📈 All the latest updates on the Stock Market: signals, news, and everything that might move the narrative — all in one place.
😉 We keep an eye on the price; you can just watch us do it.
Buy Ads: @JamesCookTg
Last updated 4 weeks, 1 day ago
The official Yescoin™
Probably something.
Play🕹️: @realyescoinbot
Player support: @yescoincare
Business: @advertize_support
Last updated 2 months ago
Fast transfers & trading, send meme gifts 🎁 and earn 100x returns — fun and flexible crypto app!
Incubated & invested by Binance Labs
በአጠቃላይ የህሊና ጉዳት በህጉ በዝርዝር ለተቀመጡ ጥፋቶች ብቻ የሚከፈል ሲሆን የካሳው ዓላማም የገንዘብ ጥቅምን ለማስገኘት ሳይሆን ለደረሰ የስሜት ጉዳት እና ስብራት ማካካሻ ለመስጠት ነው፡፡ በመሆኑም የሞራል ጉዳት ደርሶብኛል የሚል ሰው የህሊና ጉዳት ካሳ ማግኘት እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል።
Ministry of Justice ⚖️
?የህሊና_ጉዳት_ካሳ (#Moral_Damage)
የፍትሐብሔር ሕግ የግለሰቦች፣ መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እርስ በርስ በሚያደርጉት ገንዘብ እና ንብረት ነክ ግንኙነት ያላቸውን መብትና ግዴታ የሚያስተዳድር ህግ ነው፡፡ የፍትሐብሔር ህግ ገንዘብ እና ገንዘብ ነክ ጉዳዮችን የሚያስተዳድር ህግ በመሆኑ ጉዳት የደረሰበት ሰው የሚጠይቀው የጉዳት ካሳ የሚገዛው በዚሁ ህግ ማዕቀፍ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የህሊና ጉዳት ካሳ (Moral Damage) በፍትሐብሔር ህጋችን ያለውን ሽፋን እንመለከታለን።
የህሊና ጉዳት ካሳ (Moral Damage) ምንነት የህሊና ጉዳት ካሳ (Moral damage) በአንድ ሰው ድርጊት ምክንያት ለደረሰ የስሜትና የመንፈስ ጉዳት በፍርድ ቤቶች የሚወሰን የካሳ ዓይነት ነው፡፡ የህሊና ጉዳት በተጎጂው ላይ የደረሰውን የስሜት መጎዳት፣ የሥነ-ልቦና ጉዳት፣ ሐዘን፣ ሀፍረት፣ ውርደት፣ አእምሮአዊ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ መጥፎ ስም፣ የቆሰሉ ስሜቶች፣ የሞራል ድንጋጤ፣ ማህበራዊ ውርደት፣ በአካላዊ ስቃይ ምክንያት የተከሰተ የሞራል ጉዳት እና ተመሳሳይ ጉዳቶች ያካትታል። ከፍትሐብሔር ግንኙነት በተጨማሪ በወንጀል ጉዳይ ተጎጂው በተከሳሹ የወንጀል ድርጊት ምክንያት የደረሰበትን የሞራል ስቃይ ለመካስ ያገለግላል።
?የህሊና ጉዳት ካሳ ፅንሰ-ሀሳብ በባህሪው ተጎጂው የደረሰበት ጉዳት ለማካካስ የሚሰላ ነው፡፡ እንዲሁም ተጎጂው በገንዘብ ረገድ ለደረሰበት ጉዳት ሳይሆን በህሊናው ላይ ለደረሰበት ጉዳት የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡ ስለሆነም የሞራል ጉዳት ወይም የህሊና ጉዳት ካሳ ቁሳዊ ላልሆኑ ጉዳቶች እንደ ማከሚያ የተሰጡ የጉዳት ክፍያዎች ናቸው፡፡
የህሊና ጉዳት ካሳ የሚያስከፍሉ ጉዳቶች በፍትሐብሔር ህግየህሊና ጉዳት ካሳ በመሰረቱ ለደረሰው ጉዳት ካሣ ለመክፈል ተመዛዛኝ በሆነ አድራጎት ሊፈፀም በሚቻልበት ጊዜ ሁሉ ጥፋተኛው በደሉ ለሚያስከትለው የሕሊና ጉዳት ካሳን መክፈል እንደሚገባ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2105(1) ስር ተደንጓል፡፡
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2105(2) የህሊና ጉዳት በሕጉ በግልፅ ካልተመለከተ በቀር የገንዘብ ካሳ የማያስከፍል መሆኑ ተቀምጧል። በሌሎች ህጎች ስለ ሞራል ካሳ የተደነገጉ ድንጋጌዎች እንዳሉ ሆነው በፍትሐብሔር ሕጉ ከውል ውጪ ስለሚደርስ ሃላፊነት ሥር የገንዘብ ካሳ የሚያስገኙ የህሊና ጉዳት ዓይነቶች በፍትሐ ብሔር ሕጉ ከቁጥር 2106 እስከ ቁጥር 2115 ድረስ ያሉት ብቻ ናቸው።
በፍትሐብሄር ህጉ የህሊና ጉዳት ካሳ የሚያስከፍሉ ጥፋቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
# ታስቦ የተደረገ ጥፋት (በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2106)፡- በከሳሹ ላይ ታስቦ የህሊና ጉዳት በሚደርስበት ጊዜ ዳኞች በዚሁ በደል ካሳ ስም ተከሳሹ ለከሳሹ በርትዕ ካሳ እንዲከፍል ወይም ከሳሹ ላመለከተው በጎ አድራጎት ድርጅት እንዲከፈል ለመፍረድ ይችላሉ።
#በተበዳዩ ሰውነት ላይ ስለሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2107)፡-
ተከሳሹ በከሳሹ ላይ አስቀያሚ ወይም የሚያስጠላ መጥፎ መንካት በሚያደርግበት ወቅት ለተበዳይ ካሳ ይከፈለዋል።
#ያለአግባብ ሰውን በመያዝና በማገድ የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2108)፡- ተከሳሹ ህግን ተቃራኒ በሆነ አኳኋን የከሳሹን ነፃነት አግዶ በተገኘ ጊዜ የሚከፈል የህሊና ጉዳት ካሳ ነው፡፡
#በስም ማጥፋት ስለሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2109)፡- ከሳሹ ተሰድቦ ወይም ስሙ ጠፍቶ ሲገኝ
#ከሳሹ በወንጀል ህግ የሚያስቀጣ ወንጀል ሰርቷል በማለት ስሙን በማጠፋት የበደለው እንደሆነ፣
#የስም ማጥፋት ሥራዎች ከሳሹን በሞያ ሥራ ችሎታ የሌለው ወይም እውነተኛነት የሌለው መሆኑን ለማሳመን የተደረገ እንሆነ፣
# ነጋዴ ሆኖ ዕዳውን ለመክፈል አይችልም በማለት አስመስሎ ለማሳመን የሆነ እንደሆነ፣
#ተላላፊ በሽታ አድሮበታል በማለት ለማሳመን የሚጥር እንደሆነ፣
#አስነዋሪ የሆነ ጠባይ አለው በማለት አስመስሎ ለማሳመን የሚጥር እንደሆነ የህሊና ጉዳት ካሳ እንዲከፈለው ይሆናል።
# የባልና ሚስትን መብት በመድፈር የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2110)፡- ተከሳሹ የባልነት ወይም የሚስትነትን መብቶች ነክቶ የተገኘ እንደሆነ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡
# ልጅን ነጥቆ በመውሰድ የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2111)፡-
የልጁ ጠባቂነት የከሳሹ ሆኖ ተከሳሹ ልጁን ነጥቆ በመውሰዱ ጥፋተኛ ሆኖ በወንጀል በሚቀጣበት ወቅት የሚከፈል ክፍያ ነው።
#ንብረቶችን በመድፈር የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2112)፡-
ከሳሹ እንዳይደርስበት በግልፅ ያስታወቀውን በመቃወም ተከሳሹ በደንብ በእጁ ወይም በይዞታው የሚገኘውን ንብረት የወሰደበት እንደሆነ ወይም በርስቱና በቤቱ የገባበት እንደሆነ በከሳሹ ላይ ስለ ደረሰው ጉዳት ለዚህ በደል ካሳ ሊወሰን ይችላል።
#በአካል ጉዳት ወይም በሞት የሚደርስ ጉዳት(በፍ/ሕ/ቁ 2113)፡- አካሉ በመጉደሉ ለተበደለው ሰው ወይም ሰውየው የሞተ እንደሆነ ለዘመዱ የጉዳት ካሳ በአስተያየት ተገቢ ኪሳራ ዳኞች ሊቆርጡ ይችላሉ፡፡
#የንፁህ ህሊናን ክብር በመድፈር የሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2114)፡- ማንኛውም ሰው በመድፈር ሥራ ወይም ለክብረ ንፅህና ተቃራኒ በሆነ ተግባር በወንጀል የተቀጣ እንደሆነ ዳኞቹ ለተደፈረችው ሴት በህሊና በደል ካሳ ስም ተከሳሹ የሚሰጠውን በርትዕ የሚገባ ካሳ ሊቆርጡ ይችላሉ። እንዲሁም ለሴቲቱ ባል ወይም ቤተ ዘመዶች ካሳ ሊቆረጥ ይችላል።
# በሚስት ላይ ስለሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2115)፡-
ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ሚስት ላይ የአካል ጉዳት በማድረሱ በትዳር በኩል ለባሏ የምትሰጠው ጥቅም ወይም ደስታ እንዲቀንስ ያደረገ እንደሆነ ስለበደል ካሳ ዳኞች በበዳዩ ላይ ለባለቤቷ በርትዕ ተገቢ የሆነ ኪሳራ ሊቆርጡለት ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክንያት በሚስት ላይ ለደረሰው ጉዳት ባል የሚያቀርበው ክስ ሚስቱ ለደረሰባት ጉዳት ስለካሳ ጥቅም ከምታቀርበው ክስ ተጨማሪና የተለየ ነው፡፡
የህሊና ጉዳት ካሳ ክፍያ መጠን
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2116 ስር እንደተደነገገው የካሳ ልክ ምን ያህል መሆኑን በርትዕ በአስተያየት ለመወሰንና የቤተ ዘመዱ እንደራሴ ሆኖ ለመነጋገር የሚችል ማን እንደሆነ ለማወቅ ዳኞች የአገር ልማድን መሰረት በማድረግ የሚወስኑ ሲሆን የጉዳት ካሳውም በማናቸውም ምክንያት ከ1000 የኢትዮጵያ ብር የበለጠ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የገንዘብ መጠን ሕጉ በወጣበት ዘመን ከፍተኛ ነው ሊባል ቢችልም በአሁኑ ጊዜ ግን በጣም አነስተኛ ነው፡፡ በመሆኑም በዛ በኋላ በወጡ ልዩ ህጎች የህሊና ጉዳት ካሳ መጠን ላይ መሻሻሎች ታይተዋል፡፡ ለምሳሌ የቤተሰብ ሕግጋት ሲሻሻሉ ሕግ አውጪው የሞራል ካሳውን መጠን በገንዘብ መጠን ሳይወስን ዳኞች እንደጉዳዩ እንዲወስኑ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡ የደቡብ ክልል የቤተሰብ ሕግ ግን በባልና ሚስት መካከል ያለው የመከባበር፣ የመተጋገዝና የመተማመን ግዴታ ከተጣሰ እስከ ብር 10,000 ድረስ ካሳ ዳኞች ሊወስኑ እንደሚችሉ በሕጉ መቀመጡ የተሻለ ሕግ አድርጎታል፡፡ እንዲሁም በቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ቁጥር 410/1996 አንቀፅ 34(4) መሰረት የሕሊና ጉደት ካሳ 100,000 ብር የማያንስ መሆኑ ይደነግጋል፡፡ በሌላ በኩል የመገናኛ ብዙሀን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀፅ 84(2) ለስም ማጥፋት ወንጀል የሚወሰነው የሞራል ካሳ መጠን ከብር 300,000 እንደማይበልጥ ይደነግጋል፡፡
Saddened to hear this. May your soul rest in eternal peace ?️
Condolences to his families, friends, and the law school community.
📈 All the latest updates on the Stock Market: signals, news, and everything that might move the narrative — all in one place.
😉 We keep an eye on the price; you can just watch us do it.
Buy Ads: @JamesCookTg
Last updated 4 weeks, 1 day ago
The official Yescoin™
Probably something.
Play🕹️: @realyescoinbot
Player support: @yescoincare
Business: @advertize_support
Last updated 2 months ago
Fast transfers & trading, send meme gifts 🎁 and earn 100x returns — fun and flexible crypto app!
Incubated & invested by Binance Labs