Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net

Description
“እውነት ለሁሉ” በዓለም ዙርያ በሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ክርስቲያኖች የተመሠረተ ድረ-ገፅ ሲሆን እስልምናንና ክርስትናን የተመለከቱ መጣጥፎችን፣ መጻሕፍትን፣ ዜናዎችንና የመሳሰሉትን ያስነብባል፡፡ የኦዲዮና የቪድዮ መረጃዎችንም ያቀርባል፡፡ የበለጠ ለማወቅ http://www.ewnetlehulu.org ይጎብኙ።
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 Wochen, 2 Tage her

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 Tag, 13 Stunden her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 Monate, 2 Wochen her

1 month, 1 week ago

♦️ ኪሩቤል በሰማይ ለጌታ ለኢየሱስ ይሰግዳሉ!

ከራዕይ 5:8 የምንረዳው እውነት ይህ ነው። በሰማይ ኪሩቤል ለጌታ ለኢየሱስ ይሰግዳሉ። መጽሐፉን ከአባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከወሰደ በኋላ በመታረዱና የሰውን ልጅ በመዋጀቱ ምክንያት ኪሩቤል ለበጉ ሰግደውለታል። ይህ እጅግ አስገራሚና አስደናቂ ነገር ነው። ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት የሚነግረን ነገር አለ።

ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው፥ ሰማያዊያን ፍጥረታት ወይም መላእክት የሚሰግዱት ለእግዚአብሔር ነው፦

"ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ #መላእክቱ ሁሉ፥ #ስገዱለት።"
(መዝሙረ ዳዊት 97:7)

"አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ፤ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጥረሃል፥ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፤ #የሰማዩም_ሠራዊት ለአንተ #ይሰግዳሉ።"
(መጽሐፈ ነህምያ 9:6)

➣ ይህም ሀቅ በዚያው በራዕይ መጽሐፍ የተረጋገጠ ሀቅ ነው። መላእክት የሚሰግዱት ለእግዚአብሔር ነው፦

" #መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑና በሽማግሌዎቹ በአራቱም እንስሶቹ ዙሪያ ቆመው ነበር፤ በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው #ተደፉ#ለእግዚአብሔርም #እየሰገዱ።"
(የዮሐንስ ራእይ 7:11)

በተለይም ደግሞ በራዕይ 5:8 ላይ በበጉ ፊት የወደቁት አራቱ እንስሳት (ኪሩቤል) ለማን እንደሚሰግዱ በዚያው በራዕይ መጽሐፍ ተረጋግጧል። ኪሩቤል የሚሰግዱት ለእግዚአብሔር ነው፦

"ሀያ አራቱም ሽማግሌዎችና #አራቱ_እንስሶች በፊታቸው #ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው #ለእግዚአብሔር። አሜን፥ ሃሌ ሉያ እያሉ #ሰገዱለት።"
(የዮሐንስ ራእይ 19:4)

✍️ የመጽሐፍ ቅዱሱ ትምህርት ግልፅ ነው። መላእክት በተለይም ኪሩቤል የሚሰግዱት ለእግዚአብሔር ነው። በራዕ 5:8 ላይ ግን ለበጉ ሰግደውለታል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?

ኪሩቤል ለታረደው በግ ሊሰግዱ የቻሉት በጉ ጌታችን ኢየሱስ የተሰገወው እግዚአብሔር በመሆኑ ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ በወንጌሉ ላይ ቃል እግዚአብሔር እንደነበር (ዮሐ 1:1) በኋላም ስጋ እንደሆነ (ዮሐ 1:14) በመንፈስ ቅዱስ ጥንሳሴ ነግሮናል። ይህንኑ ትምህርት በመልእክቱ ላይም ደግሞታል። እርሱም ልጁ ጌታ ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ (1ዮሐ 5:20) ደግሞም በስጋ እንደመጣ (1ዮሐ 4:2) ተናግሯል። ይህንኑ የታመነ ትምህርት ደግሞ በራዕዩ በድጋሚ እየገለፀ ነው። ጌታ ኢየሱስ አልፋና ኦሜጋ ፊተኛውና ኋለኛው እንደሆነ (ራዕ 1:17-18 ራዕ 22:13-16) ነገር ግን ምን አልፋና ኦሜጋ ቢሆንም ሕጻን ሆኖ እንደተወለደ (ራዕ 12:5) በራዕዩ ተመልክቷል። ስለዚህ ይህ ክርስቶስ ሰው ሆኖ የተወለደው/የተሰገወው አምላክ በመሆኑ የታረደ፥ ደሙን ያፈሰሰ ቢሆንም በሰማይ ከኪሩቤል ስግደትን የሚቀበል አምላክ ነው።

ለዚህ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ መላእክት ሁሉ ለእግዚአብሔር ልጅ እንደሚሰግዱ በመንፈስ ቅዱስ ጥንሳሴ የጻፈው፦

"ደግሞም #በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ። የእግዚአብሔር #መላእክት ሁሉም ለእርሱ #ይስገዱ ይላል።"
(ወደ ዕብራውያን 1:6)

ልክ በራዕ 5:8 እንዳየነው በዕብ 1:6 ላይም መላእክት ለእግዚአብሔር ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሰግዳሉ። ምክንያቱም ሰማይና ምድርን የሰራው (ዕብ 1:10) አባቱ አለማትን የፈጠረበት (ዕብ 1:2) ፍጥረት ሲለወጥ የማይለወጠው (ዕብ 1:11-12) የክብሩ ነጸብራቅና የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ፥ ሁሉን በሃያል ቃሉ ደግፎ የያዘው (ዕብ 1:3) በግርማው ቀኝ የተቀመጠ (ዕብ 1:3 ዕብ 1:13) ከመላእክት እጅግ የሚበልጥ (ዕብ 1:4) ኃጢአታችንን ያነጻ (ዕብ 1:3) ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ (ዕብ 1:8) እና ጌታ (ዕብ 1:10) በመሆኑ ነው። ለዚያ ነው ልክ እንደ ራዕ 5:8 በዕብ 1:6 ላይም መላእክት ሁሉ ለእርሱ የሰገዱት። ይህ ግልፅ የሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ነው።

እናም ከራዕ 5:8 ካስገረሙኝና ላካፍላችሁ ከወደድኩት እውነታዎች ዋነኛው ይህኛው ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ በኪሩቤል የሚሰገድለት አምላክ ነው። ክብር ለስሙ ይሁን! እኛም ከኪሩቤልና ከመላእክቱ ጋር ሆነን ይህን ንጉስና እናመልከዋለን። አምልኮ፥ ውዳሴ፥ ሃይል፥ ክብር፥ ምስጋና፥ በረከት፥ ስግደት፥ ሞገስ፥ ንግስና፥ ልዕልና፥ ጌትነት፥ ግዛት፥ መፈራት፥ ብርታትና እልቅና ለታረደው በግ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ልጅ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን!

✏️ ከክርስትና ውጪ ላሉ ወገኖቻችን (በተለይ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ልጅ የጌታ ኢየሱስን አምላክነት አያስተምርም ለሚሉ ወገኖች) ጥያቄ፦

1) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኪሩቤል በሰማይ የሚሰግዱት ለማን ነው?

2) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኪሩቤል የሰገዱለት ፍጡር አለ?

3) ክርስቶስ ኢየሱስ በስጋ የመጣው መለኮት ካልሆነ ኪሩቤል በሰማይ እንዴት ሊሰግዱለት ቻሉ?

✍️ በማሰረጃ እንድትመልሱልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ

▶️ ይቀጥላል

1 month, 1 week ago

የሆነ ጊዜ ላይ የራዕይን መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር። በሰአቱ እውቁ ዐቃቤ እምነት ሳም ሻሙን ያን መጽሐፍ እያስተማረ ስለነበር መጽሐፉን በጥንቃቄ ከመጀመሪያው ጀምሮ ማንበብ ጀመርኩ። እጅግ በጣም የሚያስገርም መጽሐፍ ነው። በእውነቱ የእግዚአብሔር ቃል ሁሌም አዲስና ተዝቆ የማያልቅ ሀብት ነው። ስለ ቃሉ የቃሉን ባለቤት አመሰግናለሁ

እናም በዚሁ የዮሐንስ ራዕይ ንባቤ ላይ አንድ ክፍል ትኩረቴን ሳበው። ከዚህ በፊት አንድምታውን አስተውዬው አላውቅም ነበር። በኋላ ላይ ግን ክፍሉን ሳጠናው ትርጉሙ እጅግ በጣም አስገራሚና አስደናቂ እንደሆነ ተረዳሁ። እናም ላካፍላችሁ ወደድኩ።

ክፍሉ እነሆ፦

"መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ #አራቱ_እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች #በበጉ ፊት #ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።"
(የዮሐንስ ራእይ 5:8)

በዚህ ክፍል ላይ የእግዚአብሔር በግ የሆነው ጌታ ኢየሱስ ሰባቱ ማህተሞች ያሉበትን መጽሐፍ ከአባቱ ከእግዚአብሔር አብ በወሰደ ጊዜ በሰማይ የሆነውን ነገር እናነባለን። እንደሚታወቀው የራዕይ መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝጊያ ስለሆነ፥ በውስጡ የሚያካትታቸው ስዓላዊ ትዕይንቶች (imageries) በሙሉ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ የተብራሩና የተገለጹ ናቸው። ጌታ ኢየሱስም በበግ የተመሰለው ለዚሁ ነው። የአለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ መሆኑ በሌላው መጽሐፍ ተገልጿልና (ዮሐ 1:29) ስለዚህ በዚህም ክፍል ላይ የተባሉትን ነገሮች መረዳት ያለብን ከሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር በማሰናሰል ነው።

በራዕይ 5:8 ላይ በጉ መጽሐፉን በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በፊቱ እንደወደቁ እናነባለን። ከዚያም እያንዳንዳቸው በገናን እና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ እንደያዙ ተገልጾ እንመለከታለን። ሐዋርያው ዮሐንስ ያያቸው እነዚህ ነገሮች በሙሉ አስገራሚና አስደናቂ ትርጉም አላቸው። በዚህ ክፍል ላይ የተነገሩት ነገሮች በሙሉ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት የሚናገሩት ነገር አለ። አንድ በአንድ ለመመልከት እንሞክር

✍️ አራቱ እንስሳት ማናቸው?

ሐዋሪያው ዮሐንስ በራዕዩ እንደተመለከተው በራዕይ 5:8 ላይ በጉ መጽሐፉን ከወሰደ በኋላ ከሀያ አራቱ ሽማግሌዎች ጋር ሆነው በፊቱ የወደቁት አራቱ እንስሳት ናቸው። እነዚህ አራቱ እንስሳት ማናቸው?

ሐዋሪያው ዮሐንስ በራዕይ መጽሐፉ ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህን አራት እንስሳት የተመለከታቸው በምዕራፍ አራት ላይ ነው። ሐዋሪያው የሚያየው ይህ ራዕይ በሰማይ ውስጥ የሚሆን ክስተት ሲሆን (ራዕ 4:2) እነዚህን እንስሳት ሲያያቸው በእግዚአብሔር ዙፋን መካከልና ዙሪያ ነበሩ፥ በፊትና በኋላም ዓይኖች ሞልተዋቸው ነበር (ራዕ 4:6 ራዕ 4:8) መልካቸውም የፊተኛው የአንበሳን፥ ሁለተኛው የጥጃን፥ ሶስተኛው እንደ ሰው ያለ፥ አራተኛው ደግሞ የንስርን ይመስል ነበር (ራዕ 4:7) ከዚያም ባለፈ አራቱም እንስሶች ስድስት ክንፎች ነበሯቸው (ራዕ 4:8)

▶️ ሐዋርያው ዮሐንስ በዚህ ራዕዩ ያያቸው እንስሳት ነቢዩ ሕዝቅኤል በራዕዩ ያያቸው ኪሩቤል ናቸው። የሕዝቅኤል መጽሐፍን ስናጠና ነቢዩ ሕዝቅኤል በራዕይ አይቷቸው የገለጻቸው ኪሩቤል ሐዋርያው ዮሐንስ በራዕዩ ያያቸው እንስሳት መሆናቸውን እንረዳለን።

ነቢዩ ሕዝቅኤል ልክ እንደ ሐዋርያው ዮሐንስ የእግዚአብሔርን ራዕይ ባየ ጊዜ (ሕዝ 1:1 ዮሐ 1:1) የአራት እንስሳትን አምሳያ ይመለከታል (ሕዝ 1:5) እነዚህም እንስሳት ከእግዚአብሔር ዙፋን በታች ያሉ (ሕዝ 1:26) አራት ፊቶች ያሏቸው እንስሳት ሲሆኑ አንደኛው እንደ ሰው ፊት፥ በስተቀኛቸው እንደ አንበሳ ፊት፥ በስተግራቸው እንደ ላም ፊት፥ ደግሞም የንስር ፊት ነበራቸው (ሕዝ 1:10) ከዚህ በተጨማሪም አራት አራት ክንፎች የነበራቸው ሲሆን (ሕዝ 1:6) በዙሪያቸው ዓይኖችን ተሞልተው ነበር (ሕዝ 10:12) ከዚህ ሁሉ የምንረዳው ነገር፥ ነቢዩ ሕዝቅኤል በራዕዩ ያያቸው እንስሳት ሐዋርያው ዮሐንስ ያያቸው ራሳቸው እንስሳት መሆናቸውን ነው። ምክንያቱም በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተገለጹበት አገላለጽ በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ ከተገለጹበት አገላለጽ ጋር አንድ አይነት ነውና።

ይህንንም እውነት የዮሐንስ ራዕይንና የሕዝቅኤል መጽሐፍን በጥልቀት ስናጠና በይበልጥ እንረዳዋለን። ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለ እነዚህ እንስሳት በራዕዩ ካያቸው ነገሮች አንዱ፥ ለእያንዳንዳቸው በክንፋቸው በታች እጅ ያላቸው መሆኑ ነው (ሕዝ 1:8) እነዚህ እንስሳት ከክንፋቸው በታች እጅ እንዳላቸው በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ እንጂ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ አልተነገረም። ነገር ግን በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ አራቱ እንስሳት እጅ ያላቸው እንደሆነ ተመላክቷል። በራዕ 15:7 እንደምናነበው ከአራቱ እንስሳት አንዱ የእግዚአብሔርን የቁጣ ጽዋ ቁጣውን ለሚያስተላልፉት ሰባት መላእክት ይሰጣቸዋል። ሐዋርያው ዮሐንስ እንስሳው ጽዋን ለመላእክቱ ሲሰጣቸው ሊያይ የቻለው ያ እንስሳ ነቢዩ ሕዝቅኤል እንዳየው እጅ ስላለው ነው። ይህ በእርግጥም ሐዋሪያው ያያቸው እንስሳት ነቢዩ ያያቸው ራሳቸው እንስሳት ለመሆናቸው ግልጽ ማረጋገጫ ነው

እነዚሁ እንስሳት ኪሩቤል መሆናቸው በዮሐንስ ራዕይ ላይ ባይገለጽም፥ በሕዝቅኤል መጽሐፍ ላይ ተገልጿል፦

"እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ #በኪሩቤል ራስ ላይ ባለው ጠፈር #በላያቸው እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ እንደ #ዙፋን የሚመስል መልክ ተገለጠ።"
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 10:1)

በሕዝ 10:1 እንደምናነበው እንደ ሰንፔር የሚመስለው ዙፋን ያለው በኪሩቤል ራስ ባለው ጠፈር እላይ ነው። ስለዚህ ከኪሩቤል ላይ ጠፈር አለ፥ ከጠፈሩ ላይ ደግሞ ዙፋኑ አለ። ይህ ምስል ነቢዩ በምዕራፍ አንድ ላይ ያየው ምስል ነው። በምዕራፍ አንድ ላይ እንደምናነበው፥ ከአራቱ እንስሳት ራስ በላይ ጠፈር አለ (ሕዝ 1:22-23) ከጠፈሩ በላይ ደግሞ እንደ ሰንፔር ያለው ዙፋን አለ (ሕዝ 1:26) ስለዚህ በሕዝ 10:1 ላይ ኪሩቤል የተባሉት፥ በሕዝ 1 ላይ ነቢዩ ያያቸው አራት እንስሳት ናቸው ማለት ነው። ስለዚህ እነዚያ አራቱ እንስሳት ኪሩቤል ለመሆናቸው ይህ ማረጋገጫ ነው።

እነዚያ አራት እንስሳት ኪሩቤል ለመሆናቸው ከሕዝቅኤል መጽሐፍ ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንመለከታለን። በሕዝቅኤል 10:20-22 ላይ እንደምናነበው፥ ነቢዩ ሕዝቅኤል በኮበር ወንዝ ማዶ (ሕዝ 1:1 ሕዝ 1:3) ያየው እንስሳ ኪሩቤል እንደሆኑ ያስተውላል። ምዕራፍ አንድ ላይ እንዳየው እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበሯቸው (ሕዝ 1:6/ሕዝ 10:21) ፊቶቻቸውን በኮቦር ወንዝ ማዶ ያያቸውን ፊቶች ይመስሉ ነበር፥ እርሱና መልካቸውም እንዲሁ ነበር (ሕዝ 10:22) ይህ ሕዝቅኤል ያያቸው አራቱ እንስሳት ኪሩቤል ለመሆናቸው ግልፅ ማሳያ ነው። ከዚያም በተጨማሪ በሕዝ 10 ላይ ስለ አካሄዳቸው የተገለጸው ነገር ምዕራፍ 1 ላይ ካለው አገላለጽ ጋር አንድ ነው። በሁለቱም ቦታ ሲሄዱ ሳይገላመጡ እንደሆነ ተነግሯል (ሕዝ 1:9/ሕዝ 10:11) ይህ ሁሉ ሕዝቅኤል ያያቸው አራቱ እንስሳት ኪሩቤል መሆናቸውን በሚገባ ያሳያል።

ከላይ በማስረጃ እንደተመለከትነው ግን እነዚህ ነቢዩ ሕዝቅኤል ያያቸው አራቱ እንስሳት (ኪሩቤል) ሐዋርያው ዮሐንስ ያያቸው እንስሳት ናቸው። ሐዋሪያው ዮሐንስ በራዕዩ ሲያያቸው የነበሩት አራቱ እንስሳት እነዚህ ኪሩቤል ናቸው። ስለዚህ በራዕይ 5:8 ላይም በበጉ ፊት የወደቁት እነዚሁ ኪሩቤል ናቸው ማለት ነው።

2 months, 1 week ago

የክርስቶስ ትንሣኤ ታሪካዊነት የቀጥታ ትምህርት ይከታተሉ።

4 months, 3 weeks ago

ባሳለፍነው ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ፣ከካሪቢያንና ከፓሲፊክ የተውጣጡ ሀገራት ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የሚቆይ የንግድና ኢኮኖሚ ትብብር ስምምነትን ከአውሮፓ ህብረት ጋራ #ሳሞዋ በምትባል ሀገር በፈረሙ ወቅት አገራችን #ኢትዮጵያም ይህንኑ ስምምነት ተቀማጭነታቸው ብራሰልስ በሆኑ አምባሳደር አማካኝነት #በፊርማ_አጽድቃለች፡፡ ይህ #አደገኛ_ይዘቶች ያሏቸውን አንቀጾች የያዘው ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ከሚቀጥለው #ጥር ወር ጀምሮ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

ይህ የትብብር ስምምነት በውሥጡ የያዛቸውን አስራ ሁለት ዋና ዋና አደገኛ ይዘቶችን ጠቅልለው የሚይዙ የተወሰኑ ሀሳቦች ለመጥቀስ ያህል ፡-

ሀ) የሀገር ሉዓላዊነትን የሚጥሱ አንቀጾች በግልጽ መቀመጣቸው፣

ለ) ግብረሰዶማዊነት፣ የጾታ መቀየርና፣ውርጃና ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን የመሳሰሉ እኩይ አጀንዳዎች በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በሌሎች አሳሳች ሀረጎች ተሰውረው የገቡበት መሆኑ፣

ሐ) ግብረሰዶማዊነት በርካታ ቀውሶች ማለትም በአካል፣ በሥነልቦናና በማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያስከትልና ለሀገር ደህንነትም አደጋ መሆኑ፣

መ) የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን የሚንድ መሆኑ፣

ሠ) የሀገራችንን ሀይማኖት፣ባህልና እሴቶች የሚንዱ ጸያፍ ልምምዶችን እንድንቀበል በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በእርዳታ ስም የምንገደድበትና ለዘመናዊ ባርነት ወይንም ቅኝ አገዛዝ ታልፈን የምንሰጥበት መሆኑ፣

በአጠቃላይ ይህ አዲስ የአጋርነት ስምምነት ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡና ትውልድንና ብሎም ሀገርን እጅግ የሚጎዱ በርካታ አንቀጾች የተካተቱበት መሆኑ ለሀገራችን ህዝብ ዕድገትን ሳይሆን ውድቀትንና ከፍተኛ የሞራል ዝቅጠትን የሚያስከትል መሆኑን በሚገባ ተረድተናል፡፡

በተጨማሪም ከተጠበቀው ውጭ ሀገራችን ይህንን ስምምነት በመፈረሟ የተጋረጠብንን እጅግ አሳሳቢ አደጋ ለመቀልበስ አስፈላጊ የሆኑ ሰላማዊና ህጋዊ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም መንግስት ትኩረትን እንዲሰጠው ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

በመሆኑም ይህ የመንግስት ውሳኔ እንደገና ተጠንቶ ውሳኔው እንዲቀለበስ ማለትም ስምምነቱ አስፈላጊው ሁሉ ማስተካከያ እስኪደረግበት ድረስ ወይንም እጅግ አደገኛ የሆኑት አንቀጾች ተነቅሰው ወጥተው የማንቀበላቸው መሆናችንን በይፋ ማሳወቅ (Submission of an Interpretive Declaration) እስከምንችል ድረስ የምንወዳት ሐገራችን ኢትዮጵያ #ፊርማዋን_በመሰረዝ_ከስምምነቱ ራሷን እንድታገልል በሐገራችን ከፍተኛው የሥልጣን አካል ለሆነው ለተከበረው #የህዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤትና ለሐገሪቱ መሪ #ለክቡር_ጠቅላይ_ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በታላቅ አክብሮት እጅግ አስቸኳይ ጥሪን እናደርጋለን፡፡

የፊርማ ማሰባሰብ ሂደቱን ለመደገፍ ከታች ያለውን ማስፈንጠርያ ይጠቀሙ።

👉 https://keap.page/gq193/.html

5 months ago

♦️ ስለዚህ በዘፍጥረት 32 ታሪክ ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ የጸለየውን ጸሎት ሰምቶ ከወንድሙ ከኤሳው ያዳነው ማነው?

በዘፍጥረት 32 ላይ የያዕቆብን ጸሎት ሰምቶ ከወንድሙ ከኤሳው እጅ ያዳነው ማን ነው ለሚለው ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው መልሱን ይሰጠናል፦

"24፤ ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ #ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር። 25፤ እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ ያዕቆብም የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ። 26፤ እንዲህም አለው። ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም። #ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው። 27፤ እንዲህም አለው። ስምህ ማን ነው? እርሱም። ያዕቆብ ነኝ አለው። 28፤ አለውም። ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና። 29፤ ያዕቆብም። ስምህን ንገረኝ ብሎ ጠየቀው። እርሱም። ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? አለው። በዚያም ስፍራ #ባረከው። 30፤ ያዕቆብም። #እግዚአብሔርን ፊት ለፊት #አየሁ#ሰውነቴም #ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው።"
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 32:24-30)

➣ ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ የምናነበውን ጸሎት ካቀረበ በኋላ የሆነውን ነገር በዚህ ስፍራ ላይ እናነባለን። ለወንድሙ ለኤሳው እጅ መንሻን ካዘጋጀ በኋላ ቤተሰቡንና ከብቱን በረድፍ በረድፍ አሰልፎ የያቦቅ ወንዝን ያሻግራቸዋል (ዘፍ 32:13-23) እርሱ ግን ወንዙን ሳይሻገር ለብቻው ወደ ኋላ ይቀራል። ያኔም አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር። እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፥ ያዕቆብም ደነዘዘ። ሊነጋ ሲያቅላላ ልቀቀኝ ሲለው፥ ያዕቆብ ካልባረከኝ አልለቅህም አለው። ካልባረከኝ አልለቅህም ማለት በዚህ አውድ ከወንድሜ ከኤሳው ካላዳንከኝ አልለቅህም ማለት ነው። በሰአቱ ለያዕቆብም ጭንቅ የሆነበት ጉዳይ እርሱ ነበርና። ካልባረከኝ አልለቅህም ማለት ከወንድሜ ከኤሳው ካላዳንከኝ አልለቅህም ማለት ነው። በዚህ አውድ በረከት ከጠላቱ ከኤሳው መዳኑ ነውና

ከዚያም የታገለው ሰው ስሙን ወደ እስራኤል ከቀየረው በኋላ፥ በዚያ ስፍራ እንደባረከው በዘፍ 32:29 እናነባለን። ይህ ማለት ደህንነቱ ተረጋገጠ ማለት ነው። ያ የታገለው ሰው ያዕቆብን በመባረክ ከወንድሙ ከኤሳው አዳነው። ከላይ እንዳልነው ያዕቆብ ካልባረከኝ አልለቅህም ሲለው ከወንድሜ ከኤሳው ካላዳንከኝ አልለቅህም ማለቱ ነው። ስለዚህ የታገለው ሰው ያዕቆብን ሲባርከው አዳነው ማለት ነው። እርሱን መባረኩ ከወንድሙ ከኤሳው ማዳኑ ነው። ያዕቆብ በዘፍ 32:11 ላይ በጸሎት የለመነውን ነገር እርሱን በመባረክ ፈጸመለት። ስለዚህ በዘፍ 32:11 ላይ ያዕቆብ ከወንድሜ ከኤሳው አድነኝ ብሎ የጸለየውን ጸሎት ሰምቶ እርሱን በመባረክ ከኤሳው በማዳን የመለሰለት፥ ይህ ለብቻው ሳለ አግኝቶት የታገለው ሰው ነው።

✏️ ታዲያ ይህ ያዕቆብን የታገለው ሰው ማነው?

መጽሐፍ ቅዱስ በዘፍ 32 ላይ ያዕቆብን የታገለው ማን ነው ለሚለው ጥያቄ መልሱን በዚህ መልኩ ይሰጠናል፦

"4፤ በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱም ጊዜ ከአምላክ ጋር ታገለ፤ 5፤ #ከመልአኩም ጋር #ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም ከእኛ ጋር ተነጋገረ። 6፤ እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፤ የመታሰቢያው ስም እግዚአብሔር ነው።"
(ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ 12:4-6)

መጽሐፍ ቅዱስ በትንቢተ ሆሴዕ 12 ላይ በግልጽ እንደሚነግረን፥ ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ የታገለው ከመልአኩ ጋር ነበር! ከአምላክ ጋር ታገለ፥ ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ በማለት ያዕቆብ በያቦቅ ወንዝ ማዶ የታገለው መልአኩ መሆኑን በግልጽ ይናገራል። ስለዚህ በዘፍ 32 ላይ ያለውን የያዕቆብን ጸሎት ሰምቶ፥ በትክክል ሊያድነው የመጣው አምላክ መልአኩ ነበር ማለት ነው። በዘፍ 32ም በሆሴ 12ም መልአኩ እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራ ሲሆን፥ ያዕቆብ አድነኝ ብሎ የጸለየውን ጸሎት ሰምቶ ሊመልስለት መምጣቱ በእርግጥም ያዕቆብ ወደ እርሱ ሲጸልይ የነበረው አምላክ መልአኩ መሆኑን ያረጋግጣል።

ለዚያ ነው በዘፍ 32:30 ላይ "..ሰውነቴ ድና ቀረች.." ያለው። እግዚአብሔርን ስላየና፥ ስለባረከው ዳነ። ከላይ በዘፍ 32:11 ላይ አድነኝ ብሎ ነገር የጸለየው። አሁን ግን የተገለጠለትን እግዚአብሔር (መልአኩን) ካየ በኋላ ሰውነቴ ድና ቀረች አለ። ከወንድሜ ከኤሳው ድኛለሁ ማለቱ ነው። ያ እግዚአብሔር ታይቶት ስለባረከው፥ ደህንነቱ ተረጋገጠ ወይም ዳነ። በቁ.30 ላይ "ድና" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "נָצַל/ናትጻል" ሲሆን በቁ.11 ላይ "አድነኝ" ተብሎ የተተረጎመው ቃል ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት በቁ.11 ላይ የጸለየበት ጉዳይ በቁ.30 ላይ ተፈጻሚነት እንዳገኘ ለማሳየት ነው። ይህ የያዕቆብን ጸሎት ሰምቶ፥ ከወንድሙ ከኤሳው ያዳነው እግዚአብሔር መልአኩ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል። መጥቶ የታገለው፥ የተገለጠለት፥ ደግሞም የባረከው አምላክ እርሱ ነውና። ይህ መልአኩ ጸሎት የሚሰማው አምላክ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ያረጋግጣል።

▶️ ይቀጥላል

5 months ago

ይህን እውነት ግልፅ ከሆነ በኋላ ግን፥ አንድ ሊጠየቅ የሚገባው ጥያቄ አለ። እርሱም፦

♦️ በዘፍጥረት 28 ላይ ለያዕቆብ ተገልጦለት የነበረው አምላክ ማነው?

ከላይ በብዙ ማስረጃዎች ለማየት እንደሞከርነው፥ ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ እየጸለየ የነበረው በዘፍ 28 ላይ ተገልጦለት ወደነበረው አምላክ ነው። ታዲያ ይህ በዘፍ 28 በቤቴል ለያዕቆብ ተገልጦለት የነበረው አምላክ ማነው ብለን ስንጠይቅ፥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው መልሱን ይሰጠናል፦

"10፤ እንዲህም ሆነ፤ በጎቹ በጎመጁ ጊዜ ዓይኔን አንሥቼ #በሕልም አየሁ፤ እነሆም፥ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ነበሩ። 11፤ የእግዚአብሔርም #መልአክ በሕልም። ያዕቆብ ሆይ አለኝ፤ እኔም። እነሆኝ አልሁት። 12፤ እንዲህም አለኝ። ዓይንህን አቅንተህ እይ፤ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ናቸው፤ ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና። 13፤ #ሐውልት_የቀባህበት_በዚያም_ለእኔ_ስእለት_የተሳልህበት_የቤቴል_አምላክ_እኔ_ነኝ፤ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ፥ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 31:10-13)

▶️ በዚህ ስፍራ ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ለያዕቆብ በሕልም ተገልጦ የተናገረውን ነገር እንመለከታለን። የላባ ልጆች ያዕቆብ የአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ ይህን ሁሉ ክብር ከአባታችን ከብት አገኘ ብለው ያሉትን ሰሞቶ፥ የላባን ፊት ካየ በኋላው ከላባ ጋር እንደ ድሮ መሆን ያቆማሉ። በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ወደ አባቱ ምድር እንዲመለስና በዚያም ከእርሱ ጋር እንደሚሆን ይናገረዋል። ይህን የሰማው ያዕቆብም ራሔልና ልያን አስጠርቶ እንዴት አባታቸውን በቅንነት እንዳገለገለው፥ ነገር ግን እሱ አስር ጊዜ ደሞዙን እንደለዋወጠበት፥ ነገር ግን እግዚአብሔር በጎቹን ሁሉ እንደሰጠው ካስታወሳቸው በኋላ፥ በጎቹ በጎመጁ ጊዜ ያየውን ሕልም ነገራቸው።

እርሱም የእግዚአብሔር መልአክ እንደጠራውና፥ ላባ በእርሱ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ እንዳየ ከገለፀለት በኋላ፥ በቀጥታ ሀውልት የቀባበትና፥ በዚያም ለእርሱ ስዕለት የተሳለበት የቤቴል አምላክ እንደሆነ ይነግረዋል። ይህ ቃል በቃል የተነገረ ቃል ሲሆን፥ በዘፍ 28 ላይ ለያዕቆብ የተገለጠለት አምላክ ማን እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል። በዘፍ 28 በቤቴል ለያዕቆብ የተገለጠለት አምላክ መልአኩ ነበር! ለዚህ ነው በቀጥታ ሀውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስዕለት የተሳልክበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ ያለው።

በዘፍ 31:10-13 እንደምናነበው መልአኩ የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ ነው ያለው። ቤቴል ማለት በዘፍ 28 ላይ እግዚአብሔር ለያዕቆብ በሕልም የተገለጠለት ቦታ ሲሆን፥ ከእንቅልፉ ሲነቃ ይህስ የእግዚአብሔር ቤት ነው በማለት ለስፍራው የሰጠው ስም ነው (ዘፍ 28:19) ቀጥሎም መልአኩ "..ሀውልት የቀባህበት.." በማለት እርሱ ያ ያዕቆብ ሀውልት የቀባበት ቦታ የተገለጠለት አምላክ መሆኑን ይነግረዋል። ይህም ዘፍ 28ን የሚያስታውስ ቃል ነው። ምክንያቱም ያዕቆብ በቤቴል ሳለ እግዚአብሔርን በሕልም ካየ በኋላ፥ ከእንቅልፉ ሲነቃ ያደረገው ይህንኑ ነው። ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ሀውልት አደረገው፥ በላዩም ላይ ዘይት አፈሰሰበት (ዘፍ 28:18)

ይህ ሁሉ የሆነው በቤቴል ሲሆን፥ መልአኩ "..ሀውልት ያፈሰስክበት .." ሲል እያስታወሰው የነበረው ይህንን ነበር። ከዚያም በተጨማሪ መልአኩ "..በዚያም ለእኔ ስዕለት የተሳልክበት.." ብሎታል። ይህም ዘፍ 28ን የሚያስታውስ ቃል ነው። ምክንያቱም ያዕቆብ በዘፍ 28 በቤቴል ካደረጋቸው ነገሮች አንዱ ስዕለትን መሳል ነው። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቢሆንና፥ በሚሄድበት ቢጠብቀው አምላኩ እንደሚሆን በመግለፅ ስዕለትን ተስሏል (ዘፍ 28:20) ስለዚህ ከዘፍ 31:10-13 የምንመለከተው ቀጥተኛ ቃል፥ መልአኩ ያኔ በዘፍ 28 ላይ በቤቴል ለያዕቆብ የተገለጠለት፥ ያዕቆብ ሀውልት የቀባለት፥ ስዕለትም የተሳለለት አምላክ መሆኑን ነው። ያ እግዚአብሔር እርሱ ነው።

✏️ ከባለፈው ክፍል ጀምሮ በማስረጃ ለማየት እንደሞከርነው ግን፥ በዘፍ 32 ላይ ያዕቆብ ሲጸልይ የነበረው በዘፍ 28 ላይ ተገልጦለት ወደነበረው አምላክ ነው። ወንድሙ ኤሳው በመጣ ጊዜ እንዲያድነው የጸለየው፥ በዘፍ 28 ላይ ተገልጦለት ወደ ነበረው አምላክ ነው። አሁን ግን ከዘፍ 31:10-13 እንደምንረዳው ያ በዘፍ 28 ላይ ለያዕቆብ ተገልጦለት የነበረው የቤቴል አምላክ መልአኩ ነበር። ስለዚህ በዘፍ 32 ላይ ያዕቆብ ሲጸልይ የነበረው ወደ መልአኩ ነበር ማለት ነው! ዘፍ 28 ላይ ተገልጦለት፥ እነዚያን ነገሮች ሊያደርግለት ቃል የገባለት፥ በኋላም በዘፍ 31:10-13 ላይ በድጋሚ ተገልጦለት የቤቴል አምላክ መሆኑን ወደ ነገረው መልአክ ነበር ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ ሲጸልይ የነበረው! ያ በዘፍ 28 የተገለጠለት አምላክ መልአኩ ነውና

ለዚህ ነው ልክ በዘፍ 32 ላይ የተባሉት ነገሮች በዘፍ 28 ላይ ከተባሉት ነገሮች ጋር እንደሚመሳሰሉት፥ በዘፍ 32 ላይ የተባለው ነገር በዘፍ 31 ላይ ከተባለው ነገር ጋር የሚመሳሰለው፦

"ያዕቆብም አለ። የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፥ የአባቴም የይስሐቅ አምላክ ሆይ። ወደ #ምድርህ ወደ ተወለድህበትም #ስፍራ #ተመለስ፥ በጎነትንም አደርግልሃለሁ #ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፤"
(ኦሪት ዘፍጥረት 32:9)

ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ ሲጸልይ "..ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበት ስፍራ ተመለስ #ያልከኝ.." ይላል። ይህ ማለት ወደ እርሱ የሚጸልየው አምላክ ወደ ምድሩ፥ ወደ ተወለደበት ምድር ተመለስ ብሎታል ማለት ነው። ይህ በዘፍ 31 ላይ መልአኩ ለእርሱ የተናገረው ነገር ነው፦

"ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ፥ ወደ #ተወለድህበትም #ምድር #ተመለስ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 31:13)

መልአኩ በሕልም ከተገለጠለት በኋላ ወደ ተወለደበት ምድር እንዲመለስ ሲነግረው እንመለከታለን። ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ "..ወደ ምድርህ፥ ወደ ተወለድክበት ስፍራ ተመለስ ያልከኝ.." ያለው ለዚህ ነው። ወደ እርሱ እየጸለየ የነበረው አምላክ ዘፍ 31 ላይ የተገለጠለት መልአክ ነበርና። በፊት እንዳየነው፥ ዘፍ 32:9 ላይ ያለው ቃል ዘፍ 28:15 ላይ የተነገረው ቃል ነው። ስለዚህ ከዚህ የምንማረው እውነት፥ በዘፍ 28:15፥ በዘፍ 31:13 እና በዘፍ 32:9 ላይ ያዕቆብን ወደ ምድሩ እንዲመለስ የተናገረው አካል አንድ መሆኑን ነው። እርሱም መልአኩ ነው። ያዕቆብን ወደ ምድሩ እንደሚመልሰው ቃል የገባለት፥ በኋላም ወደ ምድሩ እንዲመለስ ያዘዘው አምላክ እርሱ ነው። ስለዚህ ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ ወደ ምድርህ ተመለስ ያልኸኝ በማለት ወደ እርሱ ሲጸልይ የነበረው አምላክ መልአኩ ነበር ማለት ነው።

➣ ከዚህም ባሻገር በዘፍ 32 ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ የጸለየው እግዚአብሔር መልአኩ እንደነበር የምናውቅበት መንገድ አለ። እርሱም ጸሎቱን የመለሰው አካል ማንነት ነው። በዘፍ 32:11 ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ ሲጸልይ የነበረውን አምላክ እንዲያድነው ጠይቆታል። ስለዚህ ጸሎቱ የቀረበለት አካል የያዕቆብን ጸሎት መለሰ የሚባለው የጠየቀውን ነገር ሰምቶ ሲፈጽምለት ነው። ያን የጠየቀውን ነገር ሲፈጽምለት ጸሎቱን መለሰለት ይባላል። ያዕቆብ ደግሞ የጠየቀው እንዲያድነው ነው።

5 months, 2 weeks ago

"እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ። የአባትህ #የአብርሃም #አምላክ #የይስሐቅም #አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤"
(ኦሪት ዘፍጥረት 28:13)

በዘፍጥረት 28 ላይ እንደምናነበው፥ በቤቴል ለያዕቆብ የተገለጠለት እግዚአብሔር የአባቶቹ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ ነው። ስለዚህ ያዕቆብ በዘፍጥረት 32 ላይ "የአባቴ የአብርሃም ፥ የአባቴም የይስሐቅ አምላክ ሆይ" ብሎ ሲጸልይ፥ በዘፍጥረት 28 ላይ ወደ ተገለጠለት አምላክ እየጸለየ እንደነበር ከዚህ እንረዳለን።

2) ወደ ምድሩ መልሶታል

በዘፍጥረት 32 ላይ ካለው የያዕቆብ ጸሎት የሚስተዋለው ሌላው ነገር፥ ወደ እርሱ የሚጸልየው አምላክ ወደ ተወለደበት ምድር እንዲመለስ ያዘዘው መሆኑን ነው፦

"ያዕቆብም አለ። የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፥ የአባቴም የይስሐቅ አምላክ ሆይ። ወደ #ምድርህ ወደ #ተወለድህበትም #ስፍራ #ተመለስ፥ በጎነትንም አደርግልሃለሁ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፤"
(ኦሪት ዘፍጥረት 32:9)

ያዕቆብ ከወንድሙ ለመትረፍ ወደ እርሱ ሲጸልይ፥ ይህ በያቦቅ ወንዝ ማዶ ሆኖ የሚጸልይለት አምላክ ወደ ተወለደበት ምድር ተመለስ ያለው አምላክ መሆኑን ይገልጻል። ይህ እውነት በዘፍጥረት 32 ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ የጸለየው አምላክ፥ በዘፍ 28 ላይ ለእርሱ የተገለጠለት አምላክ መሆኑን ያሳያል። ምክንያቱም በዘፍጥረት 28 ለእርሱ የተገለጠው አምላክ ወደ ተወለደበት ምድር እንደሚመልሰው ቃል ገብቶለት ነበርና፦

"እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ #ወደዚችም #ምድር #እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 28:15)

በዚህ ቦታ ላይ በዘፍጥረት 28 ለያዕቆብ የተገለጠለት አምላክ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ በማለት ቃል ሲገባለት እናያለን። ከላይ ለማየት እንደሞከርነው፥ ያዕቆብ ከከነዓን ምድር ወጥቶ ወደ እናቱ አባት ቤት እየሄደ ነበር። ስለዚህ ከተወለደበት ምድር እየወጣ ነበር ማለት ነው። ይህ በቤቴል የተገለጠለት እግዚአብሔር ግን ወደዚህች ምድር (ወደተወለደባት ምድር) እንደሚመልሰው ቃል ሲገባለት እንመለከታለን። በሄደበት ምድር እንደማይቀር፥ ነገር ግን ሕልሙን ሲያይባት ወደነበረችው ምድር (የትውልድ ምድሩ) እንደሚመልሰው ይነግረዋል። ስለዚህ በዘፍጥረት 32 ላይ "ወደ ተወለድህበት ስፍራ ተመለስ ያልከኝ" በማለት ወደ እርሱ የጸለየው አምላክ፥ በዘፍጥረት 28 ላይ ከወንድሙ በሸሸ ጊዜ በቤቴል የተገለጠለት እግዚአብሔር ነው። ያዕቆብ በዘፍጥረት 28 ላይ የሚጸልየው በዘፍጥረት 32 ላይ ወደ ተገለጠለት አምላክ ነው።

3) አምላኩ መሆኑን መስክሯል

በዘፍጥረት 32 ላይ ከምንመለከተው የያዕቆብ ጸሎት የምንረዳው ሌላው ነገር ቢኖር፥ ወደ እርሱ የሚጸልየው አምላክ አምላኩ መሆኑን መመስከሩ ነው፦

" #ለባሪያህ ከሠራኸው ከምሕረትህና ከእውነትህም ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 32:10)

በዚህ ስፍራ ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ የሚጸልየው እግዚአብሔር ባሪያ መሆኑን ይመሰክራል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ፥ አንድ ሰው የእግዚአብሔር ባሪያ ከሆነ እግዚአብሔር የዚያ ሰው አምላክ ነው። ሰለሞን የእግዚአብሔር ባሪያ በመሆኑ (1ነገ 8:29) እግዚአብሔር የሰለሞን አምላክ ነው (1 ነገ 5:4) ኢያሱ የእግዚአብሔር ባሪያ በመሆኑ (መሳ 2:8) እግዚአብሔር የኢያሱ አምላክ ነው (ኢያ 9:23) ኢሳያስ የእግዚአብሔር ባሪያ በመሆኑ (ኢሳ 20:13) እግዚአብሔር የኢሳያስ አምላክ ተብሏል (ኢሳ 7:13) በዚሁ መንገድ፥ ያዕቆብ ወደ እርሱ የሚጸልየው አምላክ ባሪያ መሆኑን መመስከሩ፥ ያ አምላክ የእርሱ አምላክ መሆኑን እንደመሰከረ ያረጋግጣል።

ይህ በዘፍጥረት 32 ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ የጸለየው አምላክ በዘፍጥረት 28 በቤቴል የተገለጠለት አምላክ ለመሆኑ ተጨማሪ ማሳያ ነው። ምክንያቱም በዘፍጥረት 28 ላይ ያዕቆብ ያኔ የተገለጠለት አምላክ፥ አምላኩ መሆኑን መስክሯልና፦

"ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር #አምላኬ ይሆንልኛል፤"
(ኦሪት ዘፍጥረት 28:21)

በዚህ ቦታ ላይ ያዕቆብ በቤቴል በዘፍ 28:13-15 ላይ የተገለጠለት እግዚአብሔር አምላኩ መሆኑን ሲመሰክር እንመለከታለን። ከቁ.13-15 እንደምናነበው በዚህ ቦታ ላይ ለእርሱ የተገለጠው አምላክ ከእርሱ ጋር እንደሚሆን፥ እንደሚጠብቀውም ቃል ሲገባለት እንመለከታለን (ዘፍ 28:15) ከዚያም በማለዳ ተነስቶ፥ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት። ከዚያም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድበት መንገድ በዚህ መንገድ ቢጠብቀኝ አምላኬ ይሆናል በማለት ስዕለትን ይሳላል። ማለትም፥ በዘፍ 28:13-15 ላይ የተገለጠልኝ አምላክ የገባውን ኪዳን ቢፈጽምልኝ አምላኬ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ ያዕቆብ በዘፍጥረት 28:21 ላይ ተገልጦለት የነበረው እግዚአብሔር አምላኩ መሆኑን መስክሯል።

ስለዚህ በዘፍጥረት 32:10 ላይ ባሪያው እንደሆነ የመሰከረለት እግዚአብሔር፥ በዘፍጥረት 28:21 ላይ አምላኩ መሆኑን የመሰከረለት እግዚአብሔር ነው። ይህ በዘፍጥረት 32 ላይ ያዕቆብ እየጸለየ የነበረው በዘፍጥረት 28 ላይ ወደ ተገለጠለት እግዚአብሔር መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

♦️ ይህ ሁሉ ጸሎት ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ እንደሚጸለይ የሚያሳየው እንዴት ነው?

▶️ ይቀጥላል

5 months, 2 weeks ago

🚩 ወደ ጌታ ኢየሱስ እና ወደ መንፈስ ቅዱስ አይጸለይም? (ክፍል 2)

ባለፈው ክፍል ፓስተር ያሬድ ጸሎት ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ መቅረብ አለመቅረቡን አስመልክቶ ለተናገረው ፍጹም ስህተት ለሆነ ንግግሩ መልስ መስጠት ጀምረን ነበር። እንደ እርሱ መረዳት ከሆነ ጸሎት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወደ እግዚአብሔር አብ ይቀርባል እንጂ ወደ ራሱ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ እና ወደ መንፈስ ቅዱስ አይጸለይም። ይህ ፈጽሞ ስህተት የሆነ አቋም ነው

በፊት እንዳልነው፥ ጸሎትን መስማት የመለኮት ባህርይ ነው። አንድ አካል ጸሎትን አይሰማም ከተባለ ወይንም ደግሞ ወደ አምላክ እንደሚጸለየው ወደ እርሱ አይጸለይም ከተባለ ያ አካል አምላክ አይደለም ማለት ነው። አምላክነት በተግባር ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ ጸሎት ሰሚነት ነውና። ስለዚህ ይህ አምላካዊ ባህርይ የሚጎድለው አካል አምላክ አይደለም። ከዚህ የተነሳ ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አይጸለይም የሚል መረዳት የክርስቶስ ኢየሱስን አምላክነት የሚቃረን የተሳሳተ ትምህርት ነው።

✍️ ከእርሱም ባሻገር፥ መጽሐፍ ቅዱስ በትክክል ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚጸለይ ማስተማሩን በበዙ ማስረጃዎች ለማየት ሞክረን ነበር። ባለፈው ክፍል ለማሳየት እንደሞከርነው፥ ሰማዕቱ እስጢፋኖስ ነፍሱን እንዲቀበልለት ወደ ጌታ ኢየሱስ እንደጸለየ፥ ወደ እርሱም የጸለየበት መንገድ ራሱ ጌታ ኢየሱስ እና የብሉይ ኪዳን ነቢያት ወደ እግዚአብሔር ከጸለዩበት መንገድ ጋር አንድ አይነት እንደሆነ ለመመልከት ሞክረን ነበር።

በተጨማሪም እስጢፋኖስ ጌታ ኢየሱስን በጸሎት የጠየቀው ነገር፥ መለኮት ብቻ ለፍጡራን የሚያደርገው ነገር እንደሆነና ይህም የብሉይ ኪዳን ነቢያት እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርግ የሚችለውን ነገር እንዲያደርግላቸው በጸሎት ከጠየቁበት መንገድ ጋር አንድ አይነት መሆኑን ለማየት ሞክረን ነበር።

በመቀጠልም እስጢፋኖስ ወደ ጌታ ኢየሱስ የጸለየው በራሱ ተነሳሽነት አለመሆኑን፥ ነገር ግን በራሱ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ መሆኑንም ለመመልከት ሞክረን ነበር። እስጢፋኖስ ወደ ክርስቶስ የጸለየው ጌታ ኢየሱስ ወደ አብ ከሄደ በኋላ ተከታዮቹ በስሙ እንዲለምኑና፥ የሚለምኑትን ነገር ሁሉ ከአባቱ ጋር ካለበት ከሰማይ ሆኖ እንደሚያደርገው ቃል ስለገባላቸው እንደሆነም አይተናል። ይህ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ ይጸለያል ብሎ እንደሚያስተምር ያሳያል።

▶️ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዚህ ክፍል ላይ ለዚህ እውነት ተጨማሪ ማስረጃዎችን ማቅረብ እንቀጥላለን። እርሱም መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥም ወደ ክርስቶስ ይጸልያል ብሎ እንደሚያስተምር ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማቅረብ እንሞክራለን፦

"9፤ ያዕቆብም አለ። የአባቴ የአብርሃም #አምላክ ሆይ፥ የአባቴም የይስሐቅ #አምላክ ሆይ። ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ፥ በጎነትንም አደርግልሃለሁ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፤ 10፤ ለባሪያህ ከሠራኸው ከምሕረትህና ከእውነትህም ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ። 11፤ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ #አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና። 12፤ አንተም። በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ #እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ #አደርጋለሁ #ብለህ ነበር።"
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 32:9-12)

✏️ በዚህ ክፍል ላይ ያዕቆብ ከላባ ቤት ከወጣ በኋላ ቤተሰቡን ይዞ ወደተወለደበት ምድር ወደ ቤቴል ሲጓዝ የገጠመውን ታሪክ እናነባለን። ከላባ ጋር አንዳቸው ወደ ሌላቸው ድንበር እንዳይተላለፉ ከተማማሉ በኋላ ያዕቆብ ከነ ቤተሰቡ መንገዱን ሄደ። ያኔም ወደ ወንድሙ ወደ ኤሳው ምድር ወደ ሴይር መልእክተኞችን ይልካል። በላባ ቤት በስደት መቀመጡንና አሁን ላይ ያገኘውን ሀብት ለማሳወቅ እንደሆነም ይገልጽለታል። በዚያን ጊዜም መልእክተኞቹ ወደ ያዕቆብ ተመልሰው ወንድሙ ኤሳው ሊቀበለው እንደሚመጣና፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች እንዳሉ ይነግሩታል። በዚያን ጊዜም ይህን የሰማው ያዕቆብም እጅግ ፈርቶ ይጨነቃል፥ ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎችና ከብቶች "ኤሳው መጥቶ አንዱን ወገን ቢመታ ሌላው ወገን ያመልጣል" በሚል ስሌት ለሁለት ይከፍላቸዋል። ይህን ካደረገም በኋላ በዘፍ 32:9-12 ላይ የምናየውን ጸሎት ይጸልያል።

➣ ከያዕቆብ ጸሎት ምን እንረዳለን? ወደ ማንስ ነው እየጸለየ የነበረው?

በወንድሙ መምጣት እጅግ የፈራው ያዕቆብ እየጸለየ የነበረው በዘፍጥረት 28 ላይ በቤቴል ለእርሱ ወደ ተገለጠለት እግዚአብሔር ነው። የጸሎቱ ተደራሲ በቤቴል የተገለጠለት አምላክ ነው። በዘፍጥረት 28 ላይ እንደምናነበው፥ የያዕቆብ አባት ይስሐቅ ለልጁ ለያዕቆብ ከከነዓናውያን ሴቶች ሚስት እንዳያገባና ይልቁንም ወደ በሁለቱ ወንዞች መካከል ወደ እናቱ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሄዶ ሚስትን እንዲያገባ ይነግረዋል። ከዚያም ሁሉን የሚችል አምላክ እንዲባርከውና ለአብርሃም የሰጠውን መሬት እንዲወርስ ከመረቀው በኋላ ሂድ ወዳለው ስፍራ ይሰድደዋል። ያዕቆብም የወላጆቹን ቃል በመስማት ወደ በሁለቱ ወንዞች መካከል ይሄዳል

ከዚያም መንገድ ላይ እያለ ጸሐይ ስለጠለቀች ከዚያ አደረ። ድንጋይ አንስቶም ተንተርሶት ተኛ። በዚያን ወቅትም ሕልም አለመ። ሕልሙም ከሰማይ እስከ ምድር የሚደርስ መሰላል ሲሆን በመሰላሉ ላይ የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡና ይወርዱ ነበር። በመሰላሉ ላይም እግዚአብሔር ቆሞበት ነበር። ቀጥሎም በዘፍ 28:13-15 ላይ የምናነበውን ነገር ለእርሱ ተናገረው

"13፤ እነሆም፥ #እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ። የአባትህ የአብርሃም #አምላክ የይስሐቅም #አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤ 14፤ ዘርህም እንደ ምድር #አሸዋ ይሆናል፤ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ። 15፤ እነሆም እኔ #ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ #እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ #አልተውህምና።"
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 28:13-15)

🖋 በቤቴል የተገለጠለት ይህ እግዚአብሔር ማን እንደሆነና በቀሪው የሕይወት ዘመኑ ምን እንደሚያደርግለት ቃል ይገባለታል። ይህ ክስተት ያዕቆብ ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔርን የተገናኘበት ክስተት ሲሆን፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ የሚያስታውሰው ክስተት ነው። ቀጥለን እንደምንመለከተው፥ በዘፍ 32:9-12 ላይ ባለው ጸሎቱ እየጸለየ የነበረው በቤቴል ወደ ተገለጠለት እግዚአብሔር ነው። እያስታወሰ የነበረውም በቤቴል የተገለጠለት እግዚአብሔር የገባለትን ኪዳን ነው።

1) የአባቶቹ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ መሆኑን ገልጿል

በዘፍጥረት 32 ላይ በምናነበው የያዕቆብ ጸሎት ውስጥ የምናስተውለው የመጀመሪያው ነገር እየጸለየ የነበረው ወደ አባቶቹ ወደ አብርሃምና ይስሐቅ አምላክ እንደነበር ነው፦

"ያዕቆብም አለ። የአባቴ #የአብርሃም #አምላክ ሆይ፥ የአባቴም #የይስሐቅ #አምላክ ሆይ። ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ፥ በጎነትንም አደርግልሃለሁ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፤"
(ኦሪት ዘፍጥረት 32:9)

ይህ ሲጸልይ የነበረው በዘፍ 28 ወደ ተገለጠለት አምላክ መሆኑን ያሳያል። ምክንያቱም በቤቴል የተገለጠለት አምላክ የአባቶቹ አምላክ ነው፦

5 months, 3 weeks ago

♦️ በሐዋርያት ሥራ 7 ላይ ግን እስጢፋኖስ ነፍሱን እንዲቀበልለት የጸለየው ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። እስጢፋኖስ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ የጸለየው መለኮት ብቻ ሊያደርገው የሚችለውን ነገር እንዲያደርግለት ነው። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ መለኮት ብቻ የሚያደርገውን ነገር እንዲያደርግ ወደ እርሱ የሚጸለይ አምላክ መሆኑን ያረጋግጣል።

የብሉይ ኪዳን አማኞች እግዚአብሔር፥ መለኮት ብቻ ሊያደርግላቸው የሚችለውን ነገር እንዲያደርግላቸው ወደ እርሱ እንደ ጸለዩት ነው፥ እስጢፋኖስም ወደ ልጁ ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የጸለየው። የሚያድነው እግዚአብሔር በመሆኑ (መዝ 3:8) ዳዊት እንዲያድነው ወደ እርሱ ጸልዮአል። የሚፈውሰው እግዚአብሔር በመሆኑ (ዘጽ 15:26) ኤርምያስ እንዲፈውሰው ወደ እርሱ ጸልዮአል። የሚምረው እግዚአብሔር በመሆኑ (ዘዳ 4:31) ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲምራቸው ወደ እግዚአብሔር ጸልዮአል። እስጢፋኖስም ወደ ጌታ ኢየሱስ የጸለየው በዚሁ መንገድ ነው። ወደ እርሱ የጸለየው ያን መለኮት ብቻ ሊያደርግለት የሚችለውን ነገር (ነፍስን መቀበል) እንዲያደርግለት ነው።

✏️ እስጢፋኖስ ወደ ጌታ ኢየሱስ የጸለየው፥ እንዲሁ በራሱ ተነሳሽነት አይደለም። እስጢፋኖስ ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የጸለየው፥ ጌታ ኢየሱስ ሰዎች ወደ እርሱ እንዲጸልዩ በማዘዙ ነው፦

"13፤ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ #የምትለምኑትን ሁሉ #አደርገዋለሁ። 14፤ ማናቸውንም ነገር #በስሜ ብትለምኑ #እኔ #አደርገዋለሁ።"
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14:13-14)

በዚህ ቦታ ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በግልጽ ሰዎች ወደ እርሱ እንዲጸልዩ ሲያስተምር እንመለከታለን። ወደ አብ እንደሚሄድና፥ አብ ስለ እርሱ እንዲከብር በስሙ የምንለምነውን ነገር ሁሉ እንደሚያደርገው ይገልጻል። ቀጥሎም ማናቸውንም ነገር በስሙ ብንለምን እርሱ እንደሚያደርገው ቃል ሲገባ እናነባለን። ማናቸውንም ነገር በእርሱ ስም ብንለምን፥ እርሱ ያደርገዋል። ይህ ክርስቶስ በቀጥታ ወደ እርሱ እንድንጸልይ ያስተማረበት ክፍል ነው።

እስጢፋኖስም ወደ ጌታ ኢየሱስ የጸለየበት ምክንያት ይህ ነው። ጌታ በስሙ የሚጠይቁትን ነገር እንደሚያደርገው ቃል ስለገባላቸው ነው። ወደ አብ ከሄደ በኋላ (ዮሐ 14:13) በስሙ የሚለምኑትን እንደሚያደርግላቸው ተናግሯል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን፥ የአብ መኖሪያ በሰማይ ነው (ሉቃ 11:2) ስለዚህ ወደ አብ እሄዳለሁ ማለት ወደ ሰማይ አርጋለሁ ማለት ነው። ስለዚህ በስሙ የምንለምነውን ነገር ሁሉ የሚያደርግለን በአባቱ ዘንድ በሰማይ ሆኖ ነው ማለት ነው። እስጢፋኖስም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ያየው እንደዚያ ነው። ሰማያት ተከፍተው ጌታ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ሆኖ ነው የተመለከተው (ሐዋ 7:55-56) ይህ ክርስቶስ በሰማያት ሆኖ ጸሎትን የሚሰማው አምላክ መሆኑን በግልፅ ያሳያል።

ወደ አብ እሄዳለሁ፥ አብም በወልድ እንዲከብር በስሜ የምትለምኑትን አደርጋለሁ እንዳለው፥ እስጢፋኖስም ክርስቶስን በስሙ ነው የለመነው። ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል በማለት በስሙ ወደ እርሱ በመጸለይ ነፍሱን እንዲቀበለው ለምኖታል። እስጢፋኖስ የጌታ የኢየሱስን ስም ጠርቶ ወደ እርሱ የጸለየው ጌታ በዮሐ 14:13-14 ላይ ክርስቲያኖች በስሙ እንዲለምኑ ስላዘዘ ነው። እየተገበረ የነበረው ያንኑ ስለነበር ነው። በስሙ ከመጸለዩ በተጨማሪም፥ በቀጥታ ነፍሱን እንዲቀበል የለመነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ነው።

በዮሐ 14:13-14 ላይ ጌታ ኢየሱስ በስሙ የሚለምኑትን ነገር እርሱ እንደሚያደርገው ነበር የተናገረው። "..ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ #እኔ_አደርገዋለሁ.." በሐዋርያት ሥራ 7 ላይ ባለው የእስጢፋኖስ ጸሎት የምናየው ይህንኑ እውነት ነው። ነፍስን የመቀበሉን ተግባር እንዲያደርግለት ወይም እንዲፈጽምለት የጠየቀው ጌታ ኢየሱስን ነው። እስጢፋኖስ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል በማለት በቀጥታ ክርስቶስ ነፍሱን እንዲቀበልለት የጸለየው፥ ጌታ ወደ አብ ከሄደ በኋላ በስሙ የሚለምኑትን የክርስቲያኖችን ልመና እንደሚያደርግ ቃል ስለገባላቸው ነው። ስለዚህ እስጢፋኖስም ይህን ቃል ኪዳን ተንተርሶ ነፍሱን እንዲቀበልለት በቀጥታ ወደ ጌታ ኢየሱስ ጸልዮአል። በሰማይ ሆኖ ልመናን ሰምቶ የሚፈጽመው አምላክ ነውና። ይህ ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚጸለይ የሚያሳይ ግልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ነው።

▶️ ይቀጥላል

7 months, 3 weeks ago

🚩 አብና ወልድ አባትና ልጅ ሆነው ሳለ በመካከላቸው እንዴት የዕድሜ መቀዳደም ላይኖር ቻለ?

🚩 ከአብና ከወልድ ማነው እግዚአብሔር?

(ለአቡ ሐይደር የተሰጠ ምላሽ)

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 Wochen, 2 Tage her

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 Tag, 13 Stunden her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 Monate, 2 Wochen her