القناة الرسمية والموثقة لـ أخبار وزارة التربية العراقية.
أخبار حصرية كل مايخص وزارة التربية العراقية.
تابع جديدنا لمشاهدة احدث الاخبار.
سيتم نقل احدث الاخبار العاجلة.
رابط مشاركة القناة :
https://t.me/DX_75
Last updated 1 year, 9 months ago
Last updated 3 months, 2 weeks ago
? ከሰጋጆች ስህተቶች
❨¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯❩
➽ ብዙ አባቶችና ወንድሞች ላይ ከሶላት ጋር የተገናኙ መስጂድ ሲገባ ጀምሮ በጀማዓም ይሁን በግል በሚሰገድበት ጊዜ የሚስተዋሉ ስህተቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ዱዓቶችና ኡስታዞችም ጭምሮ የሚሰሩዋቸው ይገኙበታል። ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ግን ትኩረት ያጡ ሆነው ይስተዋላሉ። ከእነዚህ ሶላት ውስጥ ከሚታዩና ልናስተካክላቸው ከሚገቡ ስህተቶች ውስጥ፦
❶ኛ በሶላት ውስጥ አለመረጋጋት
♻️ ይህ የሶላት ሩክን ሆኖ ሳለ ብዙዎች ጋር የሚታይ ስህተት ነው። ሩኩዕ ላይ፣ ከሩኩዕ ቀና በሚባልበት ጊዜ (ኢዕቲዳል) ላይ፣ ስጁድ ላይ፣ በስጁድ መካከል መቀመጥ ላይና የመሳሰሉ ቦታወች ላይ መረጋጋት ግዴታ ነው። ካልሆነ ሶላት ያበላሻል።
❷ኛ እንቅስቃሴ ማብዛት
↪️ ይህ ኹሹዕ ከማጣት የሚመጣ ከሶላቱ ጋር በሚገናኝ ጉዳይና ሸሪዓዊ ለሆነ
ጉዳይ ካልሆነ በጣም የተጠላ ነው።
❸ኛ ኢማምን መሽቀዳደም
♻️ ኢማምን መከተል ግዴታ ሲሆን እሱን መሽቀዳደምና ቀድሞ መነሳት፣ ሩኩዕ ማድረግ፣ ከሩኩዕ ቀና ማለትና ከስጁድ መነሳት የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ሶላት ያበላሻሉ።
❹ኛ ኢማሙ የሁለተኛውን ተስሊም ሳይጨርስ ያመለጠን ለሞሙላት መነሳት
❺ኛ በንያ ድምፅ አውጥቶ መናገር
➧ ንያ ቦታው ቀልብ ስለሆነ ድምፅ አውጥቶ መናገር አያስፈልግም።
❻ኛ መስጂድ ገብቶ ኢቃም እስከሚባል ቆሞ መጠበቅ
♻️ አዛን ከተባለ በኋላ መስጂድ የገባ ሰው ወዲያውኑ ሁለት ረካዓ መስገድ ይኖርበታል። ነብዩ ﷺ በሁለት አዛኖች (በአዛንና ኢቃም መካከል ሶላት አለ) ስላሉ ቆሞ መጠበቅ አያስፈልግም። ቀብልያ ያለው ሶላት ሆነም አልሆነም ለተሒየቲል መስጂድ ለሱነተል ውዱእና ለሱናውም ይሆንለታል።
❼ኛ መስጂድ ገብቶ ኢማሙ ስጁድ ላይ ወይም ተሸሁድ ላይ ከሆነ ቆሞ መጠበቅ
➲ ይህም በጣም ስህተት ነው። ኢማሙ ባለበት ሁኔታ ተከትሎ ያመለጠውን ኢማሙ ሲጨርስ ሞሙላት ነው ያለበት።
❾ኛ አይንን ግራና ቀኝ ወይም ወደ ሰማይ ማድረግ
↪️ ሶላት በምንስግድበት ጊዜ ወደ ስጁድ ማድረጊያ ቦታ ማየት ነው የሚያስፈልገው። ሸይጣን ሶላታችንን እንዳይሰርቀን!
❿ኛ በሁለት እግሮች ተረከዝ ላይ ቁጭ ብሎ ስጁድ ላይ ሁለት እጆችን እስከ ክርን መሬት ላይ መዘርጋት
⓫ኛ በሚሰግድ ሰው ፊት ለፊት ማለፍ (ሶላት ማቋረጥ)
⓬ኛ ኢማሙ ሩኩዕ ላይ ሆኖ ደርሶ ተክቢረተል ኢሕራም ሳያደርጉ ጎንበስ ማለት
⓭ኛ ሶላት ላይ ዐይኖችን መጨፈን
⓮ኛ በስጁድ ላይ የእግር ጣቶችን ማንሳት
⓯ኛ ስጁድ ሲያደርግ መሬቱን መሳም
⓰ኛ ሶላት ላይ ሲቆም ቀኝ እጅ በግራ ላይ አድርጎ አንገት ስር ማውጣት
⓱ ስጁድ ሲወረድና ከስጁድ ቀና ሲል ሁለት እጆችን ማንሳት
⓲ኛ በግንባር፣ በሁለት መዳፎችና፣ በሁለት ጉልበቶችና በሁለት አውራ ጣቶች (በሰባት አካላት) ስጁድ አለመውረድ
⓳ ሴቶች ሽቶ ተቀብተው መስጂድ መምጣት
⓴ ሴቶች በሚሰግዱበት ጊዜ እግራቸውን አለመሸፈን
♻️ እነዚህ ከብዙ ስህተቶች ጥቂቶቹ ናኛቸው ራሴንና አማኞችን ለማስታወስ እነዚህን ጠቀስኩ። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን።
https://t.me/bahruteka
Telegram
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
***🚫*** ከሰጋጆች ስህተቶች ❨¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯❩ ➽ ብዙ አባቶችና ወንድሞች ላይ ከሶላት ጋር የተገናኙ መስጂድ ሲገባ ጀምሮ በጀማዓም ይሁን በግል በሚሰገድበት ጊዜ የሚስተዋሉ ስህተቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ዱዓቶችና ኡስታዞችም ጭምሮ የሚሰሩዋቸው ይገኙበታል። ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ግን ትኩረት ያጡ ሆነው ይስተዋላሉ። ከእነዚህ ሶላት ውስጥ ከሚታዩና ልናስተካክላቸው ከሚገቡ ስህተቶች…
`ቆይ እኔ የምለዉ ሸሪዓችን ሴት ልጅ የራሷ ፀጉርኳ ወደ ላይ ጠቅልላ እንዳታስር ነዉ የተደነገገዉ። ቀደምት እናቶቻችንም በ3ት ቦታ ጎንጉነዉ ነበር የሚለቁት!!
ግን ፀጉር የሌላችሁ ጨርቅ እና የፀጉር ማሲያዢያ ከምራችሁ የምትለብሱ ሴቶች ግን ጤናችሁ ያሰጋል የሌላችሁ ማስመሰል አይደብርም ግን ??አረ ተዉ ግን በአርትፊሻል ቡትቶ ራሳችንን አናታል ቀደምቶች እናቶቻችን የበቃቸዉ ይብቃን!!`
(⚡️☝️)
?አዲስ ፒዲኤፍ (? PDF):?
የረሡል (ﷺ) ባለቤት የሆነችው፣ የሰውዳ ቢንት ዘም'ዐህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) አጭር የሕይወት ታሪክ:
•┈┈┈┈•◈◉✹❒❁❒✹◉◈•┈┈┈┈•
የመጀመሪያዋ የረሡል (ﷺ) ባለቤት የነበረችው የኸዲጃህ ቢንት ኹወይሊድ (ረዲየላሁ ዐንሃ) አጭር የሕይወት ታሪክ ፒዲኤፉን በዚህ ➘ሊንክ ያገኙታል።
https://t.me/semirEnglish/1461
•┈┈┈┈•◈◉✹❒❁❒✹◉◈•┈┈┈┈•
ለሰውዳ ቢንት ዘም'ዐህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) በከረጢት የተላከላት ዲርሃም:
•┈┈┈┈•◈◉✹❒❁❒✹◉◈•┈┈┈┈•
አሚሩል ሙዕሚኒን ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ለሰውዳ ቢንት ዘም'ዐህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) በከረጢት "#ዲርሃምን" ላከላት። የከረጢት ዲርሃሙን ይዘው ለመጡ ሰዎች: «ይህ ምንድነው?» አለች። እነሱም: «ዲርሃሞች» ናቸው ብለው መለሱላት። ከዚያም እንዲህ ብላ አለች፦ ❝ዲርሃም በከረጢት፣ልክ እንደ ቴምር?! እናንተ ሰዎች ሆይ! ዝርግ ሳህን አምጡልኝ! ከዚያም ከረጢቱን ከፈተችው፤ ሶደቃም አደረገችው (አከፋፈለችው)።
[(ሲየር አ'ዕላሚን-ኑበላዕ ገፅ:268)]](https://t.me/semirEnglish/1467) (ከፒዲኤፉ የተወሰደ።
•┈┈┈┈•◈◉✹❒❁❒✹◉◈•┈┈┈┈•
? ኢንግሊዝኛ ፅሁፍ አዘጋጅ: ኡሙ ዐብዱር-ረሕማን (አላህ ይጠብቃት)
? አማርኛ ትርጉም: አቡ ሐፍሳህ
Join us⤵️
?https://t.me/semirEnglish/1467
? ዳዒ ሆይ ሐኪም ነህ
ዳዒ ሆይ ሐኪም ነህ ። ያንተ ሕክምና ከዱንያው ሐኪም ሕክምና የሚለየው የዱንያው ሐኪም የሚታይን በሽታ ሲሆን የሚያክመው አንተ ግን የሰዎችን የእምነት በሽታ ነው የምታክመው ።
የዱንያው ሐኪም ህመምተኛ ሲመጣለት ቃለመጠይቅ አድርጎ ወደ ምርመራ ይገባል ። ህመምተኛውን አስተኝቶ እየጨባበጠ ፣ እየተጫነ ፣ እየቆነጠጠ ፣ ጎንበስ ቀና እያደረገ እዚህ ጋር ይሰማሀል ወይ ሲለው ህመሙ ያለበትን ቦታ ከተጫነውና ካገኘው በጣም ደስ ብሎት አው ይላል እንደሚድንም ተስፋ ያደርጋል ። እንዴት የሚያመኝን ቦታ ነካህብኝ ብሎ አይጮኽም ። የታዘዘለትን መድሃኒት በትክክል ይወስዳል ። በትክክል ካልወሰደ በሽታው ስር እየሰደደ ሄዶ ለሞት ሰበብ ሊሆን ይችላል ።
ሐኪሙ በሽታውን ሳይነግረው ደህና ነህ እያለ ማስታገሻ ከሰጠው ግን በሽታው እያገረሸ ሄዶ የማይድን ደረጃ ሲደርስ ዶክተሩን ይረግማል ለመሞቴ ሰበብ አንተ ነህ ይለዋል ።
አንተም ዳዒ ሆይ የህመምተኛህ ህመም የቀልብ ነው ። እየጨባበጥክ ፣ እየጨመቅህ የምትመረምረው አይደለም ። የሚመረምረው አንተ ጋር ያለው ቀርኣንና ሐዲስ ነው ። አጋሪያንን አስመልክቶ የመጡ የቀርኣንና ሐዲስ መረጃዎች ስትነግረው ያመዋል ። ይጮሀል የሚገርመው ግን ልድን ነው ብሎ ደስ ብሎት አይደለም እንዴት ቁስሌ ተነካ ብሎ ነው ። ስለ ቢዳዓም ፣ ስለ ዝሙት ፣ ስርቆት ፣ መዋሸት ፣ ማታለል ፣ እና የመሳሰሉ ወንጀሎችን አስመልክቶ የመጡ መረጃዎችን ስታስታውስ ተመሳሳይ ነገር ይገጥምሀል ። ነገር ግን ሁሉም አንድ አይነት አይደለምና ብዙ የሚድን ይኖራል ።
አንተ ብቻ በሽታውን ሳትደብቅ ተናገር እንዳይቆጣ ብለህ አስመስለህ እንዳታልፍ ። በሽታው የቢዳዓና የሽርክ ከሆነና አለባብሰህ ደህና ነህ አብሽር ብለህ ካለፍክ ለሞት ሳይሆን ለጀሀነም ነው የሚዳርገው ።
አንተና የዱንያው ሐኪም አንድ የሚያደርጋችሁ መልካም ስነምግባርና መጥፎ ስነምግባር መላበሳችሁ ነው ። መልካም ስነምግባር የተላበሰ ሐኪም ከሕክምናው በፊት በስነምግባሩ ሰዎችን አፍያ ያደርጋል ። አንተም በየትኛውም አይነት ሽርክና ቢዳዓ ላይ ያለን ሰው በመልካም ስነምግባርህ ምክንያት በአላህ እርዳታ ካለበት ሽርክና ቢዳዓ ልታወጣው ትችላለህ ። ሁለታችሁም የምታዙት መድሀኒት ፈዋሽ ይሆናል ። መልካም ስነምግባር ከሌለ አካሉ የታመመው ህመምተኛ እሱ መድሀኒት ከሚሰጠኝ ብሞት ይሻለኛል ይላል ። የሽርክና የቢዳዓ በሽታ ያለበትም ከልቡ ስለማይሰማውና ስለማያስተውለው አይጠቅመውም አንተም እንሰሳ ላይ እንደሚጮህ ሰው ትሆናለህ ።
የተዋጣለት ህክምና ማለት በሽታን ሳይደብቁ በመልካም ስነምግባር ሊድን እንደሚችል እየነገሩ መድሀኒት አዞ በትክክል መወሰዱን መከታተል ነው ። በመሆኑም ዳዒ ሆይ ሰዎች እንዳይቆጡ ብለህ በሽታ እንዳትደብቅ ። ውጤት አልባ እንዳትሆን ስነምግባሩ የተበላሸ አትሁን ። በጥሩ ስነምግባር ቁርኣንና ሐዲስን ለቀልብ በሽታ መድሃኒት እንዲሆኑ ሰበብ ሁን ።
القناة الرسمية والموثقة لـ أخبار وزارة التربية العراقية.
أخبار حصرية كل مايخص وزارة التربية العراقية.
تابع جديدنا لمشاهدة احدث الاخبار.
سيتم نقل احدث الاخبار العاجلة.
رابط مشاركة القناة :
https://t.me/DX_75
Last updated 1 year, 9 months ago
Last updated 3 months, 2 weeks ago