እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net

Description
“እውነት ለሁሉ” በዓለም ዙርያ በሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ክርስቲያኖች የተመሠረተ ድረ-ገፅ ሲሆን እስልምናንና ክርስትናን የተመለከቱ መጣጥፎችን፣ መጻሕፍትን፣ ዜናዎችንና የመሳሰሉትን ያስነብባል፡፡ የኦዲዮና የቪድዮ መረጃዎችንም ያቀርባል፡፡ የበለጠ ለማወቅ http://www.ewnetlehulu.org ይጎብኙ።
Advertising
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 2 Monate her

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 5 Monate, 2 Wochen her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 7 Monate, 2 Wochen her

1 month, 2 weeks ago

አራት ዓይነት አፈጣጠር? በሚል ርዕስ የተጻፈውን ይህንን አዲስ ጽሑፍ ያንብቡ። የኢየሱስን ከድንግል መወለድ እንደ አራተኛ የሰው አፈጣጠር መንገድ ለሚቆጥሩት ሙስሊሞች የተሰጠ የማያዳግም ምላሽ ነው https://ewnetlehulu.net/four-creation/

1 month, 3 weeks ago

የድረ-ገጻችን አምደኛ የሆነው ወንድም ሚናስ ሌላ አዲስ ጽሑፍ ይዞልን መጥቷል። ይህንን ግሩም ጽሑፍ ለማንበብ አስፈንጣሪውን ይከተሉ https://ewnetlehulu.net/carmen-christi/

2 months, 1 week ago

እየሱስ እንዴት ከመጥምቁ ዮሐንስ ቀድሞ Exist አደረገ?

ዮሃ 1:30
አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ #ከእኔም #በፊት #ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።

#ነበር የሚለው የግሪክ ቃል፣ "ኤን" የሚልው imperfect verb ሲሆን፣ Aspectቱ ያልተገደበ Continuous past existence የሚገልፅ ነው።

አሁን፣ ከኢየሱስ በፊት ዮሃንስ ቀድሞ ተወልዶ ሳለ፣ እንዴት እየሱስ ከሱ ቀድሞ ነበር ተባለለት?

መልስህ፣ አይ፣ በአምላክ አእምሮ ውስጥ እንጂ በገሃድ አይደለም ካልክ፣ ጥያቄው የሚሆነው፣ በአምላክ አእምሮ ውስጥ አንዱ ከሌላው ቀድሞ ይታወቃል እንዴ? አምላክ ስለ እየሱስ አስቀድሞ አውቆ፣ ስለ ዮሃንስ ያላወቀበት ጊዜ ነበር እንዴ? ይህ ማለት፣ አምላክ ሁልጊዜም ሁሉን አዋቂ አልነበረም ብሎ የሚያምን ሰው የሚያመጣው ትርጉም ስለሆነ ደካማ ሙግት ነው።

Unless of course, the Son of God LITERALLY existed from eternity 🙂

2 months, 2 weeks ago
2 months, 2 weeks ago
2 months, 2 weeks ago

🚩 እሬቻ

"1 በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም ተአምራትም ቢሰጥህ፥ 2 እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም። ሄደን #የማታውቃቸውን ሌሎች #አማልክት እንከተል #እናምልካቸውም ቢልህ" (ዘዳ 13:1-2)

ሰሞኑን እሬቻ የተሰኘው በአል በአዲስ አበባ ሲከበር ነበር። ይህ በአል ሃይማኖታዊ በአል ሲሆን የኦሮሞ ሕዝብ ወንጌልን ሰሞቶ ወደ ክርስትና ከመምጣቱ በፊት የነበረበት ግልጽ ጣዖት አምልኮ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ከማወቁ በፊት የነበረበት ጣዖታዊ ባዕድ አምልኮ ነው

የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው ከግብፅ ምድር የወጡት እስራኤላውያን ካወቁት አምላክ ከእግዚአብሔር/ከያሕዌ በቀር ሌሎች አማልክትን ማምለክ እግዚአብሔር የሚጸየፈው ጣዖት አምልኮ ነው። በእሬቻ በአል የሚመለከው ዋቃና ሌሎቹ ጣዖታት (አቴቴ፥ ቦርንትቻ ወዘተ...) በሙሉ እስራኤል ያላወቃቸው እርኩሳን ጣዖታት ናቸው (ዘዳ 29:17 1ነገ 11:7) እነዚህን ጣዖታት ማምለክ በጣዖት አምላኪነት ያስጠይቃል፥ የእግዚአብሔርንም ቁጣ በምድር ላይ ያመጣል

✍️ መጽሐፍ ቅዱስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ውጪ የሆኑ አማልክት በሙሉ አጋንንት እንደሆኑ ይናገራል፦

"17 #እግዚአብሔር ላልሆኑ #አጋንንት#ለማያውቋቸውም #አማልክት" (ዘዳ 32:17)

"አይደለም፤ ነገር ግን #አሕዛብ የሚሠዉት #ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ #ለእግዚአብሔር እንዳይሠዉ እላለሁ፤ ከአጋንንትም ጋር #ማኅበረተኞች #እንድትሆኑ #አልወድም" (1ቆሮ 10:20)

ስለዚህ አንድ ሰው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደዚህ በአል ከሄደና ተሳታፊ ከሆነ በአምልኮተ አጋንንት እየተሳተፈ ነው። አጋንንትን እያመለከ ነው። የእግዚአብሔር ቃል "..የአጋንንት ማህበርተኞች እንድትሆኑ አልወድም.." እያለ አንድ ሰው ወደዚህ ባዕድ አምልኮ ሄዶ ከተባበረ የእርኩሳን መናፍስት ማህበርተኛ እየሆነ ነው። እግዚአብሔርን ያልሆኑ ሰይጣናትን በቀጥታ እያመለከ ነው

በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ ክርስቲያኖች ከጣዖታት ጋር #በምንም_አይነት መንገድ ሕብረት ሊኖራቸው አይችልም፦

" #ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም #ከጣዖት ጋር ምን #መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ #መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል። በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።" (2ቆሮ 6:16)

➢ ከላይ የተገለጸው አይነት ጣዖት አምልኮ ሁሉ ደግሞ የዘላለምን ሞት እንደሚያስከትል መጽሐፍ ቅዱስ አስረግጦ ይነግረናል፦

"ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም #ጣዖትንም_የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው #በዲንና_በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም #ሁለተኛው_ሞት_ነው" (ራዕ 21:8)

"ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም #ጣዖትንም_የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ #በውጭ_አሉ" (ራዕ 22:15)

"20 መዳራት፥ #ጣዖትን_ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት 21 መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ #የእግዚአብሔርን መንግሥት #አይወርሱም" (ገላ 5:20-21)

"9 ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም #ጣዖትን_የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ 10 ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን #መንግሥት #አይወርሱም" (1ቆሮ 6:9-10)

"ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም #ጣዖትን_የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር #መንግሥት ርስት #የለውም" (ኤፌ 5:5)

▶️ የዚህ አስከፊ እርኩሰት ውጤት የዘላለም ሞት በመሆኑ፥ መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ከጣዖት አምልኮ እንድንሸሽ አዝዞናል፦

"ልጆች ሆይ፥ #ከጣዖታት ራሳችሁን #ጠብቁ" (1ዮሐ 5:21)

"ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ #ጣዖትን ከማምለክ #ሽሹ" (1ቆሮ 10:14)

"ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት #ጣዖትን #የምታመልኩ #አትሁኑ" (1ቆሮ 10:7)

"ነገር ግን #ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም #ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ" (ሐዋ 15:20)

"አምነው ስለ ነበሩ አሕዛብ ግን #ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም #ነፍሳቸውን #እንዲጠብቁ ፈርደን እኛ ጽፈንላቸዋል" (ሐዋ 21:25)

" #ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም #ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ" (ሐዋ 15:28-29)

▶️ እሬቻ ባህል አይደለም። እሬቻ በባህል ስም የሚካሄድ ጣዖት አምልኮ ነው። በባህልና በሌሎች ሰበቦች ስም እግዚአብሔር በልጁ ወንጌል ብርሃን ካዳነንና ካላቀቀን ጣዖት አምልኮ ጋር ተመልሰን መቆራኘት፥ ተቆራኝተንም በዚህ እርኩሰት ረክሰን ነፍሶቻችንን ማጣት የለብንም!

ቃሉ እንደሚለው እግዚአብሔርን #ብቻ እናምልክ!

"ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ። በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ #እግዚአብሔር አቅኑ፥ እርሱንም #ብቻ #አምልኩ፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ያድናችኋል ብሎ ተናገራቸው" (1ሳሙ 7:3)

"ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ #ለአምላክህ ስገድ እርሱንም #ብቻ #አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው" (ማቴ 4:10)

♦️ በክርስቶስ ስም የእሬቻን ጣዖት አምልኮ #እንቢ በሉት! Say #No to irecha Idol Worship in the name of Christ!

4 months, 2 weeks ago

https://t.me/+dpwXmIG4i043OTZk ጥያቄዎቻቸው እና መልሶቻችን፣ ጥያቄዎቻን እና … በዚህ ቻንለ ይስተናገዳሉ ይቀላቀሉ ያጋሩ

4 months, 2 weeks ago

ተመሳሳይ ሙግት ላቀረበ ሌላ ሙስሊም የተሰጠ ምላሽ ማንበብ ትችላላችሁ።

4 months, 2 weeks ago

በቀደምት የቁርአን የእጅ ጽሑፎች ውስጥ ለሚገኙ ልዩነቶች ምላሽ የሚሰጥ በሙስሊሞች የተሰናዳ ጽሑፍ እያነበብኩ ነበር። ምላሹን ያሰናዱት ወገኖች ለአብዛኛው ሕዝበ ሙስሊም አስደንጋጭ ሊሆን በሚችል ሁኔታ በቀደምት የቁርአን የእጅ ጽሑፎች ውስጥ በጸሐፍት የተፈጸሙ ልዩነቶች መኖራቸውን በማመን "እና ምን ይጠበስ" ዓይነት ምላሽ ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም ሙስሊሞች የቁርአን የእጅ ጽሑፎች ምንም ዓይነት ልዩነቶችን እንደማያሳዩ በኩራት ሲናገሩ እንደነበር እናውቃለን። አሁን ደርሰው ግን በቀደምት የቁርአን የእጅ ጽሑፎች ውስጥ ልዩነቶች መኖራቸውን ማመን ጀምረዋል። እንደ ያሲር ቃዲ እና ሻቢር ዓሊ ያሉ ሙስሊም ሊቃውንት አልፈው ቁርአንን በተመለከተ በሙስሊሙ ዓለም እስከ ዛሬ ሲወራ የኖረው ትራኬ ችግር እንዳለበት በግላጭ እስከ ማመን ደርሰዋል። እነዚህ ወገኖች እውነታውን መናዘዝ የጀመሩት ወደው ሳይሆን ለክፍለ ዘመናት ሕዝበ ሙስሊሙን ሲዋሹት ኖረው ክርስቲያን ምሑራን የእጅ ጽሑፎቹን አግኝተው መርምረው ቅጥፈታቸውን ማጋለጥ ከጀመሩ ወዲህ ነው። እግዚአብሔር ዕድሜ ይስጠን እንጂ ገና ብዙ እናያለን። ሙሉ ጽሑፉን ማንበብ ለምትፈልጉ እነሆ። ቅንጫቢውን ከታች በምስል አያይዣለሁ።

7 months, 1 week ago
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 2 Monate her

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 5 Monate, 2 Wochen her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 7 Monate, 2 Wochen her