Medicos Art Club (MAC-ETHIOPIA)

Description
We Medicos (Students,GPs , Residents & seniors) will explore our talent besides our education! Join us and discover your talent! "See beyond the wall"

CONTACT ADMIN @noneyes
@EdenKeb
@Tg1921
Advertising
We recommend to visit

Telegram stands for freedom and privacy and has many easy to use features.

Last updated 1 month, 1 week ago

Official Graph Messenger (Telegraph) Channel

Download from Google Play Store:
https://play.google.com/store/apps/details?id=ir.ilmili.telegraph

Donation:
https://graphmessenger.com/donate

Last updated 2 months, 3 weeks ago

This channel is managed by the Telegram team to inform users about updates related to auctions for usernames and other items on the Telegram platform.

Last updated 1 year, 12 months ago

2 months, 4 weeks ago

"Capturing every moment"
A mini commercial showing video editing skills
By Hewan
C1 AMC
@talentofmedstu

3 months ago

ለእናቴ❤️?                                                                                                                                                                                         እ-ና-ቴ: እምዬ : የኔ እናት ስላንቺ ለመፃፍ ስነሳ ገና ቃላቶች ወዴት እንደሚገቡ አላውቅም።ግነት ናቸዉ ብዬ ማስባቸው ቃላት ላንቺ ለመፃፍ ሲሆን ግዜ ግዘፍ ያጡብኛል። ቀሊል በሆኑ ቃላት ግዙፍ ነብስሽን:የእናት ማንነትሽን: ስጋ ለባሽ መለኮትነትሽን : አንቺነትሽን እንዴት መግለጽ እንደሚቻለኝ ባላውቅም : መሞከርን ካንቺ ተምሬያለሁና እሞክር ዘንድ ጀመርኩ።

እናቴ ሆይ
ምስጋና ለማህፀንሽ ዘጠኝ ወር ላደላደለኝ :
ሰማይ ምድርም ለሆነኝ :
ሳይሰስት ምቾት ለቸረኝ :
ነብስ ለዘራሁበት ቦታ:
ሠላምታ!!
ምስጋና ላጠቡኝ ጡቶችሽ : አፌን በእንገር ለሞሉ : ልፍስፍስ ሰውነቴን : መራመድ ማይችል አካላቴን : ደቃቃ እኔነቴን : ላጸኑ።
ምስጋና ለመዳፎችሽ : ፀሃይ ስታሞቂኝ : ያልጠነከሩ አጥንቶቼን በስስት እየዳሰሱ ጥንካሬን ላላበሱ - ቆሞ የመሄዴ ምክንያቶች። ደግሞም ህይወት አስከፍታኝ : እንባዬ ከተሩን አልፎ ሳነባ : አብሮኝ ሆድሽ እየባባ : የውሸትሽን ተቆጥተሽ "ወንድ ልጅ እንዴት ያለቅሳል ?" ብለሽ እየገፋሽኝ : ደግሞም ወዲያውኑ "ለኔ ይለቀስ" እያልሽ ከዕቅፍሽ ስታስገቢነኝ : ዕንባዎቼን ላባበሱ: አዎን ለመዳፎችሽ አሜን ምስጋና ለነሱ።
ምስጋና ላቀፈኝ እቅፍሽ : አጥብቆ ለያዘኝ ጉያሽ : ሺህ ሠላም ላለበት አምባ : የሆነ ልገልፀው የማልችለው ሰላም ያለበት ስፍራ : የሆነ ዓይነት የደስ ደስ ሽታ ያለው : ዓይንዓለሜ እቅፍሽ እንዴት ያለ ነው? ወይስ ትንሽ ገነት ከጉያሽ ስር ሾጉጠሽ ነዉ።
ምስጋና ለጀርባሽ መራመድ ማልችለውን እኔን ሲያዝለኝ ለጎበጠ : ለማልከብደው ። 'የት ነህ? ቢሉኝ' ከጀርባዋ ላይ ነኝ እላለሁ : እንዳዘልሽኝ ዛሬም አለሁ።                                                                                                                    ምስጋና ለእጆችሽ እዚህ እንድደርስ ከጀርባዬ ለደገፉኝ: ከወደኩበት አይዞህ ብለው እያነሱ ዛሬ ላደረሱኝ::
ምስጋና ለጣቶችሽ : እኔን ለማሳደግ ለቆረፈዱ : "የጣቶቼ ማማር ካንተ ባይበልጥ ያኔ..." ለምትይኝ። ደግሞም ጆሮዎቼን ጭኔን ለመዠለጉ : በስርዓት ላሳደጉ።
ምስጋና ለእግሮችሽ : እኔን ለማሳደግ ላይ ለወጣ ታች ቁልቁል ለወረደ : እዚህና እዛ ለዳከረ : እናት ዓለሜ እኔን ለማሳደግ ያልረገጥሽው ቦታ የታለ?
ምስጋና ለቀሚስሽ : አጥብቄ ለያዝኩት : ለተሸሸኩበት : ከዓለም ክፋት። ዛሬም ክብድብድ ሲለኝ እሩጥ እሩጥ የእናትህ ቀሚስ ስር ተሸሸግ የሚል ስሜት ይወረኛል። ዛሬስ ጨንቆኝ ብመጣ ቀሚስሽ ስር ትሸሽጊኛለሽ? - እንዴታ እናቴ አይደለሽ?
ምስጋና ለፊትሽ : መልኩን ወዙን ለኔ ሰጥቶ ለጎሰቆለ::
የደሮ ፎቶሽን አየሁት - መልከ መልካምነትሽን : ማማርሽን ውበትሽን።
አሁን አየሁሽ - ቢያምርም ፊትሽ ብዙ ያለፈው አለ :
ከኔ ፊት ላይ ያልዋለ::
ደግሞ እራሴን አየሁ - አንቺነትሽን : መልከ መልካምነትሽን : ማማርሽን ውበትሽን ።
ትዝ ይልሻል እማ? ታምሜ ሆስፒታል ወስደሽኝ እዛው እስሬ ሆነሽ ''የዚህ ልጅ እናትስ?" ሲሉሽ። አንቺን ከኔ ማመሳሰል ቢከብዳቸው እኮ ነው። እናትዬ ያንቺን አንጠፍጥፈሽ ሰጥተሽ በፈገግታ እያየሽኝ ባዶ የቀረሽ : ተጎሳቁለሽ እንዲመቸኝ እንዳደረግሽ : ቁንጅናሽን አጥተሽ ቆንጆ ያደረግሽ እንደሆንሽ መገመት እንዴት ተሳናቸው ? - ከንቱ።                                                                                                         
የማይነገር ልናገረውም የማይቻለኝ ስፍር ቁጥር የሌለውን ውለታሽን አድጌ ልከፍልሽ እችል ይሆናል ብየ አስብ ነበር አንድ ጓደኛዬ "ምጧን:ጣሯን በምን ትከፍላታለህ?" እስኪለኝ ደረስ። እንደዛ ያለኝ ቀን ደነገጥኩ : የእውነት አስቤው አላውቅም ነበር። ግርም አለኝ : በርግጥም ትንሽ ደብሮኛል : እድሜዬን ሙሉ ብጥር ልከፍልሽ እንደማልችል ማወቄ። ባለዕዳ ነኝ : ከነ ዕዳዬ የምሞት ፤ ያልተገባኝ ነኝ : ያ ሁሉ ዉለታሽ : ግን ደግሞ ሁሉን ምላሽ ባለመጠበቅ ያደረግሽ ነሽ - እናት። እኔ አቅም የለኝም እናትዬ የምተምኚው አምላክሽ ውለታሽን ይክፈልሽ። እወድሻለሁ !!

ተፃፈ : በመክብብ ኪ/ማርያም
Arsi University
PC II
@talentofmedstu

3 months ago
ከፍተኛ የሕክምና እንክብካቤ ይፈልጋሉ? ራጃጊሪ ሆስፒታል …

ከፍተኛ የሕክምና እንክብካቤ ይፈልጋሉ? ራጃጊሪ ሆስፒታል በ ህንድ የላቁ ህክምናዎችን (ካንሰር፣ የልብ ህመም፣ የነርቭ እና ሌሎችንም) በዝቅተኛ ዋጋ ይሰጣል።
ለዝርዝር መረጃ ይደውልሉኝ
ዶ/ር ጆኒ በቀለ
0969454160

መረጃውን ለሌሎች እንዲደርስ ይተባበሩን

3 months ago
Naruto never gave up—he kept pushing …

Naruto never gave up—he kept pushing forward even when everyone thought his ninja way was just a ramen-fueled fantasy!?..so you hold on

Zebiba
Black Lion
C1
@talentofmedstu

3 months, 1 week ago

this is our member's start up business please show her some support and love ??
http://t.me/yeom_accessories

Telegram

Yeom Accessories

Elevate your style. Group- @yeom\_accessoriesg Contact @yeom\_a

this is our member's start up business please show her some support and love ***?******?***
3 months, 1 week ago

???የይሁዳ ፅድቅ???
በሰዎች መካከል ሰው ሆኖ ሲፈጠር
ጌታም ተፈተኗል አንድ ላይ ለመኖር
በረት ውስጥ ተወልዶ አለምን ያዳናት
እንደማንኛውም ነበረው ውብ እናት
ዘመን እየሄደ ጊዜ እየነጎደ
ሰላሳ ሶስት ሞላው ንጉስ ከወረደ
አንዳንዱ ለማመን መቀበል ሲከብደዉ
አምኖ ከመቀበል ፈጣሪን ሲከዳው
ሌላው በ'ንባው ያጥባል ካይኑ በወረደ
እግርን በሽቶ ወርዶ እያዋደደ
አንዳንዶችም አሉ ፍቅር የተኳሉ
አቅፎ የመስጠትን ስሌትን ያሰሉ
ግና ሁሉም ብፁህ ተባይ ከሁሉ ሚጠላው
ከደቀ መዛሙር ተለይቶ ወጥቶ ጌታውን የካደው
ያንን አስመሳዩን ያስቆሮጦሱን ነው
ዛሬ ምንም በሉ ምንም ተናገሩ
እኔ መስካሪ ነኝ ለይሁዳ ክብሩ
  ጌታ ሰብስቧቸው አስራሁለቱን ሰዎች
የስጋና የደም ምሳሌ ሲያመቻች
ስለ'ናንተ ሚፈስ ደሜ ይህ ነው ብሎ
በዋንጫ ያለውን ነበር አቀብሎ
ስጋውንም ሰጥቷል ከማዕዱ ከፍሎ
ከመካከላቸው አንዱ መሰሪ ነው
አሳልፎ ሊሰጥ ፈጣሪን ሊክደው
ይህን እርሱ ያውቃል ምክንያቱም ጌታ ነው
ሁሉ ነገር አልቆ እንደተበተኑ
ይሁዳ አብሮ ነበር ከጌታው ከጎኑ
እናም ቃል በገባው ገንዘቡን ለማግኘት
አዳኙ ጌታው ላይ ተጠመጠመበት
እነዚያም ሠቃዮች ጌታውን አገኙት
ይህን ጊዜ ነበር ውለታ የዋለው
አሳልፎ ሲሸጥ ጌታውን ሲክደው
ማን ነው መልስ የሚሠጥ ምላሹን ሚያገኝ
ጌታ ባይሰቀል ማን ነበር ሚያድነኝ?
ምላሽ የሌለው ቃል እንዲው ሚያስታውቀው
ጥያቄው ሲጠየቅ መልሱም ጥያቄ ነው
አሳልፎ ባይሸጥ ይሁዳ ጌታውን
ምድር ባዶ ነበር ጨለማ ብቻውን
ገና ከጅምሩ ጌታ ይህን ያውቃል
አለምን ለማዳን ወጥቶ 'ንደሚሰቀል
ይሁዳን ምክንያቱ ሰበብ ይሁን ሲለው
ከሌሎች ለይቶ ራሱን አሸጠው
ከሌላው አብልጦ አልቀረም ሳይወደው
አለምን እንዲያድን ምክንያት ስለሆነው
ግን አሁን ላይ ሆኜ እኔ የተመኘሁት
ጌታ ለይሁዳ ጥበቡን አድሎት
ሊቁን የሠው ጠቢብ ሰለሞንን አርጎት
አለምን አዳኙን ጌታውን ሲሸጠው
ይገባው ነበረ ከሰላሳ በላይ ዲናር ሊከፈለው
ጌታ ከጅምሩ መሞት መሰቀሉን ቀድሞ ስላወቀው
ደግሞስ የኛ ጌታ ወድቆ እንኳ አልቀረ
አለምን ከማዳን እጁን አላሠረ
ሠው ገሎ ሲያሸንፍ ሲፎክር ሲዝናና
እርሱን የመሰለ ሞቶ ያሸነፈ ዉድ ሰው የት አለና
ያንን ምስኪን ፍጡር ሰበቡ አረገና
ይሄ በልቶ ሚክድ ብለው ሲሳለቁ
ያቺን ጊዜ ነበር የሊቆቹ ሊቁ
ጌታውን ሲያሳልፍ ይሁዳ መፅደቁ።

Bethelehem Fikadu
C-1
Haramaya University
@talentofmedstu

3 months, 1 week ago

Establishment on progress!

Call to join MAC Ethiopia ?? ?

Contact us: By sending Essay (Art in Medicine, focusing on your talent) & CV...via
[email protected][email protected][email protected][email protected]
@debolteam
@talentofmedstu

3 months, 2 weeks ago

Asthma
by Dr. Kinfegebreal Wagaye
Please like share and subscribe.
@talentofmedstu
https://youtu.be/y5N58upAe8s?si=Ir1HLE21AgB2rW0w

YouTube

Asthma| Acute Exacerbation of Asthma| Pathophysiology of Asthma| GINA 2024| Harrison21st edition

Asthma is common Chronic Respiratory disease. World wide more than 241 million people are suffering from this disease. Every medical professional should be equipped with basic knowledges of asthma.

3 months, 2 weeks ago
Medicos Art Club (MAC-ETHIOPIA)
3 months, 2 weeks ago
Medicos Art Club (MAC-ETHIOPIA)
We recommend to visit

Telegram stands for freedom and privacy and has many easy to use features.

Last updated 1 month, 1 week ago

Official Graph Messenger (Telegraph) Channel

Download from Google Play Store:
https://play.google.com/store/apps/details?id=ir.ilmili.telegraph

Donation:
https://graphmessenger.com/donate

Last updated 2 months, 3 weeks ago

This channel is managed by the Telegram team to inform users about updates related to auctions for usernames and other items on the Telegram platform.

Last updated 1 year, 12 months ago