★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks, 1 day ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago
**❌*?የአህያ ሥጋ ብበላ ምን ችግር አለው?*
?መምህር ኃይለማርያም
*❓ወደ አፍ እሚገባ እንዴት ያረክሳል❓ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ?*
4 ነገር ግን ከሚያመሰኩት፥ ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው ከእነዚህ አትበሉም ግመል ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።https://t.me/KIRSTOSIYESUS ⛪ማኅበረ ቅዱሳን ጠበል ጸዲቅ መርሃ ግብር??????**
“ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሠላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሠላም፡፡”“
ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ”
እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላምና በጤና አደረሰን መልካም በአል ❤️❤️
አስተያየት
ግን.. ግን.. በየከተማው አደባባይና በየመንገዱ የሚደረገው የጎዳና ላይ ስብከት ከመጠን ያለፈ፣ ከተገቢነትም የተሻገረ፣ ከትክክለኛነትም በተቃራኒ እየተጓዘ አይመስላችሁም..? ማንም ሰው እምነቱን በፈለገ መንገድ የመግለፅና ለሌላው የማስተዋወቅ መብት እንዳለው አምናለሁ። ይህ ግን ቆመንለታል ከሚሉት ዓላማ፣ ከሌላው ወገን መብትና ክብር እንዲሁም ከአካባቢ ጸጥታ አንጻር መገምገም ይኖርበታል። አሊያ ዘርፈ ብዙ ችግር እንዳያሰከትል ያሠጋል።
የጎዳና ላይ ሰባኪዎች ዓላማቸው ኢየሱስን መስበክ፣ ለሌሎች ወገኖችም የሕይወትን መንገድ ማመላከት ከሆነ በቅድሚያ ሰው እንዲሰማቸው ማድረግ ነበር የሚጠበቅባቸው። ተግባራቸው ግን ተቃራኒውን ነው የሚመስለው። ጥረታቸው በጎዳና ከሚያልፈው የራሳቸው ወገን አሜንታ ፍለጋ አሊያም በአለቆቻቸው እንደ ጀግና ለመቆጠር ከሆነ ከአዳራሾቻቸው መውጣት አያስፈልጋቸውም። አቢይ ምክንያታቸው ሌላው ሰው ላይ መድረስ ከሆነ ግን በትንሹ አክብሮትና የለዘብታ ቃል መገለጫቸው መሆን አለበት። እንደሚታወቀው ብዙው ሰው እርጋታ የተሞላበት የፍቅር ቃል እንጂ ጩኸት አይሰማም። ጯኺዎች ራሳቸውን እንደ ወንጌል ሰባኪ ቢቆጥሩም አላፊ አግዳሚውን እያደነቆሩት እንጂ እየሰበኩት እንዳልሆነ ቢያውቁት መልካም ነው። ለዚህም አነስተኛ ጥናት ቢሠሩ ደግ ነበር። በእርግጥ እዚያ አካባቢ በስሜት እንጂ በጥናት የመመራት ነገር የሚታሰብ አይደለም።
ብዙ ሰው በተግባራቸው ከመበሳጨቱ የተነሳ የሚጠሩትን ክቡር ስም እንዳያሰድቡ ይጠነቀቁ ዘንድ የሚያሳስባቸው ቢኖር እንዴት ደግ ነበር..? የአንዳንዶቹ ሰባኪያን ሁኔታ ደግሞ ይገርማል። ወንጌል በእልህ ይሰበክ ይመስል እየተንቀጠቀጡ ወጪ ወራጁ ላይ ሲጮሁ የውስጣቸውን የሰላም እጦት ሕዝቡ ላይ ለማራገፍ የሚጥሩ ነው የሚመስሉት። በቀደምለት ሜክሲኮ ጋር በተመሳሳይ እልህ ሲሰብክ የነበረ ወጣት ከጠቀስኩት ነገሮች ሁሉ አልፎ ሄዶ ፀብ ጫሪ ጩኸት ሲያሰማ ነበር። ከጩኸቱ ውስጥ "... ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት... የትኛውም ሃይማኖት አያድንም፤ የሚያድነው ኢየሱስ ነው... በሃይማኖት ገመድ የተተበተባችሁ ስሙ.. ሃይማኖታችሁ አያድናችሁም" የሚል ይገኝበታል። ከንግግሩ ጋር የድምፁ መጠንና የሚታይበት እልህ የጥላቻውን መጠን ያሳያል። ብዙ መንገደኞች እየተሳደቡ፣ ሌሎችም መሰላቸታቸውን በምልክት እየገለጡ ሲያልፉ ነበር።
ይህ ድርጊት በዚሁ ከቀጠለ ሩቅ ባልሆኑ ቀናት ውስጥ የፀብና የአምባጓሮ መነሻ እንደሚሆን መገመት ስህተት አይሆንም። ስለሆነም የሚመለከተው አካል መፍትሄ ሊያበጅለት ይገባል። የተረጋጉና ጨዋ ፕሮቴስታንቶችን ስለዚህ ጉዳይ እንዲመክሩ ማሳሰብ ጠፍቶኝ አይደለም። ሆኖም ግን እንዳለመታደል ሆኖ በዚያ ክበብ ውስጥ ምክር ቀርቶ ውግዘት የሚገታው እንቅስቃሴ እንደሌለ የታወቀ በመሆኑ ነው ያለፍኩት። ይህን አስተያየት "የክርስቶስ ስም እንዳይነገር" የተሠጠ አድርጋችሁ የምትቆጥሩ ወፈፌ ጴንጤዎች ካላችሁ ግን መልሴ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነትና ምሥክርነት እንጂ ጩኸት ወንጌል ሆኖ አያውቅም የሚል ነው። ካስፈለገም የአስቄዋ ልጆችን ድርጊትና ውጤት አስታውሳችኋለሁ። የጌታ የኢየሱስ ስም የተከበረው እነርሱ ስሙን እየጠሩ በመጮኻቸው ሳይሆን አጋንንት ያደረበት ሰው ስለዘለለባቸው፣ ቆስለውም ራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ ስለበረታባቸውና ስላሸነፋቸው ነው (ሐዋ፡19፥14-17)። እናም በቃሉ ላይ መራቀቁን ትታችሁ ይሄን የዕብድ ድርጊት አስቁሙ አሊያም በልክ አርጉት..!።
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks, 1 day ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago