★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks, 1 day ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago
✨ #አላህን_የት_ትወነጅለዋለህ??
✍አሚር ሰይድ
ከዕለታት አንድ ቀን እንድ ሰው ወደ ኢብራሃም ኢብኑ አድሀም( አላህ ይዘንላቸውና) በመምጣት ለመፈፀም የሚፈልገውን የኃጢአት ዓይነት ጠቀሰላቸው፡፡
....እሳቸውም “አላህን ለመወንጀል ከፈለግክ እሱ በፈጠራት ምድር ላይ እንዳትኖር፤ እሱ በፈጠራት ሰማይ ሥርም አትቁም' አሉት፡፡
ሰውየውም በመገረም “አላህ ከፈጠራት ምድር ሌላ ምድር አለን? እንዲሁም ከፈጠራት ሰማይ ሌላ ሰማይ አለን?" ሲል ጠየቃቸው፡፡ እሳቸውም “ታዲያ ይህን ካወቅክ በእሱ መሬት ላይ እየኖርክ በርሱ ሰማይም ስር እየተጠለልክ ልትወነጅለው ይቻልሃልን?!' አሉ፡፡ ሰውየውም ፈፅሞ አይቻለኝም በማለት በሁለተኛ ደረጃ የሚሰጡትን ምክሮ አዲለግሱት ጠየቀ፡፡
እሳቸውም “አላሁን ለመወንጀል ከፈለግክ ከሲሳዩ አንዳች ነገር አትመገብ አሉት፡፡ ሰውየው እንደገና በመልሳቸው በጣም በመገረም “ለአላህ ጥራት ይገባው! ከአላህ ሲሳይ ውጭ ሌላ ሲሳይ ይገኛልን?” ሲል ጠየቃቸው፡፡
.....እሳቸውም በምድሩ ላይ እየኖርክ፤ በሰማዩም እየተጠለልክ፤ ከሲሳዩም እየተመገብክ ልትወነጅለው ይቻልሃልን?!' አሉት::
ሌላ ምክር ይጨምሩልኝ አላቸው፡፡
....እሳቸውም ምክራቸውን ቀጥለው "አላህን (ሱ.ወ) ለመወንጀል ከፈለግክ መለከል መዉት ወደ አንተ ሲመጣ ንስሀ እስከማደርግ ድረስ ትንሽ ጊዜያት ጠብቀኝ" በለው ወይም ከርሱ አምልጥ" አሉት።
ሰውየውም በጣም የሚገርም ነው! የሰው ልጅ የሕይወት ፍፃሜ ሊዘገይ ይችላል?! ፍፁም የማይመስል ነገር ነው:። ምክንያቱም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል አይደለምን?
فَإِذَا جَاۤءَ أَجَلُهُمۡ لَا یَسۡتَـٔۡخِرُونَ سَاعَةࣰ وَلَا یَسۡتَقۡدِمُونَ
"ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት ጊዜ አንዲትን ሰዓት አይቆዩም አይቀድሙም(አን ነህል 61)
“አራተኛውን ምክርዎትን ይጨምሩልኝ" አላቸው፡፡ እሳቸውም "በአላህ (ሱ.ወ) ምድር ላይ እየኖርክ በሰማዩም እየተጠለልክ ሲሳዩንም እየተመገብክ እሱን ልትወነጅል ይቻልሃልን!? ካሉት በኋላ "አላህን (ሱ.ወ) ለመወንጀል ከፈለግክ የጀሀነም ዘበኞች ወደ ጀሀነም እሳት ይዘውህ ሊሄዱ ሲሉ ከነርሱ አምልጥ ወይም ወደ ጀነት ሽሽ አሉት፡፡ ሰውየውም “ለአላህ ጥራት ይገባው! እነሱ እኮ
عَلَیۡهَا مَلَـٰۤىِٕكَةٌ غِلَاظࣱ شِدَادࣱ لَّا یَعۡصُونَ ٱللَّهَ مَاۤ أَمَرَهُمۡ وَیَفۡعَلُونَ مَا یُؤۡمَرُونَ
በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ሀይለኞች የሆኑ መላእክት አሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምፁም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ(አት ተህሪም6)
የተባሉት መላእክት ናቸው" አላቸው፡፡ እሳቸውም “በርሱ ምድር ላይ እየኖርክ፣ በሰማዩ እየተጠለልክ፤ የመሞቻ ቀን እየተቃረበ መሆኑን እያወቅክ፤ ከጀሀነም ዘበኞች ማምለጥ እንደማትችል እየተረዳህ አላህን (ሱ.ወ) ልትወነጅል ይቻልሃልን?" አሉት፡፡ ሰውየውም “ፍፁም አይቻለኝም ካላቸዉ ቡሀላ በዚህ የኢብራሂም ኢብኑ አድሀም ምክር ወደ አላህ(ሱ.ወ)ተዉባህ አድርጎ አላህ(ሱወ)በመታዘዝ ላይ በርትቶ ብዙ አመታት ከቆየ ቡሀላ ሞተ፡፡
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
አንድ ሰው ወደ ሐሰነ-ል-በስሪይ (ረ.ዐ) መጥቶ የዝናብ መቋረጥን በምሬት ነገራቸው እሳቸውም “አላህን ምሕረት ጠይቅ" አሉት፡፡
....ሌላ ሰው መጣና የውሀ ማነስን በምሬት ነገራቸው፡፡ ለእሱም “አላህን ምሕረት ጠይቅ” አሉት፡፡
......ሶስተኛ ሰው መጣና የልጆቹ ቁጥር ማነስ በምሬት ነገራቸው፡፡ ለእሱም እንደሌሎቹ "አላህን ምሕረት ጠይቅ" አሉት፡፡
.....አራተኛ ሰው መጣና “ምድሪቱ ምርት ከመስጠት ደርቃለች" በማለት በምሬት ነገራቸው፡፡ እሱንም ለአንደኛው ለሁለተኛውና ለሶስተኛው ሰው እንዳሉት “አላህን ምሕረት ጠይቅ" አሉት፡፡
ሰዎቹ ከሄዱ በኋላ አብረዋቸው የነበሩት “ሐሰነል-በስሪይ ሆይ! የሚጠይቅዎት ስው በመጣ ቁጥር “አላህን ምሕረት ጠይቅ" ይላሉን?" በማለት በግርምት ጠየቋቸው፡፡ እሳቸውም ይህ የአላህ ቃል አልገባችሁምን? ብለው የሚከተለውን የቁርአን አንቀጽ ለሰዎቹ አነበቡላቸው፡፡
{ فَقُلۡتُ ٱسۡتَغۡفِرُوا۟ رَبَّكُمۡ إِنَّهُۥ كَانَ غَفَّارࣰا }{ یُرۡسِلِ ٱلسَّمَاۤءَ عَلَیۡكُم مِّدۡرَارࣰا
{ وَیُمۡدِدۡكُم بِأَمۡوَ ٰلࣲ وَبَنِینَ وَیَجۡعَل لَّكُمۡ جَنَّـٰتࣲ وَیَجۡعَل لَّكُمۡ أَنۡهَـٰرࣰا }
አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል፡፡በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል፡፡»(ኑህ10-12)
ወንድሜ እህቴ ሆይ አላህን ምህረት መጠየቅ እናብዛ
እድለኛ ሰው!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِنَّ السَّعِيدَ لَمَنْ جُنِّبَ الْفِتَنَ، إِنَّ السَّعِيدَ لَمَنْ جُنِّبَ الْفِتَنَ، إِنَّ السَّعِيدَ لَمَنْ جُنِّبَ الْفِتَنَ، وَلَمَنِ ابْتُلِيَ فَصَبَرَ﴾
“እድለኛ ማለት እራሱን ከፈተና ያራቀ ነው፣ እድለኛ ማለት እራሱን ከፈተና ያራቀ ነው፣ እድለኛ ማለት እራሱን ከፈተና ያራቀ ነው። በተፈተነ ግዜ ደግሞ የሚታገስ ነው።”
? አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል፡ 4263
ፆም አያበቃም
ቁርዐን አይተውም
ከመስጂድም አይቀርም
እውነቱም (ሞት) እስኪመጣ ድረስ ጌታህን ተገዛ::
የረመዳን ሳይሆን የአላህ ባሪያ ሁን!!!
ሞት!
.
.
.
ቀብር!
.
.
.
ቂያማ!
.
.
.
ሲራጥ!
.
.
.
እየጠበቁን ነዉ።
የዒድ አል-ፊጥር ቀን ተግባራዊ የሚደረጉ አስር ሱና
✋እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል_ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ‼️
?ዒድ ሙባረክ?
①. ለዒድ ቀን ማማርና መዋብ
عن ابن عباس رضي الله عنهما قال:
((كان رسول الله ﷺ يلبسُ يومَ العيدِ بردةً حمراءَ)) السلسلة الصحيحة - رقم: (1279) الألباني : إسناده جيد
②. ለዒድ ሰላት ከመውጣታችን በፊት ገላን መታጠብ
▫️ عنْ نَافِعٍ :
(( أَنَّ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عُمَرَ رضي الله عنه كَانَ يَغْتَسِلُ يَوْمَ الْفِطْرِ قَبْلَ أَنْ يَغْدُوَ إِلَى الْمُصَلَّى)) موطأ مالك - رقم : (384) صححه الألباني في الإرواء
③. ለዒድ ሰላት ከመውጣታችን በፊት በቴምር ማፍጠር ።
▫️ عنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه ، قَالَ:
((كَانَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ َلا يَغْدُو يَوْمَ الْفِطْرِ حَتَّى يَأْكُلَ تَمَرَاتٍ. ويأكلهن وِترا))ً صحيح البخاري - رقم: (953)
④. ወደ መስገጃ ቦታ በእግር መሄድ እና በእግር መመለስ
▫️ عنِ ابْنِ عُمَرَ، رضي الله عنهما، قَالَ:
(( كَانَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ يَخْرُجُ إِلَى الْعِيدِ مَاشِيًا، وَيَرْجِعُ مَاشِيًا)) حسنه الألباني في صحيح ابن ماجه - رقم : (1078)
⑤. ሶላቱል ዒድ የሚሰገደው ከመስጂድ ውጪ በሰፊ ሜዳ ላይ ወይም የዒድ መስገጃ ላይ መስገድ
▫️ عنْ ابْنِ عُمَرَ رَضِي اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَ
(( أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ كَانَ يَغْدُو إِلَى الْمُصَلَّى فِي يَوْمِ الْعِيدِ، وَالْعَنَزَةُ تُحْمَلُ بَيْنَ يَدَيْهِ، فَإِذَا بَلَغَ الْمُصَلَّى نُصِبَتْ بَيْنَ يَدَيْهِ، فَيُصَلِّي إِلَيْهَا، وَذَلِكَ أَنَّ الْمُصَلَّى كَانَ فَضَاءً لَيْسَ فِيهِ شَيْءٌ يُسْتَتَرُ بِه))ِ صححه الألباني في صحيح ابن ماجه - رقم: (1084)
⑥. ሲሄዱ በአንድ መንገድ ሲመለሱ ደግሞ በሌላ መንገድ መመለስ
▫️عنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، رَضِي اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَ :
(( كَانَ النَّبِيُّ ﷺ إِذَا كَانَ يَوْمُ عِيدٍ خَالَفَ الطَّرِيق ))َ صحيح البخاري - رقم : (986)
⑦. ከዒድ ሌሊት ጀምሮ እስከሚሰገድ ድረስ ተክቢራ ማድረግ
▫️ عن الزهري :
(( أَنَّ رَسُولَ اللهِ ﷺ كَانَ يُخْرِجُ يَوْمَ الفِطَرِ فَيَكْبُرُ حَتَّى يَأْتِي المُصَلَّى، وَحَتَّى يَقْضِي الصَّلَاةَ، فَإِذَا قَضَى الصَّلَاةَ قَطْعُ التَّكْبِيرِ ) السلسلة الصحيحة - رقم: (171) قال الألباني إسناده صحيح مرسل له شاهد موصول يتقوى به .
⑧. የዒድን ኹጥባ ማዳመጥ
▫️عن عبد الله ابن السائب رضي الله عنه قال :
(( حَضٓرَتْ العِيدَ مَعَ رَسُولِ اللهِ ﷺ فَصَلَّى بِنَا العِيدُ ثُمَّ قَالَ قَدْ قَضَيْنَا الصَّلَاةَ فَمِنْ أُحِبُّ أَنْ يَجْلِسَ لِلخُطْبَةِ فَلِيَجْلِسْ وَمِنْ أُحِبُّ أَنْ يَذْهَبَ فَلِيَذْهَبْ)) صححه الألباني في صحيح الجامع - رقم : (4376)
⑨. የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶችን መለዋወጥ
▫️ عن جبير بن نفير رضي الله عنه قال
(( كَانَ أَصْحَابُ النَّبِيِّ ﷺ إِذَا اِلْتَقَوْا يَوْمَ العِيدِ يَقُولَ بَعْضُهُمْ لِبَعْضِ: تُقُبِّلَ اللهُ مِنَّا وَمِنْكَ )) صحح إسناده الألباني في تمام المنة - رقم: (354)
⑩. ከዒድ ሶላት መልስ ሁለት ረከዓ መሰገድ
▫️ عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال :
(( كَانَ رَسُولُ اللهِ ﷺ لَا يُصَلِّي قَبْلَ العِيدِ شَيْئًا فَإِذَا رَجَعَ إِلَى مَنْزِلِهِ صَلَّى رَكْعَتَيْنِ )) حسنه الألباني في صحيح ابن ماجه - رقم: (1076)
منقول
?ዒድ ሙባረክ?
?ለይለተል-ቀድር መሆኑን ባውቅ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ?
እናታችን ዓኢሻ -ረዲየ አላሁ ዓንሀ- እንዲህ ብለዋል:–
የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለይለተል-ቀድርን ባገኝ (ያቺ ለሊት ለይለተል-ቀድር መሆኖን ባውቅ) ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? ብዬ ጠየቅኳቸው።
እሳቸውም:– « አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሂቡ አል-ዓፍው ፈዕፉ ዓኒ » ( አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ) በይ አሉኝ።
(ቲርሚዚይ፣ኢብኑ ማጃህ፣ ኢማሙ አህመድ እና ሃኪም ዘግበውታል)
ዛሬ ረመዷን 29 ነው። የመጨረሻዋ የረመዳን ዊትር ለሊት ነች።
ለይለተል ቀድር ከሚጠበቅባቸው ለሊቶች ውስጥ አንዷና የመጨረሻዋ የዊትር ለሊት ዛሬ ነች:: በዱዐ እና ዒባዳ እንበር
"ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም፡፡"
ረሱል (ﷺ)
“ፀፀት ልክ እንደ ንስሃ ነው።”
ረሱል (ﷺ)
«ውሃን በመጎንጨት ቢሆን እንኳ ስሁርን ተጠቀሙ።»
ነብዩ ሙሐመድ ﷺ
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks, 1 day ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago