★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago
?#በረሱል_ፍቅር_ሰጥሜ_መስጂዳቸውን_ጎጆዬ
............. #ላደርግ_ለአላህ_ቃል_ገባሁ.............
✍አሚር ሰይድ
ቁመቱ አጭር መልኩም የቀይ ዳማ ነው። ጀለቢያ መልበስ ያዘወትራል። ከዘምዘም ዉሀ በመዳፉ እየጨለፈ ይጎነጫል። ካገኘ ፍራፍሬ ይመገባል። ካጣም ሆዱን አጣጥፎ የጌታውን ቁርአን እያነበበ ፆሙን ያድራል። መሬት ፍራሹ፣ ብርድ ልብሱም ሠማይ ነው። የነቢ መስጂድ ውስጥ ጎጆውን ቀልሶ ለአስርት ዓመታት ኖሯል። ሰውነቱ የኮሰሰ ቀጫጫ ትውልደ አልባኒያዊ ነው።
ከነቢ ቀብር ፊት ለፊት ከሐረም አን-ነበዊ መታጠቢያ ቤት የወጣውን ይህን ወጣት አራት የሰዑዲ ፖለሶች ዘለው ተከመሩበት። በሆዱ አስተኝተው እጆቹን ቀፍድደው የፊጥኝ አሰሩት “ሽፍታም ሌባም አይደለሁም” እያለ መጮኽን መማፀን ጀመረ።
በዕድሜ የገፉ አንድ ሽማግሌ ክስተቱን ተመልክተው ቢጠጉ ገፅታው አልጠፋቸውምና “ይህን ወጣት አውቀዋለሁ” አሉ
“የረሱል መስጂድ ውስጥ እየሰገደ ሲያለቅስ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ አላህን ሲማፀን አውቀዋለሁ አዎ ራሱ ነው" አሉ መሬት ላይ የሚንፈራገጠውን ወጣት ትኩር ብለው እየተመለከቱ።
ጣል ጣል ብለው የሚታዩ የፂም ፀጉሮች ባለቤት ነው። ቀለል ያለ ሰው ፊቱ ላይ የሚንፀባረቀው ነጭ ኑር ከሩቅ ያብለጨልጫል። ሸይኹ ቀጠሉ "ምን አጥፍቶ ነው ያሰራችሁት?" ብለው ጠየቁ።
.... “አንተ ሽማግሌ!" አሉ ፖሊሶቹ" ጣልቃ አትግባ ይህ አንተን አይመለከትም" አላቸው።
“ሲሰርቅ አይታችሁታል?! ገዳይስ ነው ነፍስ ሲያጠፋስ ደርሳችሁበታል?! ወይስ ምን ወንጀል ሰርቷል?!" ሸይኹ ዳግም ግራ በመጋባት መንፈስ ጠየቁ፡፡
......“ይህ ወጣት" አሉ ፖሊሶቹ ንግግራቸውን ሲጀምሩ “ይህ ወጣት... ኑሮውን እዚህ መስጂድ ውስጥ ማድረግ ከጀመረ አስርት ተከታታይ ዓመታት ተቆጥረዋል። የመኖርያ ፈቃድ ኢቃማም ሆነ ፓስፖርት የለውም። በነቢ መስጂድ ስለተቀመጠ አባረን ልንዘው አልቻልንም ነበር። ስናሳድደው ሲያመልጠን ይሄው አስር ዓመታት ተቆጠሩ። ዛሬ ግን በእጃችን ገባ። ወደ ኤርፖርት ወስደን ወደ ሀገሩ አልባኒያ ልንመልሰው እንዳያመልጠን አድርገን አሰርነው" አሉ።
ወጣቱ የፖሊሶቹን ንግግር ሲሰማ ስቅስቅ ብሎ አያለቀሰ?? “አልሰረቅኩም ነፍስም አላጠፋሁም በረሱል ፍቅር ሰጥሜ መስጂዳቸውን ጎጆዬ ላደርግ ለአላህ ቃል ገባሁ። ሽፍታም አይደለሁም። የአላህ መልዕክተኛን ስለምወድ እዚህ ቀረሁ። ከረሱል ﷺ መስጂድ ከሳቸው ጉርብትና ተነጥዬ እንዴት መኖር ይቻለኛል?? አለ ትካሻውን አያወዛወዘ
"ተቀባይነት የሌለው ምክንያት ነዉ ። እዛዉ ወደ ሀገርህ ትመለሳታለህ አሉ ፊታቸው በንዴት የቀላው ፖሊሶች
ወጣቱ ፊቱን ወደ መስጂድ አን-ነበዊ አቅጣጭቶ : -
“አላህዬ ስምምነታችን አንዲህ ነበር? " አለ አንገቱን ወደ ሰማይ አቅንቶ “ከአላህ መልክተኛ ጎን አኑረህ አንድትገለኝ አልነበር የጠየቅኩህ?! እናትና አባቴን ትቼ ሱቄን ዘግቼ የመጣሁትስ ለዚሁ አይደል?! ፍቅራቸው ንግዱን አስትቶ እዚህ አመጣኝ። መስጂዳቸውን መኖርያዬ ላደርግ ጉርብትናቸውን ትቼ ሀገሬ ላልገባ በአንተ ቃል ገባሁ። አሁን አነዚህ ሰዎች እየከለከሉኝ መሆኑን ተመልከት....ያ አላህ ጣልቃ ገብተህ ለምን በጠየቅኩህ ዱዓ ምላሽ አትሰጥም?! ያረቢ የረሱልን ጉርብትና እለምንሀለው?" ሲል በምሬት እያነባ ጌታውን ጠየቀ።
......ከመቅፅበት በቆመበት ቦታ ተዝለፍልፎ መሬት ተደፋ። ፖሊሶቹ “ተነስ አንተ አታላይ” እያሉ በያዙት ዱላ አንድ ሁለቴ አቀመሱት። ወጣቱ ግን ምላሽ አልሰጠም መሬት አንደወደቀ ነው። ውሀ ደፉበት ሊነቃ ግን አልተቻለውም። አምቡላንስ በአስቸኳይ አስጠርተው ይዘውት ወደ ሆስፒታል አቀኑ።
ፖሊሱ ክስተቱን ሲያወጋ እንዲህ ይላል፡-
“ለሞት የሚያበቃ ዱላ አልሰነዘርንበትም። ሆስፒታል አንዳደረስነው ሀኪሞቹ የልብ ምቱን አዳምጠው ሩሑ ከጀሰዱ የመላቀቁን ዜና አረዱን። አዎ ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው ጌታ አላህ ምሳሹን ሰጠ። በረሱል ሀገር በሳቸው መስጂድ አቅራቢያ ሩሁን እንዲያወጣ መለከል መውትን አዘዘ"
ፖሲሶቹ በትዕይንቱ ዕንባ እየተናነቃቸው በሀዘን ተብረከረኩ። በድርጊታቸው ተፀፅተው በዕንባ ተዋጡ።
"ለአላህ መልእክተኛ ﷺ ይህን ያህል ፍቅር እንዳለው ብናውቅ ኖሮ ይህን ባላደረግን” እያሉ በድንጋጤ ተዋጡ።
አምቡላንሱ ጀናዛውን ይዞ ወደ በቂዕ መቃብር ጉዞውን ጀመረ። ታላላቅ ሰሐቦች ወደተቀበሩበት ሥፍራ ከነፈ።
ሸይኹ “ክስተቱን ከጀምሩ እስከ ፍፃሜው እየተከታተልኩ ነበር" ይላሉ። ታጥቦ ተከፈነ ሰላተል ጀናዛ ከተሰገደበት በኋላ ወደ ቀብሩ ልናስገባው ስንሄድ ፖሊሶቹ በትከሻቸው ተሸክመውት ነበር። ጠጋ አልኩና አኔም ጀናዛውን ልሸከም አቀበለኝ አልኩት ለአንደኛው ፓሊስ። እሱም ዓይኖቹ አያነቡ "ወንጀላችን ይብቃን ምናልባት አላሁ ተዓላ ይቅር ይለን ዘንድ ጀናዛውን እኛ አንጂ ማንም እንዲሸከመው አንፈቅድም" አለኝ
ጌታህን አብዝተህ ስታወሳ መጨረሻህ የምራልና አላህዬን ይዘህ ፅና!!
ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
⚡️⚡️ነብዩን መዉደድ ማለት ሙዚቃ የሚመስል ነሺዳን በሌላ አገላለፅ የአሁን ነሺዳ እሩብ ጉደይ ለሙዚቃ የሆነን በማዳመጥ ...አብሮ ነሺዳን በማለት በየመድረኩ ነቢይ በማለት አይደለም፡፡ የነቢይ ዉዴታ ሲኖርህ መድረክ ለመድረክ በየሚዲያዉ ነቢይ ስላልን ወደናል ማለት ራስን ማታለያ ነዉ፡፡ ራስን ማታለል ይቻላል አላህን ግን ማታለል አይቻልም፡፡ ነቢዩ ስም ልናነሳ ስንል እስክታዉ ዝላዩ ዉዝዋዜዉ ሳይሆን እንባችን ይቀድመን ነበር ወገን?
በፊት የነበሩት ትዉልዶች ነቢይ ሙሀመድ ﷺ እንዴት እንደሚወዷቸዉ በኡሁድ ጦርነት ጊዜ ነቢይ ሙሀመድ ﷺ ይወዱ የነበሩ ሱሀቦች እና አሁን እኛ ባለንበት ሀቢቡና ﷺ እንዴት እንደምንወድ ራሳችንን እንፈትሽ ለምን....ነገ የምንቀሰቀሰዉ የስራችን ሚዛን የሚለካዉ ከእነሱ ጋር ስለሆነ...እኛ የነቢይ መሀመድ ﷺ ኡመት ነንና
በቀንም በሌትም በጧትም በማታም ሶሉ አለነቢይ ሙሀመድ ﷺ?
30 አመት ያህል ነሺዳ ከማዳመጥ የአንድ ደቂቃ
ሶለዋት አለረሱል በላጭ ነዉ::
አንድ ሺህ ነሺዳ ከማዳመጥ አንድ ሶለዋት አለረሱል ብናወርድ ነዉ ለኛ ነገ ሙተን ቀብር ገብተን ለአኼራ ጥያቄ የሚጠቅመን ..
ህይወት ትላንት ወይ ነገ አይደለችም ህይወት አሁን ናት ለቀብር የሚጠቅምህን ስራ፡፡አሁን ሲያልፍ ትላንት ይሆናል የወደፊት አሁን ደግሞ ነገ ይሆናል
....ግን ነገን ማየት ላንችል እንችላለን ጀናዛ ልንባል እንችላለንና በአገኘነዉ አጋጣሚ ጊዜን በነሺዳ(እሩብ ጉዳይ ሙዚቃ) ከማዳመጥ ይልቅ ሶለዋት አንዘንጋ
ሶሉ አለነቢይ ሙሀመድ ﷺ ﷺ ﷺ???
join???
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️#ፍትሕ_ከሰማይ_ሲወርድ⚡️⚡️
✍አሚር ሰይድ
ከማህፀናቸው ፍሬ የወጣ ልጅ፣ በክፉ ጊዜም ደራሽ ዘመድ አዝማድ የላቸውም። የሰባ ዓመት ዕድሜ ደካማ ባልቴት ናቸው። “እንዴት ሰው ያለወገን ይፈጠራል?" ይባል ይሆናል። ዘመድ አዝማዶቻቸው ሁሉ ይህችን ዓለም ተራ በተራ እየለቀቁ ቀድመዋቸው ተጉዘዋል፡፡ የጤንነታቸው ጉዳይ ማጠራጠር ከጀመረ ሰንበትበት ብላል። "እንደምን ዋሉ? " ላላቸው ሁሉ "ጉልበቴን ይቆረጥመኛል፣ ወገቤን ያመኛል፣ ዓይኔንም ያዝ እያደረገኝ ነው" ሳይሉ አያልፉም። ይህ ብቻም አይደለም" አላህ መጨረሻዬን አሳምሮ ብርሀኔን ሳያሳጣኝ፣ መላወስ ሳይሳነኝ ቀልጠፍ አድርጐ በወሰደኝ" ሲሉ ያክሉበታል፡፡
ዋነኛ መተዳደርያቸው ከመንግስት የሚያገኙት ክፍያ ነው። ኸዲጃ ይሰኛሉ። እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለዉን የጡረታ ዋስትና የሚቀበሉት በዓመት አንድ ጊዜ ነው። መንግስት የሚሰጠውን ገንዘብ እንዲያገኙ የታገለላቸዉ የቅርብ ጎረቤታቸው አንድ ወጣት ነበር። ኸዲጃ ገንዘባቸውን በተቀበሉ ጊዜ ሁሉ ካንጀታቸው ይመርቁታል።
ምግባረ ሠናዩ ወጣት አካባቢውን እስከለቀቀበት ጊዜ ድረስ ወይዘሮዋ ክፍያውን ለመቀበል ሲሄዱ አጃቸውን ይዞ ወገባቸውን ደግፎ ሲያመላልሳቸው ለዓመታት ሲያገለግላቸው ቆይቶ፣ በመጨረሻ አካባቢውን ለቀቀ። ወጣቱ መኖርያውን ከቀየረ ጥቂት ወራት በኋላ የደመወዝ ክፍያ ቀን ደረሰ። ወጣቱ የለም። ከአካባቢው ነዋሪዎች እምነት የሚጣልበትና አድርሶ ሊመልሳቸው የሚችል ሰው አላገኙም።
ኸዲጃ ከዚያ የተባረከ ወጣት ሌላ እምነት የሚጥሉበት ሰው እንደማያገኙ ተረድተዋል። ብቻቸውን ለመሄድ ቆርጠው ተነሱ።ቁና ቁና እየተነፈሱ ክፍያው ከሚፈፀምበት መስሪያ ቤት በደረሱ ጊዜ የመስሪያ ቤቱ ሴት ሰራተኞች በሚገባ ተቀብለው አስተናገዷቸው። ድካማቸውን ተወጥተው፣ ደሞዛቸውን ተቀብለው ወደ ቤታቸው ለመመሰስ ሲነሱ የመስሪያ ቤቱ ሴት ሰራተኞች እስከ ታክሲ መሳፈርያው ድረስ ሸኛቸው።
ሸኚዎቻቸው ቆመው ታከሲ በመጠበቅ ላይ ሳሉ አንድ በመካከለኛ ዕድሜ ላይ የሚገኝ ባልቴቷን በስም ጠርቶ እጃቸውን በመሳም ሰላምታ ሰጣቸው። ወደ ሸኚዎቻቸው ዞሮ የቅርብ ጐረቤታቸው መሆኑን ነገራቸው። መኪና ይዟል። ሸኚዎቹ ታክሲ እየጠበቁ እንደሆነ ሲነግሩት “እኔ እያለሁ ምን ታክሲ ያስፈልጋል። እናንተ ተመለሱ እኔ አደርሳቸዋለሁ" በማለት ሸኚዎቹን አስናብቶ ባልቴቷን ወደ መኪናው ወሰዳቸው። ጎልማሳው ኸዲጃን ከጐኑ አስቀምጦ የባጥ የቆጡን እያወራ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከግማሽ ሰዓት በላይ ተጓዙ፡፡
ኸዲጃ መንገዱ ያለቅጥ ረዘመባቸውና አንዳች ነገር አእምሯቸውን ከነከነው። ጥቂት አሰቡና “ምናልባትም እግረ መንገዱን መድረስ የፈለገበት ይኖር የሆናል" ሲሉ ስጋት ያደረበት ልባቸውን መልሰው አረጋጉት። ነገሩ ግን እንደዚያ አልነበረም። ሰውየው አቅጣጫውን በመቀየር ወደ ግራ ታጥፎ ከዋናው መንገድ በመውጣት ጉዞውን ሽቅብ ወደ ተራራው አደረገ። የኸዲጃ ልብ በፍርሃት ይናጥ ገባ። መላ አካላቸው ተንዘፈዘፈ ...መጮህ ቃጣቸውና መልሰው ተውት። የሞት ሞታቸውን “ልጄ ወዴት ነው የምትወስደኝ?" ሲሉ ጠየቁት ቁርጥ ቁርጥ ባለ አነጋገር። “እዚህ ቅርብ ነው። የአትክልት ቦታዬን ማየት አለብኝ። እርስዎም ፍራፍሬዎችን ይዘው ቤትዎ ይመለሳሉ" አላቸው። ያሰበው ነገር የተነቃበት ይመስል በተሳሰረ አንደበት።
ኰሮኰንቹን ሲጨርስ መኪናውን አቆመ። ዝምታ ለደቂቃዎች ሰፈነ። ትርጉም ያለው ዝምታ ነበር፡ የባልቴቷን የሰጋት፣ የጐልማሳው ደግሞ ዘዴን የመሻት። ደቂቃዎች ተቆጠሩ። ጐልማሳው ጥጥና ጨርቃ ጨርቅ ነገር ከኪሱ አወጣ። በፍርሀት ተውጠው አቀርቅረው የተቀመጡትን ደካማ አሮጊት አንገት አነቀ። እንዳይገድላቸው ተማፀኑት። ገንዘባቸውን ወስዶ ሕይወታቸውን ብቻ እንዲያተርፍላቸው ለመኑት። ስለ ነገሩ ለማንም ትንፍሽ እንደማይሉም ገለፁለት። .....በአምሮተ ንዋይ የታወረው ጐልማሳ ግን ሊራራላቸው አልቻለም። ይልቁንም ጭካኔውን አባሰው። አፋቸው ውስጥ ጥጥ ከጐሰጐሰ በኋላ ገዘባቸውን ከጉያቸው አወጣ። አጆቻቸውን ከተቀመጡበት ወንበር ጋር የፊጥኝ አሰራቸው። ከመኪናው ወርዶ ከኋላኛው የመኪናው ኪስ አካፋና ዶማ አወጣ።
ደካማዋን ባልቴት ገድሎ ከቀበረ በኋላ በገንዘባቸው ዓለም ዘጠኝ ሊሰኝ በመወሰን ቁፋሮውን ተያያዘው። መጠኑ ብዙ በሆነው ብር የሚያገኘው ደስታ እየታየው በጥድፊያ ይቆፍር ጀመር። ቢሆንም ግን ጉድጓዱን ቆፍሮ ሳይጨርስ ድንገተኛ ፍትህ ከአላህ ዘንድ ወረደ። ርዝማኔው ከአንድ ሜትር በላይ የሆነ ኮብራ እባብ አቀርቅሮ በሚቆፍረው በዚያ አረመኔ ሰው ጀርባ ላይ ተከመረ። አራት የተለያየ ቦታ ከነደፈው በኋላ አንገቱ ላይ ተጠመጠመ። ወጣቱ ደካማዋን አሮጊት ለቀብርባት በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ተዘረረ።
ይህ ሠማያዊ ፍትሕ ከመውረዱ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት ሰውየው ጉድጓዱን በመቆፈር ላይ ሳለ የተጨነቁት ባልቴት ደጋግመው አላህን ይለምኑታል “በእርግጥም ያንተ ፍጡር ነኝ። በንፁህ ልቤም ተገዝቼሀለሁና ከዚህ ድንገተኛ መአት አድነኝ። የማሳድጋትን የቲም ልጅ ለወግ ማዕረግ ሳላበቃ አትግደለኝ" ይሉ ነበር ደጋግመው።
#ባርያውን_የማይረሳው ጌታ የእኒህን ደካማ ሴት ጥሪ ሰምቶ ፈጣን ምላሹን ሰጠ። ሕይወታቸውንም ታደገ።
ሰዓታት አንድ ሁለት ተብለው ተቆጠሩ። ህፃናት እረኞች የከብት መንጋ አየነዱ በአካባቢው ሲያልፋ የቆመ መኪና ተመልከተው ተጠጉ። በአእምሯቸው የሚከብድ ነገር አይተዋልና ለወላጆቻቸዉ ሊነግሩ ፈጠኑ። የህፃናቱ ወላጆች የሰሙትን ለፓሊስ አሳውቀው ወደ ሥፍራው ተጓዙ።
....አፋቸው በጥጥና በጨርቅ የታፈነውና እጆቻቸውም የፊጥኝ የታሰሩት አሮጊት ፖሊስ ደርሶ ከአፈናውና ከእስራቱ ነጻ አወጣቸው “አልሐምዱሊላህ" ሲሉ ተሰማ። ጉድጓድ ውሰጥ የተዘረረውን ሰው ሁኔታ ለማጣራት ፖሊሶች ፊታቸውን ወደዚያ አዞሩ። ወደ ሰውየው በማምራት ላይ ሳሉም በሰውየው አንገት ላይ የተጠመጠመው እባብ ቀስ በቀስ ተፈትቶ ወደ ጥሻ ውስጥ ተፈተለከ። የሰውየው ነገር አብቅቷል። የደም ዝውውሩ አቁሟል። አስከሬኑ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ሲላክ ደካማዋ አሮጊት ወደ ቤታቸው ተወሰዱ። አጀብ የአላህ ስራ!
#ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
አብሽሩ አይዞን ....ጥሎ የማይጥል በችግር በጭንቅ በሀሳብ ከሰዉ መፍትሄ የጠፋ ጊዜ የሚሰማ ለእኛ መፍትሄ ቅርብ የሆነ ጌታ አለን አልሀምዱሊላህ፡፡ አልቅሰን ሰደቃ ኸይር ስራ አብዝተን ወይም ተዉበተን አድርገን እንቅረበዉ እንጠይቀዉ አላህን ጠይቆ ያፈረ ባዶ እጁን የተመለሰ የለምና
??ብቻ ብቻ ጠይቀነዉ ዘግይቶ ይሆናል እንጂ የጠየቅነዉ አይቀርም.አላህ የኛን ዉስጥ ስለሚያቅ የጠየቅነዉን ቢሰጠን ለኛ የማይጠቅም ከአላህ የሚያጣላ ሊሆን ስለሚችል አስቀርቶት በአጅር በምንዳ ወይ በሌላ ለኛ በሚጠቅም
ነገር ቀይሮት ይሆናል ለምሳሌ በጤና እና ድንገተኛ አደጋ የሚመጣን በላዕ ችግር አስቀርቶልን ይሆናል፡፡ የአላህን በር አንኳክቶ ቦዳዉን ላይመልስ ቃልገብቷል፡፡ እስኪ ለሰዉ ነግረነዉ ያልተፈፀመ ከሰሚዉ ጆሮ ያላለፈዉን ጉዳይ ያአሏህ ያዘል ጀላሊ ወልኢክራም ብለን እንገረዉ ..መልስ አለ
አይዞን የምን ተስፋ መቁረጥ ጠበቅ አድርገን የአላህን ደጅ ከመፅናት እንዳናቆም .የጠየቅነዉ ሁሉ አላህ የጠየቃችሁት ከኔ የማያጣላችሁ ብሰጣችሁ እኔን ወንጅላችሁ ጀነቴን ታጣላችሁ ብሎ አስቦልን ይሆናል ያልሰጠን እንጂ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ዱአ ስናደርግ የተደረገዉ ዱአ የሚደርስ ወይም ወንጀል እንደሚያብስ ወይም ለአኼራ እንደሚቀመጥ ነግረዉናል፡፡
አይዞን
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ እንዴት ናቹልኝ...
#ሰደቀቱል_ጃሪያ_ስለሚባለው_የሰደቃ_አይነት_ምን_ያህሎቻችን_ነው_ምናውቀው?
#ሰደቀቱል_ጃሪያ:- ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ ቀጣይነት ያለው ሰደቃ /ምፅዋት/ ነው:: ቀጣይነት ያለው ሲባል ደግሞ ምንዳው ወይም አጅሩ በሕይወት እያለን በሰጠነው አንድ ሰደቃ ምክንያት ሕይወታችን ካለፈ በኃላም ምንዳው ሳይቋረጥ እየተጨመረልን የሚሄድ ማለት ነው::
#ዛሬ በዚህ ርዕስ ላይ የማወራችሁ በምክንያት ነው...
#ኢፋዳ የሚባል ኢስላማዊ ተቋም ይህንን የ #ሰደቀቱል_ጃሪያ ዕድል በአቅማችን ልክ እንድንሳተፍበት ስለጋበዘን ነው::
ምን መሰላችሁ የሰደቃው ሀሳብ..?
?በአላህ ፍቃድ 22 #የውሃ_ጉድጓዶችን ከፍተኛ የውሃ እጥረት ባለባቸው የሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ለማስወጣት እቅድ ተይዟል::
የውሃ ጉድጓድ ለተቸገሩ ሰዎች ማስቆፈር ደሞ አንዱ የሰደቀቱል ጃሪያ አይነት ነው::
በላጩ ሰደቃ ውሀ ማጠጣት ነው እንዳሉት መልእዕተኛው ?
?መቼም በዚህ ሰደቃ ላይ ለመሳተፍ የማይጓጓ ይኖራል ብዬ አላስብም... አይደለም እንዴ ውዶች?
ይህን ያህል ከተግባባን አሁን ወደ ተግባሩ ብንሸጋገር ምን ይመስላችኃል... ዳይ ወደ ሰደቃችን???
ሁላችሁም በምትፈልጉት የብር መጠን መሳተፍ ትችላላችሁ:: ከ100 ብር - 5000 ብር ድረስ የተዘጋጀ ኩፖን አለ...
የምታስገቡበት አካውንት:-
●የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ1000652519524
●ዘምዘም ባንክ 0048131010301
●ሂጅራ ባንክ 1006954160001
●አዋሽ ባንክ 014321422006700
●አቢሲኒያ ባንክ 200009207
ካስገባችሁ በኃላ ስክሪን ሹት በ @Abdu979 መላክ እንዳትረሱ
ለበለጠ መረጃ? @Abdu979
❔❔#ኢስላም_ዛሬም_አለ❓❓
✍ አሚር ሰይድ
ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ለበርካታ ዓመታት በኢስላማዊ ርዕዮተ ዓለምን ያስተዳደረው ታላቁ የዑስማኒያ ኸሊፋ በውስጥ መናፍቃንና በጠላቶቹ ሴራ ወድቋል። የፈረንሳይ ኃይሎች ደቡብ ቱርክ "ካህራማማራስ” ግዛትን ተቆጣጥረዋል። ሴቶች የሚለብሱት ኒቃብ ነበር። ያ የኢስላም መገለጫ፣ የክብራቸው ማረጋገጫ፣ የውበት ማጌጫቸው።
ታዲያ በዚህ መሐል የፈረንሳይ ጄኔራል ኒቃብ ለብሰው በመንገድ ዳር የማጓዙ ሶስት ሴቶችን ተመለከተ ውስጡ በንዴት በገነ። #ኢስላም_ዛሬም_አለ? ሲል ራሱን እየጠየቀ ተብከነከነ። ሊያጠፉት የቋመጡት ኢስላም በሕይወት በመኖሩ ልፋቱ ከንቱ የሆነ ያህል ተሰማው።
"ኸሊፋው ተወግዷል አሁን በፈረንሳይ አገዛዝ ስር ናችሁና ኒቃባችሁን አውልቁ" በማለት ጮኸ። ሴቶቹ ኒቃባቸውን ከሚያወልቁ በያዘው ጥይት ተበሳስተው ነፍሳቸውን መሰዋትን መረጡ። በኒቃባቸው ምክንያት ሸሂድ ሆነው ጌታቸውን መገናኘትን ተመኙ።
.....እሳት ጎርሶ ተጠጋቸው። የአንዷን ኒቃብ ለማውለቅ አጁን ዘረጋ። ይህን ክስተት ይመለከት የነበረ “ኢማም ሶትጆ” የተባለ ወተት ነጋዴ ሙስሊም ሴቶቹ ላይ የተጋረጠውን ጥቃት ለመከላከል የፈረንሳዩ ወታደር ላይ እንደተቆጣ ነብር ዘሎ ተጠመጠመ። ጄኔራሉ በጀርባው የሸጎጠውን ሽጉጥ ነጥቆ ተኮሰ አልሳተውም መሬት ዘረረው። ለሙስሊም ሴቶች ክብር ሲል ጥላታቸውን ጥሎ በነጠቀው ሽጉጥ አጅቦ ቤት አደረሳቸው።
በዚህ ክስተት ምክንያት በካህራማማራስ ከተማ ግዙፍ አብዮት ፈነዳ። ሁሉም ለኢስላም ሊሰዋ መሳርያ ያለው በመሳርያ ...መሳሪያ የሌለዉ በባዶ እጁ ከፊት ተሰለፈ። ፈረንሳውያንን በማባረር ከተማዋን ነፃ አወጡ።
ከተማዋ በኢማም ሶትጆ ስም አሸብርቃ ዋለች። የተሸፈነች ሙተነቀብ ሴት መሬት የወደቀ የፈረንሳይ ጄኔራልና ኢማም ሶቶጆ ሽጉጥ አነጣጥሮ ሲገድለው የሚያሳይ ምስል በከተማው አደባባይ ላይ ተተከለ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በስሙ ተሰየሙ። ታሪክ የማይረሳው ጀግና ሲሉ አስከ አሁንም የቱርክ ጎዳናዎች ያስታውሱታል።
አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው።
#ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
join???
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
#እህቴ_ሆይ_እንደምንበቀልልሽ_ቃል_እንገባለን
✍ አሚር ሰይድ
ጊዜው ሩሲያ ችቺኒያን የወረረችበት ወቅት ነው ጊዜዉ 2000 እንደ አውሮፓዉያኑ አቆጣጠር።
ዩሪ ቡዳኖቭ የተባለ የሩሲያ የጦር ጄኔራል በአንድ የቺቺኒያ መንደር በማለፍ ላይ ነው። ከአንድ ደሳሳ ጎጆ የሴት ድምፅ በመስማቱ ወታደሮቹ አንዲቆሙ ትዕዛዝ ሰጠ... ወደ ቤቱ አመራ። የ18 ዓመት ሴት ልጅን አየ በጉልበት ጎትቶ አወጣት። ልጅቷ እየጮኸች እንዲለቃት ተማፀነችው። ወላጆቿም ከልመና ውጭ ምንም ሊያደርጉላት አልቻሉም። ወደ አንድ ክፍል ይዟት ገባ። ክብሯን ነጠቃት? ሙተሒጂባዋን፣ ንፁሀን ሴት ደፈራት! በዚህም አላቆመም። ወፍራም ገመድ አምጥቶ አንገቷ ላይ ጠመጠመ። ልጅቷ በደከመ ድምፅ ትጮሀለች። ወላጆቿ ይማፀናሉ። የአካባቢው ሰዎች ይለምኑታል። ጀኔራሉ ግን ከቁብ ሳይቆጥራቸው ልጅቷን በገመድ አንቆ ገደላት። አንዱን ወታደር አዝዞ ክቡር ጀናዛዋን በታንክ ብረት ፈጨው! ወላጆቿ ፊት ገደላት። ሙስሊም በመሆኗ ብቻ! ይህ ሲሆን አሜሪካም ሆነች ፈረንሳይ ስለ ጉዳዩ አልተናገሩም። የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ድርጊቱ ለመተቸት አልፈቀደም። ስለ ሴት ልጅ ነፃነት ሲለፈልፉ የነበሩ 'የሴት ልጅ ተቆርቋሪዎች ' ያኔ አፋቸው ተለጎመ።
በአላህ ይሁንብኝ ይህ የተፈፀመው በአንድ ምዕራባዊ ውሻ ላይ እንኳ ቢሆን ጦርነት ባወጁ ነበር። ግን የተገደለችው ሙስሊም ሴት ነች፡፡ ወላጆቿ ይህን ዘግናኝ አረመኔያዊ ድርጊት የደካሞች ጌታ ለሆነው አላህ ብሶታቸውን አሰሙ።
ይህ ዜና የቺቺኒያ ሙጃሂዶች ጆሮ ደረሰ። እነዚያ የሙስሊም ደም ሲፈስ ደማቸው የሚፈላው፣ አይናቸው ለሚያነባው ብርቅዬ የኢስላም የቁርጥ ቀን ልጆች አነኸጧብ፣ አነሻሜል፣ አነ አቡል ወሊድ ዘንድ ደረሰ! ለእህታቸውና ለኢስላም ሊበቀሉ በአላህ ስም ማሉ።
ድርጊቱን የፈፀመውን ጄኔራል አሳልፈው አንዲሰጧቸው ካልሆነም ዘጠኝ የሩሲያ ልዩ ኃይል አባላት ምርኮኞችን አንደሚያርዷቸው አስጠንቅቀው መልእክት ላኩ። የ24 ሰዐት የጊዜ ገደብም ሰጡ። ጊዜው ተጠናቀቀ። ሩሲያዎች ግን አሻፈረኝ አሉ። ምርኮኞቹን ደርድረው ለተገዳይዋ ወንድም ሠይፍ በመስጠት አንገታቸው አንዲቀላ አረጉ። ቁስላቸው ግን ሊሽር አልቻለም። በ72 ሰዓታት ውስጥ አሳልፈው አንዲሰጧቸው እምቢ ካሉ ግን የከፋ አደጋ እንደሚጠብቃቸው አስጠነቀቁ።
.....72ቱ ሰዓታት አለፉ። አሁንም ሩሲያዎቹ ያንን ወታደር ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። ይልቁንስ ምን እንደሚፈጠር መጠባበቅ ያዙ።
የቀውቃዝ አንበሶች አውርተው አልቀሩም። እጅግ በማደንቅ ጀግንነት አንድ ሙሉ ፈንጅ የተጫነ
ጭነት መኪና ወደ ሩሲያ የጦር ካምፕ ግቢ ገባ። መኪናው ፈነዳ። 1,500 የሩሲያ ልዩ ኃይሎች ተገደሉ። ከነሱ ውስጥ ዘጠኙ ከባባድ የጦር ጄኔራሎች ነበሩ።
ይህ የጀግንነት ስራ የሙስሊሙ ደም ዋጋ እንዳለው ያሳየ መለያ ነው። ጀግኖቻችንን አላህ በእዝነቱ ሸሂድ ያድርጋቸው!በጀነት ውስጥ ከነ ሐምዛ ከነ ኻለድ ከነሰለሀዲን ጋር ይቀሰቅሳቸው!
#ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
ዛሬ ላይ ያለዉ ሙስሊም ምዕራባዉያን አስምረዉ ባስቀመጡልን መስመር ሁኗል የtiktok የማህበራዊ ሚዲያ ዉሽማ ሁኗል፡፡ሙስሊም ሴት ብትደፈር ሂጃቧ ቢገፈፍ ከሚዲያ ወሬ ዉጭ የማይሰራ ትዉልድ ሁነናል፡፡ሰርቶ በሀላል መክበር የማያልም ምንጩ ከማይታወቅ online ብር ለማግኘት ሙሉዉን ጊዜዉን ሰዉቶ ሀምስተር ዶግ ፓፕ እያሉ ከዲን መስመር እና ከኢባዳ ተዘናግቶ በኢስላም ካባ ተሸፍነን እየኖር ነዉ አሏህ ልቦናዉን ይስጠን
join???
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
እናትነት??
በጃፓን የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ቀዝቀዝ ካለ በኋላ የነብስ አድን ሰራተኞች በአንድ ፍርስራሽ ቤት ሲገቡ የአንዲት ሴትን እሬሳ ተመለከቱ።
ሴትየዋ በጉልበቷ ተንበርክካለች፤ ሰውነቷ ወደ ፊት ዘንበል ብሎ ነበር፣ ሁለቱ እጆቿ በአንድ ነገር ተደግፎ ነበረ። የፈራረሰው ቤት ጀርባዋ እና ጭንቅላቷ ላይ ወድቋል።
የነፍስ አድን ቡድን መሪው እጁን ወደ ሴቲቱ አካል ለመድረስ በግድግዳው ላይ ባለው ጠባብ ክፍተት ውስጥ እጁን ሴትየዋ ላይ አደረገው።
ሴትየዋ አሁንም በሕይወት ልትኖር እንደምትችል ተስፋ አድርጎ ነበር። ይሁን እንጂ ቀዝቃዛው እና ግትር ሰውነቷ በእርግጠኝነት እንደሞተች ነገረው።
እሱና የተቀሩት የቡድኑ አባላት ከሴትየዋ ቤት ወጥተው ቀጣዩን የፈራረሰውን ሕንፃ ለመፈተሽ ሄዱ።
የቡድን መሪው ግን የሆነ ነገር ተጠራጠረና ወደ ሟቾ ሴት ፍርስራሽ ቤት እንደገና ተመለሰ።
አሁንም ተንበርክኮ ከሬሳው በታች ያለውን ትንሽ ቦታ በእጁ ሲፈትሽ የሆነ ነገር አገኘ።
የነብስ አድን የቡድን መሪው በድንገት እየጮኸ ፣ “ሕፃን! ልጅ አለ! "
አንድ የ3 ወር ሕፃን ልጅ በእናቱ ሬሳ ሥር በአበባማ ብርድ ልብስ ተጠቅልሎ ነበር።
በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ሴትየዋ ልጇን ለማዳን የመጨረሻውን መሥዋዕትነት ከፍላ ነበረ።.
ቤቷ በሚፈርስበት ጊዜ ልጇን ለመጠበቅ ስትል ሰውነቷን ሙሉ ለሙሉ ህፃኑ ልጇ ላይ አድርጋው ነበረ።
የቡድኑ መሪው ህፃኑን ልጅ አንስቶ ሲያየው ህፃኑ በሰላም ተኝቷል።
የሕክምና ቡድን ህፃኑን ልጅ ለመመርመር በፍጥነት ደርሶ ብርድ ልብሱን ሲከፍቱት ብርድ ልብሱ ውስጥ የሞባይል ስልክ ተመለከቱ።
በሞባይል ስክሪኑ ላይ እንዲህ የሚል የጽሑፍ መልእክት አነበቡ።
“ከሞት ከተረፍክ እኔ እንደምወድህ ሁል ግዜም አስታውስ”? ይላል።
እንዲህ ነው እናት ለልጇ ያላት ፍቅር !!
join???
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
#ኢኽላስ_ጋ_የተጣመረ_ርዕስ_የሌለው_ጀግንነት
✍ አሚር ሰይድ
ለእስልምና መስፋፋትና ማበብ ሕይወታቸውን የገበሩ አያሌ ሙጃሂዶች በኢስላም ታሪክ ላይ በደማቁ ሰፍረዋል። ስማቸው ተዘክሯል፣ገድላቸው ተወስቷል፣ ጀብዳቸው ተተርኳል። ግን ከነዚህ ሙጃሂዶች ባሻገር የአዕላፍ ሙጃሂዶች ገድል ተቀብሯል። ያለእነሱ ያ! ድል ምኞት ነበር። እነርሱም ሙስሊሞች ዘንድ የሚታወሱበትን ስም አልተውም። ራሳቸውን ደብቀው ለነገው ቤታቸው ሰንቀዋል።
ታላቁ የጦር መሪ መስለማ አብኑ ዐብዱል መሊክ ወደ አንድ የሮማ ከተማ ዘመተ። ከተማዋ ባላት ጠንካራና ብርቱ ምሽግ ምክንያት ለሙስሊሞች ከባድ ሆነች። እንደከበቡ ብዙ ጊዜያት አለፉ። ሮሞች ከምሽጋቸው በስተጀርባ ሆነው ቀስት በመወርወር በሙስሊሞች ላይ ሌላ ራስ ምታት ሆኑ።
መስለማ ከተማዋን የሚከፍትበትን ዘዴ በማሰላሰል እንቅልፍ ከዓይኑ ጠፋ። ጠብ የሚል ሀሳብ ፍለጋ ብዙ ደከመ። ሙስሊሞችም የከበባው ርዝመት፣ የምሽጉ ብርታትና የከሀዲያኑ ቀስት ሞራላቸውን አያላሸቀው መጣ።
እንዲህ ጭንቀቱ በበረታበት አንድ ለሊት ነበር ፊቱን በጨርቅ የሸፈነ ሙጃሂድ ከሙስሊሞች ጦር በድብቅ ተነስቶ ወደ ምሽጉ ያመራው። ፍፁም ጀግንነት የተላበሰ ብቻውን ወደ ምሽጉ ሄደ። እንደደረሰም የምሽጉን ግንብ መቦርቦር ጀመረ። በስተመጨረሻም ተሳካለትና ክፍተት መፍጠር ቻለ ይህ ሙጃሂድ ስራውን እንዳጠናቀቀ ለማንም ሳያሳውቅ ወደማረፊያው አመራ።
በማግስቱ ሮሞች ቀስት ለመወርወር ተዘጋጅተዋል ያ ሙጃሂድ ወደ ቦረቦረው ክፍተት ብቻዉን በመሄድ ወደ ከተማው በስውር ዘለቀ። ቀጥታ ወደ በሩ በመሄድ የበሩን ዘበኞች ብቻውን ተፋልሞ በመዘረር ካስወገደ በኋላ በሩን ከፈተ፡፡
ሙስሊሞች የሚያዩትን ማመን አቃታቸው። ለወራት መግቢያ የሌለው አስኪመስላቸው ያለፋቸው የምሽግ በሩ ተከፈተ። ያ ሙጃሂድ ከውስጥ በኩል ብቅ ብሎ “አሏሁ አክበር" በማለት አድማሱን ሲያቀልጠው ሙስሊሞች የሱን ድምፅ ተከትለው “አሏሁ አክበር" እያሉ አስተጋቡ። ሮሞች በድንጋጤ ተሸበሩ። ሙስሊሞችን የሚፋለሙበት ወኔ ከቶውንም ሸሻቸው። የድል ፀሀይ በሙስሊሞች ላይ ፈነጠቀች።
ከድሉ በኋላ የሙስሊሞች መሪ መስለማ ሙጃሂዶቹን ሰበሰበ። “ምሽጉን ከፍቶ የገባው ማነው? ይውጣና ሽልማቱን እንስጠው" በማለት አሳወጀ።
.....ሁሉም በፀጥታ ያን ጀግና ለማየት በጉጉት ይጠባበቃል።ያ! ሙጃሂድ ግን ሽልማቱን በዱንያ ሳይሆን በአኼራ ነበር ማጣጣም ያለመዉና በመስለማ ጥሪ ምሳሹን ነፈገው።
.....መስለማ ዳግም ተጣራ የሚወጣ ግን ማንም አልነበረም። መስለማ ጥሪውን ደጋገመ። በማግስቱ ተጣራ። አሁንም የወጣ የለም።
"በሽንቁሩ የገባውን ሰው በፈለገበት ሰአት ማረፊያዬ አንዲመጣ በአላህ ስም እጠይቀዋለሁ" አለ አንዲመጣና እንዲያየው ከልቡ እየተመኘ።
ከቀትር በኋላ ሰዎች ሲያርፉ ያ ሙጃሂድ ፊቱን እንደሸፈነ ወደ መስለማ ማረፊያ መጣ።
.... መስለማም “አንተ ነህ? " አለው
“አኔ አውቀዋለሁ ግን አንድታውቀወው ከፈለክ ሶስት መስፈርቶች አሉት" አለ መጃሂዱ። መስለማ "ምንድን ናቸው መስፈርቶቹ ? " ሲል ጠየቀ፡፡
☞ ስሙን ላትጠይቀው
☞ ፊቱን ላይገልጥና
☞ ሽልማት ላትሰጠው" አለ። መስለማ ተስማማ። ሙጀሂዱም “እኔ ነኝ” አለና ሌላ ተጨማሪ ቃል ሳይናገር ወጥቶ ሄደ።
መስለማ አይኑ በእምባ ተሞላ። የዚህ ሙጃሂድ ልዕልና የእንባ ከረጢቱን ለመቆጣጠር አቅም አልሰጠውም።
ያ አላህ! ምን ያማረ ኢኽላስ! ከዚያን ቀን ጀምሮ ታዲያ መስለማ ዱዓ ሲያደርግ “ጌታዬ ሆይ! ከዚያ ሰው ጋር ቀስቅሰኝ" እያለ ነበር።
#ምንጭ ☞ ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
join???
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago