📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc
?ጥቆማ ከኢብኑ ሙነወር 【አሏህ ይጠብቀዉና】
ጥቂት ነጥቦች ለመጅሊስ
(በየትኛውም እርከን ላይ ላላችሁ ሁሉ!)
~
1- መቼም ኃላፊነታችሁ ላይ ሁሌ እንደማትቆዩ የሚታወቅ ነው። ስለሆነም እስካላችሁ ድረስ በኢኽላስ መስራት ላይ አደራችሁን። ለኢትዮጵያ ሙስሊም የምትውሉት ትልቁ ውለታ ዐቂዳውን መጠበቅ ነው። ስለዚህ በተውሒድ ላይ ከልብ ሆናችሁ ብትሰሩ መልካም ነው፣ አላህ ያግዛችሁና። ከአሕ -ባሽ ይጠበቅ ዘንድ መሬት የረገጠ ስራ ቢሰራ። በራሳችሁ ባይመቻችሁ በየ አካባቢያችሁ ሌሎች እንዲሰሩት ብታመቻቹ። በአዲስ አበባ አንዳንድ ሰፈሮች ላይ ማህበረሰቡን ባገለለ መልኩ መስጂዶች በአሕ - ባሽ በብቸኝነት እንዲያዙ የተደረጉበትን ስህተት ቢስተካከል። በዚህ ላይ ጣልቃ የሚገቡ ሰዎችን ጥግ እንዲይዙ ቢደረግ።
2- ለመስጂድ መስሪያ የተሰጡ ቦታዎች እንደምንም ብላችሁ ግንባታ እንዲካሄድ ብታደርጉ። የፖለቲካው ንፋስ ሲቀያየር ምን እንደሚመጣ አይታወቅም። የመስጂድ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ መስሪያ ቦታዎችን መጠየቁ ሊጠናከር ይገባል።
3- በፌደራልና በአዲስ አበባ መጅሊስ የሚናፈሱ አሉባልታዎችን ብተቆጣጠሩ። ወሬ የሚያናፍሱ አካላትን ማራቅ ይገባል። እስከ መቼ ነው የማህበራዊ ሚዲያ አጀንዳ የምትሆኑት? እንዲሁ እየፈጠሩ እያወሩ ከሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም።
4- አንዳንድ በመጅሊስ አመራሮች ሚዲያ ላይ የሚቀርቡ ንግግሮች የሚያሳቅቁ ናቸው። አድማጭን የሚያሳቅቅ ወይም ከዲን ጋር የሚጋጭ ንግግር ከሚወጣ ወይ ቀድሞ መዘጋጀት አልያ ፅፎ ማንበብ ይሻላል።
5- ከፌደራል ጀምራችሁ በየትኛውም ክልል ያላችሁ እባካችሁን ዘረኝነት ላይ አጥብቆ መስራት ይገባል። ለመስጂድ ኢማምነት ብሄር የሚታይባቸው አካባቢዎች አሉ። ይሄ በጣም ደስ የማይል ነገር ነው። ሳዑዲ እርስ ቤት ውስጥ በአስከፊ ሁኔታ ላይ ያሉ ወገኖቻችን በዘር ተቧድነው እየተደባደቡ ነው። መላ ብትፈልጉ። በክልሎች በዘር ግጭት እየተጎዱ ላሉ ወገኖች ለሌሎች በሚታይ መልኩ ከጎናቸው ብትቆሙ ጥሩ ነው። በዚህ ላይ ህዝብ ማስተባበር ይገባል።
6- በመጨረሻም የሸይኽ ዐብዱ ግድ.ያ ምርመራው ምን ላይ እንዳለ ብታሳውቁ መልካም ነው። ጉዳዩ እንደ ዋዛ ችላ ተብሎ የቀረ ይመስላል። ምናልባት ትኩረት ተነፍጎት ከሆነ ብታስቡበት መልካም ነው።
አላህ በኢኽላስ የምትሰሩ፣ ለተውሒድ የምትቆረቆሩ ያድርጋችሁ። ኣሚን።
?https://t.me/murselseid
መዉደቅ ማለት መሞት ማለት አይደለምና አንድ ጊዜ ከወደቅኩ በቃ አይሳካልኝም ማለት ነዉ የሚል እሳቤ እንዳይኖርህና ከትጋትህ እንዳትገታ አደራ!!
ለታላላቅ ስኬቶች የበቁ ብዙ ሰዎችን ታሪክ ብታስተዉል መነሻቸዉ ላይ ብዙ ጊዜ ወድቀዉ ነበር።
ደጋግመህ ሞክር አንድ ቀን ይሳካል አብሽር!!
?አመስጋኝ ባሪያ ሁን አታብዛ ወቀሳ
?ለስኬት አይበቃም ወድቆ ያልተነሳ
?ከዉድቀትህ ተማር ይቅር ማማረሩ
?ተዘግቶ አያዉቅም የአረህማን በሩ
✍ሙርሰል ሰይድ ጨፌ 29/11/2016
?https://t.me/murselseid
ከኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመጣውን የእርዳታ ቁሳቁስ ለጎፋ ዞን አተዳደር አስረከቡ።
..
(ሐሩን ሚዲያ፦ሐምሌ 25/2016፣ደቡብ ስቱዲዮ)
..
በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሸቻ ጎዝዴ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የእርዳታ የምግብና የመጠለያ ቁሳቁስ ከክቡር ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ እና ከስራ አስፈጻሚውቻቸው በመረከብ በደቡብ ኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሃጂ ያሲን ከድርእና ከጎፍ ዞን እስልምና ጉዳይ ስራ አስፈጻሚዎች በጋር በመሆን ለጎፋ ዞን አስተዳደር ያስረከቡ ሲሆን
.
ሶስት ሺህ ቆርቆሮ፣ 200 ኩንታል ዱቄት፣ 95 ፓኬት ሚስማርና 400 ማንጠፊያ ጂባ እና 100 ፍራሽ በአጠቃላይ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የእርዳታ ቁሳቁሶች ለዞኑ አስተዳደር አስረክበዋል።የእርዳታ ቁሳቁሱንም ካስረከቡ በኋላ ወደ ኪንቾ ሸቻ ጎዝዴ ቀበሌ ድረስ በማምራት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች አጽናንተዋል።
.
ይህ ድጋፋችን የመጀሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም በማለት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቁቋም በሚደረገው ስራ የኢትዮጲያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤትም ሆነ የክልሉ እ/ጉ/ከፍተኛ ም/ቤት ከጎፋ ዞን መንንግስት ጎን እንደሚቆም የደቡብ ኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሃጂ ያሲን ከድ አረጋግጠዋል።
.
ላደረጋችሁልን ድጋፍና ሀዘናችን ስለተጋራችሁን በጎፋ ዞን ህዝብና መንግስት ስም እናመሰግናለን በማለት ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
.
በፌደራል መጅሊሱ ፕሬዘዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው ልዑክ ያመጣውን የእርዳታ ቁሳቁስ ለደቡብ ኢትትዮጲያ ክልል የመንግስት ኃላፊዎች ማስረከባቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው።
©ሀሩን ሚዲያ
?https://t.me/murselseid
አልሀምዱ ሊላህ‼‼️
የአምባሰል ወረዳ የ02 ቀበሌ የጭሳና አካባቢዉ መጅሊስ ተዋቀረ።
?በትላንትናዉ ዕለት ሐምሌ 23/11/2015 ዓ/ል የአምባሰል ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የ02 ቀበሌ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን በአባጂበን መስጂድ ግቢ ዉስጥ በመገኘት 25 የቀበሌ መጅሊስ ጉባኤተኞችን አስመልምሎ 7 የስራ አመራሮችን በማስመረጥ እጅግ የተሳካ ስራ ሰርቷል።
በዚህም መሰረት
1—ሸይኽ ሀሰን ኑርዪን ፕሬዝዳንት
2—ሸይኽ አህመድ ጫላን ም/ፕሬዝዳንት
3—ወንድም ሁሰይን መላኩን ዋና ፀሀፊ
4ㅡሸይኽ ሙሀመድ ዘይንን አዉቃፍ ዘርፍ ተጠሪ
5—ሸይኽ ሙሀመድ ጌታሁንን የደእዋ ዘርፍ ተጠሪ
6—ሸ/ሙሀመድ ፈንታዉን አደረጃጀት ዘርፍ ተጠሪ
7—ሸ/ሁሰይን ኑርዪን እርቅና ሰላም ዘርፍ ተጠሪ
አድርጎ ማስመረጡ ታዉቋል።
ሱመልሀምዱ ሊላህ!!
ይቀጥላል
?https://t.me/ambaselweredaeslmnagudayohce
Telegram
የአምባሰል ወ/እ/ጉ/ም/ቤት ቻናል
አላማችን የወረዳችንን ህዝበ ሙስሊም ከባእድ አምልኮ እንድርቅና ተዉሒድን አጥብቆ እንድይዝ በማድረግ ቁርአናዊና ሀዲሳዊ አስተምህሮቶችን መግቦ በሀቅ ላይ ብቻ አንድ ማድረግ ነዉ።
አልሀምዱ ሊላህ‼‼️
የአምባሰል ወረዳ የ03 ቀበሌ መጅሊስ ተዋቀረ።
?በትላንትናዉ ዕለት ሐምሌ 21/11/2015 ዓ/ል የአምባሰል ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የ03 እሮቢት ቀበሌ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን የቀበሌዉ ሴንተር በሆነችዉ የመድረሳ መስጂድ ግቢ ዉስጥ በመገኘት 27 የቀበሌ መጅሊስ ጉባኤተኞችን አስመልምሎ 7 የስራ አመራሮችን በማስመረጥ እጅግ የተሳካ ስራ ሰርቷል።
በዚህም መሰረት
1—ኡስታዝ ኡስማን ይመርን.ፕሬዝዳንት
2—ሸይኽ አብዱ ሙባረክን ም/ፕሬዝዳንት
3—ወንድም ሰይድ ፈንታዉን ዋና ፀሀፊ
4ㅡቶ አስናቀ ይመርን አዉቃፍ ዘርፍ ተጠሪ
5—ወንድም አንዋር ኢድሪስን የደእዋ ዘርፍ ተጠሪ
6—አቶ ጉማታዉ ትኩን አደረጃጀት ዘርፍ ተጠሪ
7—አቶ መንግስቴ ሹመቴን እርቅና ሰላም ዘርፍ ተጠሪ
አድርጎ ማስመረጡ ታዉቋል።
ሱመልሀምዱ ሊላህ!!
?https://t.me/ambaselweredaeslmnagudayohce
Telegram
የአምባሰል ወ/እ/ጉ/ም/ቤት ቻናል
አላማችን የወረዳችንን ህዝበ ሙስሊም ከባእድ አምልኮ እንድርቅና ተዉሒድን አጥብቆ እንድይዝ በማድረግ ቁርአናዊና ሀዲሳዊ አስተምህሮቶችን መግቦ በሀቅ ላይ ብቻ አንድ ማድረግ ነዉ።
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc