★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago
ለምንድን ነው የምንጾመው?
እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡ ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው? በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን? በየቀኑ እግዚአ ብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታ ወቀ የተረዳ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ [በመጾማችን - በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?
በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾ ማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡ ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡-
#አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች - ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ - አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡ በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገ ውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡
#ኹለተኛው ምክንያት ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸ ው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋ ረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ አጥቶ የመራብ ትር ጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡ በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡
ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድ ናስብ ያስፈልጋል፡፡
#አምስቱ_የንስሐ_መንገዶች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 71-72
#ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ እንደተረጎመው
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓል #ለብዙኃን_ማርያም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
#በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹#ብዙኃን_ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው #ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም #የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል #በግሸን_ደብረ_ከርቤ_የተቀመጠበት_ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤
#በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡
#በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡
#ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን ‹‹ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ›› ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ መካከል ፫፻፲፰ (ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው ‹‹ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው›› ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም ‹‹ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን›› ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡
#፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት ‹‹ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን›› የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት ‹‹ብዙኃን ማርያም›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡
#በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤
#ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው ‹‹የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል›› አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር ‹‹የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ›› የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ ‹‹ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት›› ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡
#ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡
#መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ›› የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ›› ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡
#ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡
ምንጭ፡- መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ መ/ር አፈወርቅ ተክሌ፤ ፳፻፭ ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ ገጽ ፫፶፬-፫፶፮፡፡
የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእመቤታችን አማላጅነት፣ የክርስቶስ የመስቀሉ ኃይል፣ የአባቶቻችን ሊቃውንትና ነገሥታት በረከት አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ኵሉ ከንቱ ከንቱ ንብረቱ እስመ ኵሉ ኃላፊ ውእቱ/፪/
መድኃኔዓለም /፪/ አድኅነነ እሞተ ከንቱ/፪/
ትርጉም፡- ሁሉም ከንቱ ነው፡፡ መድኃኔዓለም ከከንቱ ሞት አድነን ፡፡
#ድንግል_ሆይ የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንፁህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ከአንቺ በነሳው ሥጋ ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ ቢያየው እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመፅሐፍ ነገረን። የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተፃፈ። የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ሥጋ ሆነ ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ ተባለ። ይደንቃል።
#ደንግል_ሆይ መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ስብሐት ለእግዚአብሔር አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ስብሐት ነው እንጂ። ሰማይ ከክብሩ የተነሳ የምትጠበውን በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ፀሐፊ ከፍቅሩ የተነሳ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና እቅም በማጣት ሠአሊ ለነ ብሎ ጽሑፉን ይዘጋዋል። አይችልምና።
#ልዑሉን_የወለድሽ_ልዕልት_ሆይ የአንቺ ሥጋ ከአቤል ይልቅ ተወደደ፤ ከደገኛው አብርሐም ይልቅ ከፍ አለ፤ ከንጉሱ ከዳዊት ይልቅ ሥጋሽ የተለየና የተመረጠ ሆነ ...ዳዊትም፦ ንጉስ ደም ግባትሽን ወደደ ብሎ ፃፈልሽ። ከእስራኤላውያን አባት ከያዕቆብ ድንኳን ይልቅ የአንቺ ሥጋ ተመረጠ። ሎጥ፦ መላእክትን ወደ ቤቴ ግቡ ቢላቸው በአደባባይህ እንሆናለን እንጂ አንገባም አሉት። ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ግን መላእክትን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆነ። ለዚህ ቃል የለም ዝምታና አንክሮ እንጂ።
#ድንግል_ሆይ የአንቺን ሥጋ በመቃብር የለም በአብ ቀኝ እንጂ። አንዳንዶች ተነስታለች ለማለት ከበዳቸው። ለመሆኑ ልጅሽ አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳ መሆኑን አላነበቡ ይሆንን? የኢያዒሮስ ልጅን ታሪክ አልተመለከቱ ይሆን አንቺ ግን ወደ ሰማያት ከተነጠቁት ከሄኖክና ከኤልያስ ትበልጫለሽ። #ትንሣኤሽን #የሚያምን ሁሉ #አሜን ይበል።
✝️ "የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል፤ የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለአለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና፤ ሆኖም
፡
#እመቤቴ_ሆይ፦ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም እንደ ዮሃንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ የዮሃንስ ፀጋ ግን የለኝም፤
፡
#እናቴ_ሆይ፦ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ አይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና አዝናለሁ ኤልሳዕ በፀሎት ሃይል የግያዝን አይን እንዳበራ አንቺም አይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ሃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡
፡
#ድንግል_ሆይ፦ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም በልጅሽ መሰረትነት የታነፅኩኝ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ ስለዚህም ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደ እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡
፡
የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡"
አማልደን ስንልህ
“ካስነሣሃቸው ከሙታን ወገን፤ ከጠበቅሃቸው ከሕያዋንም ወገን፤ ካነጻሃቸው ከርኩሳን ወገን፤ ካጸደቅሃቸው ከኃጥአንም ወገን፤ ከሰበሰብሃቸው ከተበተኑት ወገን፤ ከመለስሃቸው ከበደሉትም ወገን ላንተ መታመን አለህ አሜን፡፡
እንሰግድልሃለን፤ እናመሰግንሃለንም፡፡ የጥበብ ነገር የምክርም ቃል የረድኤት መዝገብ የደስታ መኖሪያ፡፡ የጥቅም መገኛ፤ የትንቢትም ምንጭ ደገኛ ፈሳሽ በሐዋርያት የተመሰገንህ የክብር ጉድጓድ፤ የመንግሥት ጌጥ፡፡ የካህናት ንጹሕ ዘውድ፤ ዘውዱ የተመሰገነ ንጉሥ፤ የሚሰግዱለት የምስጋና መገኛ፤ የክብር ብርሃን፡፡ ያልተሠራ ልብስ ያልተፈተለ ቀሚስ፤ ወደ አባቱ ለመድረስ ጎዳና፤ ወደ ወለደው ለመግባት የሚሆን በር፡፡ የተገለጸ ወርቅና የተገኘ ዕንቍ ነው፡፡ የበዛ ምናን፡፡ እጽፍ ድርብ የሆነ መክሊት፡፡ ዱቄትን የቻለው እርሾ፣ አልጫ የሆነውን ያጣፈጠው ጨው፡፡
ጨለማን ያሳደደው ብርሃን፤ ዓለምን ሁሉ ያበራው ፋና፤ የማይነዋወጥ መሠረትና የማይፈርስ ግንብ፡፡ የማይሰበር መርከብና የማይሰረቅ ማኅደር፡፡ ያማረ ቀንበርና የቀለለ ሸክም፣ እርሱ ለአባቱ ኃይሉ ጥበቡም የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
ለሁሉ ያስባል ሁሉንም ያጠግባል፡፡ ለዕውራን ያዩ ዘንድ ብርሃንን ይሰጣቸዋል፤ የተዘጉ መስኮቶችን ይከፍታል፡፡ ጽሙማንን ያሰማቸዋል፡፡ የተደፈነችውን ጆሮ እንድትሰማ ያደርጋል፡፡ ከሰውነት የለምጽን ልብሶች ገፎ የሥጋ መጎናጸፊያ ያለብሳቸዋል፡፡
የደረቀውን የሰለለውን የእጅ ክንድ ያቀናል፤ የአንካሳውን እግር እንዲሄድ ያደርጋል፡፡ ነፍስን ወደ ሕዋስዋ ይመልሳታል፡፡ መንፈስንም በማደሪያዋ ያኖራታል፡፡ አለቆች ባሏቸው አጋንንት የእሪያን መንጋ ያሰጥማል፡፡ ከደከመችውም ሰውነት ደዌን ያርቃል፡፡
ከክንፍህ የጽድቅ ፀሐይና የጥቅም ምንጭ የሚወጣ የጽድቅ ፀሐይ ሆይ ለአንተ ጌትነትና ክብር ምስጋናም ይገባሃል ለዘላለሙ” /
✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦
#ይህንን_ምሳሌ_ለወጣቶች_ሁሉ
#ለመስጠት_እፈልጋለው!!!
✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦
✍ህይወታችሁ ሁለት ሰዎች እንደሚሰሩባት ጀልባ ናት የአንደኛው ስራ #መቅዘፍ ሲሆን የጀልባዋን #አቅጣጫ _መቆጣጠሪያ (መልህቅ) የሚይዝ ነው፡፡ ጠቢብ ሰው "#ጌታ_ሆይ_አንተ_አቅጣጫ_መቆጣጠሪያው_ያዝ_እኔ_ደግሞ_መቅዘፊያውን_ልያዥ!" ይላል፡፡✍
#እንደ_አለመታደል_ሆኖ_ብዙ_ጊዜ_እኛ #አቅጣጫ_ጠቋሚውን_ለመያዝ_የምንታገል_ሲሆን #እግዚአብሔር_ግን_ቀዛፊ_እንዲሆን_እንፈልጋለን፡፡
✍የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደእራስ ምርጫ አድርጎ የመቀበል ጥቅሙ ህይወት ወዴትም አቅጣጫ ቢያመጣህ እግዚአብሔር እንደፈቀደው ስለምታውቅና እግዚያብሔር የፈቀደልኝ ነው ስለምትል አትፈራም።✍
በአጭር ቃል "አልወደውም!" የሚባል አይነት ነገር ቢሆንም እንኳን በእርግጥ በጎ ፣ ፍፁምና ደስ የሚያሰኝ ነው።
✍"ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሳቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን!"✍
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦
ተግባራዊ ክርስትና ከሚለው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ....
አዘጋጅ:- አቡነ አትናስዮስ እስክንድር
ትርጉም:- ሄኖክ ኃይሌ
"አስታውስ"
(#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ)
† ደካማነትህን አስታውስ፣ ያንጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም፡፡
† የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ፣ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል። በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል፡፡
† የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ፡፡ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል፡፡
† ሞት እንዳለ አስታውስ፣ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ፡፡ "ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው፡፡" መክብብ 1፥14 ማለትን ትረዳለህ፡፡
† በእግዚአብሔርፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፣ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና፡፡
† ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ፡፡ በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣ "በዋጋ ተገዝታችኋልና" 1ኛ ቆሮ.6:20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ፡፡
† በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ፡፡
† በዚህ ዓለም እንግዳመሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ፡፡ ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ፡፡
† በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ፡፡ ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና፡፡
† ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ፣ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ፡፡
† የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ፡፡ እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል፡፡
† የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ፡፡ በውስጥህ ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን፡፡ ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን፡፡
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago