جماعة المدرسة العباسية

Description
🔊→በቡታጀራ ከተማ የሚሰጡ ደርሶች፣ደዕዋዎች፣መልዕክቶች እና አዲስ ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
🔆←{{إِثْبَتْ عَلَى الْحَقْ وَلَوْ كُنْتَ وَحْدَكْ}}
🔆→[[በሀቅ ላይ ፅና ብቻህም ብትሆን]]

ለአስተያየት እና ለጥያቄ
@Alabasiyabot
We recommend to visit

للتواصل @Gggslbot
مرحبا بكم في قناة مسلسلات نتفليكس الاصلية✅
نقوم في نشر اكثر من مسلسل في اليوم
للاعلانات @PpFFBOT

قناتنا الاخرى للافلام? @Qaflam
لطلب المسلسلات✅ @netflix239bot

القناة الرسمية لمسلسل أبو العروسة الموسم الثالث علي تيليجرام?

- بوت تحميل من الأنستا ومن جميع مواقع التواصل الإجتماعي: ✅ .

- بوت التحميل من التيك توك: @EEEBOT

بوت التحميل من الأنستا: @xxzbot

- بوت التحميل من اليوتيوب: @EMEBOT

- ? ? .

- للتمويل: @NNEEN

1 year, 6 months ago

‏عاجل:

‏رؤية هلال رمضان في تمير..
‏وغدا السبت أول أيام رمضان بالسعودية .

1 year, 6 months ago

ረመዷን እና ተውበት

እንደሚታወቀው ታላቁ የረመዷን ወር ሊገባ የተወሰኑ ቀናት ብቻ ቀርተውታል።እናም መቃረቡን አስመልክቶ በተለያዩ አጋጣሚዎች ይህንን ወር ካጠፋናቸው ጥፋቶች ወደ አሏህ በፀፀት ተመልሰን በንፁህ ልብ መቀበል እንዳለብን በሰፊው ትምህቶች ሲሰጡ ይስተዋላል።ይሁን እንጂ እነዚህን ትምህርቶች በቅጡ ያልተረዱ ወንድሞችና እህቶች ስህተቶችን ሲፈፅሙ ይታያል።ከነዚህ ስህተቶች መካከል አንዱን ብቻ ለማሳያነት ልጥቀስ

\  ረመዷን ሲመጣ ሁሉም በሚባል ያህል ሙስሊሙ ኡማ ባለቺው እውቀት ልክ ይዘጋጃል።ከነዚህ ዝግጅቶች መካከል በተውበት ወደ አሏህ መመለስ አንደኛውና ዋንኛው ነው።ነገር ግን ተውበታችን ተውበታችንን በሚያበላሽ እሳቤ( ኒያ) ላይ ተመስርቶ ይታያል።ይህ እሳቤ ምንድነው ካላቹህ ? መልካም !! ነገሩ ወዲህ ነው, ገና ተውበት ስናደርግ ለተውበታችን የመነሻና የመድረሻ ጊዜ ገደብ እናበጅለታለን።

ለምሳሌ፦ አንድ ሶላት የማይሰግድ ሰው ረመዷንን ከዚህ ጥፋቱ ተመልሶ መቀበል ይፈልጋል።ነገር ግን ሶላቱን የሚጀምረው የረመዷን የመጀመሪያው ቀን  ወይም ከሱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ይሆናል፤ይህም ብቻ አይደለም ረመዷን መጨረሻ አካባቢም በነሻጣ የጀመረውን ሶላት አቋርጦ ፆሙን ብቻ ያስቀጥላል። የዚህን ሰው ተውበት ስናይ የተውበትን መስፈርት ያሟላ አይደለም።ምክንያቱም ተቀባይነት ያለው ተውበት በጥቂቱ ሶስት መስፈርቶችን ያሟላ መሆን አለበት።እነርሱም

➊ ተውበት ለማድረግ ከወሰነበት ሰዓት ጀምሮ ከወንጀሉ ተነቅሎ መውጣት

➋ በሰራው ወንጀል መፀፀት

➌ ዳግም ወደዛ ወንጀል ላለመመለስ ቁር፞ጥ ያለ ውሳኔ መወሰን

★ ከላይ ለምሳሌነት ያነሳነው ሰውዬ ግልፅ በሆነ መልኩ የመጀመሪያውንና የመጨረሻውን መስፈርት ያሟላ አይደለም።ምክንያቱም ተውበት ለማድረግ የወሰነው ምናልባት ረመዷን ሳምንት ሲቀረው ይሆናል ነገር ግን ሶላቱን የሚጀምረው ረመዷን ሲገባ ነው።ይህም ማለት ተውበት ለማድረግ ከወሰነበት ሰዓት ጀምሮ ከወንጀሉ ( ሶላቱን ከመተው) አልወጣም ማለት ነው።በዚህ መሰረት የመጀመሪያውን መስፈርት አጓድሏል።ሌላኛው ደሞ ረመዷን ሲወጣ አብሮ ሶላቱንም ይተዋል።ይህ ከሆነ  ደሞ ተውበት ስናደርግ ዳግም ወደዛ ጥፋት ላለመመለስ ቁር፞ጥ ያለ ውሳኔ መወሰን አለበት ብለን ሶስተኛ ላይ ያሰቀመጥነውን መስፈርት ያላሟላ ሆኖ ይገኛል ማለት ነው።ተውበታችን ደሞ ተቀባይነት የሚኖረው ሁሉንም መስፈርት ስናሟላ ነው።ያለበለዚያ ተውበታችን አሁን አፏን ጠርጋ ምንም ሳትቆይ ዳግም ቆሻሻ ለመልቀም እንደመትመለሰው ዶሮ ነውና የሚሆነው ልንጠነቀቅ ይገባል።ሶላቱን ካሁኗ ሰዓት ጀምረን ላለማቋረጥ ወስነን መጀመር አለብን። ለምሳሌ ብለን ሶላትን መተው አነሳን እንጂ ከሌሎችም ጥፋቶቻችን ስንመለስ በዚህ መልኩ መሆን ይኖርበታል።

እናስተዉል!!

ተውበት ማለት ካሳለፍናቸው የወንጀል ቆሻሾቻችን የምንፀዳበት የአዛኙ ጌታችን ትልቅ ስጦታ መሆኑን ማስተዋል ይጠበቅብናል።ተውበት ማድረግ ባይኖር እና በእያንዳንዱ ወንጀላችን አሏህ ቢተሳሰበን  ምን ይውጠን ነበር!? የትስ እናመልጥ ነበር? ስለዚህ ወንድም እና እህቶች የተውበትን ፀጋነት አስተውለን ይህንን ድንቅ የአሏህ ስጦታ እሱ ባዘዘን እንዲሁም መልዕክተኛው ( አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ባሳዩን መልኩ ልንጠቀምበት ይገባል እንጂ እንደ ቀልድ የምናስመልጠው እድል መሆን የለበትም።ከዚህ በተጨማሪ ተውበት ማለት ልክ እንደ ሶላት ፣ ፆም ፣ ዘካና መሰል የሆኑ ኢባዳዎች እራሱን የቻለ ዒባዳ መሆኑን ጠንቅቀን አውቀን በተገቢው መልኩ ልንፈፅመው ይገባል።

በመጨረሻም አሏህ

َّ (وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ)

(ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ ።)
【አል—ኑር 31】

ብሏልና  ይህንን የተከበረውን እንግዳ  አድርሶን ፤ እሱ በሚፈልገው መልኩ ወደሱ በፀፀት ተመልሰው ይህንን ታላቅ ወር የሚቀበሉ እና በውስጡም መልካሙን ሁሉ ገጥሟቸው የውመል ቂያማ በፆማቸው አጅር ምክንያት ከሚደሰቱት ያድርገን ።

አሏሁመ አሚን!!

1 year, 6 months ago

ኮርሱ ነገ ከፈጅር በኃላ ይቀጥላል ...

1 year, 8 months ago
***?*** **ዑዝር ቢል'ጀህል ተከታታይ ሙሐደራ:-**

? ዑዝር ቢል'ጀህል ተከታታይ ሙሐደራ:-

➤  ክፍል 【❶】
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy/822
➤  ክፍል 【❷】
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy/831
➤  ክፍል 【❸】
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy/836
➤  ክፍል 【❹】
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy/696
➤  ክፍል 【❺】
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy/768
➤  ክፍል 【❻】
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy/814

? ይቀጥላል -ኢንሻ አሏህ-!!!

?አቡ ዒምራን
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy

1 year, 9 months ago

ውድ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ (Freshman) ሙስሊም ተማሪዎች

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
  እንደሚታወቀው በ2017 ዓ.ል በአላህ ፍቃድ ወደ ግቢ መግቢያ ቀናችሁ ህዳር 26 እና 27 ነው ።

ስለሆነም ይህን በማስመልከት የወልቂጤ  ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ሙስሊም ወንድምና እህቶቹን ተቀብሎ ማንኛውንም ዲናዊም ሆነ አካዳሚክ  መረጃዎችን  ለመስጠት እና ለመተባበር በጉጉት እየጠበቅናችሁ እንገኛለን፡፡
ስለዚህ ስለሚያስፈልጋችሁ ማንኛውም አይነት ጥያቄም  ይሁን ትብብር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስልኮች ደውላችሁ ሙሉ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
1,አንዋር ሁሴን
ስ'ቁ +251931797988
2,ቢላል ሺከታ
0968510115(የእህቶችን ቁጥር ለምትፈልጉ በዚህ ቁጥር ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።)
አላህ በሰላም ያገናኘን።

Kabajamtoota barattoota muslimaa sirreeffamaa haaraa Yuunivarsiitii Wolqiteetti ramadamtan hundaa!!
            Assalamu Alaikum Warahmatullahi Wobarekathu
Barattoota muslimaa sagantaa sirreeffamaatiin Yuunivarsiitii Wolqiteetti haaraa ramadamtan hundaaf, barattoonni sirreeffamaa Wolqiteetti ramadaman ta'uu beekuu barbaanna University in the year 2017 will enter on November 26 and 27, 2017. A.D. jedhamuun beekama....so,for those who speak oromiffa language and need any information related to WkU,you can contact;

Our brother REMEDAN S.

Lakk 09 16 45 35 31
?????

https://t.me/Wku_ms_Official_Channel

1 year, 9 months ago

1ኛ፦ ዑለማኦቹ ዝም እንዳሉ ምን አሳወቃችሁ? እናንተ ካላወቃችሁ ደጋፊ ናቸው ነው የሚባለው? ዘመኑ የኢንተርኔት ነው ቢቃወሙ እናገኘው ነበር የሚል አይቻለሁ። በዚህ መልኩ ከደነ -ቆረ አካል ጋር መግባቢያው ሩቅ ነው። ለማንኛውም ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
مَنْ أَرَادَ أَنْ يَنْصَحَ لِذِي سُلْطَانٍ فَلَا يُبْدِهِ عَلَانِيَةً، وَلَكِنْ يَأْخُذُ بِيَدِهِ فَيَخْلُو بِهِ، فَإِنْ قَبِلَ مِنْهُ فَذَاكَ وَإِلَّا كَانَ قَدْ أَدَّى الَّذِي عَلَيْهِ
"ለባለስልጣን መምከር የፈለገ ሰው ባደባባይ አያውጣው። ነገር ግን እጁን ይዞ ገለል አድርጎ ይምከረው። ከተቀበለ እሰየው። ካልሆነ ግን ያለበትን አደራ ተወጥቷል።" ሸይኹል አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። (አንዱ ሐይሠሚ ዶዒፍ ብለውታል እያለ ገፅ ጠቅሶ ሲዋሽ አይቻለሁ። ቦታው ላይ የሌለ ቅጥፈት።)

እናንተ ስላላያችሁ ብቻ ዑለማኦች ዝም እንዳሉ ነው የምታስቡት? እንዲህ አይነቱ ጥያቄ ሶሐቢዩ ኡሳመቱ ብኑ ዘይድ ላይ ተነስቶ ነበር። "ለምን ዑሥማንን ገብተህ አታናግርም?" ሲሏቸው እንዲህ ነበር ያሉት፦
إِنَّكُمْ لَتُرَوْنَ أَنِّي لاَ أُكَلِّمُهُ إِلَّا أُسْمِعُكُمْ، إِنِّي أُكَلِّمُهُ فِي السِّرِّ دُونَ أَنْ أَفْتَحَ بَابًا لاَ أَكُونُ أَوَّلَ مَنْ فَتَحَهُ
"እናንተ ካላሰማኋችሁ በስተቀር እንደማላናግረው ነው የምታስቡት። እኔ የሸር በር ከፋች ሳልሆን በሚስጥር አናግረዋለሁ፤ የመጀመሪያው ከፋች አልሆንም።" [አልቡኻሪይ፡ 3267] [ሙስሊም፡ 2989]

ኢብኑ ዐባስም የሃገር መሪን በመልካም ስለ ማዘዝና ከመጥፎ ስለ መከልከል ሲጠየቁ "የግድ የምታደርገው ከሆነ ባንተና በሱ መሀል ይሁን።" [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይበህ፡ 7/470] [ሹዐቡል ኢማን፣ በይሀቂይ]

ይሄ ነብያዊ መንገድ፣ ይሄ የሶሐቦች አካሄድ የኢኽዋንና የኸዋ - ሪጅ በቀቀኖች ዘንድ የመድኸሊያ እምነት ነው። ሐዲሦቹንና ኣሣሮቹን አትፍቋቸው እንግዲህ። ዑለማኦቹ የናንተን ክስ ፈርተው ነብያዊውን አስተምህሮት ጥለው የሰካ.ራም ህግ ይከተሉ ወይ? እነዚህ የኢኽዋን መንጋዎች ድንቁ -ርናቸውን ንቃት ያደረጉ የመሀይማን መንጋ ናቸው። ፕሮፌሰሩ ከተራው ሰው አይለይም። ጭንቅላት ከሆድ የከበረ አካል ነው። ይሁን እንጂ ጭንቅላት አንድ ከሆድ የሚያንስበት ነገር አለው። ባዶ ሲሆን አይናገርም። ሳይነቃ እንደነቃ ያስባል። በዚህ ጉዳይ ላይ ንቃት ያለው በነሱ ጩኸት ውስጥ ይመስላቸዋል። ግና ንቃት ያለው በዑለማእ አካሄድ ውስጥ ነው። ኢብኑል ቀዪም እንዲህ ይላሉ፦
"ረቂቅ ከሆኑ ማስተዋሎች ውስጥ የሆነው የአዛዥን ስህተት ባደባባይ አለመመለስህ ነው። ስልጣኑ ስህተቱን ለመርዳት እንዲያነሳሳው ያደርገዋልና። ይሄ ሁለተኛ ስህተት ነው። ነገር ግን ሌሎች በማያስተውሉበት ሁኔታ ተለሳልሰህ አሳውቀው።" [አጡሩቁል ሑክሚያህ፡ 1/103]
"መድኸሊይ" በሏቸው እሳቸውንም።

2ኛ፦ "የሳዑዲ መንግስት ሐቅ የሚናገሩ ዓሊሞችን ይገድላል፣ ያስራል" ትላላችሁ አይደል? ያ ከሆነ ዓሊሞቹ ዝም ለማለት በቂ ምክንያት አላቸው ማለት ነው። ሸሪዐው የሚለው "መናገር ያልቻለ ሰው በልቡ ይጥላ" ነው።
3ኛ፦ በቱርክ፣ በኢራን፣ በሙርሲ አስተዳደር ወቅት ስለተከሰቱ ጥፋቶች ዝም ያሉ አልፎም አድናቂ የሆኑ ምሁራኖች ላይ ለምን ተመሳሳይ ክስ አላነሳችሁም? ጩኸታችሁ በተለየ የሱና ዑለማኦችና ሰለፊያ ላይ የሚሆነው ለምንድነው?
4ኛ፦ ቡድናዊ ጥላቻ አስክሯችሁ እንጂ እውነት እናንተ ኢስላምን የሚያጠለሹ ጥፋቶች ላይ በመናገር ምን የረባ ታሪክ አላችሁ? "የበደዊ ቀብር ላይ በያመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ሺርክ ሲፈፅም አልአዝሀር ዩኒቨርሲቲ የታለ? የኢኽዋን መሪዎች ለምን ዝም ይላሉ? ነው ወይስ የቀብር አምልኮ ሺርክ ከጭፈራ ያነሰ ጥፋት ነው? በነ ገኑሺ የኢኽዋን አስተዳደር ላይ የቀይረዋን ዩኒቨርሲቲ፣ የቱኒዚያ ምሁራን፣ እናንተን ጨምሮ ምን አደረጋችሁ?ሱኒዮችን በመጨፍጨፍ፣ በኣሉል በይት ላይ ድንበር በማለፍ ሺርኪያት ከሚፈፅሙ፣ ሶሐቦችን ከሚያወግዙ ሺዐዎች ጋር ህብረት የመሰረተው የነ ቀርዷዊ ማህበር ተመሳሳይ ዘመቻ ተከፍቶበታል ወይ? ዐሊይን ጨምሮ ብዙ ታላላቆችን የሚያከ - ፍሩት ኢባዲያ ኸዋ -ሪጆች ከነ ቀርዷዊ ማህበር ውስጥ የታቀፉ ናቸው። የኢባ .ዲያው ሙፍቲ አሕመድ አልኸሊሊ የማህበሩ ምክትል ነው። በሱና ዑለማእ ላይ እየጮኸ ያለው የሺ0፣ የሱፊያ፣ የኢኽዋን፣ የኸዋ .ሪጅ ጭፍራ እዚህ ሰፈር ድምፁን አያሰማም። "ሙፍቲ" ዑመር ጠቅላዩን "መለይካ ይመስላል" ሲል ይሄ አሁን የሚጮኸው መንጋ ትንፍሽ አላለም። አደም ካሚል ጠቅላዩን ከታላላቅ ነቢያት በላይ አድርጎ ሲያወድስ የኢኽዋን መንጋ ያሰማው ተቃውሞ የለም። የት ነበራችሁ? ከዑለማኦቻችን ላይ እጃችሁን አንሱ። ምላሳችሁን ሰብስቡ። ኢንሻአላህ እናንተን እርቃናችሁን ለማስቀረት የሚሆን አቅም አናጣም።
5ኛ፦ ደግሞስ ሃሜት ተፈቀደ እንዴ? የተረጋገጡ ጥፋቶችን ስናስጠነቅቅ የዑለማእ ነውር እየተከታተሉ የምትሉ አይደላችሁምን? ታዲያ ምነው መርሃችሁን ለቃችሁ ያውም በሌሉበት ዑለማኦችን ታጠለሻላችሁ? ቀርዷዊ ዘፈን ሲፈቅድ፣ አጅነቢያ ሴት ሲጨብጥና መጨበጥን ሲፈቅድ፣ ዲሞክራሲ ከኢስላም ነው ሲል፣ ሰይድ ቁጥብ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ሲያስተባብል፣ ሶሐባ ሲሳደብ፣ ህዝብ ሲያከ - ፍር፣ "ሙፍቲ" ዑመር በሙስሊሞች ላይ ጠላት ሲቀሰቅስ፣ ... እስኪ የተቃወማችሁበትን አሳዩን? ጭራሽ ለምን ተነኩ ብላችሁ አይደለም ወይ የምትጮሁት? የቢድዐ ቁንጮዎች ላይ ስንናገር ሃሜተኛ፣ ዑለማእ ተሳዳቢ ስትሉ አልነበረም ወይ?

ፅሁፌን ሳጠቃልል ሰዑዲያ ውስጥ በሚፈፀም ጥፋት ሁሉ ሰለፊያን ተጠያቂ የሚያደርጉ ደናቁ - ራን ናቸው። ቱርክ ከሰዑዲያ የበለጠ ከኢስላም የራቀች ናት። ነገር ግን ቱርክ ውስጥ የሚፈፀሙ ጥፋቶችን ወደ ሱፊያም፣ ወደ ኢኽዋንም አያስጠጉም። የሰለፊያ መንገድ ዘፈንና ጭፈራ አይደለም ከዚህ ያነሱ ነገሮችን ያወግዛል። የሱና ዑለማኦች አቋም ለወዳጅ ቀርቶ ለጠላት የሚታወቅ ነው። ዘፈን የሚፈቅዱት እነ ቀርዷዊ ናቸው። ሲኒማ ለማየት ሶላት ጀምዕ ያደረጉት፣ የፈረንጅ ዳንስ እየከፈሉ የተማሩት እነ ዑመር ቲልሚሳኒ ናቸው፣ የኢኽዋን ሶስተኛ ሙርሺድ። ሺርክን ዲን አድርገው የሚዋጉለት ኢኽዋንና ሱፊያ ናቸው።
ለማንኛውም ኢብኑ ሰልማን ወይም ቱርኪ አሉሸይኽ የሰለፊያ ዓሊሞች አይደሉም። የተከሰተውን ጥፋትም የሰለፊያ አቋም ነው ብለው አላቀረቡም። እነሱ ላይ የሚታይን ሁሉ ወደ ሰለፊያ የሚያስጠጋ አካል በነ ኤርዶጋን፣ በነ ዑመር አልበሺር፣ በነ ቱራቢ፣ በነ ገኑሺ፣ በነ መሃቲር ፖለቲካ ሁሉ ኢኽዋንና ሱፊያ ሲከሰስ ሊቀበል ይገባል። እንዲያውም ከፖለቲከኞቹ አልፎ የነ ሐላጅ፣ ቢስጧሚ፣ ኢብኑ ዐረቢ፣ ኢብኑል ፋሪድ፣ ኢብኑ ሰብዒን፣ ቲልሚሳኒ፣ የነ ቀርዷዊ፣ ኩፍ - ሪያት ሲነገሩ የምትጮሁ እንደሆናችሁ እናውቃለን። ገዛሊና የምታስተዋውቁት ኪታቡ ኢሕያእ ዑሉሙዲን ብዙ ሙንከራት የያዘ እንደሆነ የራሱ ተማሪዎች ጭምር የተናገሩት ነው። የሱና ዑለማእ ላይ የምትሰነዝሩትን ሩብ ያህል እንኳ እዚህ ላይ አትናገሩም። ይልቁንም እንዲህ አይነቱ እውነት መነገሩ ነው የሚያበሳጫችሁ። ስለዚህ የፖለቲከኛን ጥፋት ሰለፊያ ላይ ሊደፈድፍ የሚነሳን አካል የራሱ ቡድን ቁንጮዎችን ጠማማ አካሄድ ምን እንደሚመስል አፍንጫውን ይዘን ልንግተው እንገደዳዋለን።

1 year, 10 months ago

ትክክለኛዉ የልብ ደስታ ሚገኘዉ አላህን በመያዝ ነዉ ።
… ዘመን ተሻጋሪ መረጋጋት ምናገኘዉም በተዉሂድ ላይ ቀጥ ስንል ብቻና ብቻ ነዉ።
አሁን አሁን አብዛሀኞቻችን የደስታችን ሰበብ አርገን የያዝናቸዉ ብዙ ነገሮች ከዉስን ጌዜ ቡሇላ የነፍስ ስቃይ አዉርሰዉን ነዉ ሚሸሹት…
ግድ የለንም አንድዬዉን እንያዝ አናፍርበትም… የመልክተኛዉን መንገድ መንገዳችን ይሁን ደስታ ይቀርበናል።

ግድ የላቹም የዲን ስብእናችን እናሳድግ

https://t.me/ALABASIYA

1 year, 10 months ago

الشيخ عبد السلام الشويعر
ድንቅ ምክሮች የያዘ መልክት ነዉ
https://t.me/ALABASIYA

1 year, 11 months ago

**بكاء شديد من الشيخ
عبد الرزاق البدر - حفظه الله-

بعد تذكره نعمة التوحيد**

https://t.me/abuUseyminabdurehman

2 years, 2 months ago

? የክረምት የተማሪዎች ኮርስ ?

? የመድረሰቱል አባሲያ ጀማዓ ለዚህ ሁለት ወር (ሀምሌ እና ነሀሴ) በተለመደው መልኩ ለልጆች የኮርስ ፕሮግራም አዘጋጅቱዋልⵆ

? የኮርሱ ሂደት፡-

  1. ቃዒደቱል ነውራንያ ( አጣርቶ ማንበብ )
  2. የተለያዪ አጫጭር ( ረሳዒል ) ኪታቦችን ( ማስገንዘብ )

? አድራሻ፡- መድረሳ(ዑስማን መስጂድ) የሴቶች መግብያ አጠገብⵆ ክፍል ተራ ቁጥር 1 እና 2

❗️ማሳሰብያ፡-

  1. ለልጆ የሚሰጠው የምዝገባ ፎርም በአግባቡ እንዲሞሉ እናሳስባለንⵆ
  2. ለትምህርት ጥራት እንዲያመች የምዝገባ ዋጋ በተማሪ 200 ብር መሆኑ በአክብሮት እንገልጻለንⵆ
  3. ከ ቅዳሜ ቀን 29/10/2016 ምዝገባ ተጀምሮ እስከ ሰኞ ቀን 1/11/2016 ምዝገባ ምናጠናቅቅ ይሆናል፡፡
  4. ከማክሰኞ 2/11/2016 እስከ ሀሙስ 4/11/2016 ምዝገባ ከ100ብር ቅጣት ጋር የምንቀበል ሲሆን ከነዚህ ቀናቶች ቡሀላ በማንኛውም ምክንያት ተማሪ አንቀበልም፡፡
  5. ተማሪው ብያንስ 7 አመት የሞላው መሆን አለበት፡፡
  6. በሰዓቱ ለተመዘገቡ ተማሪዎች በአላህ ፍቃድ በዚህ ሁለት ወር ስኬታማ የሆነ ትምህርት እንደሚቀስሙ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

? “የሰው ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣልⵆ ሶስት ነገራቶች ሲቀሩ፡-
1. መልካም ልጅ ዱዐ ሚያደርግለት
2. ቀጣይነት ያለው ሰደቃ
3. ሰው የሚጠቀምበት እውቀት” ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)ⵆ

ለአስተያየት ወይም ለጥያቄ ፡-
0902912413
0972014889

We recommend to visit

للتواصل @Gggslbot
مرحبا بكم في قناة مسلسلات نتفليكس الاصلية✅
نقوم في نشر اكثر من مسلسل في اليوم
للاعلانات @PpFFBOT

قناتنا الاخرى للافلام? @Qaflam
لطلب المسلسلات✅ @netflix239bot

القناة الرسمية لمسلسل أبو العروسة الموسم الثالث علي تيليجرام?

- بوت تحميل من الأنستا ومن جميع مواقع التواصل الإجتماعي: ✅ .

- بوت التحميل من التيك توك: @EEEBOT

بوت التحميل من الأنستا: @xxzbot

- بوت التحميل من اليوتيوب: @EMEBOT

- ? ? .

- للتمويل: @NNEEN