📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc
" መርምሩ፤ ያልተመረመረ ሕይወት ርባና የለውም። "
#ፍትሕ ለሄቨን?
የስልሳ አመቷ እናት Nokubonga Qampi በትንሽ ስልካቸው ብርሀን እየታገዙ በእጃቸው ትልቅ ቢላ ይዘው ድቅድቅ ባለው ጨለማ ውስጥ እየሄዱ ነው ።
.....
እና ትንሽ እንደተጓዙ ልጃቸው አለችበት የተባለው ቤት ደረሱ ፡ የልጃቸው ጓደኛ ነበር የደወለችላቸው ፡ የልጃቸው ጓደኛ በተደናገጠ ድምፅ ፡ በሰፈሩ የሚታወቁ ሶስት ጉልበተኞች የእሳቸውን ልጅ አስገድደው ሊደፍሯት እየሞከሩ እንደሆነ ገልጻ እሷ ሸሽታ ማምለጧን ነገረቻቸው ።
....
አዛውንቷ Nokubonga ይህን እንደሰሙ ወደፖሊስ ስልክ ደወሉ ፡ ስልኩ አይነሳም ፡ ማድረግ ያለባቸው ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ማመልከት ነው ። ያ እስኪሆን ደግሞ ልጃቸው በደፋሪዎቿ ህይወቷ ሊያልፍ ይችላል ።
....
ስለዚህ ማድረግ ያለባቸው ከልጃቸው ጋር አብሮ መሞት ነበርና ፡ ከኪችን ትልቅ ቢላ ይዘው ነበር ልጃቸው አለችበት ወደተባለው ቦታ የደረሱት ።
....
ልክ እንደደረሱ የልጃቸው የድረሱልኝ ድምፅ ተሰማቸው ፡ እና ትንሽ ስልካቸውን እያበሩ ድምፅ ወደሰሙበት መኝታ ቤት ሲደርሱ ፡ ሶስት በሰፈሩ በረብሻና በጉልበተኝነት የሚታወቁ ጎረምሶች በክፍሉ ውስጥ ሆነው አንደኛው ልጃቸውን ሲደፍር ተመለከቱ ፡ እና ትልቅ ቢላቸውን አጥብቀው ይዘው ልጃቸውን እያስገደደ ወዳለው ወጣት ሮጡና በሀይል ወጉት ፡ ድርጊቱ ቅፅበታዊ የሆነባቸው ደፋሪዎች እመዛውንቷን እናት ለማጥቃት ተጠጉ ፡ ሴትዮዋ ከየት እንዳመጡት በማያውቁት ጉልበት ፡ ቢላቸውን ሰንዝረው ወደሳቸው የተጠጉትን ሁለት ወጣቶች ወጓቸው ።
.....
ያላሰቡት ጥቃት የገጠማቸው ሁለት ጎረምሶች በመስኮት ዘለሉ ፡ Nokubonga ቀድመው የወጉትን ደፋሪ አዩት ለመነሳት እየሞከረ ነው ። እዛው እንዳለ ደገሙት ።
.....
ወዲያውኑ ፀጥ አለ ።
.......
እና ቢላቸውን ጥለው ልጃቸውን ደግፈው ከክፍሉ ወጠው ሰወች እንዲደርሱላቸው መጣራት ጀመሩ ።
......
በአካባቢው ያሉ ሰወች ጥሪያቸውን ሰምተው የመጡት የአካባቢው ሰወች ፡ ልጃቸውን ወደሆስፒታል ይዘው ሄዱ ፡
....
ግርግሩን ሰምተው የመጡ የፖሊስ አባላት አዛውንቷን ወደ ጣቢያ ወሰዷቸው ፨
......
አዛውንቷ Nokubonga በአንድ ሰው ግድያ እና በሁለቱ ላይ ባደረሱት ከፍተኛ ጉዳት ክስ ተመሰረተባቸው ።
....
ልክ ይህ ዜና እንደተሰማ ፡ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ሶሻል ሚዲያና እንዲሁም በተለያየ ቦታዎች ያሉ ሰወች የአዛውንቷን መከሰስ ተቃውመው ሰልፍ ወጡ ።
.......
ጉዳዩ ቫይራል ሆነ ፡ ሴትየዋ ያደረጉት ማንም እናት እና አባት ልጁ ስትደፈር ማድረግ የሚችለውን ነውና መከሰስ የለባቸውም ተባለ ።
....
ህዝብ በአንድ ድምፅ ከእናትና ልጅ ጎን ቆመ ።
......
ብዙም ሳይቆይ ፍርድቤቱ አዛውንቷ Nokubonga ን በነፃ ለቀቃቸው ። ልጃቸውም ሙሉ ጤና ሆና ከሆስፒታል ወጣች
......
ከዚህ ድርጊት መከሰት በኋላ የደቡብ አፍሪካ ህዝብ ለኚህ እናት አዲስ ስም አወጣላቸው ። Lion mama የሚል ።
....
አሁን አሁን ሰው የሚያውቃቸው በዚህ ስም ነው ።
....
የደቡብ አፍሪካ ህዝብ ከነዚህ እናትና ልጅ ጋር እንደቆመው ፡ እኛም ከዚህ የባሰ ወንጀል ለተፈፀመባት ለህጻን ሄቨን ፍትህ እንላለን ። እናም ከስር በተቀመጠው ሊንክ በመግባት እየተሰበሰበ ያለውን የፊርማ ካምፔን ይቀላቀሉ ።
ከ 0.2 ቶን ጀምሮ መግዛት የምትፈልጉ ? @Um_the_first
አልሞትም!
(በእውቀቱ ስዩም)
ስሚ!
እኔ በዚህ ዐለም ፤ብዙ ብሰቃይም
አንድ ሀሙስ የቀረው፤ መስየ ብታይም
አምሮቴን ሳላገኝ፤ሱሴን ሳላከትም
በመሬት ከርስ ውስጥ ፤ገላየን አልከትም
አልሞትም!
ማንም ባልደፈረው፤ መንገድ ሳልገሰግስ
እንደ ንጉስ አይዙር፤ግማሽ ቀን ሳልነግስ
በጠገበው ሳልስቅ፤ ለራበው ሳልደግስ
አልሞትም!
ዝማሜን ሳላወልቅ፤ ያንድበቴን ግድብ
ዙፋን ላይ ሳልሸና፤ ጌቶቼን ሳልሰድብ
ከድሃ ሳላብር፤ ከገባር ሳልወግን
ከምድር በረከት፤ ድርሻየን ሳልዘግን
አልሞትም፤
ስሚ!
ልቤ እንደምኞቱ፤ ቢያገኝ እንደምርጫው
ያላማየ ማብቂያ፤ አንቺ ነሽ መቁዋጫው
እና
አገሬን ለቅቄ፤ ልብሽህ ላይ ሳልከትም
በውብ ከንፈርሽ ላይ፤ ከንፈሬን ሳላትም
አልሞትም!
"♥~ለምንም~♥”
"ምናባሽ ስሰሪ ሰበርሽዉ ኧ? አንቺን እኮ ነዉ አትንኪ ያልኩሽን እቃ ለምን ነካሽሽሽ..."
ጎረቤቶቻችን ናቸዉ እኔ ነፍስ እስካወኩበት ጊዜ ድረስ አብረን ነዉ የኖርነዉ::
ምን ያደርጋል ጥል ለመገላገል እንኳን የማይበቃ ጉርብትና...
የኔ እኩያ የሆነች ልጅ አለቻቸዉ:: እናቷ ጥላት ከኮበለለች በኋላ ይህች እኩያዬ ከአባቷ ጋር ነዉ የምትኖረዉ...ይኸዉ ዛሬም እሷ ስትደበደብ እየሰማሁ ምንም ማድረግ አልቻልኩም "ለመገላገል የማይበቃ ጉርብትና" ብያችሁ የለ::
በነገራችን ላይ እኔን የሚያሳዝነኝ ዉሃ ቀጠነ በሚል ምክንያት መመታቷ እንጂ ማንም እኮ በወላጆቹ ተቀጥቶ ነዉ የሚያድገዉ: እኔም ሳጠፋ እኮ እቀጣለሁ::
ብቻ ግን እንዲህ በሆነዉ ባልሆነዉ የሚቀጠቅጧት ልጃቸዉ የሰፈሩ ጨዋ መሆኗን ቢያዉቁ ምን ይሰማቸዉ ይሆን::
"ኸረ እንደሷ ቻይም የለ ትግስት ራሷ ማለት ናት" ይላሉ እነ እማዬ::
እዉነትም ትዕግስት ይህ ሁሉ ዉርጅብኝ ወርዶባት እንኳን ለተጠየቀችዉ ጥያቄ "ለምንም" ከሚል በሳግ ከታፈነ ምላሽ በቀር ቃል አይወጣትም::
ምናለ ጥፋቷን አምናለች ብለዉ እንኳ ቢተዋት?
ፀጋ?
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc