Telegram stands for freedom and privacy and has many easy to use features.
Last updated 1 month, 2 weeks ago
Sharing my thoughts, discussing my projects, and traveling the world.
Contact: @borz
Last updated 1 month, 2 weeks ago
Official Graph Messenger (Telegraph) Channel
Download from Google Play Store:
https://play.google.com/store/apps/details?id=ir.ilmili.telegraph
Donation:
https://graphmessenger.com/donate
Last updated 7 months, 1 week ago
﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)
"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)
اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد
ጁምዓ እና የመውጫ ፈተና (Exit Exam) UPDATE!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የትምህርት ሚኒስቴር በጁምዓ ቀን የተማሪዎችን መብት በመጣስ ከ5:30 - 8:00 የመውጫ ፈተና ለመስጠት ማሰቡን ተከትሎ ህብረታችን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቅሬታ ደብዳቤ ማስገባቱ ይታወቃል:: ይህንንም ተከትሎ የህብረቱ ተወካዮች በዛሬው እለት ከትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ዴኤታ ፅ/ቤት በተሰጣቸው መልስ በፕሮግራሙ ላይ ማስተካከያ እንዳደረጠ አሳውቋል:: በዚህም መሠረት በመጪው ጁምዓ የሚሰጠው Exit Exam ከ7:30-10:00 እንደሚሆን ገልፇል:: ይህንንም ለሚመለከታቸው አካላት እንዳሳወቁ ገልፀዋል:: ሆኖም ግን እስካሁኑ ሰዓት ድረስ በይፋ ማስታዎቂያ ያሳወቀው ነገር የለም:: እኛም የሚኖሩ ሁነቶችን እየተከታተልን ለማስተካከል የምንሰራ መሆናችንን እንገልፃለን::
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!
በነገው ዕለት final exam የምትጀምሩ የመጀመሪያ አመት ወንድምና እህቶች ሁሉ መልካም እድል እንመኛለን።
አላህ ፈተናችሁን ያገራላችሁ ዘንድ ዱዓችን ነው፤ ካሰባችሁት በላይ ያቅልልላችሁ፤ ጥሩን ውጤት ይወፍቃችሁ፤ በሰላም ጀምራችሁ በሰላም የምትጨርሱ ያድርጋችሁ። ከፈተናውም በኃላ ለራሳችሁም፣ ለሙስሊሙም ማህበረሰብ የምትጠቅሙበትን የትምህርት ክፍል ይወፍቃችሁ።
ፈተናውን ጀምራችሁ እስከምትጨርሱ ኢስላማዊ አደብ እና ስነ-ምግባር ትላበሱ ዘንድ እና ለጊዜያዊ ጥቅምና ደስታ ብላችሁ ጌታችሁን የሚያስቆጣ ድርጊት ከመፈጸም ትቆጠቡ ዘንድ አደራችን ነው!
﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)
"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)
اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد
ታላቅ የምስራች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች! የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ስር ከሚገኘውና ከዚህ በፊት በሐገራችን የሸሪዓ በተለይም የተውሂድ እውቀትን በማስፋፋት ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ከነበረው ነሲሃ አካዳሚ ጋር በመተባበር ልዩ የሆነ ተከታታይ የሸሪዓ ትምህርት እንዳዘጋጀ ሲገልፅ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው:: አጠቃላይ ትምህርቱ ለሶስት…
በ አዲስ አበባ ዩኒቨረስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የ6ኪሎ ጀመዓ አሚር የሆነው ወንድማችን ኢስማዒል አብዱሮ በሲራራ አዋርድ የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ለመወዳደር ሀሳቡን አቅርቧል::
እና ሁላችሁም ከታች ባለው link በመግባት ሀሳቡን አይታችሁ በሒጅራ ባንክ የኮሜንት ሳጥን ላይ ላይክ ታደርጉ እና አስተያየት ትሰጡ ዘንድ ጋበዝኳችሁ!?
Obboleessi keenya Amiirri Jama'aa Barattoota Musliima Yunivarsiitii Finfinnee Campus 6-kilo baankii hijraa irratti dorgommii business plan dorgomaa jira waan ta’eef fuula Facebook hijra bank link armaan gadii kanaan seenuun comment isaa like akka gootan isin affeera.
???? like his comment.
በአዲሱ የAAU ተማሪዎች ዲሲፕሊን መመሪያ ዙሪያ የህብረቱ እንቅስቃሴ እና የዩኒቨርሲቲው አቋም!
የሙስሊም ተማሪዎችን መብት የሚረግጠው መመሪያ ከወጣ ጊዜ አንስቶ የአዲስ አበባ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ከተለያዩ አካላት ጋር በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ ለማምጣት ሰፊ እና ጥልቅ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል:: መጀመሪያ ላይ መመሪያው የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ረግጦ ተግባራዊ ሊደረግ በተሞከረበት እለት 6ኪሎ የነበሩ የጀመዓ ተወካዮች ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የዚያኔ አመራሮቹ እንደ ምክንያት የጠቀሱት "ሴኩላሪዝም!" የሚለውን ሰበብ ነበር::
ውይይቱ ያለመስማማት ተቋጭቶ የነበረ ሲሆን በ2ኛው ውይይት ላይ አመራሮቹ ሴኩላሪዝም የሚለውን ምክንያት ሙሉ ለሙሉ "ኒቃብ የደህንነት ስጋት ነው!" ወደሚል ቀየሩ:: ስብሰባው ላይ የነበሩ የህብረቱ ተወካዮች ኒቃብ የደህንነት ስጋት እንደማይሆን በምክንያት እና በማስረጃ ሙግት ሲያቀርቡ እዚያው በዚያው ያንን ምክንያት በመተው "ኒቃብ ክላስ ውስጥ በመምህሩ እና በተማሪዋ መካከል የሚኖረውን መናበብ ያከብደዋል:: ኒቃብ የምትለብስ ተማሪ ሙሉ ለሙሉ መሳተፍ ይከብዳታል::" ወደሚል ቀየሩ:: ለዚህም ውሃ ለማይቋጥር ሰበብ የህብረቱ ተወካዮች አሳማኝ መልስ በማቅረባቸው ውይይቱ ያለስምምነት ተቋጭቶ የመጨረሻ መፍትሔ ለማምጣት ዩኒቨርሲቲውም ሆነ ህብረቱ የመፍትሔ ሀሳብ ይዘው እንዲመጡ ቀጠሮ ተያዘ::
በዚህም ውስጥ ህብረቱ ከአዲስ አበባ መጅሊስ ጋር በመወያየት የደህንነት ስጋት እና የተማሪዎችን ማንነት መለየት አይቻልም ለሚሉት ማሳበቢያዎች መጅሊሱ ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በጣት አሻራ የሚለይበትን ቴክኖሎጂ እንደሚያስገባ ዝግጁ መሆኑን ገልፆ ህብረቱ እንደመፍትሔ ሊያቀርብ በተያዘለት ቀጠሮ ዝግጁ ሆኖ ሳለ ዩኒቨርሲቲው የቀጠረውን ቀጠሮ አልወያይም በማለት ሰረዘ:: ከዚያም ቡሃላ ዩኒቨርሲቲው ያወጣውን መመሪያ ሁለት ጊዜ ያሻሻለ ሲሆን ምክንያት ከመቀያየር ውጭ መብታችንን የሚረግጡ ድንጋጌዎችን አላስተካከለም:: ህብረታችንም መፍትሔ ፍለጋ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ከአዲስ አበባ እና ከፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር ውይይቶችን አድርጓል:: እንደ መፍትሔም በቅርቡ አጠቃላይ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ይሆናል::
በዚህ ውስጥ እኛ እንደ ሙስሊም ተማሪዎች የሃይማኖታችንን ድንጋጌ ተከትለን እየደረሰብን ያለውን የመብት ጭቆናና ረገጣ በሰላማዊ መንገድ ልንፈታ መጓዛችን ሰላም ወዳድ ከመሆናችን እንጅ ከፍርሃት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል:: በመብታችን በተለይም እምነት ሃይማኖታችንን አስታኮ በሚመጣ ጭቆና ፈፅሞ አንደራደርም:: ሃይማኖታችን የተፈጠርንበት ብሎም የምንኖርለት እና የምንሞትለት እንቁ የሁለት ሀገር ሀብታችን ነው:: የሚከፈለውን መስዋዕትነት ከፍለን መብታችንን እናስከብራለን:: መብታችንን ሊረግጡ የሚመጡ አካላትንም ተጠያቂ እንዲሆኑ እናደርጋለን::
ነፃነት በነፃ አይገኝም!
ጥያቄ አለን!!
መልስም እንፈልጋለን!!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!!!!
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሁንም በድጋሚ ጥቅምት 28 አዲሱን የተማሪዎች የስነምግባርና የዲሲፕሊን ደንብ ለሁለተኛ ጊዜ እንደገና ያሻሻለ ቢሆንም፤ አሁንም ግን የሙስሊም ተማሪዎችን ቅሬታና ጥያቄ ችላ በማለት የኒቃብና የጀመዓ ሰላትን አሁንም ከለክላለሁ እያለ ነው።
እኛም እንላለን፡-
#ጥያቄ_አለን #መልስም_እንፈልጋለን!!
መቼም ወደኃላ አንልም፤ መቼም እጅ አንሰጥም!!
﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)
"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)
اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد
ይህ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው:: በቻናሉ ከዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች እና የህብረቱ የዕለት ተዕለት ክዋኔዎች ይቀርባሉ::
በአላህ ፍቃድ እና እርዳታ ከዚያም ከሙስሊም ተማሪዎች ጋር በሚኖር መናበብና መተጋገዝ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ሙስሊም ተማሪዎች መብታቸው ተከብሮ ይማሩ ዘንድ እንተጋለን::
መረጃዎች ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ይደርሱ ዘንድ ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU