★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 7 months, 4 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 3 weeks ago
ሊቀ መአምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በአጠቃላይ በቀኑ የተካሄደው ጉባኤ የቤተክርስትያን ጉዳይ ርእስ የሆነበት እና ሌሎች ክፍሎችም በዚሁ መልኩ በእቅድ የተመራ አሰራር ለማምጣት ሰንበት ት/ቤቶች ሀገረ ስብከቱን የመደገፍ ስራ መስራት አለባችሁ ያሉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ስርአተ ትምህሩቱን ለመተግበር ያለውን የሀገረ ስብከቱ የገጠመውን በጀት ችግር እንደ ሀገረ ስብከት እንደሌላው ሀገረ ስብከት ሁሉ በጀት እንደሚመደብ ተገልጿል።
የሰንበት ት/ቤቶች የመማሪያ እና ሌሎች አገልግሎት የሚውሉ ለቢሮ ግንባታ የሚውል ቦታ ጉዳይ ወጥ የሆነ የህንጻ ዲዛይን የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አንድነት እንዲያዘጋጅ መመርያ ያስተላለፋ ሲሆን በዛም መሰረት በየቦታው የሚገነቡ የሰንበት ት/ቤቶች ህንጻ አንድ አይነት እስታንዳርድ እንዲሆኑ እንዲሁም እስከ አሁን መማርያ መጽሐፍት ያልገዙ አጥቢያዎችን በሊስት እንዲቀርቡ መመረያ አስተላልፈዋል።
ብጹእ አቡነ ቀለሜንጦስ ለውጥ የሚመጣው እቅድን መሠረት አድርጎ ሲሰራ እና ዛሬ እንዳየነው ጉባኤ አባላት በጠንካራ ሀሳብ ሲሞግቱ መሆኑን ገልጸው ይህ አስራር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ከዛም በተጨማሪ የበጀት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አለመኖሩ ግርምት የፈጠረባቸው መሆኑ እና ለስንት ሀገረ ስብከት በፈሰስ እያስተዳደረ ያለ ምሳሌ የሆነ ሀገረ ስብከት እንዴት ለራሱ አካል አጠገቡ ላለው በጀት አይኖረውም የሚል ጥያቄ ለክቡር ስራ አስኪያጁ አቅርበዋል። በምላሹም የበጀት ጉዳይ ጅማሮ እንዳለ እና እልባት እንደሚያገኝ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ለብጹእነታቸው ቃል ገብተዋል።
በስተመጨረሻም በተጓደሉ አመራር ምትክ ዲ. በእሱፈቃድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዋናስራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ በጉባኤ ጸድቆ ጉባኤው ከምሽቱ 12:30 በጸሎት ተጠናቋል።
ለምሳ እረፍት ከመውጣቱ በፊት የሀገረስበከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀመአምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ሀገረ ስብከቱ ሊመለሱ የሚገባቸውን ጥያቄዎች እና አጠቃላይ በእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ ምክረ ሀሳብ ሰጥተው ጉባኤው ለምሳ እረፍት ወጥቷል።
ከሰአት በውኃላ ጉባኤው የቀጠለ ሲሆን ከዚህ ቀደም በትግበራ ሙከራ ላይ የነበረው የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶችን የማንዎል መረጃ አያያዝ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወደ ዲጅታል የመቀየር እና የሰንበት ት/ቤቶችን አሰራር በማዘመን እና አገልግሎታቸውን ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ ተጀምሮ የነበረውን እና በ25 ሰንበት ት/ቤቶች ሙከራ ላይ የነበረው የመጀመሪያ ዙር የዳታ ቤዝ ማበልጸግ የመጀመሪያ ደረጃ የተጠናቀቀ እና ከዛሬ ጀምሮ በሰንበት ት/ቤቶች ወደተግባር የሚገባ መሆኑ ተገልጿል።
በአበልጻጊው ባለሙያም ሰንበት ትቤቶችም ይህን በመተግበር አሰራራቸውን በማዘመን የተዘጋጀውን ሲስተም እንዲጠቀሙ ጥሪ ያስተላለፋ ሲሆን በዚህኛው ዙር ያለውን ጠንክረው በመተግበር ቀጣይ ለሚመጣው በከፍተኛ ደረጃ ሰንበት ት/ቤቶች አገልግሎትን ለማዘመን የሚያሰችለውን የሲስተም ማበልጸግ ስራ እድል እንዲጠቀሙ ጥሪ ተላልፏል ።
በሁለተኝነት በልማት ተነሺዎች ዙሪያ ከተደረገው ጥናት በመነሳት ሰንበት ት/ቤቶች ራሳቸውን ካለው ወቅታዊ የልማት ሂደት ጋራ አገልግሎታቸውን ቀጣይ እንዲሆን ምን ማድረገ ይችላሉ የሚለው እና አባላት ካሉበት ቦታ ወደ ሌላ ሲዛወሩ እንዴት መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ይቀጥሉ የሚለው የቀረበ ሲሆን ሁሉም ሰንበት ት/ቤት የልማትስራው እየቀጠለ በመሆኑ ራሳቸውን ዝግጁ በማድረግ የአባለቱን መረጃ በተገቢው በመያዝ ኩነቱ በአጥቢያቸው ከደረሰ አባላቶቻቸው በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ፣በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዬች ሊፈጠሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችንም ሆነ እድሎችን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው በዲ.ዳንኤል ገብረ ማርያም የአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት ሰንበት ት/ቤት አንድነት ዋና ጸሐፊ ተብራርቷል።
ቀጥሎም በወጣት ኤልያስ አበበ የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ምክትል ሰብሳቢ በቤተክርስትያን አስተዳደርያዊ ችግሮች የሰንበት ት/ቤት ድርሻ በሚል መነሻ ሀሳብ የቀረበ ሲሆን በአጥቢያ፣ በመካከለኛ መወቅሮች እና በከፍተኛ መዋቅሮች ያሉ መሠረታዊ የቤተክርስትያን ችግሮች የተነሱ ሲሆን እነዚህ ችግሮች ካልተፈቱ እና ካልቀነሱ ለቤተክርስትያን አደጋ መሆናቸውን ግንዛቤ ተወስዶ ለመፍትሄው ሰንበት ት/ቤቶችም ከአጥቢያ ጀምሮ መረጃ እና ወቅታዋ ጉዳይ ክፍሉን በማደራጀት በተዋረድ ካሉ ክፍለ ከተማ አንድነት እና ሀገረስብከት አንድነት ከተዋቀሩ መረጃ እና ወቅታዊ ጉዳይ ክፍሎች ጋር በተወረድ በሚዘጋጁ መድረኮች በመወያየት ከሚመለከተው የቤተክርስትያን ኃላፊዎች ጋር በመረጃ በተደራጀ መልኩ በውይይት የሚፈቱትን በውይይት መፍታት እንዲሁም በውይይት የማይፈቱትን ባለን የልጅነት ግዴታ እና የአስተዳደር ድርሻ የሚመለከተውን አካል የቤተክርስትያናችንን ቃለ አዋዲ እና ሌሎች ህጎች በመንተራስ በመሞገት ወደ መፍትሄ እንዲመጡ የበኩላችንን እንድንወጣ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል ።
በዚህም በተለይ አሁን አሁን አንድ አንድ ኃላፊዎች በቤተክርስትያን ጉዳይ ምእመናን ምን አገባቸው እና ሰንበት ት/ቤት ተወካዮችን አለማሳተፍ እና እንደ ባለቤት አለማየት ከፍተኛ ችግር እየሆነ መምጣቱ ተጠቁሟል ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የ፵፫ኛውን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤
የተከበራችሁ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያውና የየድርጅቱ ኃላፊዎች፤
የአዲስ አበበ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ተወካዮች፤
ከሀገር ውስጥና ከውጭ የመጣችሁ የየሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎችና ተሳታፊዎች፤
በአጠቃላይ በ43ኛው ዓመታዊ ዓለም ዐቀፍ የጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ለመሳተፍ በዚህ የተገኛችሁ በሙሉ፤
“አሠንዩ ፍኖተ ዘተሰመይክሙ ኖሎተ ከመ ትርዓዩ መርዔተ ከመ ዐሠርቱ ወክልኤቱ ሐዋርያቲሁ እለ መሀሩ በስሙ፡- ኖሎት የተባላችሁ ሆይ በስሙ እንዳስተማሩ እንደ ዐሥራ ሁለት ሐዋርያት መንጋውን ትጠብቁ ዘንድ መንገድን አሳምሩ” (ቅዱስ ያሬድ)
በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው ሹመት ወይም ኃላፊነት ካለ ተጠያቂነት የማይቀር ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም ሹመት የሚሰጠው ስራ እንዲሰራበት እንጂ እንዲሁ ለከንቱ ስላልሆነ ማለት ነው፡፡
ሹመት የመፈጸምና የማስፈጸም ሕጋዊ መሳሪያ ነው፤ መሳሪያውን በአግባቡ ከተጠቀምንበት የምንመሰገንበት፣ ያ ካልሆነ ግን የምንወቀስበት፣ ምናልባትም የምንቀጣበት አጋጣሚ ሊያስከትል ይችላል፤ ይህም በየጊዜው በሥዩማን ላይ ሲደርስና ሲፈጸም የምናየው እውነታ ነው፡፡ እኛ ካህናትና ምእመናን የእግዚአብሔርን መንግሥት ተልእኮ ልናስፈጽም በሕዝበ እግዚአብሔር ላይ የተሾምን ሥዩማን ነን፤ የመንግሥተ እግዚአብሔር ተልእኮ ከሰው ወገን አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ መጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የልጅነት ሥልጣን የተሰጠን እኛ ወደ መንግሥቱ በረት ያልገቡትን የማስገባት፣ ገብተው የወጡትን መልሶ የማስገባት፣ በበረቱ ያሉትን በጥሩ ውሀና በለመለመ መስክ በማሰማራት የመጠበቅ ኃላፊነት አለብን፡፡
ይህንን ኃላፊነታችን በትክክል ለመወጣት ከሁሉ በፊት እኛ ሥዩማን ተልእኮአችንን በውል መገንዘብ አለብን፤ ለተመደብንበት ተልእኮም በጽናት መቆም አለብን፣ በትጋትም መስራት ይጠበቅብናል፤ ከዚህም ጋር በእምነት በሥነ ምግባር በሥራ አፈጻጸም ከምንጠብቃቸው መንጋዎች በእጅጉ የላቅን ሆነን መገኘት በጣም አስፈላጊያችን ነው፡፡ በመንግሥተ እግዚአብሔር ተሹሞ ወደሥራ የተሠማራ ሰው ሥራው ፍጹም የተቃና ይሆንለት ዘንድ “ራሱን ክዶ” መስቀሉን መሸከም ግድ ይለዋል፤ ያለዚያ ውጤታማ መሆን አይቻልም፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
አሁን ያለነው ሥዩማን በዚህ ዘመን ላለችው ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት ሆነን የተሾምን ነን፤ ወደ በረቱ ያልገባ፣ ገብቶም የወጣ ካለ ማስገባትና መመለስ ያለውም በተመቻቸ መልካም አስተዳደር፣ በለመለመ ትምህርተ ወንጌል፣ በጥሩ ሥነ ምግባር አርአያ ሆኖ መጠበቅ ከኛ ይጠበቃል፡፡ ታድያ ይህንን በተግባር መተርጐም ችለናል ወይ? በጎቻችን አልቦዘኑም ወይ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ከሁላችን ይጠበቃል፡፡
ይህ ዓቢይ ጉባኤ የተሰበሰበበት ምክንያትም ይህንን ተልእኮ ለማስፈጸም በሚደረገው ጥረት ያጋጠሙ ነገሮች ካሉ ለመስማትና ለመገምገም እንደዚሁም የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ በተቀመጠው መሪ ዕቅድ አማካኝነት ተልእኮውን ለመወጣት ነው፤ ‹‹የሚደርስበትን የማያውቅ የሚሄድበትን አያውቅም›› የሚለው ብሂል በአሠራራችን ቦታ እንዳይኖረው መጠንቀቅ አለብን፡፡
በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያናችን መዳረሻ የማይታወቅ አይደለም፤ ቤተ ክርስቲያናችን በቀጣዮቹ ዐሥር ዓመታት የት ልትደርስ እንደምትችል ቅዱስ ሲኖዶስ ባጸደቀው መሪ ዕቅድ በግልጽ ተቀምጦአል፤ ይህ መሪ ዕቅድ ሁላችንም ትኵረት ሰጥተን ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይኖርብናል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
እንደ እውነቱ ከሆነ አሁን ባለን ክህነታዊ አገልግሎትና አስተደደር ክፍተቶች እንዳሉን የማይካድ ነው፤ ዘመኑ የፈጠረብን ጫና ሳያንስ በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጐደላቸው አሰራሮችም ለተልእኮአችን ከባድ ዕንቅፋት እየሆኑብን ነው፡፡ ሰበካ ጉበኤ የተቋቋመው በተዘረጋው መዋቅር አማካኝነት ቤተ ክርስቲያንን በማኅበረ ካህናት ወምእመናን የጋራ ጥበቃ ለአዲሱ ትውልድ ለማሸጋገር እንደሆነ ሁላችን አንስተውም፡፡ ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያናችን ይህን ያህል የመልካም አስተዳደር ክፍተት እየታየ የሰበካ ጉባኤ ዓላማ ግቡን መትቶአል ለማለት ስለማያስደፍር በዚህ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች በሙሉ ሊቀርፍ የሚችል አሰራር ቀይሶ ችግሩን ለመቀልበስ በጥናት ላይ የተመሠረተ ዘላቂና ፈጣን መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
ያለፈው ዓመት በዝቋላ ገዳምና በሌሎች አካባቢዎች አበው መነኮሳት፣ ቀሳውስት እንደዚሁም በርከት ያሉ ምእመናን በግፍ የተገደሉበት ሆኖ አልፎአል፤ አሁንም ችግሩ እየቀጠለ ነው፤ በቅርቡም በምሥራቅ ሸዋ ከነቤተሰባቸው የተገደሉ አዛውንት ካህን ሁናቴ የችግሩን ቀጣይነት ይጠቁማል፡፡
በመጨረሻም፤
በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ካህናትና ምእመናን ልጆቻችን፣ የቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና ሃይማኖት፣ ቀኖና እና ሥርዓት ተጠብቆ እንዲቀጥል ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ሁላችንም ተባባሪ እንድንሆን፣ በሀገራችን ያለው አለመግባባት በሰላምና በውይይት ተፈትቶ ፍጹም ሰላም ይሰፍን ዘንድ በጸሎትና በአንድነት እንድትተጉ አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን 43ኛው ዓመታዊ ዓለም ዓቀፍ ጠቅላላ መንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተከፈተ መሆኑን እናበስራለን፡፡
መልካም ጉባኤ ያድርግልን፤
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
©የኢኦተቤ ሕዝብ ግነኙነት መምሪያ
«ለእግዚአብሔር ጊዜ ማጣት»
...... በዓለም እና በማሕበራዊ ሕይወት ተፅዕኖ ስር ወድቀን መንፈሳዊ ሕይወታችን ፈጽሞ መርሣት የለብንም፡፡ ስለ መንፈሳዊ ሕይወታችን የሚያስብልን ማን ነው? መንፈሳዊ ቤታችንን ማን ይስራው? በመንፈሳዊ ጽጋችን ለማገልገል ምን አደረግን ? ስለእነዚህ ነገሮች እኛ ካለሰብን ፤ ጊዜ ካልሰጠን ማን ይስጥልን ?ለምንሰራው ነገር በረከት ከወዴት እናግኝ ?ሕይወታችንስ ሰላማዊ እና ጤነኛ መሆን ይችላል? ለምንለፋው ሁሉ ተመጣጣኝ ፍሬ እያገኘን ነው?
እዚህ ላይ ቅዱሳን ሐዋርያትን ማሰብ ያስፈልጋል ፡፡‹‹ትምህርቱንም ከፈጸሙ በኋላ ስምዖንን ወደ ጥልቁ ባህር ፈቀቅ በል፡፡መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ አለው ፡፡ስምዖንም መልሶ መምህር ሌሊቱን ሁሉ ደክመናል የያዝነው የለም ፡፡ነገር ግን ስለ አዘዝኸን መረባችንን እንጥላለን አለው›› ሉቃ 5÷4-5
አስተውሉ ሕይወታችን ከዚህ ታሪክ ጋር የሚመሳሰል ስንት ሰዎች አለን? ቀን ከሌሊት ደክመን ያተረፍን ስንቶቻችን ነን? ሥራ እንደበዛብን እናስባለን ፤ እንደክማለን ፤የያዝነው ነገር የለም፡፡ያም ሆኖ እየሆነ ያለውን ረስተነዋል፡፡ማንም በድካሙ መጠን ፍሬ እንዳላፈራ እንኳ የሚያውቅ የለም ፡፡ ጌታችን ስምዖንን መረባችሁን ጣሉ እና ዓሣ አጥምዱ ብሎ ሲናገረው ስምዖንን የመረጠበት ምክንያት በዓጋጣሚ አይደለም፡፡ ስምዖን አንድ የተረዳው ነገር ነበር ፡፡ሌቱን ሁሉ ደክሞ ምንም እንዳላተረፈ ስለሚያውቅ ነበር ፡፡
የብዙዎቻችን ችግር ይህ ነው፡፡ምንም እንዳላተረፍን አለማወቃችን ነው፡፡ስምዖን ‹‹ስለታዘዝን መረቡን እንጥላለን››ማለቱ ዓሣ ማግኘት እንደማይችል ተስፋ መቁረጡን እንዲሁም የቀንም ሆነ የሌሊት ድካም ጌታ ከሌለበት ውጤቱ ምን እንደሆነ እንደተረጋ ያሳያል፡፡
ለስምዖን ያች ዕለት ሰዓትና ሁኔታ የተለየች ናት ፡፡ስምዖን ምን ያህል ችኩል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ይህ ሙሉ የሆነ ደስታ በሕይወቱ ሆነ ፡፡ጀልባው ላይ ሆኖ ዘለለ፡፡ሌሊቱን ሁሉ በፍለጋ ደክሞት ነበር ፡፡መረቦቹን አጥቦ ምንም ሳያገኝ እንደሚመለስ ተረድቷል ፡፡ለቤተሰቦቹ ምንም እንዳልያዘ አውቆታል፡፡ሲባክን አድሮ አንድም ዓሣ ሳያገኝ አድሯል ፡፡በድንገት ይህ ሁኔታ ተቀየረ፡፡ለጓደኞቹ ፤ ለቤተሰቦቹ እንዲሁም ለሌሎቹ የሚሆን ዓሣ አገኘ ፡፡
ተመልከቱ ሙሉ ሕይወታችንን ያለ እግዚአብሔር ልናሳልፍ እንችላለን፡፡ከእርሱም ልንርቅ እንችላለን ፡፡ነገር ግን ከእግዚአብሔር የራቅንበት ጉዳይ ያለ እግዚአብሔር ልንፈጽመው አንችልም፡፡ከስምዖን ሕይወት የምንማረው ይህን ነው ያለ እግዚአብሔር ከኖርነው ረጅም ጊዜ ይልቅ ከእርሱ ጋር በሆንን አጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ውጤታማ እንሆናለን፡፡
*ምንጭ ለእግዚአብሔር ጊዜ ማጣትና ሌሎችም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እና በሌሎችም አባቶች።
*?*?⚜?????⚜???⚜????⚜????⚜????????⚜?⚜ *በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
"ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ ፥ በመንፈስ የምትቃጠሉ ኹኑ ፥ ለጌታ ተገዙ" {ሮሜ 12፥11}
‹‹#ትብብራችን_ለአንድነታችን››
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥር ለምትገኙ የየሰንበት ት/ቤቱ የሥራ አመራር የጽ/ቤት አባላት (ዋና ሰብሳቢ ፥ ምክትል ሰብሳቢ እና ዋና ጸሐፊዎች) በሙሉ የተላለፈ #የ13ኛ_ዓመት_2ኛ_መደበኛ_ጠቅላላ_ጉባዔ ጥሪ!!! #ሐምሌ_14_2016_ዓ_ም#ከጠዋቱ_3_00_11_00_ሰዓት *የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት #የ13ኛ_ዓመት #2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፤ የክብር እንግዶች እና የአንድነቱ የጠቅላላ ጉባዔ አባላት በተገኙበት #ትብብራችን_ለአንድነታችን **በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 14/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00-11:00 ሰዓት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያከናውናል።
? #በጉባዔው_የሚነሱ_የመወያያ_አጀንዳዎች ፦
? የሥራ አስፈጻሚ የስድስት ወር የአፈጻጸም ሪፖርት ፤
? የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ክፍል የስድስት ወር ሪፖርት ፤
? የአ/አ/ሰ/ት/ቤቶች አንድነት የ2017 ዓ.ም እቅድ ፤
? የአ/አ/ሰ/ት/ቤቶች አንድነት እስትራቴጂክ ፕላን ፤
? የአ/አ/ሰ/ት/ቤቶች አንድነት መዋቅር ፤
? የተጎደሉ የሥራ አመራር አካላትን በመተካት ማጸደቅ የሚሉ አጀንዳዎች ናቸው።
? በመሆኑም ፦
?#ሐምሌ_14_2016_ዓ_ም?#ከጠዋቱ_3_00_11_00_ሰዓትየየሰንበት ት/ቤቱ የሥራ አመራር የጽ/ቤት አባላት (ሰብሳቢ፥ ም/ሰብሳቢ እና ጸሐፊ) የሆናችሁ ፤ የሰባቱም ክፍላተ ከተማ አንድነት የሥራ አመራር አባላት የሆናችሁ ፤ በአንድነቱ ክፍላት ውስጥ እያገለገላችሁ የምትገኙ አባላት ፤ እንዲሁም የቀድሞ የአንድነቱ አመራር የነበራችሁ በሙሉ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት (4 ኪሎ) የስብሰባ አዳራሽ በመገኘት የስብሰባው ተሳታፊ እንድትሆኑ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን በጥብቅ እናሳተላልፋለን ።#የአዲስ_አበባ_ሀገረ_ስብከት_የሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት ??⚜?????⚜???⚜????⚜????⚜????????⚜?⚜**
??? ማስታወቂያ ???
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በሥሩ በሚገኙ እና ሥርዓተ ትምህርቱን እየተገበሩ በሚገኙ ከ120 በላይ በሚሆኑ ሰንበት ት/ቤቶች #የ4ኛ ፣ #የ6ኛ እና #የ10ኛ ክፍል የናሙና (ሞዴል) ምዘና ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ማካሄዱ ይታወቃል። በመሆኑም አስፈታኝ ሰንበት ት/ቤቶች የተማሪዎችን ውጤት እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም በተላከላችሁ Excel ፋይል በመሙላት እንድትልኩ በድጋሚ እናሳስባለን። በናሙና ምዘናው ላይ ያላችሁን አስተያየት ለማጠቃለያ ምዘናው ይረዳን ዘንድ ለክፍለ ከተማችሁ ትምህርት ክፍል በጽሑፍ እንድትልኩ እየጠየቅን የማጠቃለያ ምዘና ሐምሌ 21/2016 ዓ.ም ስለሚሰጥ ከወዲሁ ተማሪዎችን እንድታዘጋጁ እናሳስባለን።
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ትምህርት ክፍል
ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች የተናበበ ወጥ ዝርዝር መዋቅራዊ አደረጃጀት ሰነድ ተግባራዊ እንዲሆን 13ኛ ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በወሰነው መሠረት ለሁሉም መዋቅር ተላከ:-
ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰ/ት/ቤቶች ማ/መመሪያ ዓለም አቀፍ ስ/ት/ቤቶች አንድነት በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት ከአጥቢያ ስንበት ትምህርት ቤቶች ጀምሮ እስከ መንበረ ፓትርያርክ ያለው የስንበት ት/ቤቶች አገልግሎት ወጥ፣ የተናበበ፣ በዕቅድ የሚመራ እና በተደራጀ ሥርዓተ ትምህርት የሚያስተምሩ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ወደ ተደራጀ መዋቅራዊ አደረጃጀት እንዲመጡ የሚመራ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በመመሥራት ሥራ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የዚህ ዓመት 13ኛው የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 15ና 16/2016 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ከተወሰኑ ውሳኔዎች መካከል የሰንበት ት/ቤቶች ዝርዝር መዋቅራዊ አደረጃጀት በሁሉም መዋቅር ተግባራዊ እንዲሆን እና የሁሉም መዋቅራት አመራር ምርጫ በአንድ ጊዜ እንዲፈጸም ነው፡፡
በዚህም መሠረት ከመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት እስከ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ድረስ እንዲተገበር የተዘጋጃው ዝርዝር መዋቅራዊ አደረጃጀት ተደራሽ እንዲሆን በስስ ቅጅ በድረ ገጹ https://eotc-gssu.org/a/ ስለ አንድነቱ በሚለው ገጽ የተቀመጠ ሲሆን በየደረጃው የሚገኘው የሰ/ት/ቤቶች አንድነት መዋቅራት እስከ አጥቢያ ከሚመለከተው መዋቅር ጋር በመናበብ የማሰልጠን እና የማስገንዘብ ሥራዎችን በመሥራት ሁሉም መዋቅር በተዘጋጀው አፈጻጸም መሠረት ሥራ አመራር አባላትን በማስመረጥ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ሀገረ ስብከቶች ለሁሉም አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች በደብዳቤ እንዲገለጽላቸው ተያይዞ የተላከ ሲሆን ቀጥታ ለማውረድ የሚከተለውን ሊንክ ቀጥታ ይጠቀሙ
፩_ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ የሰንበት-ት-ቤቶች-ተቋማዊ-አደረጃጀት (PDF) https://eotc-gssu.org/a/የሰንበት-ት-ቤቶች-ተቋማዊ-አደረጃጀት/
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
? Youtube
? Telegram
? Tiktok
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 7 months, 4 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 3 weeks ago