★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago
ተወኩልህን አሳምር!
1 ዶላር 1 ሺህ ብር ቢሆንም፤ በሶስት ጨለማ ውስጥ ፍጡራኑን የሚረዝቀዉ አላህ አንተን
ከመረዘቅ ወደ ኋላ አይልም።
እርሱ ሆዷ ባዶ ሆኖ ማለዳ ወጥታ ሆዷ ሞልቶ ማታ የምትገባውንም ወፍ ይረዝቃል።
ያንተ ሪዝቅ ገና የ4 ወር ጽንስ ሳለህ ተጽፏል። ቀለሙም ደርቋል፣ ወረቀቱም ተጠቅልሏል።
አይረሳህም! ተረጋጋ!
لو أن الارزاق لم تكن بيد الله لما اكل العصفور مع النسر
لن ينساك فطمئن✨
Dear brothers and sisters do you know the best times to make Dua?
በዱዓእና በመልካም ስራ ተጠበቅ!
ረሱል እንዲህ ብለዋል፦
﴿لا يَرُدُّ القضاءَ إلّا الدعاءُ، ولا يَزيدُ في العُمرِ إلّا البِرُّ﴾
“የአላህን ውሳኔ የሚመልሰው ዱዓእ ብቻ ነው። ዕድሜን የሚያስረዝመው መልካም ስራ ብቻ ነው።”
ቲርሚዚ ሀሰን ብለውታል፡ 2139
?الله اكبر ?الله اكبر ?الله اكبر
?ولله الحمد
?تقبل الله منا ومنكم جميع صالح الأعمال
وتجاوز ما كان من تفريط ونقصان
وجمعنا في الجنة مع النبيين والأبرار
✨عيدكم مبارك .? عيد سعيد✨
Eid Mubarak.
ኢድ አል ፊጥር ረቡዕ የሚከበር ይሆናል..
ነገ ረመዷን 30 እንፆማለን ኢንሻአላህ
ዛሬ የመጨረሻው ተራዊህ ይሆናል
ዒድ - ህግጋትና ስርአቱ
~
በኢስላም አመታዊ በአሎቻችን ሁለት ናቸው። እነሱም ዒደል ፊጥርና ዒደል አድሐ። የመጀመሪያው ረመዳን እንዳለቀ በሸዋል ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ ይውላል። ሁለተኛው - ዒደል አድሐ- ደግሞ የዙልሒጃ ወር በ10ኛው ቀን ላይ። ነብዩ ﷺ መዲና ሲገቡ የመዲና ሰዎች የሚጫወቱባቸው ሁለት በአላት ነበሯቸው። “ምንድን ናቸው እነኚህ ቀናት?” ሲሉ ጠየቁ መልእክተኛው ﷺ። እነሱም “ከጃሂሊያህ ዘመን ጀምሮ የምንጫወትባቸው ቀናት ናቸው” ብለው መለሱ። ነብዩ ﷺ “አላህ ከነሱ በተሻሉ ቀናት ተክቷችኋል፡- በአድሐ ቀን እና በፊጥር ቀን” አሉ። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1039]
ጥቂት ስለዒድ፡-
ቀኑ የደስታ ቀን ነው፡-
1.1. “ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም” እያሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጥ ከሶሐቦች ተገኝቷል። [አልፈታዋ፡ 24/253]
1.2. ልጃገረዶች እየዘፈኑ መጫወት ይችላሉ። [ቡኻሪ፡ 949] [ሙስሊም፡ 892]
1.3. እለቱ የደስታ፣ የመብያና የመጠጫ ቀን ነው። [ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 777]
1.4. ስለሆነም ቀብር ዚያራና የመሳሰሉ የእለቱን የደስታ ድባብ የሚያደፈርሱ ድርጊቶችን መፈፀም አይገባም። [አልኢብዳዕ፡ 263]
1.5. የምንደሰትበት ግን ፈፅሞ በሐራም ነገር መሆን የለበትም። “የትም ብትሆን አላህን ፍራ!” የሚለው ሐዲሥ አይረሳ።
ተክቢራ፡-
2.1. የሚባልበት ጊዜ፡-
በዒደል አድሐ - ደግሞ ከዐረፋ ቀን ፈጅር ሶላት አንስቶ እስከ ዙልሒጃ 13 ዐስር ድረስ ከግዴታ ሰላቶች በኋላ ተክቢራ ማድረጉ ከሶሐቦች ተገኝቷል። [አልኢርዋእ፡ 653] እንዲያውም ኢጅማዕ (ወጥ ስምምነት) የመጣበት ጉዳይ እንደሆነ ነወዊይና ኢብኑ ረጀብ ጠቅሰዋል። [አልመጅሙዕ፡ 5/32] [ፈትሑል ባሪ] በዒደል ፊጥር ጊዜ ከግዴታ ሶላቶች በኋላ ተክቢራ ማድረጉ በቂ ማስረጃ የለውም።
2.3. አደራረጉ፡- ሁሉም በየፊናው እንጂ አንዱ እያወጣ ሌሎች በመከተል በህብረት ባንድ ድምፅ አይባልም። [መጅሙዑፈታዋ ኢብኒ ባዝ፡ 13/21] ባይሆን ይሄ ጉዳይ በዑለማዎች የተለያየ ሀሳብ የተሰነዘረበት ፊቅሃዊ ጉዳይ እንደመሆኑ ጉዳዩን በልኩ መያዝ ይገባል።
2.4. ድምፅን በተክቢራ ከፍ ማድረግ የተወደደ ነው። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 4934]
2.5. ተክቢራው ሴቶችንም በተመሳሳይ የሚመለከት ነው። [ቡኻሪና ሙስሊም] ድምፃቸውን ግን ዝቅ ሊያደርጉ እንደሚገባ ዑለማዎች ይመክራሉ።
2.5. አንዳንድ አካባቢዎች እንደሚታየው በተክቢራ ሙሉ ሌሊቱን ሳይተኙ ማሳለፍ፣ ሰፈር ጎረቤቱን በከፍተኛ ድምፅ ማወክ ማስረጃ የሌለው ስራ ነው። “የሁለቱን ዒድ ሌሊቶች ነቅቶ ያደረ ሰው ልቦች በሚሞቱበት ቀን ልቡ አይሞትም” የሚለው “ሐዲሥ” በነብዩ ﷺ ላይ የተቀጠፈ እንጂ ጤነኛ መረጃ አይደለም። [አዶዒፋህ፡ 520]
2.6. ከሶሐቦች የተለያዩ የተክቢራ አፈፃፀሞች የመጡ ሲሆን የተለየ አይነት ገደብ የለውም። ከሰሐቦች የተገኙትን መያዙ በላጭ ነው።
2.7. እነዚህን ተክቢራዎች ማለት በጀማዐ ለሰገደም፣ ብቻውን ለሰገደም የተወደደ ነው። ግዴታ ግን አይደለም። [ሸርሑል ሙምቲዕ፡ 5/165]
ወደ መስገጃው ቦታ መውጣት፡-
3.1. ወደ መስገጃ ቦታ ሲወጣ መታጠብን፣ ሽቶ መቀባትን የሚመለከት ከሶሐቢዩ ኢብኑ ዑመር ተገኝቷል። [አልኢርዋእ፡ 104] ከነብዩ ﷺ ግን ምንም የለም። የመታጠቢያ ጊዜውም ከእለቱ ፈጅር ሶላት መልስ ቢሆን ይመረጣል። ይህን የሚያመላክት ከሰለፎች ተገኝቷል። [አልመጣሊቡል ዓሊያህ፡ 2753]፣ [አሕካሙል ዒደይን ሊልፊርያቢይ፡ 16] ትጥበቱም ሴት ከወንድ፣ ህፃን ከአዋቂ ሳይለይ ሁሉንም እንደሚመለከት ነወዊይ ጠቁመዋል። [አልመጅሙዕ፡ 2/233]
3.2. በእለቱ አቅም በፈቀደ ባማረ ልብስ ሽክ ማለት ተወዳጅ ነው። [ቡኻሪና ሙስሊም]
3.3. ለቻለ ሰው ወደ መስገጃው ቦታ በእግር መሄዱ ሱና ነው። [አልኢርዋእ፡ 636]
3.4. የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ወደ መስገጃው ሜዳ መውጣታቸው ከሱና ነው። ከመስገጃው ቦታ ግን ገለል ይላሉ። [ቡኻሪ] ሴቶች ወደ መስገጃው ቦታ ሲወጡ ሽቶ ከመቀባትና ካላስፈላጊ አለባበስ መራቅ አለባቸው።
3.5. ስጋትና እንቅፋት ከሌለ ልጆችም ሊወጡ እንደሚችሉ የሚጠቁም ማስረጃ አለ። [ቡኻሪ፡ 977] ባይሆን ሰጋጆችን እንዳይበጠብጡ ወላጆች ሊቆጣጠሯቸው ይገባል።
3.6. ከመስገጃው ቦታ ሲመለሱ መንገድ ቀይሮ መመለሱ በላጭ ነው። [ቡኻሪ፡ 986]
የዒድ ሶላት፡-
4.1. ሶላቱን በተመለከተ ሚዛን የሚደፋው አቋም “ግዴታ ነው” የሚለው እንደሆነ ኢብኑ ተይሚያ፣ ሶንዓኒይ፣ ሲዲቅ ሐሰን ኻን፣ ሸውካኒይ፣ አልባኒይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን እና ሌሎችም አስረግጠው ተናግረዋል።
