★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago
ሰው ጨካኝ ሲሆን #እግዚአብሔር ግን ሁሉን የሚወድ ቸርና ርህርህ ነው፡፡ ለዚህም ነው ንጉስ ዳዊት ከሦስቱ ቅጣቶች መካከል አንዱን እንዲመርጥና አማራጩ ሲቀርብለት የተናገረው ቃል ድንቅ ነው፡፡ " ምህርቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ በሰው እጅ ግን አልውደቅ፡፡" 2ኛ ሳሙ 24 ፥ 14፡፡ ጻድቁ እዮብም በሦስቱ ባልደረበቹ እጅ በወደቀ ጊዜና እነርሱም እርሱን መውቀሳቸውን ባላቋረጡ ጊዜ እንዲህ ነበር ያላቸው ፡- "ነፍሴን የምትነዘንዙ በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው? ይኸውም ስትሰድቡኝ አሥር ጊዜ ነው፡፡" ኢዮ 19 ፥ 2 - 3፡፡ #እግዚአብሔር ግን ከሰው በእጅጉ በተለየ መልኩ መሐሪና ርህርህ መሆኑን በሚከተሉት ውስጥ እንመለከታለን፡፡
?
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።
በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።
ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5
የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።
በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።
ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27
በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።
በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።
?
ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።
ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።
አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።
በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9
(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)
?
የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን።
?
" ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና "
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
✝ የርኩሳን መናፍስት ስብስብ
በሰይጣን የሚመሩት ርኩሳን መናፍስት ንስሓ በገቡትና በአማኞች ላይ ስለሚከፍቱት ውጊያ ዕቅድ ለማውጣት ይወያዩ ዘንድ ጉባኤ ተቀመጡ ። በዚህ ጊዜ ሊቀ መንበሩ አማኞችን ሊያጠፋ የሚያስችል እጅግ አዲስ ዕቅድ እንዲያቀርቡ አባላቱን ጠየቀ ።
አንደኛው ርኩስ መንፈስ እንዲህ አለ : " #የእግዚአብሔርን ሕልውና እንዲጠራጠሩ እናድርጋቸው ። "
ሁለተኛው " መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጠራጠሩ እናድርጋለው ። " አለ ።
ሌላኛው ደግሞ " ዘላለማዊነትን እንዲጠራጠሩ እናድርጋቸው ። " አለ ።
አራተኛው " በምኞትና በፈተናዎች እናታላቸው ። " ብሎ ተናገረ ።
እነዚህን የሚሙስሉ አሳቦች ከየአቅጣጫው መወርወራቸው ይቀጥል እንጅ ሊቀ መንበሩን አንዱንም አሳብ ሊያጸድቅ አልፈለገም ፤ ሁሉም የቆዩና ከዚህ በፊት #የተጠቀሙባቸው_ዕቅዶች_ነበሩና ። ሁሉም እርግጠኛ የሆኑ ውጤቶች ሊያቀርቡ ስላልቻሉ ብዙ ሰዎች ከእነርሱ እያመለጡ ወደ እምነት ጎራ መግባት ቻሉ ።
