★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 7 months, 1 week ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 1 week ago
"አንድ አሳዛኝ እውነታ አለ እሱም መጅሊሱ የሚመራው በዱኒያ ሰው እንጂ በዲን ሰዎች አይደለም። ለዚህም ምስክር ስራቸውን ተመልከቱ ቁርአን ሀዲስን ነገር ችላ ብለውት በራሳቸው ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ለዱኒያቸው በሚመች መልኩ እንደፈለጉ በዲን ስም ይጨማለቃሉ። እና ከዚህ ነጂስ ማለቴ መጅሊስ ምን አይነት ተስፋ ነው የምታደርጉት?"
ድብቁ የሙስሊም እህቶቻችን የእርቃን ፎቶ ንግድ!
ሰሞኑን ከአንድ የስራ ባልደረባዬ ጋር ስናወራ ዲጂታል መፅሄት ላይ የሠፈረ አንድ ጥናታዊ ፅሁፍ ላከልኝ።
ጸሀፊው ምንተስኖት ደስታ ይባላል በሥነ-ሕብረተሰብ (ሶሲዮሎጂ) ከሐረማያ ዩንቨርስቲ የተመረቀ ሲሆን በአሁን ሰዓት በስንቅ ዩዝ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት ማናጀር ነው ጥናታዊ ፅሁፉም ቴሌግራም ላይ ቻናል ግሩፕ ከፍተው የታዋቂ ሴቶችን ወይንም የድሮ የዝሙት ጓደኞቻቸውን እርቃን ፎቶ እየለቀቁ ብር ስለሚያስከፍሉ የቻናብ ባለቤቶች ያትታል።
ለአንድ እርቃን ፎቶ ከ 3000- 6000 እንደሚያስከፍሉም በጥናታዊ ፅሁፉ ሰፍሯል። እኔን ቀልቤን የሳበኝ እና ከባልደረባዬ የሰማሁት የሙስልም እህቶቻችን ከዚህም በላይ ከፍ ያለ ዋጋ እንዳለው ነው። በእርግጥ ለማመን ቢከብደኝም በገበያው ብዙም ስለማይገኝ ይሁን ለሙስሊም እህቶች ያላቸው መጥፎ እሳቤ በውድ ዋጋ እንደሚቸበቸብ ለዚህ ዋነኛ ተጠቂዎች የአረብ ሀገር እህቶች እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደሆኑ ነው የሰማሁት።
በእርግጥ ግቢ ውስጥ በነበርንበት ሰአቶችም ይሁን ከግቢ ከወጣን በኋላ አንዳንድ ሽምግልናዎችን ታዝበናል። ከዛም አልፎ ህግ ደረጃ የደረሱም ነበሩ። ሽያጭ ደረጃ ይደርሳል የሚል ምንም አይነት ግምት አልነበረኝም።
በእርግጥ በሰላም ጊዜ ፍቅር ውስጥ በነበሩበት ጊዜ የሚላላኩዋቸው ልቅ ምስሎች ናቸው በኋላ በጠብ ጊዜ ህይወታቸውን የሚያመሰቃቅሉት።
ከሁሉም የከፋው ደግሞ. . .
? እህቶቻችን በማያውቁት መንገድ አብረው ከሚኖሯቸው ሙስሊም ካልሆኑ እህቶች ወይንም ዲናቸውን ጠንቅቀው በማያውቁ ሙስሊም እህቶች ተቀርፀው የሚላኩ ምስሎች ናቸው። በተለይ ሙተነቂብ ሲሆኑ ደግሞ በካሜራ ያድኗቸዋል አሳልፈው ለባዕድ ወንድ ይሰጧቸዋል።
? ይሁን እና ብዙ ኡዝታዞች እና መሻይኾች ይህንን ጉዳይ ዘርዘር አድርገው ህዝበ ሙስሊሙን ቢያነቁበት ባይ ነኝ።
ኮፒ
"የክፋት መንገዶች 3 ናቸው።
አመፀኛ ጠባይ ፣ ቅናት እና ስስት።
አመፀኝነት ሰይጣንን ከመታዘዝ ከልክሎታል ።
ቅናት ቃቢል ወንድሙን ሀቢልን እንዲገል አድርጎታል ።
ስስት አደምን ከጀነት አባሮታል።"
?:-ሀሰን አል-በስሪ(ረ.ዐ)
Copy
በሲድናያ እስር ቤት ታሳሪ የነበረ የተጅዊድ መምህር ሸይኽ እንዲህ ይተርካል ፦
ሙሉ እርቃን አድርገው አራቆቱኝ። ፀጉሬንም ላጩት ። በአንድ ክፍል ያጎሩን ሁሉ እርቃናችንን ነበርን። ከሴራሚክ ውጭ የምንቀመጥበት ነገር የለም። ልብሳችን ሀዘን፣ ህመም፣ርሃብና ማቃሰት ነበር። ቦታው ጠባብ ስለነበር እድሌ ሆነና ማደሪያዬ ሽንት ቤቱ ጋር ሆነ። የምበላው የምቀመጠውና የምተኛው እርሱ ጋር ነው።
አንድ ሰው ውሃ ሽንት ሲጠቀም ከሽንቱ የተወሰነው ይረጭብኝ ነበር። ደግነቱ ጥቂት ምግብ እንጅ ስለሌለ «ትልቁን ሽንት» በቀን አንድ ጊዜ ወይም በ2 ቀን ወይም በ3 ቀን አንድ ጊዜ ነበር እስረኞች የሚጠቀሙት። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ሶላት የምሰግደው አይኔን በማንቀሳቀስ ብቻ ነበር ።ሙሉ ለሙሉ እርቃን ሆኜ።
ምክንያቱም በእስር ቤቱ ህግ ሶላት የሚሰግድ ሰው ቅጣቱ የሚገለፅ አይደለም! ሞ ት ከርሱ ይሻላል። የአሰድ የእስርቤት ጠባቂዎች ሲሰግድ ያገኙትን ሰው ወይ ወገቡን ሰብረ ውት፣ ወይ 5 የጎን አጥንቱን ሰብረ ውት ፣ ወይ አይኑን አጥ ፍተ ውት ወይ አጥንቱን ሰብረው ት ወይ እጁን ሽ ባ አድርገውት ወይ እግሩን አንካ* ሳ አድርገውት እንጅ አይገኝም!
ስለሆነም ለሁለት ወር በሽንት ቤት ፣ ሙሉ እርቃን ሆኜ በነጃሳ ቦታ ወደ ቂብላም ሳልዞር አይኔን በማንቀሳቀስ ብቻ ሰገድኩ! አንዳንዴ እየሰገድኩ የአንዱ እስረኛ ሽንት ሲንጠባጠብብኝ ይሰማኝ ነበር! ይላል።
#ላ_ኢላሃ_ኢለላህ!
የዚህ አይነት ሶላት ሰምታችሁ ታውቃላችሁ! ?
የዚህ አይነት ጨካኝ አምባገነን ስርአትስ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?
? ራቁት ሆኖ ከመዝፈን በአላህ ላይ ማጋራት ይበልጣል !
ወንጀል በየትኛውም ሀገር በማንም ቢሰራ ወንጀል ነው ። የሆነ ሀገር ስለተሰራ ከወንጀልነት አያወጣውም ። ሪያድ ላይ በሆነ ፕሮግራም ላይ የነበረ አሳዛኝና አስቀያሜ ተግባር ሶሞኑን ሰዎች ሲያወሩ ሰምቼ ምንድነው ብዬ ለማየት ሞከርኩ ። ድርጊቱ በጣም ፀያፍና አላህን የሚያስቆጣ ተግባር ነው ። የካዕባ ምስል ተሰርቷል ለብሰዋል ለማለት የማያስደፍር ዘፋኝ ሴቶች በምእራባዊያን አኳኋል ያብዳሉ ። የዚህ አይነቱ ተግባር ፍፁም ከኢስላም አስተምሮ የራቀ አስቀያሚ ተግባር ነው ። ይህን ክስተት በተለይ የግብፅና የፍልጢን አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች የሳውዲን መሪዮች ለማክፈርና ለመርገም ምቹ አጋጣሚ ሆኖላቸው አየሁ ።
በጣም የሚገርመው አንድ የእናቱን ፊት የተዋሰ የሚመስል የግብፅ ጋዜጠኛ ከሱረቱል ق የተወሰኑ አንቀፆችን ቀርቶ አላህ ፊት የቂያማ ቀን ስለመቆምና ስለሚኖረው ጭንቅ ከተናገረ በኋላ ለሳውዲ መሪዮች ጥያቄ ያቀርባል ። ሱብሓነላህ እንዴት የሚገርም ለዲን መቆርቆር ነው በጣም ደስ ይላል ። በዚህ መልኩ ወንጀልን መፀየፍና ማውገዝ ከኢስላም መርሆች ውስጥ ዋነኛው ነው ።
ነገር ግን እኔ ለእነዚህ አካላት ጥያቄ አለኝ እነዚህ ወንጀሎች ሳውዲ ውስጥ ሲሰሩ ነው በዚህ መልኩ የምትቆረቆሩትና የምታወግዙት ወይስ ሀገራችሁም ላይ ? ለመሆኑ ከአላህ ውጪ ላለ አካል ለአላህ እንጂ የማይገቡ የአምልኮ አይነቶችን መስጠት አሁን እያወገዛችሁት ካለው ወንጀል እንደሚበልጥ ታውቃላችሁን ? በግብፅ ምድር ላይ የአሕመደል በደዊ ቀብር ከ3 · 5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ጠዋፋ ሲያደርግበት ፣ የቀብሩን አፈር በጥብጦ ሲጠጣ ፣ ከአላህ እንጂ የማይጠየቁ እንደ ከጭንቅ አውጡኝ ፣ አፍያ ስጡኝ ፣ ርዝቄን አስፉልኝ ፣ ዘር ስጡኝ ፣ እና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ለአሕመደል በደዊና ለዱሱቂ ፣ ለዘይነብና ለመሳሰሉ ሙታኖች ሲጠይቁ የት ነበራችሁ? የዚህ አይነቱ የቀብር አምልኮ መንግስታችሁ ባጀት መድቦ ሰራዊት አሰልፎ እንደባአል እንዲከበር ሲያደርግ ታወግዛላችሁ ? ወይስ ይህ በናንተ ሀገር ሲሰራ ወንጀል አይደለም ? ቤቱ በመስታወት የሆነ ሰው በሰው ቤት ላይ ድንጋይ አይወረውርምና ተረጋጉ እንላለን ።
ሳውዲ ላይ የሚሰራ የትኛውም ወንጀል ከወንጀልነት ሊወጣ አይችልም ። በወንጀልነቱ ይወገዛል ። ነገር ግን መሪዮችን ለማክፈር መንገድ አድርጎ መጠቀም የኸዋሪጆች አካሄድ ነውና ተጠንቀቁ ነው የሚባለው ። የሳውዲ መሪዮች ደማቸው አረንጓዴ ነው አይነኩም ለማለት አይደለም ። ከመሪዮች የሚሰራ ስህተት የሚታረምበት መንገድ መልእክተኛው ነግረውናል ። ሰለፎችም ተግብረው አሳይተውናል ። የመሪዮችን ስህተት በኹጥባ ፣ በሙሓደራ ፣ በጋዜጣ ፣ በመፅሄት ፣ በተለያዩ ሚዲያዎች ማሰራጨት የነብዩና የሶሓቦች መንገድ የሚከተሉ ሰዎች አካሄድ አይደለም ።
መጥፎን ነገር ስንለካ በሸሪዓ መለኪያ እንጂ በስሜታችን መሆን የለበትም ። የወንጀሎችን ክብደትና ቅለትም እንደዚሁ ይህን መሰረት አድርገን ነው ሁሉንም በልኩ ማውገዝ ያለብን ። ሳውዲ በሽርክ ጉዳይ አንገት እየቀላች ድግምተኞችንና መተተኞችን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣች ከተለያየ ሀገር መውሊድ ለማክበር የተሰበሰቡ ሱፍዮችን እየበተነችና አሰተባባዮችን በቁጥጥር ስር እያዋለች ማየት ያልቻሉት ወይም አይተው አላየንም የሚሉት በሀገራቸው ላይ ከሚሰራው አመፅና ወንጀል ሊወዳደር የማይችል ወንጀል ሳውዲ ላይ ሲሆን መሪዮች ለማክፈር መንገድ አድርጎ መጠቀም በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም ።
መሪዮች ሲያጠፉ በግል ይመከራሉ ዱዓእ ይደረግላቸዋል ። እንጂ በአደባባይ ከበሮ አይደለቅም ። ምክንያቱም የዚህ አይነቱ ተቃውሞ መሪዮቹ አፀፌታውን እንወስዳለን ብለው የበለጠ ጥፋት ሊመጣ ስለሚችልና መሪና ተመሪ መካከል ያለው መተማመን ጠፍቶ ሀገር ስለሚበጠበጥ ነው ። ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ወንጀል ማንም የትም ቢሰራው ወንጀል ነው ይጠላል ይወገዛል ። ነገር ግን የሚወገዝበት መንገድ ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ መሆን አለበት ነው ትልቁ ነጥብ ።
በአሁኑ ጊዜ ሰዎች የሆነ ሰው ነፍሰጡር ሴትን ገደለ ፣ እናቱን ተገናኘ ፣ ከእህቱ ወለደ ፣ አስገድዶ ደፈረ ፣ ህፃን አረደ ሲባል ቢሰሙ ይሰቀጥጣቸዋል ይዘገንናቸዋል በጣም ያወግዙታል እንደ ጭራቅ ያዩታል ። ይህ ባልከፋ ነበር ። ከባድ ወንጀል ስለሆነ ሊወገዝ ይገባልና ነገር ግን እገሌ የሚባል ሰው የቀብር አፈር በጥብጦ ጠጣ ፣ ቀብር ጋር ሄዶ ጫማውን አውልቆ ስልኩን ዘግቶ እያለቀሰ የሞተውን ሰው እርዱኝ ድረሱልኝ አለ ፣ ሌላኛው ለጂኒ አርዶ ደሙን ጠጣ ፣ ሌላኛው ልጅ ፍለጋ ጠንቋይ ቤት ሄደ ቢባሉ ምንም አይመስላቸውም ። ‼ ይህ ሊስተካከል ይገባል ሙስሊሞች በሽርክና በቀባባድ ወንጀሎች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲያውቁ ማስተማር ያስፈልጋል ።
አላህ በሱ ላይ ማጋራትን በፍፁም አልምርም ሲል ከሽርክ በታች ያሉ ወንጀሎችን ለሻው ሰው እንደሚምር ነግሮናል ። ሽርክ ስራን በሙሉ አበላሽቶ የዘላለማዊ ጀሀነም ባለቤት ሲያደርግ ከባባድ ወንጀሎች ግን አላህ ለሻው ሰው የሚምር ሲሆን ከቀጣውም በወንጀሉ ልክ ተቀጥቶ ከእሳት እንደሚወጣና የጀነት እንደሚሆን ኢስላም ያረጋግጣል ።
ታዲያ ግብፅ ውስጥ ያለው የቀብሮች አምልኮ ሳውዲ ውስጥ ከተሰራው የሴቶች ተራቁቶ መዝፈን ጋር ሲነፃፀር የሰማይና የምድር ያክል ልዩነት አለው ። ነገር ግን ሁሉም ወንጀሎች በመሆናቸው ይወገዛሉ ይሁን እንጂ አይገናኙም ።
ቀልድ ማብዛት ልብ ያደርቃል? ልብ ሲደርቅ ተቅዋ ይጠፋል? ተቅዋ ሲጠፋ ወንጀል መስራት ይበዛል? ወንጀል መስራት ሲበዛ ዱኒያም አኼራም ይበላሻል።
ቀልድ ምታበዙ ወንድም አና እህቶቼ አላህን ፍሩ ከዚህ ተግባራቹ ተቆጠቡ። በተለይ እህቶች ቀልድ ማብዛታቹ የሴትነት ጌጣቹ ማለትም ሀያእ እንዲጠፋባቹ ያደርጋል። ስለዚህ ለዱኒያቹም ለአኼራቹም እንዲሁም ለክብራቹ ጉዳት ያለውን ነገር ራቁ።
? ሬቻ ባህል ወይስ ባእድ አምልኮ አብዛኞች ሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ባአል ነው ይላሉ ። በዚህም ሙስሊሙም ክርስቲያኑም እንዲያከብረው ብዙ ይወተውታሉ ። ለዚህም ይመስለኛል አብዛኛዎች ሙስሊሞች እንደውም ተውሒድን ተረድተናል የሚሉትም ጭምር ይህን ባአል ሲያከብሩ የሚታዩት ። ለማንኛውም ለባአሉ የሚሰባሰቡ አካላት የሚፈፅሙትን ተግባር በማየት ምንነቱን ማወቅ ይቻላል…
? ሬቻ ባህል ወይስ ባእድ አምልኮ
አብዛኞች ሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ባአል ነው ይላሉ ። በዚህም ሙስሊሙም ክርስቲያኑም እንዲያከብረው ብዙ ይወተውታሉ ።
ለዚህም ይመስለኛል አብዛኛዎች ሙስሊሞች እንደውም ተውሒድን ተረድተናል የሚሉትም ጭምር ይህን ባአል ሲያከብሩ የሚታዩት ። ለማንኛውም ለባአሉ የሚሰባሰቡ አካላት የሚፈፅሙትን ተግባር በማየት ምንነቱን ማወቅ ይቻላል ።
በዚህ ባአል ላይ ከሚፈፀሙ ተግባራት ውስጥ የአባ ገዳ ምልክት የሆነውን ዛፍ ቅቤ መቀባት ፣ መሳለም ፣ አጠገቡ ደርሶ ስጁድ መውረድ ፣ እጅ ዘርግቶ መለመን እንዲሁም ወንዝ አጠገብ ስጁድ መውረድ ፣ በሳር ከወንዙ ነክሮ በራስ ላይ መርጨትና የመሳሰሉ ተግባራቶች ይገኙበታል ።
እነዚህ ተግባራት በየትኛው መመዘኛ ነው የፈጣሪ ማመስገኛ የሚሆኑት ? ምናልባት ፈጣሪዬ እንጨት ነው ብሎ የሚያምን ካልሆነ በስተቀር ። እንዴት አንድ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ ሌላ አምላክ የለም ብሎ የምስክርነት ቃሉን የሰጠ ሙስሊም በእንደዚህ አይነት የባእድ አምልኮ ውስጥ ይዘፈቃል ?
እስልምና አላህ ማለት ሁሉን የፈጠረ ፣ የፍጥረተ ዐለሙ አስተናባሪ የሆነ ፣ አምሳያ የሌለው ፣ ያልወለደ ፣ ያልተወለደ ፣ ያማሩ ስምና ባህሪይ ያሉት ፣ በአምልኮት ብቸኛ የሆነ አምላክ እንደሆነ ነው የሚያስተምረው ። አማኞች አላህን የሚገዙባቸው የአምልኮ አይነቶች ፈርድና ሱና ( ግዴታና በፈቃደኝነት የሚሰሩ ) ብሎ ደንግጓል ።
የአላህ መልእክተኛ እኔ ባላዘዝኩት መልኩ አላህን የተገዛ ሰው ስራው ተመላሽ ነው አላህ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ብለው አላህን የምንገዛባቸው የአምልኮ አይነቶች በመረጃ ላይ የተገደቡ መሆናቸውን ገልፀው ትልቅ መርህ አስቀምጠዋል ።
ለአላህ ብቻ የሚገቡ የአምልኮ አይነቶች እንደ ስጁድ ፣ ስለት ፣ ዱዓእ ( ሰላምን ፣ ፍቅርን ፣ ዝናብን ፣ ጤናን ፣ በረከትን ፣ ስኬትን ፣ መለመንን) ከአላህ ውጪ ካለ አካል ከመላኢካም ፣ ከነብይም ፣ ከወልይም ፣ ከጅንም ፣ ከአድባርም ፣ ከቆሌም ፣ ከጨሌም ፣ ከእንጨትም ፣ ከድንጋይም … ወዘተ መፈለግ ከእስልምና የሚያወጣ የሽርክ ተግባርና አላህ የማይምረው መሆኑን ቁርኣንና ሐዲስ አፅኖት ሰጥቶ ገልፆታል ።
ታዲያ እንዴት ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት የሚከናወኑበትን ሬቻ ሙስሊሞች ያከብሩታል ? እንዴትስ ለእንጨት መስገድና ቁርባን እያቀረቡ ችግራቸውን ነግረው ፈረጀት መጠየቅ ባህል ሊሆን ይችላል ? ለወንዝ እየሰገዱ ፈውስ ፍለጋ ከውሀው መረጨት እንዴት ከአምኮትነት ወጥቶ ባህል ይሆናል ? ከሆነም የሽርክና የኩፍር ባህል ነው ሊሆን የሚችለው ። ኢስላም የዚህ አይነቱን አምኮ ፈጣሪን ሳይሆን ሸይጣንን ማምለክ እንደ ሆነ ነው የሚያስተምረውና ሙስሊሞች አኼራችሁን እንዳትከስሩ ተጠንቀቁ !!! ።
"ኢኽዋኖቹ እነ በድሩ ሁሴን እና መሰሎቹ በዳእዋ ስም ዝሙት እንዲስፋፋ ሰበብ እየሆኑ ነው ያም ሴት እና ወንድ በአንድ አደራሽ በኢኽጢላጥ እየጋበዙ ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ እነ ኢልያስ አህመድ እና መሰሎቹ እነኚህ ሰዎች ጥፋት ሲሰሩ እያዩ ማስጠንቀቅ ሲገባቸው አብረዋቸው አንድነት ከነሱ ጋር መመስረታቸው ነው።"
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 7 months, 1 week ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 1 week ago