4.2. ወቅቱ፡- ፀሀይ ወጥታ የጦር ቁመት ያክል ከፍ ካለች ጀምሮ በአናት ትይዩ እስከምትሆን ድረስ ያለው ነው። የዒደል ፊጥር ሶላት ዘግየት፣ የዒደል አድሐ ደግሞ ቀደም ቢል ተመራጭ ነው። [አተልኺስ፡ 144] [ሙስነዱ ሻፊዒይ፡ 74] ምክንያቱም የዒደል ፊጥር ጊዜ ዘግየት ማለቱ ዘካተል ፊጥር ለሚሰጡ ሰዎች ጊዜ እንዲኖራቸው ሲያደርግ የዒደል አድሐ ጊዜ ቀደም ማለቱ ደግሞ ከሶላት ቶሎ ተመልሰው ኡዱሒያ የሚያርዱበት ጊዜ እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል።
4.3. የሚሰገድበት ቦታ፡- ዝናብ፣ የፀጥታ ስጋት፣ ወዘተ ካልኖረ ወጣ ያለ ሰፊ ሜዳ ላይ መሆኑ ሱና ነው። [ቡኻሪይና ሙስሊም]
4.4. ለዒድ ሶላት አዛንም ኢቃማም አይደረግም። [ቡኻሪይ፡ 962] [ሙስሊም፡ 886]
4.5. የረከዐው ብዛት፡- 2 ነው። [ቡኻሪይ፡ 964] [ሙስሊም፡ 884]
4.6. የዒድ ሶላት ውስጥ ያሉት ተጨማሪ ተክቢራዎቹ ሙስተሐብ እንጂ ግዴታ አይደሉምና በመርሳትም ሆነ ሆን ተብሎ ቢቀሩ ሶላቱ አይበላሽም። [አልሙግኒ፡ 3/275]
4.7. ቁጥራቸውም የመጀመሪያው ረከዐ ላይ ከመክፈቻው ተክቢራ ውጭ 7፤ ሁለተኛው ረከዐ ላይ ደግሞ ከመነሻው ተክቢራ ውጭ 5 ተክቢራ ነው። ይሄ ከብዙሃኑ ሶሐቦችና አኢማዎች የተገኘው እንደሆነ ኢብኑ ተይሚያ ገልፀዋል። [አልፈታዋ፡ 24/220] ብዙሃኑ ዑለማዎች ያሉትም እዚህ ላይ ነው። ባይሆን የመጀመሪያውን 7 የሁለተኛውን ስድስት፣ የመጀመሪያውን 6 የሁለተኛውን 5 ማድረጉም ተገኝቷል። 4፣ 11፣ 12፣ 13 ተክቢራዎችን ማለት እንደሚቻልም ከሰለፎች ተገኝቷል። ከዚህ በመነሳት ነገሩ ሰፊ እንደሆነና በሶሒሕ ማስረጃ በመጡት ሁሉ መስራት እንደሚቻል ያሳያል ይላሉ ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ። [አልኢርዋእ፡ 639]
4.8. በተጨማሪ የዒድ ተክቢራዎች ላይ እጅን ማንሳት ከሶሐቦች፣ ከዐጣእ፣ አውዛዒይ፣ አቡ ሐኒፋህ፣ ሻፊዒይ፣ አሕመድና ሌሎችም ተገኝቷል። ነብዩ ﷺ ደግሞ ጥቅል በሆነ መልኩ የሶላት ተክቢራዎች ላይ እጃቸውን ያነሱ እንደነበር ማስረጃ አለ። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 715]
አጭር ማስታወሻ ስለ ዱዓእ
~
ዱዓእ ተቀባይነት ያገኛሉ ተብለው በሚታሰቡ በላጭ ሰዓቶች ላይ ከፍ ላሉ ጉዳዮች ትኩረት እንስጥ።
አላህ ቀልባችንን እንዲያስተካክልልንና ዲን ላይ እንዲያፀናን። የነብዩ ﷺ ዱዓእ በብዛት እንዲህ የሚል ነበር፦
يا مُقلِّبَ القلوبِ ثبِّت قلبي على دينِكَ
በየትኛውም ዲናዊ ጉዳይ ለተሻለው እንዲመራን። ነብዩ ﷺ የሌሊት ሶላታቸውን በዚህ ዱዓእ ነበር የሚከፍቱት
اللَّهُمَّ رَبَّ جِبْرَائِيلَ، وَمِيكَائِيلَ، وإسْرَافِيلَ، فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالأرْضِ، عَالِمَ الغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ، أَنْتَ تَحْكُمُ بيْنَ عِبَادِكَ فِيما كَانُوا فيه يَخْتَلِفُونَ، اهْدِنِي لِما اخْتُلِفَ فيه مِنَ الحَقِّ بإذْنِكَ؛ إنَّكَ تَهْدِي مَن تَشَاءُ إلى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ.
ወንጀላችንን ምሮ ከእሳት እንዲጠብቀን፣ ጀነትን እንዲያድለን:- የሙስሊም ትልቁ ሃሳብ ጭንቀቱ ይሄ ነው መሆን ያለበት።
اللَّهمَّ إنِّي أسألُك الجنَّةَ وأعوذُ بِك منَ النَّارِ
የአላህን ይቅርታ ለማግኘት መትጋት። እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ ለነብዩ ﷺ ለይለተል ቀድር መሆኑን ካሰብኩ ምን ልበል ስትላቸው የጠቆሟት ዱዓእ ይሄ ነበር፦
اللَّهمَّ إنَّكَ عفوٌّ، تُحِبُّ العفوَ فاعفُ عنِّي.
ለዚክር፣ ለምስጋና፣ ላማረ የዒባዳ አፈፃፀም እንዲወፍቀን
اللهمَّ أعني على ذكرِك وشكرِكَ وحسنِ عبادتِكَ
ለወገኖቻችንም እንዲሁ የጠመሙትን እንዲያቀናልን፣ የሞቱትን እንዲምርልን፣ ለወላጆቻችን እንዲያዝንላቸው፣ በሃገራችን፣ በፊለስጢን፣ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በሌሎችም ቦታዎች መከራ ላይ ያሉትን ከፈተና እንዲያወጣልን፣ ሰላም እንዲሰጠን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።
* ባጠቃላይ በዱንያም በኣኺራም መልካሙን እንዲያድለን ጠቅላይ ጠቅላይ ዱዓኦችን መምረጥ መልካም ነው። ነብዩ ﷺ ያዘወትሯቸው ከነበሩ ዱዓኦች ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነበር፦
اللَّهُمَّ رَبَّنَا آتِنَا في الدُّنْيَا حَسَنَةً، وفي الآخِرَةِ حَسَنَةً، وقِنَا عَذَابَ النَّارِ.
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
*?سُبْحَانَ اللهِ وَالْحَمْدُ لِـلّٰـهِ وَلَا إِلٰهَ إِلَّا الله وَاللهُ أَكْبَرُ ?***
« ሱብሃናላህ ወልሃምዱሊላህ ወላኢላሀ ኢለላህ ወሏሁ አክበር » . . . . . . . . .❤️****
ዓለም ትኩረት የነፈጋት ምድር። ግፍ እየተቦካ የሚጋገርባት በተንኮል ጭስ የታፈነች መንደር። በደም አበላ የታጠበች በሰምዓታት አጥንቶች የተከበበች አምባ። ከሀሞተ-ቢስ ትውልድ የፀዳች ጀግንነት በሁለት እግሩ ከነ ነፍሱ የቆመባት ሰፈር። ድንጋይ ከታንክ ጋር የተፋጠጠባት የምድራችን ክፍል። ውርደት ያሻፈረው ህዝብ የከተመባት ቀየ።
የዕድሜን ጥግ ያዩ አዛውንቶች በባሩድ ሽታ መሐል ድንጋይ አየሸከፉ በፅናት የሚታገሉባት ተዓምራዊ ቦታ። ጡት ያልጣለውን ጨቅላ ህፃን ከቤቷ አስቀምጣ ዕብሪተኞችን አንገት ለአንገት የምትተናነቅ እንስት ያፈለቀች ምድር። አዎ አካሉ ቢጎል በዊልቸር ታግዞ ታንከኞችን በፍርሃት የሚንጥ ትውልድ የፀነሰች መሬት። የተባረከችው የፍልስጤም ምድር!
በዱዓ አንርሳቸው እጃችንን ከፍ አድርገን ያ አላህ እንበልላቸው
ዱዐ ላይ ወጥሩ አደራ እኔንም እንዳትረሱኝ
ፋጢማ رضي الله عنها ጁሙዐ ቀን ሲሆን አገልጋዩዋን ፀሀይን እንዲያይላት ትልከው ነበር ፀሀዩም ለመግባት በተቃረበ ጊዜ ፀሀዩ እስኪገባ ድረስ ቁጭ ብላ ዱዐ ታደርግ ነበር .
فتح الباري - كتاب الجمعة ( ۱۹۲۲)?*ምንጭ
? ኢብኑ አል ቀይም رحمه الله :*
"ከደጋግ ሰዎች አንዱ ጁሙዐ ቀን ከዐሱር እስከ መግሪብ ባለው ሰአት ውስጥ አላህን ምንም ሀጃ ጠይቄው አላቅም የተቀበለኝ ቢሆን እንወጂ አረ የዱዐዬና የአላህ እሺ ማለት በዝቶ እስከማፍር ድረስ ይላል።.
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago