መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪

Description
@zemarian የቀደመው ቻናል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡

ለማንኛውም አስተያየት ..@zemariiii_bot
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago

1 year, 4 months ago

#ከንስሐ_ርቀን_ይቅርታን_አናገኝም

ንስሐ ለተጠመቁ ሰዎች ከጥምቀት በኋላ የተሰጠች ሀብት ናት፡፡ ይህንንም የሚያስረዳ ነገር በጥምቀት ከእግዚአብሔር ከምትገኝ ልጅነት ሁለተኛ ማዕረግ ናት፡፡ በሃይማኖት ገንዘብ ያደረግነው  የመንግስተ ሰማይ መያዣ ከናት፡፡

በንስሐ ምክንያት የእግዚአብሔርን ቸርነት እናገኛለን፡፡ ንስሐ ለሚሿት ሰዎች የተከፈተች የይቅርታ በር ናት፡፡ በንስሐ በርነት ከፈጣሪ ወደሚገኝ ቸርነት እንቀርባለን፡፡ መከላከያ ከሚሆን ከንስሐ ርቀን ይቅርታን አናገኝም፡፡

አምላክ የጻፈው መጽሐፍ እንደተናገረ ሁላችን በድለናልና ያለ ዋጋ በይቅርታው ከኃጢአት እንነጻለን፡፡ ንስሐ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በሃይማኖትና በልቡና የምትገኝ ሁለተኛ ጸጋ ናት፡፡ ሀብታተ ምስጢራት ከሚገኙበት ከመንፈሳዊ ፍቅር እስክንደርስ ድረስ የሚጠብቀን መንፈሳዊ ዕውቀት ነው፡፡

(ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ)

1 year, 5 months ago

ስድብ ኃጢአት ባይሆን ኖሮ መሰደብ የሚገባው ዲያቢሎስ ነው:: ፍጥረት ሁሉ ስድብ ቢያዋጣ ለዲያቢሎስ የሚመጥን አይሆንም:: የክፋት ምንጭ ለሆነ ለእርሱ ሁሉም ክፉ ቃል መገለጫው ነው::
ይሁንና ቅዱስ ሚካኤል ይህንን ክፉ ጠላት ደፍሮ አልሰደበውም:: "እግዚአሔር ይገሥጽህ!" አለው:: (ይሁ 1:9)

እንደ ሚካኤል ንጹሕ በእኛ ዘን ማን አለ? እንደ ዲያቢሎስስ ክፉ በእኛ ዘንድ ማን አለ?

መልእክቱ ግልጽ ነው:: አንሆንም እንጂ እንደ ሚካኤል ንጹሕ ብንሆን እንኳን እንደ ሰይጣን የከፋን ሰው እንኳን መሳደብ አንችልም::

የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከሥልጣኑ የወረደውን የቀድሞውን የመላእክት አለቃ ዲያቢሎስን አንድም ክፉ ቃል አልተናገረውም:: አንዱ ከሥልጣኑ ወድቆ ሌላው ሲሾም አዲሱ ተሿሚ ስለወደቀው ምን እንደሚል እናውቃለን:: አንደበቱ ስድብ በመናገር ያልረከሰው ቅዱስ ሚካኤል ግን ወድቆ በማያርፈው ዲያቢሎስ ላይ የስድብን ቃል አልተናገረም::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Deacon Henok Haile
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ

1 year, 5 months ago

Share 'አመ ፲፱ ለሐምሌ ገብርኤል ሥርዓተ ማኅሌት (1).pdf'

1 year, 6 months ago

ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን
እንኳን አደረሰን!

በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ እንጨት፣ ያለ ጭቃና ያለ ውኃ በሰኔ ፳ ቀን ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሦስት ድንጋዮች ቤተ ክርስቲያን ያነጸበት ዕለት የከበረ በዓል ነው፡፡ ይህም የሆነው ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ገብተው በክርስቶስ ስም አሳምነው ብዙ አሕዛብን ካጠመቁ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩላቸው ፈልገው በተነሡበት ጊዜ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያኗንም ለመሥራትም ለርእሰ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ላኩበት፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ በርናባስ ጋር በኢየሩሳሌም ተገናኙ፤ ቅዱስ ዮሐንስም ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር አብሮ መጥቶ ነበር፡፡

በዚያም በአንድነት ሱባዔ ይዘው በለመኑት ጊዜ ጌታችን የሞቱትን አስነሥቶ፣ ያሉትንም ጠርቶና ቅዱሳን ሐዋርያትን በፊልጵስዩስ ሀገር ሰብስቦ ‹‹በእናቴ በድንግል ማርያም ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ
የሚሠራውን የአብያተክርስቲያናት ሥራ ላሳያችሁ፤ ሥርዓቱንም ላስተምራችሁ ሰብስቢያችኋለሁ›› ብሎ ወደ ምሥራቅ ይዟቸው ወጣ፡፡ (መጽሐፈ ሥንክሳር ሰኔ ፳ ቀን)

በዚያ ሥፍራ የነበሩትን ሦስት ድንጋዮችንም የተራራቁትን አቀራርቦ፣ ጥቃቅኑን ታላላቅ አድርጎ ቁመቱን በ፳፬፣ ወርዱን በ፲፪ ክንድ ለክቶ ለቅዱሳን ሐዋርያት ሰጣቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ድንጋዩ በእጃቸው ላይ እየተሳለ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ፈጽመውታል፡፡ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራውም ጌታችን በዐረገ በ፲፱ኛው፣ እመቤታችን በዐረገች በ፬ኛው ዓመት ሰኔ ፳ ቀን ሲሆን በማግሥቱ በ፳፩ኛው ቀን ኅብስት ሰማያዊ፣ ጽዋዕ ሰማያዊ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ወረደ፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችን ጋር ከሰማየ ሰማያት መጥቶ እመቤታችንን ታቦት፣ ሐዋርያትን ልዑካን አድርጎ፣ እርሱ ሠራዒ ካህን ሆኖ ቀድሶ አቆረባቸው፡፡

ከዚያም በኋላ ‹‹እምይእዜሰ   አንትሙኒ  ከመዝ ግበሩ፤  ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንደዚህ አድርጉ›› ብሎ  አዟቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ቁመት የ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል ነው፤ ወርዱ ደግሞ የ፲፪ቱ ሐዋርያት ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴ አምሳል ምሳሌ ናቸው፤ ከታች አቀማመጣቸው ሦስት፣ ከላይ ሕንጻቸው አንድ መሆኑ የሥላሴን ሦስትነትና አንድነት ያስረዳል፡፡ የሠሩትም ሦስት ክፍልም የመጀመሪያው ክፍል የታቦተ አዳም፣ ሁለተኛው የታቦተ ሙሴ፣ ሦስተኛው የታቦተ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ አንድም የሦስቱ ዓለማት ማለትም የጽርሐ አርያም፣ የኢዮር፣ የጠፈር ምሳሌ ነው፡፡ አንድም አንደኛው የኤረር፣ ሁለተኛው የራማ፣ ሦስተኛው የኢዮር አምሳል ነው፡፡ በኤረር፡- መላእክት፣ መኳንንት፣ ሊቃናት፤ በራማ፡- ሥልጣናት፣ መናብርት፣ አርባብ፤ በኢዮር፡- ኃይላት፣ ኪሩቤል፣ ሱራፌል ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ዘጠኙ ነገደ መላእክት የዘጠኙ መዓርጋተ ቤተ ክርስቲያን (መዓርጋተ ክህነት) አምሳል ሲሆኑ ይኸውም መላእክት የመዘምራን፣ የመኳንንት የአናጕንስጢሳውያን፣ ሊቃናት የንፍቀ ዲያቆናት፣ ሥልጣናት የዲያቆናት፣ መናብርት የቀሳውስት፣ አርባብ፣ የቆሞሳት፣ ኃይላት፣ የኤጲስ ቆጶሳት፣ የሱራፌል፣ የጳጳሳት፣ የኪሩቤል እንዲሁም የሊቃነ ጳጳሳት ምሳሌዎች ናቸው፡፡

ይህም በምድር የሚኖሩ ደቂቀ አዳም ከቅዱሳን በቀር ወደ ሰማይ መውጣት እንደማይቻላቸውና ከመዘምራን እስከ ጳጳሳት ድረስ ያሉ ካህናትም ከእነርሱ በላይ ያሉትን መዓርግ መሥራት  እንደማይቻላቸው ያስረዳል፡፡ እንደዚሁም መላእክት ወደ ምድር መውረድ እንደሚቻላቸውና ሊቃነ ጳጳሳትም ከእነርሱ በታች ያሉ ካህናትን ተልእኮ መፈጸም እንደሚቻላቸው ያስረዳል፡፡ በጽርሐ አርያም መንበረ ብርሃን፣ ታቦተ ብርሃን፣ መንጦላዕተ ብርሃን እንደዚሁም ፬ ፀወርተ መንበር፣ ፳፬ አጠንተ መንበር (መንበሩን የሚያጥኑ) መላእክት አሉ፡፡ ጽርሐ አርያም  የመቅደስ፣ መንበረ ብርሃን የመንበር፣ መንጦላዕተ ብርሃን የቤተ መቅደሱ መጋረጃ፣ ፬ቱ ፀወርተ መንበር የ፬ቱ ሊቃነ ጳጳሳት ወይም የመንበሩ እግሮች፣ ፳፬ቱ አጠንተ መንበር የጳጳሳት (የኤጲስ ቆጶሳት) ምሳሌዎች ናቸው፡፡

ምንጭ፡-መጽሐፈ ስንክሳር፣ ሰኔ ፳  ቀን እንዲሀም መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ገጽ ፫፻፵፱-፫፻፶፩

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

1 year, 6 months ago

Watch "#ፈተና_ቢገጥማት #በዘማሪት_የማርያም_ብሥራት 
#ፍሬ_ሃይማኖት_ሰ/ት/ቤት #መዝሙረ #ማኅሌት" on YouTube
https://youtu.be/ZspVvC9NMy0

YouTube

#ፈተና_ቢገጥማት #በዘማሪት_የማርያም_ብሥራት #ፍሬ_ሃይማኖት_ሰ/ት/ቤት #መዝሙረ #ማኅሌት

@zemariian on tg ***🌍***

1 year, 6 months ago
1 year, 6 months ago
1 year, 6 months ago

https://t.me/zemariian/16199

Telegram

መዝሙረ ማኅሌት

https://youtu.be/U2m-ufd\_oGc

1 year, 7 months ago
  • ++ እግዚአብሔር ዐረገ +++ (መዝ 46:5)

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ዕርገቱ እንዲህ አለ "ለምድርም እንኳን የተገባን  የማንመስል እኛ ዛሬ ወደ ሰማይ ከፍ አልን፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም የእርሱ አካል ብልቶች እንደመሆናችን ከሰማይ በላይ ከፍ አልን፡፡ ወደ ንጉሣዊ ዙፋንም ደርሰናል፡፡"  (Homily II on the Acts of the Apostles)

አምላክ ሆይ ከከፍታችን ወርደን ለነፍሳችንም ለሥጋችንም በማይጠቅመን የዘረኝነት ነገር ተጠምደናል፡፡ ከፍ ባደረግከን የሰውነትና የክርስትና ከፍታ ልክ ከፍ ለማለት አብቃን!!

በትሕትና ከሰማይ ወርደህ በልዕልና ተዋሕዶ  ሥጋችንን በዕርገት ከፍ እንዳደረግህ ይህን የሰጠኽንን ሰው የመሆን ከፍ ሲልም አንተን የማመን ጸጋ እናውቅ ዘንድ አንተ እርዳን!! 

ልበ አምላክ ዳዊት  “በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።” ብሎ እንደዘመረለት በታላቅ ኃይልና ሥልጣን በምሥራቅ በኩል በይባቤ መላእክት ወደ ሰማይ ለወጣ ለድንግል ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይሁን!! (መዝ 68:33)
ዕለተ ዕርገት

1 year, 7 months ago

“ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዲህ አለ:-

በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ ... የተራ ቀለማት
መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡

የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ስለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡

እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር? እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ! ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ!

ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤
የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ
ይሻለኛል? ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳልሆንሁ
በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ
መናገር ያምረኛል፡፡...

ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን ከንፈሮች በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት! ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች’

(የብርሃን እናት ገፅ 352)

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago