ግጥም በ ኤዶምገነት

Description
ግጥም ብቻ ቤተሰብ ይሁኑ።

የቻናላችንን የመወያያ ግሩፕ ለማግኘት
https://t.me/slegtmenawga

tiktok.com/@edom_ge

ኤዶምገነት @Edom_Ge
We recommend to visit

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 7 months, 1 week ago

🇪🇹 የምርጥ ሙዚቃዎች መገኛ 🇪🇹

#ካሮት_ሙዚክ✋


ሰለ ቻናላችን ማንኛውንም የፈለጉትን ሙዚቃ እና ያለወትን ቅሬታ
ሆነም አስተያየት በማለት
በዚህ #bot✍ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
???????????
http://t.me/yekonjochumenahriabot
እናመሰግናለን?
Admin
@Aymu_xo

3 weeks, 4 days ago

#ለምን_በሌት_ብቻ .
ቀኑንም ጨምሬ
አንተኑ ለማለም፣
ምነው ቀሪ እድሜዬን
በተኛሁ ዘላለም!
#ኤዶምገነት_ፃፈችው@arifgtmbcha

4 weeks, 1 day ago

"እኔ ሳድን የሷን ጥላ፣
ሄደች ሌላ ተከትላ።"

ብሎ አዎራ ከጄርባዬ
  አንሾካሽኮ እንደፈሪ
    ሀሜት ቢጤ ደራርቦበት፣
አሳምኖ ከወሰደኝ
  እንቅፋቴን እያነሳ
    ብከተለው ምን አለበት?*#ኤዶምገነት_ፃፈችው@arifgtmbcha

1 month ago

***ያቺን ቀን....
ምነው በሰረዛት
  ከህይዎቴ መዝገብ፣
ተገብቶሽ አይደለም
  ዘለፋ እና ስድብ፣
ተደፍቼ ላልቅስ
  ከደጀሰላሙ፣
መቅለሌን ባየና
  በሰጠልኝ ላንቺ
    የይቅርታ ልቡን።

ይህቀረን የምለው
  እንደሌለ አውቃለው፣
ከልቤ ነው ማማ
  መልካሙን መልካሙን
    በሄድሽበት ሁሉ
      እመኝልሻለው፣
ዳግም ከሕይዎትሽ
  ላልገባብሽ ፍፁም
    እምልልሻለው።***#ተፃፈ_በዳዊት@Davunin

3 months ago

#ዶሮን_ሲያነቃቋት .
ላባም ክንፍም አለሽ እንደ አዋፋቱ፣
በግዝፈትም ቢሆን
ንስር ካንች አያንስም ቢለካ ክብደቱ፣
ትበሪያለሽ ተነሽ
ጭልፊትም አትበልጥሽ ካሞራም አታንሺ፣
እንደ ድንቢጦቹ
በረዥሙ ዛፍ ላይ ጎጆሽን ቀልሺ።
.
አሏት
#ኤዶምገነት_ፃፈችው@arifgtmbcha

3 months, 1 week ago

*የተደበቀ ንስሀ
"""""""""""""""""
አስመሳይ ነኝ ወረተኛ
ታውቀኛለህ የኔ ጌታ፣
እየጠራሁ ለማመስገን
አንደበቴም አይፈታ፣

እልልታዬ ጊዜያዊ ነው
ማወደሴ ማሞገሴ፣
በቃልህ ጠግቤ ባድርም
ሽንገላ ነው ጠዋት ቁርሴ፣
አትማርም! ሀጢያት ተንኮል
ማታለል ነው ግብሯ ነብሴ፣
ክብር አድርገህ ያለበስከኝ
ተቀዳዷል ፀጋህ ልብሴ፣

ጎደሎ እምነት የበዛውን
ጾም ጸሎቴን አርገህ መባ፣
ለይስሙላ ደጆህ ስቆም
ብትፈቅድልኝ እንድገባ፣
ምህረትህ አረስርሳኝ
በንስሀ ብታጠብም፣
ዛሬም ልቤ ክፉን ብቻ
በጎን ነገር አያስብም።

ታውቀዋለህ ክንብንቤን
ገመናዬን ሁሉ ገልጠህ፣
ግን አኖርከኝ በም'ረትህ
ከበደሌ እኔን መርጠህ፣

ተዘርግተዋል እጆችህ
ሊቀበሉኝ በይቅርታ፣
ስሼሽ አይተህ አተዎኝም
አንተን መቅረብ ሳመነታ፣
በሀጢያቴ ስቅበዘበዝ
በስህተቴ ስደናቀፍ፣
አትሰለችም በምህረት
በቃሽ ብለህ እኔን ማቀፍ፣

ይቅር ባይ ነህ አትለወጥ
ለዘላለም በጎ መልካም፣
በቤትህ መመላለሴን
ቆጥረህልኝ እንደ ድካም፣
የሚያድነኝ አጣሁ ብልም
ብታነቅም በሾህ መሀል፣
ትርጉም የለሽ ልመናዬ
ጭንቅ ሀዘኔ ተሰምቶሀል።

ትሰማለህ ሹክሹክታዬን
ትረዳለህ የኔን ስሜት፣
አቻየን ካገኘሁ ቤትህ
ይቀናዋል ላኣፌ ሀሜት።

በከበረው አፀድ ቅጥር

ያንደበቷ ቃል የማይጥም
ብኩን ልጁን የሚያስገባት፣
የት ይገኛል ከአንተ በቀር
የሰማይስ የምድር አባት?*#ኤዶምገነት_ፃፈችው@arifgtmbcha

3 months, 1 week ago

ሲያለቅሱ ሳይ
   አይናቸውን ሲያባብሱ፣
ስለናፍቆት
   ስለማጣት እያዎሱ፣
የሚብሰኝ
   የሚያደርገኝ ሆደ ባሻ፣
የሚያስነባኝ
   ከንጋቱ እስከ ማምሻ፣
ናፍቆት አለኝ
   ያላገኘ መጨረሻ።
.
.
ካልሰማሁኝ ሲቃቸውን
   ካላየሁኝ እያነቡ፣
ደርሶ ሊከፋኝ ይቅርና
   እንኳን ልሆን ሆደ ቡቡ፣
ደስተኛ ነኝ ያለምክንያት
   ፈገግታዬ መች ያበቃል፣
ይሄ ጥርሴ አስመሳይ ነው
   ከሳቁ አልፎ ያሳስቃል።*#ኤዶምገነት_ፃፈችው@arifgtmbcha

6 months, 1 week ago

*ጠበቀኝ

መሀላው እውነት ነው
ይህን ውስጤ ያውቃል፣
አላሳፈረኝም
አክብሮት ተገኘ የገባልኝን ቃል፤

"ያቃረበ ፍቅር ሲለዩ ይጠብቃል፣
ያንቀላፋ ትናንት በናፍቆት ይነቃል፡"
እያልኩኝ እስክቀኝ፣
ከአመታት በፊት ከቀጠረኝ ቦታ
ብቻውን ጠበቀኝ።*

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha

6 months, 1 week ago

#የዋህ *"አቅል አሳጣኝ ፍቅር
ልቤን አንገላታው፣
ከያዘኝ ትብትቦ
መች ነው የምፈታው?"

ብዬ ብጠይቀው
ያማክረኝ መስሎኝ፣
ንግግሬን ሳይቋጭ
ገፍቶ፡ ሄደ ጥሎኝ፤

ከዛ ቀን ቡሀላ
ተጋጥሞ አሸንፎ
ተገፋትሮ ጠልፎ፡
እንደተሸለመ
የጉብዝና ሜዳል፣
እኔን ባየ ቁጥር
በኩራት ይሄዳል፣

ጎብለል ጎብለል ይላል
ማ'ረግ እንዳለው ሰው፣
ጀነን ጀነን ይላል
ጌታ ከመንበሩ ንግስና እንዳዋሰው፤

ባያቅ ነው
ቢመስለው
በእኔ የቀለደ የተረማመደ፣
ጓደኛውን እንጂ
እሱን መች ሆነና
ቀልቤ የወደደ።*#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
███▓▒►JOIN ►▒▓███

6 months, 2 weeks ago
11 months, 1 week ago

#ተነበብኩ *.
.
በክንዱ ላይ በግራ እጁ ሰአት ሳስር፣
አየሁ እና ውስብስብ ስ'ል...
አነበብኩት የደሙን ስር፣
ተመለከትኩ ተሰድረው ተደርድረው ፌደላቱ፣
ተነበበኝ ስልተ ለዛው ልበ ምቱ፣
.
ብዳብሰው ቃል አይቼ ደም ይዞት ሲያልፍ፣
ክዱ አሞቀኝ በረድ ጣቴን የእጄን መዳፍ፣
የደሙም ስር አንዲትን ቃል መላለሰ፣
ፍቅር.. ፍቅር..ደረቅ ልቤ ለሰለሰ፣
.
ወርቅ ለበስ የእጁ ሰአት ያሰተተው፣
እልፍ.. እልፍ.. ይባክናል ሰከንድ አይተው፣
እኔም እርፍ..
ንባብ ምኔ ትውት እርግፍ፣ 
ክንዱን ትቼ....
ትከሻውን ጥብቅ እቅፍ፣
.
የኔ ባሰ....
ደሜም ስሩን ጣሰ፣
ዐይኔ እንባ አፈሰሰ፣
አሳዘንኩት ተሳሰረ አንደበቴ፣
አከበረኝ አባበለኝ እንደ አባቴ፣
.
.
ስረጋጋ ሳቅ እራሴን ደነገጥኩ፣
ላነብ ያልኩት አንባቢዋ ተነበብኩ።

ኤዶምገነት ፃፈችው*@arifgtmbcha@arifgtmbcha

We recommend to visit

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 7 months, 1 week ago

🇪🇹 የምርጥ ሙዚቃዎች መገኛ 🇪🇹

#ካሮት_ሙዚክ✋


ሰለ ቻናላችን ማንኛውንም የፈለጉትን ሙዚቃ እና ያለወትን ቅሬታ
ሆነም አስተያየት በማለት
በዚህ #bot✍ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
???????????
http://t.me/yekonjochumenahriabot
እናመሰግናለን?
Admin
@Aymu_xo