አንድ የሚሻል ልምድ ያለው ርኩስ መንፈስ የሰው ልጆችን ሊያጠፋ የሚችል አንድ አዲስ እና ስኬታማ ዕቅድ ለማዘጋጀት ኃላፊነቱን ከወሰደ በኋላ እንዲህ በማለት ተናገረ ፦ " ስለ #እግዚአብሔር ሕልውና ፤ ስለ መጨረሻው ፍርድ እውነትነት ፤ ስለ ዘላለማዊው ቅጣት ፤ ስለ ገነትና ስለ ሲዖል መኖር መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር ሁሉ ትክክለኛ እና እውነት መሆኑን አጉልተን እናሳያቸው ። ከዚህ በተጨማሪ ንስሓ አስፈላጊና መቅረት የማይገባው ጉዳይ መሆኑንም እናሳያቸው ..." በዚህ ጊዜ እያንዳንዱ ርኩስ መንፈስ እጅግ በቁጣ ተሞልቶ ንግግሩን ከመጨረሱ በፊት አቋረጡትና ዕቅዱን በውግዘት ውድቅ አደረጉበት ። ተቃውሞአቸው እጅግ መራር ነበር ።
በዚህ ጊዜ ሊቀ መንበሩ ርኩስ መንፈሱ እቅዱን ገልጾ እስኪጨርስ ድረስ እንዲረጋጉ ምልክት ሰጣቸው ።
ይህን ተንኮል አዘል አሳብ ያቀደው ርኩስ መንፍስ ንግግሩን እንዲህ በማለት ቀጠለ ፦ " እነዚህን ነገሮች በሙሉ ለሰው ልጆች እጅግ አጉልተን ስናሳያቸው ከእኛ ጋር ተደላድለው መኖር ይጀምራሉ ፤ በምክራችንም ይታመናሉ ። በዚህ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ ንስሓ የሚያደርሷቸውን ቀና እርምጃዎች መራመድ ሲጀምሩ ንስሐቸውን ለጥቂት ጊዜ ምናልባትም እስከ ነገ ድረስ እንዲያቆዩት እናድርጋቸው ። ይህን የምናደርገውም ኃጢአትን እስከሚሰናበቱትና ፍላጎታቸውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያረኩ ነው ። በዚህ መንገድ ንስሓ ለመግባት ከተዘጋጁ በኋላ እስከ ነገ ድረስ እናቆየው እያሉ ይቆያሉ ። በመጨረሻም ቀናቶቻቸው ስለሚጠናቀቁ ንስሓ የመግባት ዕድሉን ከነጭራሹ ያጡታል ። "
እያንዳንዳቸው ብድግ ብለው ርኩሱ ጥበቡን በማድነቅ አጨበጨቡለት ። ታውቃላችሁ? ! ከዚያን ጊዜ በኋላ ሰዎች በቡድንም ሆነ በነጠላ በኃጢአት መውደቅ ስለ ጀመሩ መጨረሻ ወደሌለው ጥልቅ ጉድጓድ ይወድቁ ጀመር ። ይህ ሊደርስባቸው የቻለውም #በእግዚአብሔርና በመጽሐፍ ቅዱስ ወይም በዘላለማዊነት ስላላመኑ አይደለም #ንስሓ_የመግባት_ዕድሉን_ካገኙት_በኋላ_ለነገ_በማለት_ስላዘገዩት_እንጂ ።
ወንድሜ ሆይ ፦ እንዲህ ያለውን አጭበርባሪ ወጥመድና አረመኔያዊ ብልጠት ተጠንቀቀው!! " ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ. .." [ዕብ 47 ] የሚለውን የመጽመፍ ቅዱስ ቃል በውስጥህ ሸሽግ ።
አንተ ዛሬ ልትሞት ስለምትችል ንስሓህን እስከ ነገ ድረስ አታዘግየው ።
ወይም ደግሞ ነገ ሊመጣ ቢችልም ባተሌ ልትሆንና ብዛት ባላቸው ነገሮች ልትወጠር ትችላለህ ። ወይም ደግሞ ነገ ልብህ ሊደነድንና የመንፈስን አነሳሽነት ልታጣው ትችላለህ ።
ለንስሓ እጅግ ተመራጩ ጊዜ አሁን ነው ፦ " በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳን ቀን ረዳሁህ ይላልና ፤ እነሆ ፦ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው እነሆ ፦ የመዳን ቀን አሁን ነው ። " [ 2ኛ ቆሮ 62]
ንስሓ ትገባ ዘንድ #እግዚአብሔር አምላክ ጸጋውን ያድልህ ።
አባት ዘካርያስ ቡትሮስ እንደጻፉት
ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ #እግዚአብሔርም በፍጥረታቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር በዝምታ ይሠራል። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው #የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሰራ አድርገው ያስባሉ። እነርሱ #እግዚአብሔር አይሰራም በሚያስቡበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ በጥልቅ እየሰራ ነው። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ #የእግዚአብሔርን ሥራና የስራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይነቻቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል።" #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብህም ይጽና #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፡፡" መዝ 26 ፥ 14።
†እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ራሱን በራሱ ያጎሳቁል ለነበረው ወጣት ያደረገችው ተአምርና የሰጠችው ምክር †
ራስን በራስ ማጎሳቆል የዚህ ዘመን ትልቁ ፈተና ነው፡፡ ብዙ ወጣቶች በዚህ ሱስ ይያዛሉ፡፡ ወደ ትዳር ገብተው ራሱ ከዚህ ሱስ መውጣት አቅቷቸው ከትዳር አጋራቸው ጋር የተገባ ሩካቤን የማይፈጽሙ ቊጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች ንስሓ መግባት ራሱ ያሳፍራቸዋል፡፡
እስኪ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ክሪሶስቶሞስ (አፈ ወርቅ) የተባሉ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ራሱን በራሱ ያጎሳቁል (Masturbate ያደርግ) ስለ ነበረ አንድ በዓሥራዎቹ ዕድሜ ስለሚገኝ ወጣት የጻፉትን ላካፍላችሁ፡-
“አንድ ወጣት አንድ ጊዜ የሚከተለውን ነገረኝ፡፡ በዓሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያለ ለስፖርቶች በተለይም ለትግል ልዩ ፍላጎት ነበረው፡፡ ወደ ዓሥራ አምስት ዓመቱ ገደማም አንድ የቡድን ጓደኛው ራስን ስለ መበደል ኃጢአት አስተዋወቀው፡፡ ከማፈሩ የተነሣም ንስሓ አልገባም ነበር፡፡ አንድ ቀንም ከአንድ ወር በኋላ ከታላቅ ወንድሙ ጋር እየታገሉ እያለ በወንድሙ ደረት ላይ ዘፍ ብሎ ወደቀ፡፡ መተንፈስ አልቻለም፡፡ ሞተ፡፡
“በዚህ ውስጥ ኾኖም የገዛ አስከሬኑን፣ ወንድሙና እናቱ ተደናግጠው እርሱን ለመርዳት ሲሯሯጡ፣ ነፍሱ ደግሞ በጠባቂ መልአኳ ታጅባ ከቤቱ ስትወጣ፣ ከሚኖርበት ከተማም እጅግ ከፍ ብላ በመጨረሻም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ስትኼድ ይመለከት ነበር፡፡ ከዚያም ጥልቅ በኾነ ጨለማ ውስጥ ራሱን አገኘው፡፡ ከዚያ አልፎም መጨረሻ ላይ ብርሃንንና ገነትን ተመለከተ፡፡
“ወደዚህ ብርሃን እንደ ገባም ወላዲተ አምላክን አያትና ጠባቂ መልአኩን ለምን እንደ አመጣው ጠየቀችው፡፡ መልአኩም የልጁን አሟሟት በዝርዝር ነገራት፡፡ በዚህ ጊዜ እመቤታችን ለዚያ ልጅ ‘ትድንላት ዘንድ እናትህ አጥብቃ እየለመነቺኝ ነው፤ ልጄም ጸሎቷን ሰምቷል” አለቺው፡፡ ያ ልጅ ግን በገነት ውበት ስለ ተማረከ በዚህ ይቆይ ዘንድ ለመናት፡፡ ወላዲተ አምላክ ግን ‘አይኾንም' አለቺው፡፡ ‘ለእናትህ ስትል መመለስ አለብህ፡፡ ነገር ግን አድምጠኝ፡- ከአንድ ወር በፊት ስለ ሠራኸው ኃጢአት ልትናዘዝ ይገባል፡፡ ይህ እጅግ አስጸያፊ ኃጢአት ነው፡፡ ይህን ለካህን ካልተናዘዝክ፥ ምን እንደሚያገኝህ ተመልከት፡፡' ከዚህ በኋላ ወላዲተ አምላክ የሲዖል ሥቃይ ምን እንደሚመስል እንዲያሳየው ለቅዱስ ሚካኤል አዘዘችው፡፡ የሚመለከተው ነገር እጅግ የሚያስፈራ ከመኾኑ የተነሣ፥ ልጁ ራሱን እስከ መሳት ደረሰ፡፡
“ከዚያ በኋላም ወደ ጥልቁ ጨለማ፣ ቀጥሎም ወደ ሰማያት፣ ዝቅ ብሎም ይኖርበት ወደ ነበረ ከተማ - ወደ መኖሪያ ቤቱ - ቤተሰቦቹ አስከሬኑን ከብበው ወደሚያለቅሱበት ክፍል ወረደ፡፡ በሰውነቱ ላይ ከፍተኛ የኾነ መጫጫን ከተሰማው በኋላም ነፍሱ ወደ ቦታዋ ተመለሰች፤ ዓይኖቹንም ከፈተ፡፡ ከዚያም የኾነውንና የተመለከተውን ኹሉ ለቤተሰቦቹ ነገራቸው፡፡ በኀዘን ተጎድታ የነበረችው እናቱም ይህን በሰማች ጊዜ እመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ ስላማለደቻት አመሰገነቻት፡፡ እጅግ እያለቀሰችም ልጇን ዕቅፍ አድርጋ ሳመችው፡፡”
ፈጣኗ ደመና ወላዲተ አምላክ በዚህ ሱስ ውስጥ ያሉትን ኹሉ ከዚህ በደል ይወጡ ዘንድ ትድረስላቸው፡፡
✝በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ #እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ !!
#እግዚአብሔርን ከወደዳችሁት ትጸልያላችሁ ። አብዝታችሁ የምትጸልዩ ከሆናችሁ ከቀን ወደ ቀን ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረና እየጠለቀ ይሄዳል ። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው ምክንያቱም አንድ ሰው ከወደዳችሁ ከእርሱ ጋረ መነጋገርን ትወዱታላችሁና ። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጸሎት ነው ።
በመጸለይ እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ ። ለማለት የፈለግሁት ወደ እርሱ ፍቅር በሚመራችሁ መንገድ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ ለማለት ነው ።
በእናንተም ቢሆን እንዲሁ ነው ይበልጥ #ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገራችሁ ስትመጡ አንደበታችሁ ይበልጥ ከእርሱ ጋር መነጋገርን እየለመደ ይመጣል ። ከዚህ በኋላ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር መነጋገርን ታውቃላችሁ ።
✝መስጠት ወይም ልግስና ትእዛዙን ሟሟላት ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ "እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና።" /2ቆሮ 9፥7/ እንዲል። #እግዚአብሔር የምትሰጠውን ገንዘብ ሳይሆን የመጀመሪያውን ፍሬ እና ቃል ኪዳን የሆነውን ከማዕረጎች ሁሉ የሚልቀውንና ያለ ነቀፋ በነፃነት የሚሰጠውን ፍቅር ከአንተ ይጠብቃል።
ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ የመጀመርያ ፍሬ ነው። ስለዚህ ጌታ የኤፌሶንን ቤተ ክርስቲያን በነቀፋ ንሥሓም እንዲገባ በጠራው ጊዜ ነቀፋውን የተወሰነ ኃጢአትን በመግለጽ ሳይሆን በአንድ ሐረግ አጠቃልሎ "ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።" /ራዕ 2፥4/ በማለት ነው።
#እግዚአብሔር ይህንን ፍቅር ይፈልጋል ስለዚህ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።" /ምሳ 23፥26/ አለ። ትእዛዙን መፈጸም የፍቅር ተፈጥሮአዊ ፍሬ ነው።
ውጪያዊ የንሥሓ ሕይወት ብቻ የሚኖሩ ነገር ግን ውስጣዊ ፍቅር የሌላቸው ይወድቃሉ። ምክንያቱም ሥራዎቻቸውና #ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት ፍቅር የጎደለው ነውና።
#መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሕግ ማንኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው መልስ "ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፣ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርሷም ባልጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትል ናት። ኦሪትና ነቢያት በነዚህ በሁለቱም ትእዛዛት ጸኑ።" /ማቴ 22፥36-40/ የሚል ነበር።
በዚያን ቀን ብዙዎቹ "ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም በስምህ አጋንንት አላወጣንም?" /ማቴ7፥22/ ይሉታል። ነገር ግን እርሱ ይህን ሁሉ ትቶ በውስጣቸው ስላለው ፍቅር ይጠይቃቸዋል።
ይህ የተአምራት እና የስጦታዎች ችግር አይደለም፣ ባሏቸው በተሰጡአቸው ስጦታዎች የተነሳ የሚጠፉ ብዙዎች ናቸውና። ለዚያ ነው ሐዋርያት ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ባወሩ ጊዜ ሁሉ ይህንን ከሁሉ ይልቅ በተሻለ መንገድ አብራርተውታል።
✝መስጠት ወይም ልግስና ትእዛዙን ሟሟላት ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ " #እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና ።" /2ቆሮ 9*7 / እንዲል ። #እግዚአብሔር የምትሰጠውን ገንዘብ ሳይሆን የመጀመሪያውን ፍሬ እና #ቃል_ኪዳን የሆነውን ከማዕረጎች ሁሉ የሚልቀውንና ያለ ነቀፋ በነፃነት የሚሰጠውን #ፍቅር_ከአንተ_ይጠብቃል ።
ፍቅር #የመንፈስ_ቅዱስ የመጀመርያ ፍሬ ነው ። ስለዚህ ጌታ የኤፌሶንን ቤተ ክርስቲያን በነቀፋ ንሥሓም እንዲገባ በጠራው ጊዜ ነቀፋውን የተወሰነ ኃጢአትን በመግለጽ ሳይሆን በአንድ ሐረግ አጠቃልሎ " ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና ። " / ራዕ 24 / በማለት ነው ።
እግዚአብሔር ይህንን ፍቅር ይፈልጋል ስለዚህ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ ።" / ምሳ 2326 / አለ ። #ትእዛዙን_መፈጸም_የፍቅር_ተፈጥሮአዊ_ፍሬ_ነው ።
ውጪያዊ የንሥሓ ሕይወት ብቻ የሚኖሩ ነገር ግን ውስጣዊ ፍቅር የሌላቸው ይወድቃሉ ። ምክንያቱም ሥራዎቻቸውና #ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት ፍቅር የጎደለው ነውና ።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሕግ ማንኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት ? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው መልስ " ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ፣ ታላቂቱና ፊተኛይቱ #ትእዛዝ_ይህች_ናት ። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርሷም ባልጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትል ናት ። ኦሪትና ነቢያት በነዚህ በሁለቱም ትእዛዛት ጸኑ ። " / ማቴ 22*36-40/ የሚል ነበር ።
በዚያን ቀን ብዙዎቹ " ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም በስምህ አጋንንት አላወጣንም ...? " /ማቴ7*22/ ይሉታል ። ነገር ግን እርሱ ይህን ሁሉ ትቶ በውስጣቸው ስላለው ፍቅር ይጠይቃቸዋል ።
ይህ የተአምራት እና የስጦታዎች ችግር አይደለም ፣ ባሏቸው በተሰጡአቸው ስጦታዎች የተነሳ የሚጠፉ ብዙዎች ናቸውና ። ለዚያ ነው ሐዋርያት ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ባወሩ ጊዜ ሁሉ ይህንን ከሁሉ ይልቅ በተሻለ መንገድ አብራርተውታል ።
✝ ሁል ጊዜ ሕሊናህን በመንፈሳዊ ነገሮች ሙላ !!
ይህን የምታደርግ ከሆነ ዲያብሎስ መጥፎ አሳብ ሊያስተዋውቅህ ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህ የሚለው ሕሊና አያገኝም። እንደ መከላከያ መፍትሔ ይሆንህ ዘንድ ዘወትር ራስህን በሥራ ባተሌ አድርግ። ዲያብሎስ ወደ እርሱ ገብቶ የወደደውን ዘር እንዳይዘራበት ሕሊናህን ባዶ አታድርገው።
መንፈሳዊ ንባብ ሕሊናን በሥራ ለመጥመድና መጥፎ አሳቦችን ለማራቅ ብቻ ሳይሆን ሌላም ታላቅ ጥቅም አለው። ንባብ ሕሊናን በተመስጦ ሊሞላ የሚችል መንፈሳዊ ዘዴ ከመስጠቱም በላይ ተቃዋሚ አሳቦችን የሚያጠፋውንና #እግዚአብሔርን መውደድ የሚያስችለውን ስሜት በልብ ውስጥ ያጎናጽፋል።
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago