የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion ? @Share_Home
Last updated 2 weeks, 5 days ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 6 months, 3 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 8 months, 3 weeks ago
ወንድ ልጅ እህቱን የሚቆጣጠራትን እና የሚያስብላትን ያህል ለሌሎች ሴቶችም ሐላፊነት የሚሰማው ቢሆን ኖሮ አንድም ሴት ባልተጎዳች? ነበር።
✍ታዚ
**ከአንድ ሳምንት በፊት ደውላ እንደደበራትና ከቻልኩ እንዳገኛት ጠይቃኝ ነበር!....እኔም በሰዓቱ “ውይ አንቺና ድብርት ግን ስትዋደዱ!... ወይ ለምን ተጋብታችሁ አብራችሁ አትኖሩም እ'? ብዬ ቀለድሁባት
...እሷም “ ሰርግ ደግሰን እወቁልን አላልንም እንጂ ከተጋባንማ ቆየን እኮ"አለችኝ...ያው ሁሌ ስለምንቀላለድ ንግግሯን ከ ቁም ነገር ሳልቆጥረው ሰሙኑን እንደማገኛት ነግሪያት ስልኩን ዘጋሁት!
ከሁለት ቀን በኋላ ደግማ ደወለችልኝ...ጫጫታ ቦታ ነበርኩ!...ስልኬ ሶስት ግዜ እንደ ጠራ አነሳሁትና “ቤቲዬ ጫጫታ ቦታ ላይ ነኝ ያለሁት አይሰማኝም መልሼ ልደውልልሽ!?...አልኳት!
"እዮብ በጣም ከፍቶኛል ምትችል ከሆነ አሁን ቤት ና በናትህ..አለችኝ
ያለሁበት ቦታ ጫጫታ ብዙም እያሰማኝ ስላልነበር “ቆይ ቤቲዬ ከ 5 ደቂቃ በኋላ ደውልልሻለሁ እሺ' ብዬ ስልኩን ዘጋሁት!....ቀኔ አድካሚ ስለነበር መደወሉን ረስቼ ቤቴ እንደገባሁ እራቴን እንኳ ሳልበላ ተኛሁ!...ጠዋት ተነስቼ ስልኬን ሳየው ቴክስት ገብቶልኛል... ቤቲ ነበር የላከችው!..ሰዓቱን አየሁት!... ትናንት ምሽት ሁለት ሰዓት
ነው የተላከው….. “ቻው እሺ እዮብዬ የማልደበርበት ቦታ ሄጃለሁ" ይላል!...ምን ለማለት ፈልጋ ነው? ግራ ገባኝ...ስልኳ ላይ ደወልኩ አይነሳም!...ደጋግሜ ሞከርኩ መልስ የለም!...ጫማዬን አደረኩና የቤቴን በር እንኳ ሳልቆልፍ በፍጥነት ወጣሁ!
የነ ቤቲ በር ላይ ስደርስ ድንኳን ተጥሏል! ልቤ ለሁለት ሲሰነጠቅ ተሰማኝ!...እግሬ እየተንቀጠቀጠ ወደ ውስጥ ገባሁ!...እናትየው የቤቲን ፎቶና የሆነ ወረቀት በእጃቸው ይዘው ግራና ቀኝ በሁለት ሰዎች ተይዘው እያቃሰቱ ቁጭ ብለዋል! ...ሰማይ ምድሩ ተደበላለቀብኝ!...የግዴን “ም… ምንድነው ማዘር'' ብየ ጠየኳቸው!...ምንም መልስ አልሰጡኝም!...ከ ጎን ያለችው ልጅ እምባ በተናነቀው ድምፅ! ልጃቸው አርፋለች አለችኝ!....''ማ ..ቤቲ?'' አልኳት...''አዎ'' አለችኝ!....''እራሷን ከ ማጥፋቷ በፊት ይሄን ወረቀት ፅፋ ነበር'' ብላ ከ እናትየው እጅ ላይ ወረቀቱን ወስዳ ሰጠችኝ!...እጄ እየተንቀጠቀጠ ተቀበልኳትና አየሁት ....''አይዞሽ የሚለኝ ሰው ብቻ ነበር የፈለኩት ....'' ይላል! ምንም አላልኩም.... ወረቀቱን እንደያዝኩ እግሬን እየጎተትኩ ከድንኳኑ ወጣሁ!...በእርግጥ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም!
! ይሄ ፅሁፍ የሚያስተምረን በሂወታችን ችላ የምንለው ነገር እስከ ሂወት ማጣት ድረስ ዋጋ እንደሚያስከፍለን ነው**
✍ታዚ
አንድ ብልህና እውነተኛ ወንድ ሚልዮን ሴቶችን የሚያፈቅር ሳይሆን አንድ ሴትን በሚልዮን መንገድ ማፍቀር የሚችል ነው።
Unkown
✍ታዚ
Emotional Intelligence ምንድን ነው?
Emotional intelligence ('የስሜት ልህቀትን') በተመለከተ ዳንኤል ጎልማን ጥሩ መጽሃፍ ጽፏል::
ለመሆኑ Emotional intelligence ምንድን ነው?
I- የመጀመርያው Self Awarness and recognizing emotion ነው::
ይህም ሁነቶችን ተከትሎ ምን እየተሰማን እንደሆነ ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ማጤንን እና በቃላት መግለጽ መቻላችንን ያመለክታል::
በነገራችን ላይ ስሜቶቻችን የሰውነት ስርዓታችንን የመወሰን አቅም አላቸው:: ታዲያ self awareness መኖሩ አንድም የሰውነት ስርዓትን እንደማስጠበቅ ነው::
እዚህ ጋር Alexythymia የሚባል ነገር እናንሳ:: ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ምን እየተሰማቸው እንደሆነ ይህ ነው ብለው መናገር አይችሉበትም:: በዚህም ምክንያት ብዙ ተግዳሮቶች ሲገጥማቸው ይስተዋላል::
ሌላም በከባድ Trauma ያለፉ ሰዎች ከሚቸገሩባቸው ጉዳዮች አንዱ ስሜታቸውን ማጤን እና መግለጽ አለመቻላቸው ነው:: በስነልቦና ህክምና ወቅትም ይህን ችሎታ እንዲያዳብሩ ይሰራል::
- Managing emotion:-
ስሜቶቻችንን ካጤንን በኋላ መግራት እንድንችል ይጠበቃል:: አሪስቶትል እንደሚለው 'መናደድ ቀላል ነው.. ግን ይህን ንዴት በትክክለኛው ቦታ፣ በትክክለኛው ሰው ላይ፣ ለትክክለኛ አላማ፣ በተመጠነ ሁኔታ መጠቀሙ ችሎታን ይጠይቃል '::
ታዲያ ይህ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ስሜቶቻቸውን አጢነው መግራት የሚችሉ፣ 'የስሜት ልህቀት' ያላቸው ናቸው::
- Motivating oneself-
ስሜቶቻችን የተገሩ ሲሆኑ ያኔ ውስጣዊ ሰላላምን እንቀዳጃለን፤ እምቅ ችሎታዎቻችን መገለጥ ይጀምራሉ:: ስሜታችንን መግራት በመቻላችን የአላማ ሰዎች እንሆናለን፣ ከግልፍተኛ ውሳኔዎች እንታቀባለን፣ እምቅ ችሎታችንን እንረዳለን፣ ከራሳችን ጋር መናበብ ይቻለናል:: ይህ ደግሞ ያበረታናል::
- Recognizing emotions in others
የራሳችንን ስሜቶች ማጤን፣ መረዳት እና መግራት ስንችል፤ የሌሎችን ስሜት ማጤን እና መረዳት ይቻለናል:: Empathy, self-attunment ..የሚባሉ ጽንሰ-ሃሳቦች እዚህ ጋር ይመጣሉ::
የስሜት ልዕልና ላይ ስንደርስ ርህራሄ እና እዝነት ያለን ሰዎች እንሆናለን:: ነገሮችን በሌሎች ጫማ ላይ ሁነን መመዘን እንጀምራለን፤ ለኛ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ስሜትም ግድ የሚሰጠን ሰዎች እንሆናለን:: ከራሱ ጋር መደማመጥ እና መግባባት የቻለ ሰው ከሌሎች ጋር መደማመጥ እና መግባባት አይከብደውም::
- Handling relationships
ከላይ የተጠቀሱ ጉዳዮችን ስናዳብር ተገባቦታችን መልካም ይሆናል፤ ሰላማዊ ግንኙነቶችን መፍጠር ይቻለናል:: ይህም የስራ፣ የትዳር እና ሌሎች የህይወት መስኮቻችንን በአግባቡ እንድንመራ ያስችለናል::
**
አነዚህን ጉዳዮች ከግምት ውስጥ በማስገባት 'Emotional intelligence' ከ 'IQ' አስፈላጊነቱ ቢበልጥ እንጂ አንደማያንስ መረዳት እንችላለን..የሚያስበልጡትም አሉ::
ቢቻል በሁለቱም ልህቀት ቢኖረን መልካም ነው:: IQ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጉ ግን ብዙ ዋጋ ያስከፍላል:: እውቀቱ ኑሯቸው ነገር ግን ማህበራዊ ክህሎታቸው ሳይዳብር ቀርቶ ከሰው ይሁን ከራስ ተግባብቶ መኖር እና መስራት ያቃታቸው ብዙ አሉ::
አሻም አሻም!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
✍ታዚ
*Anxious Preocupied Attachment Style
ከሰዎች ጋር የምታረጉት ማንኛውም አይነት የቅርርብ ወይም የ connection አይነት Attachment Style ይባላል። የእናንተን attachment Style በማወቃችሁ ከሰዎች ጋር በምታደርጉት ማንኛውም አይነት ግንኙነት ላይ የተፈጠሩትን ስህተቶች ማወቅ ትችላላችሁ። አራት አይነት Attachment styles አሉ። ከአራቱም አንዱን ልንገራችሁ። በምትገቡበት Relationship ውስጥ ለዛ ሰው ብቁ እሆን አልሆን እያላችሁ የምትጨነቁ ከሆነ፣ Overthinker ከሆናችሁ ማለትም ከዚያ ሰውጋ ያወራችሁት ነገሮች አእምሯችሁ ላይ በተደጋጋሚ እያወጣችሁ እያወረዳችሁ የምትጨነቁ ከሆነ በራስ፣ መተማመን እናሙዳችሁ አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ እያለባችሁ የምትቸገሩ ከሆነ፣ በዋነኝነት ደግም Constant Reassurance የምትልጉ ማለትም በዛ ሰው ህይወት ውስጥ ቦታ እንዳላችሁ አሁንም አሁንም በተደጋጋሚ ካልተነገራችሁ ሰላም የማይሰማችሁ ከሆተ Anxious Preocupied Attachment Style ትጠቀማላችሁ ማለት ነው።
ይሄን style የሚጠቀሙ ሰዎች በሚገቡበት R/ship ውስጥ የፍቅረኛቸውን ደስታ አስቀድመዎ የራሳቸውን ደስታ ይዘነጉታል። በR/ship ውስጥም እንደሚፈልጉት ያህል ትኩረት ካልተሰጣቸው ይለዩኝ ይሆን እያሉ በጣም ይጨነቃሉ። ስለሚጨነቁም ምንም ያህል የማይገባቸው ነገር Relationship ውስጥ ቢፈጠር ለራሳቸው መቆም ሆነ ያንን r/ship ማቆም ይከብዳቸዋል።
ይህም ባህሪ የሚዳብረው ከልጅነት ሲሆን On and Off ከሆኑ አሳዳጊዎች ካደጉ ማለትም ይህ የሚሆነው ፍቅራቸውን አንዴ ከሚሰጡ አንዴ ደገሞ ዝም አሳዳጊዎች ነው።Incosistent በሆነ ቤተሰብ ውስጥ ማደግ ማለትም ከአሳዳጊዎቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ጥሩ የሚባል ቢሆንም አሳዳጊው ልጁ በዛ ሰዓት የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ሁሉንም ሰዓት አልተገኘም ወይም ደግሞ በተደጋጋሚ በሚፈለግበት ቦታ ላይ አልተገኘም ማለት ነው። ይህ ድግግሞሽ አለው እናም ይህ ድግግሞሽ ነው የልጁን አዕምሮ Programming የሚሰራው ። ስለዚህ ከእንዲህ አይነት Attachment Style ካላቸው ልጆች እጅግ በጣም ለሰው የሚሰጡት ቦታ ከፍ ያለ ይሆንና ግን ሁሌ ሰው ትቶኝ ሊሄድ ይችላል የሚል ፍራቻ ኖሯቸው ነው የሚያድጉት።
ለዚህም መፍትሔ የሚሆነው ትኩረታቸውን ከሌላው አንስተው ወደ ራሳቸው እንዲያደርጉ ራስን በማሰልጠን ነው።
✍️በኃይሉ(ታዚ*)
Attachment styles
➖➖➖➖➖➖➖
ትልቆች ሁነን ስለራሳችን እንዲሁም ስለሌሎች የሚኖረን አተያይ እና ተግባቦት: በልጅታችን ከወላጅ/አሳዳጊዎቻችን: በተለይም ከእናታችን ጋር የሚኖረን ግንኙነት እና መቀራረብ መሰረት የሚቃኝ ነው::
በተለይም የመጀመርያዎቹ 3 አመታት ይህ Attachment የሚከወንበት ወሳኝ ጊዜ እንደሆነ ይነገራል::
ይህ Attachment ካደግን በኋላ በሚኖሩን ግንኙነቶች ይገለጣል::
1️⃣ Anxious/Preoccupied
ስለራሳቸው አነስተኛ ግምት ያላቸው ናቸው:: ከራሳቸው ይልቅ ሌሎችን አግዝፈው ያያሉ::
ለራሳቸው በሚኖራቸው አነስተኛ ግምት ምክንያት : በጓደኝነት መሃል መከዳትን አብዝተው ይፈራሉ::
ዘወትር ጓደኞቻቸው እንደማይከዷቸው መተማመኛን እንዲሰጧቸው ይሻሉ:: ይህ ጓደኞቻቸው ላይ መታከትን ሊፈጥር ይችላል::
አብዝተው Reassurance ይፈልጋሉ::
2️⃣ Avoidant/Dismissive
ለራሳቸው የተሻለ ምልከታ አላቸው:: በአንጻሩ ለሌሎች አሉታዊ ምልከታ ይኖራቸዋል::
ብቻቸውን መሆንና ነገሮችን በራሳቸው ማድረግን ይመርጣሉ::
ከሌሎች ሰዎች ጋር መቀራረብን እንደ ጥገኝነት ሊቆጥሩት ይችላሉ::
በዚህም ምክንያት ጋብቻንና ሌሎች መወዳጀቶችን ሲሸሹ ይስተዋላል::
3️⃣ Disorganized
ስሜታቸውን መግራት አይችሉበትም፤
በመፈለግና አለመፈለግ መሃል ይዋልላሉ
ስሜትን ለማጋራት ይሰስታሉ ምክንያቱም እንጎዳለን ብለው ስለሚያስቡ
ግልፍተኝነት፣ ስሜትን ለመቆጣጠር መቸገር፣ ራሳቸው ላይ ጉዳት ማድርስ(በሰበብ አስባቡ ራስን ለማጥፋት ማንገራገር እንዲሁም መሞከር) እና የስሜት መለዋወጦችን መለያ ባህርያቸው ናቸው::
4️⃣ Secure:
የተረጋጉ እና በሚኖራቸው ግንኙነቶች መማመን ያላቸው ናቸው::
ግንኙነቶቻቸው የተረጋጉ እና ሰላማዊ ናቸው::
ነገሮችን ከስሜታዊነት ይልቅ በጥበብና በብልሃት ስለሚፈቷቸው የስነልቦና ልዕልናቸው ከፍ ያለ ነው::
የናንተ Attachment style የቱ ነው?
✍️ታዚ
1."የፍቅር ስሜቶች ልክ እንደ አውሎ ንፋስ ናቸው። መቼ ፣የት ና ወዴት እንደሚነሱ ማንም አያውቅም።"
ፓትሞር
2."ፍቅር ዕርቃኑን ያለ ህፃን ማለት ነው። ታዲያ ለገንዘብ ማስቀመጫ ኪስ ያለው ይመስላችኋል?"
---ኦቬድ
3."ዝነኛው ፍቅር ሆይ አንዳንዴ አውሬን ሰው ታደርገዋለህ። አንዳንዴ ደግሞ ሰውን ወደ አውሬነት ትለውጣለህ።"
--ዊሊያም ሼክስፒር
4."ከጌታዬ ሶስት ነገሮችን አጥብቄ እፈልጋለሁ አንድ ጥበብ፤ ሁለት ጥንካሬ፤ ሦሥት ፍቅር። ከነዚህ ከሦስቱ የበለጠ የምሻው ግን ፍቅርን ነው።ፍቅር ሲኖረኝ ሁሉም ነገር አለኝ ነፃነትም ቢሆን። "
---ማርቲን ሉተር ኪንግ
5."ሴቶች ልታይ ልታይ ባይ ለብ ለብ ወንድ ይፈልጋሉ። ወንዶች ደግሞ ሴቶች የሚፈልጉትን ለመሆን መከራቸውን ያያሉ።"
--ማርጋሬት ሚድ
✍tazi
የመኖር ጥበብ
በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ታዲያ ይህ ሰው፣ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በኑሮው ከሚገጥመው ችግር የተነሳ፣ ሁልጊዜም በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም።
አንድ ቀን ግን ከሚኖርበት ሥፍራ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ከተማ ዘንድ፣ አንድ ታላቅ የኃይማኖት አባት ከአጃቢዎቻቸው ጋር እንደመጡ ይሰማል። ይህን ጊዜም እኚህን አባት ማግኘት አለብኝ ብሎ ይወስናል።
በመሸም ጊዜ እኚህ አባት ያሉበት ሥፍራ ይደርስና፡ እሳቸውን ለማግኘት ቁጭ ብሎ መጠባበቁን ይይዛል። ከረጅም ቆይታ በኋላም እኒያን አባት ያገኝና ጥያቄውን ይጀምራል።
"አባቴ፥ በህይወቴ ፍፁም ደስተኛ አይደለሁም፤ በቃ ሁሌም በችግር የተከበብኩኝ ሰው ነኝ... በዚህ በኩል የሥራ ጭንቀት፣ በዚህ ደግሞ የጤና ቀውስ፣ በዛላይ የቤቴ ውስጥ ችግር... ብቻ ተደማምሮ እረፍት ነስቶኛል፣ ደስታም ርቆኛል፤ እባክዎትን አንዳች የመፍትሄ ሀሳብ ይስጡኝና፡ ደስተኛና የሰላም ኑሮ እንድኖር ይርዱኝ!"
ሽማግሌውም ፈገግ ብለው "ልጄ፥ ለችግርህ ነገ ጠዋት ላይ መፍትሄ እሰጥሃለሁ፤ ነገር ግን አሁን ባዝህ፣ ጥቂት የኔን ሥራ ልትሠራልኝ ትችላለህን?" አሉት። ሰውዬውም በዚህ ይስማማል።
እሳቸውም ቀጥለው፦ "በጉዞአችን የያዝናቸው መቶ ግመሎች በዚህ ይገኛሉ፤ እናም ዛሬ ምሽት የነርሱን ነገር አደራውን ላንተ ሰጥቻለሁ፤ ሁሉንም ግመሎች እመሬት ላይ ካስቀመጥክ በኋላ ወደ መኝታ መሄድ ትችላለህ"። አሉት።
ይህንንም ብለው ወደ ድንኳናቸው ሲያቀኑ፣ ሰውዬውም የታዘዘውን ሊያደርግ ምሽቱን ግመሎቹ ዘንድ አመራ።
በቀጣይ ቀንም ሽማግሌው ማልደው ወደ ሰውዬው በማቅናት "ልጄ፥ ሌሊቱን ጥሩ ተኝተህ አደርክ?" ብለው ይጠይቁታል።
ሰውዬው ግን ኅዘን በተሞላበት ስሜት ሆኖ "አባቴ፥ ለዐፍታ እንኳን እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነው ሌሊቱ የነጋው። ብዙ ለፋሁ፣ ብዙም ጣርኩኝ፡ ይሁንና በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች እንዲቀመጡ ማድረግ አልቻልኩም። አንዳንዶቹ ራሳቸው ይቀመጣሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ላስቀምጣቸው ብሞክርም እንኳን አይቀመጡም፤ አንዱ በዚህ በኩል ሲቀመጥ፡ በሌላ በኩል ያሉት ይነሣሉ"።
ይህን ጊዜ ሽማግሌው ፈገግ እያሉ እንዲህ አሉ፦ "ካልተሳሳትኩኝ፡ ይህ የሆነው ትላንት ማታ ነው አይደል?"
- ራሳቸውን በራሳቸው ያስቀመጡ ብዙ ግመሎች ነበሩ!?
- ብዙዎቹ ደግሞ በአንተ ጥረት ሊቀመጡ ችለዋል!?
- ቀሪዎቹ ልታስቀምጣቸው ሞክረህ እንኳን አልተቀመጡም፤ ከቆይታ በኋላ ግን በጊዜ ውስጥ ራሳቸውን አስቀምጠው አግኝተሃቸዋል!?
ሰውዬውም፦ "አዎ! አዎ!...ትክክል!" ብሎ መለሰ።
ሽማግሌውም ቀጠሉና፦
"ስለዚህ አሁን አንድ ነገር ተረዳህን?፤ በህይወት ያሉም ችግሮች እንዲሁ ናቸው...
- አንዳንዶቹ በራሳቸው መፍትሄ ያገኛሉ።
- አንዳንዶቹ በአንተ ጥረት መፍትሄ ያገኛሉ።
- አንዳንዶቹ ደግሞ በአንተ ጥረት እንኳን አይፈቱም፤ እነዚህን ችግሮች ለጊዜ ተዋቸው። ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ በራሳቸው ይፈታሉና/መፍትሄ ያገኛሉና/።
ትላንት ማታ፣ ምን ያህል ብትሞክር በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች ማስቀመጥ እንዳልቻልክ ትምህርት ወስደሃል። አንዱን ግመል በዚህ ጋር ስታስቀምጥ በሌላ በኩል ያሉት ይነሣሉ። ልክ እንዲሁ፤ እዚህ ጋር አንዱን ችግር ፈታሁ/ተፈታ ስትል እዛ ደግሞ ሌላ ችግር ተነስቶ ይጠብቅሃል። ህይወት እንዲህ ነውና!። ችግሮች የህይወት አካል ናቸው፤ አንዳንድ ጊዜ ጥቂት፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በርካታ ችግሮች ይኖራሉ። ይሄ ማለት ግን ስለነሱ ሁሌ ማሰብ አለብህ ማለት አይደለም። እነሱን ለጊዜ እየተወክ ወደፊት ተጓዝ። በእያንዳንዱ እርምጃም ወደ ዓላማ-ህይወት (Purpose of life/self- realization/) ማደግን ተማር።
ልብ በል፤
• አንዳንድ ጊዜ፤ ደስታን ለማወቅ በኅዘን፣ ዝምታን ለማድነቅ በጩኸት፣ የመኖርን ዋጋ ለማወቅ ባለመኖር መንገድ ልታልፍ ግድ ነው።
ይኸውልህ፤ ህይወት በተቃርኖ የተሞላች ነች። እያንዳንዱ ስኬት ከሸክም ጋር ነው የሚመጣው። ትልቅ ቤት ማግኘት ስኬት ሲሆን፣ ብዙ የሚጸዳ መኖሩ ሸክም ነው። ልጅ መውለድ ስኬት ሲሆን፣ በእኩለ ሌሊት መነሳቱ ሸክም ነው። ባለስልጣን መሆን ስኬት ሲሆን፣ የህዝብን ጩኸት ማስተናገዱ ሸክም ነው።
ብዙ ጊዜ የምንሠራው ስህተት- ስኬቱን ያለ ሸክም ከመፈለግ የሚመጣ ነው። ይህ ግን እውነታው አይደለም። የሚመጡት በጥቅል (package) ነው። ዋናው ነገር፣ ሸክሙም እያለ በስኬቱ/በበረከቱ መደሰትን መማሩ ላይ ነው!!
✍tazi
አታድርጉት!
• ገንዘብን ለማግኘት ብላችሁ ጤንነታችሁን አትሰው!
• ሰዎችን ላለማጣት ብላችሁ ከራሳችሁ ጋር አትለያዩ!
• ስልጣንን ለመጨበጥ ብላችሁ ከሕብረተሰብ ጋር አትጣሉ!
• አጉል ልማዳችሁን ላለመልቀቅ ብላችሁ ከሕይወት መስመር አትውጡ!
• ላለመሸነፍ ብላችሁ ቤተሰባችሁን አታፈራርሱ!
ይቅርባችሁ!
✍ታዚ
? ቅብጥብጡ ውሻ
✨የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡
?በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡
የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡
?የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን እንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡
?ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡
ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . .
?ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡
ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!
ዶ/ር እዮብ ማሞ
✍tazi
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion ? @Share_Home
Last updated 2 weeks, 5 days ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 6 months, 3 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 8 months, 3 weeks ago