★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago
*?* በጉጉት የሚጠበቅ ታላቅ የሙሀደራ ፕሮግራም
? የአዲስ አበባ እምብርት በሆነችው ሜክሲኮ ጀርመን ግቢ ተባረክ መስጅድ በአይነቱ ልዩ የሆነ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እናንተን ይጠብቃል።
ተጋባዥ ዳዒዎች:
1⃣ ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
2⃣ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
3⃣ ኡስታዝ ሳዳት ከማል
ለሴቶችም በቂ እና ምቹ ቦታ ተዘጋጅቷል።
? መኪና ይዘው ለሚመጡ በቂ መኪና ማቆሚያ አለ።
? ቀን: ማክሰኞ ዙልቂዳህ 20 /45 ወይም ግንቦት 20/2016 ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ
☎️ ለበለጠ መረጃ : +251936650001 : +251921543862 : +251941961928 አዘጋጅ: የሸይኽ ጃማዕ እና ተባረክ መስጅድ ወጣቶች!
⚠️ ድንገት መምጣት ላልቻሉ በቴሌግራም የቀጥታ ስርጭት ለመከታተል: ?? t.me/nurmesjed መቅረት አይደልም ማርፈድ ያስቆጫል‼**
ኢስላም ያለ አንድ ሰይፍ አውሮፓን እያጥለቀለቀ ነው
~
ኢስላም በአሁኑ ሰዓት በምእራቡ አለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው። ብሪታንያን እንደ ምሳሌ እንመልከት። መረጃዎቼን የወሰድኩት የኢስላም በሃገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት መስፋፋት እንቅልፍ የነሳው ፀሐፊ “ለንደን 500 ቤ/ክርስቲያናትን ዘግታ 423 አዳዲስ መስጂዶችን ከፈተች” በሚል ርእስ ከፃፈው አርቲክል ሲሆን በዚህ ድረ ገፅ ታገኙታላችሁ። http://yournewswire.com/london-churches-mosques/
ኢስላም ብሪታንያን እየዋጣት ነው ይላል የፅሁፉ ጭብጥ። ይህንን ለማሳየትም የተለያዩ መረጃዎችን ዘርዝሯል። ሀሳቡ ሲሰበሰብ የሚከተለውን ይመስላል:-
በሂያት ዩናይትድ ቤ/ክ በግብፃውያን ኮሚዩኒቲ ተገዝቶ መስጂድ ሆኗል። ቅዱስ ጴጥሮስ ቤ/ክ “መዲና መስጂድ” ተብሎ ተቀይሯል። ብሪክ ሌን መስጂድ ቀድሞ የሜተዲስት ቤ/ክ ነበር።
ህንፃው ያለ ምክንያት አልተቀየረም። ህዝቡም እየተቀየረ ሆኖ እንጂ። አዎ የሰለምቴዎች ቁጥር በእጥፍ አድጓል። ፀሐፊው ዴይሊ ሜይልን አጣቅሶ እንደፃፈው በለንደን እምብርት ውስጥ በጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ቤ/ክ እና መስጂድ ይገኛሉ። ይሄ ምንም አይደንቅም። የሚደንቀው 1,230 ሰዎችን ለማስተናገድ የተዘጋጀው ቅዱስ ጊዮርጊስ በተሰኘው ቤ/ክ ውስጥ ሳምንታዊ ባእልን ለማክበር የተገኘው ክርስቲያ 12 ሰዎች ብቻ መሆናቸው ነው። በሳንታ ማሪያ ደግሞ 20 ብቻ። በአንፃሩ በአቅራቢያው የሚገኘው የብሩን ስትሬት ኢስቴት መስጂድ የገጠመው ችግር ከዚህ የተለየ ነው፣ ለሰጋጆች የሚበቃ ቦታ በማነሱ መጨናነቅ! መስጂዱ 100 ሰዎችን ብቻ የሚያስተናግድ ጠባብ ክፍል ያለው በመሆኑ ለጁሙዐ የሚታደመው ምእመን ጎዳና ላይ ሊፈስ ግድ ሲለው ይታያል። ይህ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ክርስትና በእንግሊዝ ወደ ታሪካዊ ቅርስነት እየተቀየ ሲሄድ ኢስላም ግን የሃገሪቱ የወደፊት ሃይማኖት ይሆናል።
ይህን ግምት የሚያጠናክሩ ተጨባጭ እውነታዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ አንዱ ከሃገሪቱ ሙስሊም ማህበረሰብ ውስጥ ግማሽ (50%) አካባቢው ከ25 አመት እድሜ በታች መሆኑ ሲሆን ከክርስቲያኑ ህዝብ ደግሞ ሩቡ (25%) ከ65 አመት እድሜ በላይ ያሉ አዛውንቶች መሆናቸው ነው። ይህም ከ20 አመታት በኋላ ወደ ቤ/ክ ከሚሄዱ ክርስቲያኖች የሚልቁ ንቁ ሙስሊሞች ይኖራሉ ማለት ነው፤ የናሺናል ሴኪዩላር ሶሳይቲ ዳይሬክቴር የሆነው ከይዝ ፖርቺየስ እንደገለፀው።
በሌላ በኩል የሃገሪቱ ክርስቲያን በየጊዜው ለክርስትናው ጀርባውን እየሰጠ በመሆኑ የተነሳ የቤ/ክርስቲያናቱ ቁጥር በፍጥነት እያሽቆለቀለ ነው። ከ2001 ጀምሮ ለንደን ውስጥ ብቻ 500 ቤ/ክርስቲያናት ወደግል መኖሪያነት ተቀይረዋል። በተመሳሳይ ጊዜ በሃገሪቱ የሚገኙ መስጂዶች ቁጥር ሲታይ ግን በከፍተኛ ፍጥነት እያሻቀበ ነው ያለው።
ከ2012 እስከ 2014 ባሉት አመታት ራሳቸውን የአንግሊካን ክርስትና ተከታዮች እንደሆኑ ሲገለፁ የነበሩ እንግሊዛውያን ቁጥር ከ21% ወደ 17% በማሽቆልቀል በሶስት አመታት ውስጥ ብቻ ቤ/ክርስቲያኗ የ1.7 ሚሊዮን ተከታይ ኪሳራ ደርሶባታል። የሙስሊሙ ቁጥር ግን በአንድ ሚሊዮን አካባቢ እድገት አሳይቷል። ይሄ 5% ከማይሞላው ከሃገሪቱ የሙስሊሙ ቁጥር አንፃር ሲታይ እጅግ ከፍተኛ እድገት ነው። (ይስተዋል! በጁላይ 2015 በተካሄደው የህዝብ ቆጠራ መሰረት የእንግሊዝ ህዝብ ብዛት 64 ሚሊዮን ሲሆን የሙስሊሙ ቁጥር ከዚህ ውስጥ 4.4% ነው።) ሆኖም ግን ግምቶች እንደሚያስቀምጡት በ2020 የጀማዐ (ህብረት) ሶላት ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች ቁጥር ቢያንስ ወደ 683ሺ ያሻቅባል ተብሎ ይጠበቃል። በአንፃሩ ሳምንታዊው በዓል ላይ የሚገኙት ክርስቲያኖች ቁጥር ወደ 679ሺ ይወርዳል ተብሎ ይገመታል።
ወደ ቤ/ክ የሚመላለሰው ህዝብ ቁጥር ወደ መስጂድ ከሚመላለሰው ሙስሊም ህዝብ ጋር ሲነፃፀር በአንድ ትውልድ ዘመን ውስጥ ብቻ ሶስት እጥፍ ያነሰ ይሆናል።
በ2015 በተደረገ ትንተና በሃገሪቱ የብዙ ሰዎች ስያሜ በመሆን ልቆ የተገኘው “ሙሐመድ” የሚለው ስም ነው። ታላላቅ የሃገሪቱ ከተሞች ከፍተኛ የሙስሊም ቁጥር አላቸው። ማንቸስተር 15.8%፣ በርሚንግሀም 21.8%፣ ብራድፎርድ 24.7%። በክርስቲያን ቤተሰብ ከሚወለደው ይልቅ በሙስሊም ቤተሰብ የሚወለደው ህፃን ቁጥርም የላቀ ነው። በብራድፎርድና በሌስተር ከከተማዎቹ ህፃናት ግማሾቹ ሙስሊሞች ናቸው። ከተወሰኑ አመታት በኋላ የከተማዎቹ ነዋሪዎችን የህዝብ ብዛት ስብጥር ይገምቱ እንግዲህ።
በሌላ በኩል ለንደን ውስጥ ብቻ ኦፊሻሊ የሚታወቁ 100 የሸሪዐ ፍርድ ቤቶች አሉ። የሃገሪቱ ህግ አንዳንድ የሸሪዐ ህጎችን እንዲያካትት በሃገሪቱ ታዋቂ የሆኑ ግለሰቦች ሳይቀሩ እየጠየቁ ነው ያሉት። የብሪታኒያ ዩኒቨርሲቲዎችም ኢስላማዊ ህግ እያስተማሩ ነው። (የኛዎቹ ያሉትንም እየዘጉ እንደሆነ ልብ ይሏል።)
በሳዑዲ ዐረቢያ የብሪታኒያ አምባሳደር የሆነው ሲሞን ኮሊስ ኢስላምን ተቀብሎ ወደ መካ በመሄድ ሐጅ አድርጓል። ጠላቶቹ የፈለገ ቢያሴሩ መጪው ዘመን የኢስላም ነው። በሃገራቸው ያለው አንፃራዊ ነፃነት ለኢስላም መስፋፋት ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሆነ የገባቸው ምእራባውያን በነፃ መድረኩ “ፍልሚያ” ኢስላም ልቆ እየወጣ እንደሆነ ቢረዱ ጊዜ በሙስሊሞች ላይ የነፃነት ምህዳሩን ማጥበብ፣ ሃይማኖቱን ጭራቅ አድርጎ የመሳል (islamophobia) ሰፋፊ ዘመቻዎችን መደገፍ፣ እንደ ዳዒሽ (isis) ያሉ ጠርዘኞችን በስውር መደገፍ፣ ኢስላማዊ ሃገራትን ማፈራረስና ሙስሊሞችን በገዛ ቀያቸው መጨፍጨፍ እንዲሁም ፀረ ኢስላም ፖሊሲ የሚያራምዱ አምባገነን ሃይላትን በፀረ ሽብር ዘመቻ ስም ያልተገደበ ድጋፍ ማድረግ አማራጭ ፖሊሲያቸው ሆኖ በገሃድ እየታየ ነው። “ልፋ ያለው በህልሙ ዳውላ ይሸከማል” እንዲሉ መስሏቸው እንጂ የኢስላም ግስጋሴን ምድራዊ ሃይል አይገታውም። ምክንያቱም ከላይ የተገባ መለኮታዊ ቃል አለና።
{ یُرِیدُونَ لِیُطۡفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفۡوَ ٰهِهِمۡ وَٱللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡكَـٰفِرُونَ }
“የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ። አላህም ከሃዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው።” [አሶፍ፡ 8]
[{ የሸሪያ ዕውቀት አስፈላጊነት }]
? በኡስታዝ አህመድ ሙሀመድ አርባ ምንጭ /ገራዶ
➽ በሙሐደራው ከተዳሰሱ ነጥቦች መካከል
➪ ሸሪያዊ ዕውቀትን መፈለግ ያለው ደረጃ
➱ ዕቀትን ለመፈለግ በዋነኝነት ምንድነው የሚያስፈልገን?
➱ የዕውቀት ዓይነቶች
ፈርዱል ዓይን
ፈርዱል ኪፋያ
ሱና
➩ የሸሪያን ዕውቀት መፈለግ ብይኑ ምንድነው?
➩ ዕውቀትን ከማን ነው የምንወስደው
?በወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ
ጁመዓ 4/08/2016
ከመጝሪብ እስከ ኢሻ የተደረገ ዳዕዋ
የጁመዓ ኹጥባውንና ከጁመዓ በሗላ የተደረገውን ዳዕዋ ኢንሻ አላህ እንለቃለን ...
https://t.me/tewuhidWereilu/5270
? ?ረመዷናዊ ምክር - 09??
??*?በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም ሀፊዘሁላህ*
?ስለ "መልካም ስነምግባር " ተዳሷል
?ዛሬ እሮብ ረመዷን 17-1445 (መጋቢት 18-2016) ከዓሱር ሰላት በኃላ ፉሪ አቡበክር አስ'ሲዲቅ መስጂድ የተሰጠ ምክር ነው ።
?
? አላህን መፍራት (ተቅዋ) ማለት ምን ማለት ነው ?
?በወንድም ኑረድን አል ዓረቢ ሃፊዘሁላህ
በወረኢሉ ከተማ
? በዘምዘም መስጅድ
13/06/2016
ከኢሻ ሶላት እስከ ተራዊህ ድረስ
በጥቅሉ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ አቅማችን በፈቀደ ግን ዘወትር ልናርምና ልናሻሽል ይገባል፡፡ በዙሪያችን ያሉ ዐሊሞችንም ምክርና ሀሳብ መስማት ደግ ነው፡፡ መግቢያየ ላይ እንዳልኩት ደካማ ጎን የመሰለኝን ለመጠቆም ይህን አልኩ እንጂ በጎ ስራዎቻችሁን ዘንግቼ አይደለም፡፡ ከዚያ ባለፈ እንዲሁ ችግሩ እኔንም ሌላውን በብዛት ስለሚያጋጥም እንጂ ሁሉንም በጅምላ ልፈርጅም አይደለም፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡ በሀሳቤ የምትስማሙ ካላችሁ እባካችሁን ችግሩ ላለባቸው አድርሱልኝ፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 23/2006)
ለተራዊሕ ኢማሞች (በተለይ ለወጣቶቹ)
----------------------------------
ስለ ስራችሁ መልካምነት ላወራ አልፈልግም፡፡ እሱን “አገር” ያውቀዋልና፡፡ እናም የሚታወቀውን ለማሳወቅ በከንቱ መድከም አልፈልግም፡፡ ይልቁንስ ፅሁፌ እርማት የሚሻ ነገር አለና አትዘንጉት ለማለት ነው፡፡ ነብያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደሚሉት “ዲን መመካከር ነው፡፡” ስለሆነም ከተራዊሕ ኢማሞች በስፋት ይታያሉ የምላቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው አስፍሪያለሁ፡፡
1. የኹሹዕ መቅለል፡- ኢማሞቻችን ላይ ጎልተው ከሚታዩ ድክመቶች በሰላት ላይ ኹሹዕ አለመኖር ነው፡፡ እንደሚታወቀው የሰላት ሩሑ ኹሹዕ ነው፡፡ ኹሹዕ ከሌለ የሰላቱ ህልውና እራሱ ጥያቄ ላይ ወድቋል፡፡ ዛሬ ግን ይሄ ወሳኝ ነገር አደጋ ላይ ነው፡፡ ሰላቱ ሩጫ ሆነ፡፡ ወላሂ በረመዳን መግባት ተደስተን ሳንጨርስ፣ የተራዊሕን ጥዑም ድባብ ሳናጣጥም ውስጣችን ወከባ በበዛበት የአሰጋገድ ስርኣት እየደፈረሰ ነው፡፡ ወላሂ ከስንት መስጂድ ውስጥ ነው ተሸሁድ (አተሒያቱን) ሳንጨርስ የሚሰላመትብን፡፡ እንዴት ተደርጎ እንደሚቀራ አላውቅም፡፡ ሩጠን እንኳን መድረስ አልቻልንም፡፡ እስኪ እራሳችንን ከዚህ ሐዲሥ አንፃር እንገምግመው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መስጂድ ውስጥ ተቀምጠው ሳለ አንድ ሰው ገባና ሰገደ፡፡ ሰላቱን እንደ ጨረሰ ለአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰላምታ አቀረበ፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ተመለስና ስገድ፡፡ ምክኒያቱም አልሰገድክምና!” አሉት፡፡ ተመልሶ ሰገደና መጥቶ ሰላምታ አቀረበ፡፡ “ወዐለይከሰላም፡፡ ተመለስ ስገድ አልሰገድክም!” አሉት፡፡ ሶስት ጊዜ ከፈፀመ በኋላ “በሐቅ በላከህ እምላለሁ! ከዚህ የበለጠ አላሳምርም፡፡ አስተምረኝ” አላቸው፡፡ ይህን ጊዜ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉት፡- “ለሰላት ስትቆም “አላሁ አክበር” በል፡፡ ከዚያም የተገራልህን ያክል ቁርኣን ቅራ፡፡ ከዚያም ሩኩዕ አድርግ፡፡ ሩኩዕ ላይ እስከምትረጋጋ ድረስ፡፡ ከዚያም ቀና በል፡፡ ተስተካክለህ እስከምትቆም ድረስ፡፡ ከዚያም ሱጁድ አድርግ፡፡ በሱጁድ እስከምትረጋጋ ድረስ፡፡ ከዚያም (ከሱጁድ) ቀና በል፡፡ ተስተካክለህ እስከምትቀመጥ ድረስ፡፡ ከዚያም በሰላትህ ባጠቃላይ እንዲሁ ፈፅም፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ነው፡፡) እስኪ አሁን የኛን የተራዊሕ ሰላት በዐይነ-ህሊና እንቃኘው፡፡ ጤነኛ የሚባል ነው? ከሆነ እሰየው!!
2. ቁርኣን ሲሳሳቱ የሚስተዋሉ ችግሮች፡- ወንድሞቼ እውነት ለመናገር ምግባራችሁ ያማረ ምግባር ነው፡፡ ነገረ ግን ኢኽላስ ከጎደለው፣ በማልቀስ “አላህን ፈሪ” መባል ከታሰበ፣ “ጎበዝ ሐፊዝ” ለመባል፣ ወይም “ድምፁ ያምራል” ለመባል የሚሰራ ከሆነ ምንኛ አስቀያሚ ተግባር ነው?! አንዳንዶቹን ኢማሞች ቁርኣን ሲሳሳቱ ማረም ከባድ ነገር ነው፡፡ ከኋላ ያለ ሰው የሚያርማቸውን ጥለው በራሳቸው ችክ ብለው የሚታገሉ አሉ፡፡ (አራሚው ላይ ያለው ችግር በራሱ እንዳለ ሆኖ፡፡) አንዳንዶቹ የጠፋባቸውን ለማግኘት ሲሉ ሰው የሚነግራቸውን ጥለው በጣም ወደ ኋላ ርቀው ይመለሳሉ፡፡ አንዳንዶቹ የሚነገራቸውን ትተው እንደፈለጉ አድርገው ይቀጥላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ መጀመሪያ ረከዐ ላይ የጠፋባቸውን ቦታ ለማረም ቀጣዩ ረከዐ ላይ ተመልሰው የሚታገሉ አሉ፡፡ ይሄ ከሐፊዝ የማይጠበቅ አሳፋሪ ባህሪ ነው፡፡ የተሸከሙት ቁርኣን በቀዳሚነት የሚያጠነጥነው ስለኢኽላስ ነው፡፡ ስህተታችንን ብዙሃን ስለሰማው የምንሸማቀቅ ከሆነ ነፍስያችንን ማሸነፍ አቅቶናል ማለት ነው፡፡ መሳሳቱ እኮ ምንም ክብርን ዝቅ አያደርግም፡፡ አይደለም ሌላ ቀርቶ ቁርኣኑ የወረደባቸውን ነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንኳን ያጋጥም አልነበር እንዴ፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እያሰገዱ ሳለ ቂራኣታቸው ተቀላቀለባቸው፡፡ ሲጨርሱ ኡበይን ረዲየላሁ ዐንሁ “ከኛ ጋር ሰግደሃል?” አሉት፡፡ “አዎ” አላቸው፡፡ “ታዲያ እንዳታስታወስኝ የከለከለህ ምንድን ነው?” በማለት ሊያስታውሳቸው ይገባ እንደነበር ተናገሩ፡፡
3. መሰረታዊ የሰላት ድንጋጌዎችን አለመለየት፡- እያሰገዱ ቢሳሳቱ ምን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የሚያውቁት ስንቶች ይሆኑ? የማካካሻ ሱጁድ እንደተፈፀመው ስህተት ከማሰላመት በፊት ወይም በኋላ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ጠንቅቀው የሚለዩት ምን ያክሉ ናቸው? በአጭሩ አንድ ሰው አንድ ሀላፊነት ላይ እስካለ ድረስ ሀላፊነቱን ባግባቡ እንዲወጣ የሚያስችሉትን መሰረታዊ ተግባራት ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡ ያለበለዚያ ኢማምነት ሀላፊነት ነው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ኢማም ሀላፊ ነው” ማለታቸው ከግምት ይግባ፡፡ እሱ ባግባቡ ሲሰግድ ነው ተከታዮቹ ባግባቡ ሊሰግዱ የሚችሉት፡፡ ኢማሙ አሳስቶ የሚፈፅማቸው ተግባራት በተከታዮቹ (መእሙሞቹ) ይበልጥ የበላሸት እድል አላቸው፡፡ ይሄ ነገር በደንታ ቢስነት ከተፈጸመ ደግሞ ከራሱ አልፎ በሌሎች ስህተት የሚጠየቅበት ሁኔታ ሊኖር ይችላልና መጠንቀቅ የግድ ይላል፡፡
4. ሱናው ላይ ከማነጣጠር ይልቅ ታዋቂ ኢማሞችን ለመምሰል መጣር፡- የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የረመዳን ሰላት እጅግ ያማረ እንደነበር እናታችን ዓኢሻ ተናግራለች፡፡ “ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መመሪያ ነው፡፡” ሩኩዕና ሱጁድ አልፎም ተሸሁድ ላይ አሯሩጣችሁ ቁኑት ላይ 20 ደቂቃ፣ 30 ደቂቃ መገተሩ የጤና ነው? ይህን ልክ ያለፈ ማስረዘም በርካታ ዐሊሞች እንደሚኮንኑት ልናውቅ ይገባል፡፡ እንዳውም አንዳንዶቹ “ቢድዐ ነው” እስከማለትም ደርሰዋልና ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ ደግሞስ ምነው ይሄን ያህል የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የቁኑት ዱዐ ተዘነጋ? ስንቶች ናቸው ዛሬ በዱዐ አጉል ፀጉር ስንጠቃ ውስጥ የሚገቡት? ስንቶችስ ናቸው የዱዐቸው እያንዳንዱ ዐረፍተነገር አንድ አይነት ምት (ሪትም) እንዲኖረው የሚጨናነቁት? ስንቶችስ ናቸው ድምፃቸውን ከፍ ዝቅ እያደረጉ አላስፈላጊ ዜማ የሚያዜሙት? ስንቶችስ ናቸው ሳይመጣባቸው የግድ ለማልቀስ የሚታገሉት? ስንቶችስ ናቸው ገደብ ያለፈ ጩኸት የሚጮሁት? ስንቶችስ ናቸው በዱዐቸው ላይ ልክ ባለፈ መልኩ ዝርዝር የሆነ ነገር የሚተነትኑት? ሰሐባው ዐብዱላህ ኢብኑ ሙገፈል ረዲየላሁ ዐንሁ ልጁን “ጌታየ ሆይ! ጀነት እንደገባሁ በቀኝ በኩል የሚገኝ ነጩን ህንፃ እለምንሃለሁ” እያለ ዱዐ ሲያደርግ ሰማው፡፡ ይህኔ አባት እንዲህ አለው፡፡ “ልጄ ሆይ! አላህን ጀንትን ጠይቀው፡፡ በሱም ከእሳት ተጠበቅ፡፡ እኔ የአላህ መልእክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ከዚህ ህዝብ ውስጥ በጡሃራ እና በዱዐ ድንበር የሚያልፉ ሰዎች ይመጣሉ” ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው፡፡ ሐዲሡን ሸይኹል አልባኒ “ሰሒሕ” ብለውታል፡፡ ሱብሓነላህ!! ኪታብ ላይ ያለውን ጥለን ሰዎች ላይ ያየነውን ለምን እናስቀድማለን? “እከሌ ቦታ እየተሰራ አይደለም ወይ?” የሚል የየዋህ ደሊል ከአስተዋይ ሰው አይጠበቅም፡፡ የትም ቦታ፣ በየትኛውም ሸይኽና ኢማም ከሚሰራው ይልቅ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰሩት በላጭ እንደሆነ ለማንም አይሰወርም፡፡ ታዲያ ምን ሲባል በላጩን ጥለን ዝቅ ያለው ላይ ይህን ያክል ሙጭጭ እንላለን? ምናለ ለቁኑት የሚሰጠው ረጂም ጊዜ መሰረታዊ ለሆኑት የሰላቱ ክፍሎች ተሰጥቶ ተረጋግተን ብንሰግድ?
ጨረቃ ስለታየች በሳዑዲ ነገ ፆም 1 ብሉ ይጀምራል።
ለዚህ ወር ያደረሰን አምላክ የላቀ ምስጋና ይድረሰው
ሙሓደራ ክፍል 189
አዲስ ሙሓደራ ክፍል 01
ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ
የ ሚዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት ?
““የ አብዱል ሀሚድ አልለተሚይ እና ሁሰይን ሙሀመድ ስህተቶች እና ግጭጭቶች…““
? በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሐቲም)
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago