎስ ምራቀ ምክሩን እየተፋ ወደ ሲኦል ላወረደው ለአዳም ሊክስለት የማኅበረ አይሁድን ምራቅ ክብር ይግባውና አምላካችን በትዕግሥት ተቀብሎታል፡፡

ይኽ ለካሳ አምላካችን ስለፈጸመው የድኅነት ምስጢር ቅዱሳት ደናግል ሲያብራሩ “አስተቀጸልዎ ከመዝ ለርእሰ ሕይወት አክሊለ ሦክ…” (የሕይወት መገኛ ርሱን የእሾኽ አክሊልን አቀዳጁት፤ መላእክትን የብርሃን ራስ ቁር የሚያቀዳጃቸው የነገሥታት ገዢ የሚኾን ርሱን የሾኽ አክሊል አቀዳጁት፤ በሾኽ አክሊልም ከራሱ ክፍል ያቆሰሉት ሺሕ ናቸው፤ ከራሱም ቊስሎች ደም እንደ ውሃ በዝቶ ፈሰሰ፤ ፊቱም ደምን ለበሰ ሰውነቱም በደም ተጠመቀ፤ የጽዮን ልጆች እናቱ ያቀዳጀችውን አክሊል ተቀዳጅቶ አዩት፤ ተድላ ደስታ የሚያደርግበትና የሙሽርነቱ ቀን ነውና፤ በቀኝ እጁ ዘንግ አስያዙት፤ ሲያሽሟጥጡ በፊቱ እየወደቁ እጅ ነሡለት፤ የመላእክት ሰራዊት እየደነገፁ የሚሰግዱለትን የአይሁድ ንጉሥ ቸር ውለኻል አሉት፤ ሥልጣናትና ሊቃናት እየፈሩ ለሚሰግዱለት ለርሱ በትዕቢት እጅ ነሡት፤
ዐምስት የሚኾኑ መዘባበቻቸውን ከጨረሱ በኋላ በምራቁ ኹለተኛ ዐይኖችን በሚፈጥር በርሱ ፊት ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዳግመኛም ፊቱን በጥፊ መቱት፤ ኪሩቤል ፊቱን ከማየት የተነሣ በእሳት አክናፍ የሚሰወሩት ያልበደላቸውን ርሱን አይሁድ በጥፊ መቱት፤ ፊቱ እንደ መንፈስ ቅዱስና እንደ አባቱ ሲኾን በተዋሐደው ሥጋ ፊቱን ጸፉት ከፊቱ ግርማ የተነሣ ፍጥረቱ ኹሉ የሚርዱለት የሚንቀጠቀጡለት የፈጣሪያቸውን ፊቱን ጸፉት፤ መዠመሪያ በመመታቱና የሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ራሱ የቈሰለ ከመኾኑም በላይ

2 months, 3 weeks ago

❖ ❖ ❖ ኪዳነ ምህረት (የካቲት 16) ❖ ❖ ❖
               ❖ ❖ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ❖
   ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችም እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄዘንድ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ  እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጸውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ሕያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡
   ሌላው በላዔ ሰብ በአማርኛ ሰው በላ ማለት ነው፤ ትክክለኛ ስሙ ግን ስምዖን ይባላል ቅምር በሚባል አገር የሚኖር እጅግ ባለጸጋ ነበር፤ እንደ አብርሃም እንግዶችን እየተቀበለ ድሆችን እየመገበ የሚኖር ጻድቅ ነበር፤ ሰይጣን በዚህ ስራው ቀናበት ሊፈትነውም በሦስት አረጋዊ ሽማግሌዎች ሥላሴ ነን ብሎ ተገለጠለት ልክ እንደ አብርሃም፤ ሐዋርያው ጳውሎስ ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ይመጣል እንዳለ፤ እርሱም ሥላሴ መስለውት ተቀበላቸው ተንከባከባቸውም፤ ምግብ አቀረበላቸው ምግብ አንበላም የምንጠይቅህን ግን ትፈጽምልን ዘንድ ቃል ግባልን አሉት ቃል ገባላቸው እንግዲያውስ የምትወደን ከሆነ አንድያ ልጅህን ሰዋልን አሉት፤ መጀመሪያ ደነገጠ ኃላ አብርሃም ልጁን ሊሰዋ አልነበረምን እኔንም ሊፈትኑኝ ይሆናል ብሎ ለማረድ ተዘጋጀ፤ ተው የሚለው ድምጽ አልሰማም፤ አረደው አወራረደው ይዞላቸው ቀረበ፤ መጀመሪያ ቅመስልን አሉት ቀመሰው ወዲያው እነዚያ ሰዎች ተሰወሩበት እርሱም አህምሮውን ሳተ ተቅበዘበዘ ከዚያ በኃላ ምግብ አላሰኘውም የሰው ስጋ እንጂ መጀመሪያ ቤተሰቦቹን በላ ከዚያም ጓደኞቹን ጦርና የውኃ መንቀል ይዞ ከቤቱ ወጣ ያገኘውን ሰው እየገደለ ይበላል የበላቸው ሰው ቁጥር 78 ደረሰ፤ በመንገድ ተቀምጦ የሚለምን በደዌ የተመታ አንድ ደሃ አገኘ ሊበላው ወደ እርሱ ተጠጋ ግን ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፤ ደሃውም “ስለ እግዚአብሔር ከያዝከው ውኃ አጠጣኝ” አለው “ዝም በል ደሃ” ብሎት አለፈ፤ “አረ በውኃ ጥም ልሞት ነው ስለ ጻድቃን ስለ ቅዱሳን” አለው አሁንም ዝም ብሎት ሄደ ለሦስተኛ ጊዜ “ስለ አዛኝቷ ስለ ድንግል ማርያም” አለው፤ ሰውነቱን አንዳች ነገር ወረረው “አሁን የጠራከውን ስም እስኪ ድገመው ስለ ማን አልከኝ” አለው፤ ስለ አዛኝቷ ስለ እመቤቴ ማርያም አለው፤ ይህቺስ ደግ እንደሆነች በምልጃዋም ከሲኦል እንደምታወጣ ህጻን እያለው እናትና አባቴ ይነግሩኝ ነበር፤ በል እንካ አለው እጁን ዘረጋለት ጥርኝ ውኃ ጠብ አደረገለት ወደ ጉሮሮው አልወረደም የተሰነጠቀ እጁ ውስጥ ገባ እንጂ፤ በለዔ ሰብ ከዚያች ደቂቃ በኃላ አዕምሮው ተመለሰለት እንዲህም አለ “በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብቼ ስለ ኃጢያቴ አለቅሳለሁ ስጋዬ ከአጥንቴ እስኪጣበቅ እጾማለሁ ወዮሊኝ ወዮታም አለብኝ አለ፤ ወደ ዋሻ ገባ ምግብ ሳይበላ ውኃም ሳይጠጣ 21 ቀን ኖሮ በርሃብ ሞተ ይላል ተአምረ ማርያም። ጨለማ የለበሱ ሰይጣናት እያስፈራሩ እያስደነገጡ ነፍሱን ወደ ሲኦል ሊወስዷት መጡ፤ እመቤታችን ፈጥና በመካከላቸው ተገኘች፤ ልጄ ወዳጄ ይህችን ነፍስ ማርሊኝ አለችው እናቴ ሆይ 78 ነፍሳትን የበላ እንዴት ይማራል አላት፤ የካቲት 16 ቀን በጎልጎታ የገባህልኝ ቃል ኪዳን አስብ ስምሽን የጠራ መታሰቢያሽን ያደረገን እምርልሻለው ብለኸኝ የለምን አለችው፤ እርሱም እስኪ ይህቺን ነፍስ በሚዛን አስቀምጧት አለ ቢያስቀምጧት ጥርኝ ውኃው መዝኖ ተገኘ፤ ስላንቺ ስል ምሬታለው ሰባት ቀን ሲኦልን አስጎብኝታችሁ ወደ ገነት አግቧት አላቸው። ቦታሽ እዚህ ነበር እያሉ ሲኦልን አስጎብኝተው ወደ ገነት አገቧት። ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን።
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
በዕለቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚቀርበውን የምስጋና ቃል እንደሚከተለው አቅርበናል መልካም በዓል፡፡
           ❖ ❖ ❖ ዋዜማ ❖ ❖ ❖
ሃሌ ሉያ (፬) ርግብየ ይቤላ በእንተ የዋሃታ፤
በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ፤
እንዘ አመቱ እሞ ረሰያ ፤
ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
          ❖ ❖ ❖ ምልጣን ❖ ❖ ❖
እንዘ ዓመቱ እሞ ረሰያ ፤
ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
        እግዚአብሔር ነግሠ
        እንተ ክርስቶስ በግዕት እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ብሔር፤
        በቤተልሔም አስተብረከት ዕጓለ አንበሳ ግሩመ ወለደት፡፡
           ❖ ❖ ❖ ይትባረክ ❖ ❖ ❖
እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤
ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፡፡
           ❖ ❖ ❖ ሰላም ❖ ❖ ❖
ሃሌ ሉያ (3) ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋትሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤
የሐንፁ አሕዛብ አረፋተኪ በዕንቊ ክቡር፤
ወመሠረትኪ በወርቅ ንጹሕ ይሰግዱ ለኪ ውስተ ገጸ ምድር፤
በእንተ ዕበየ ክብርኪ አምላከ ፳ኤል ውእቱ ረዳኢኪ
ዘአድኀነኪ እምእደ ጸላዕትኪ፤
ወረሰየ ሰላመ ለበሐውርትኪ፡፡
         ❖ ❖ ❖ መልክአ ሥላሴ ❖ ❖ ❖
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፡
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፡
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ፡
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል
          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤
እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፤
ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም፤
ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤
ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ፤
ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡
         ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ;
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪየኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኀኒት ለነፍስ ወሥጋ፤
እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ፤
ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዩ ፍኖተ፤
ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ መድኀኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ፡፡

❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማልዎ በኮከብ፤
ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤
ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ፤
ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ሕሊና ቀዳማይ አብ፤
አመ እምገነቱ ተሰደ በኃዘን ዕፁብ፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ፤
አመ ይሰደድ እምገነት፡፡
          ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት በዓል ❖ ❖

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago