Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

WeCare ET

Description
WeCare is Ethiopia’s digital healthcare platform where treatment seekers can discover practitioners to directly book appointments for online consultation or in clinic visits.

Info@wecare.et

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient
Advertising
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 1 day, 12 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 6 days, 8 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago

1 month, 2 weeks ago

https://youtu.be/zb5F8Ir1hHA?si=qYrtuEe0_aYMCnRN

YouTube

ጾም ለጤና (Intermittent Fasting )

ጾም በሀገራችን ታዋቂ የሆነ የ ሃይማኖት ስርዓት ነው ። ነገር ግን ጾም ለጤና እጅግ ጠቃሚ የሆነ እና ውፍረት በፍጥነት ለመቀነስ እንደሚረዳ ያውቃሉ ፣ በሳይንሳዊ አጠራሩ intermittent fasting የሚባለው የአመጋገብ ስርዓት በዓለማቸን ታዋቂነት እያገኘ ያለ ለውጡም በበርካታ ጥናታዊ ምርምሮች የተረጋገጠ ነው ። በዚህ ቪዲዮ ዶ/ር ሃና ስለዚህ የአመጋገብ ስርዓት በጥልቅ ታስረዳናለች ።

1 month, 2 weeks ago

https://youtu.be/XVBIWXjYVno

YouTube

የተልባ የጤና ጥቅሞች

መተግበሪያችንን በመጠቀም ስለማንኛውም አይነት የጤና ችግር እና ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ያግኙ። ***🚨*** ሐኪሞቻችንን ለማግኘት መተግበሪያችንን ከ Play store ያውርዱ። ***👇🏼******👇🏼*** https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient ስለጤንነትዎ መረጃዎችን ለማግኘት wecare.et ን ይጎብኙ። ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ***👩‍⚕️******👨🏽‍⚕️***…

1 month, 2 weeks ago

📣ዛሬ መጋቢት 24 ፣ የዓለም ኦቲዝም ቀን ነው!

ኦቲዝም ያለባቸውን ግለሰቦች ልዩ ችሎታ እና ብቃት ለማክበር፣ ግንዛቤን ለማስጨበጥ እና ተቀባይነትን እናበረታታ።
❤️ 💛💚 💙💜💛 💙

*📢 ይህን ያውቁ ኖሯል?*

📌 ኦቲዝም ወይም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር (ASD) በማህበራዊ ግንኙነት፣ በባህሪ እና በስሜት ህዋሳት ሂደት ልዩነት ተለይቶ የሚታወቅ የነርቭ እድገት ሁኔታ ነው።

📌 ኦቲዝም የስፔክትረም ዲስኦርደር ነው፡ ይህም ማለት በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ በተለያየ መልኩ ይታያል። አንዳንዶቹ ቀላል ተግዳሮቶች ሊኖራቸው ይችላል፣ ሌሎች ደግሞ የበለጠ ከፍ ያለ ድጋፍ ሊፈልጉ ይችላሉ።

📌 ኦቲዝም በሁሉም ዘር፣ ብሄረሰብ፣ ጾታ እና ማህበረሰብ ደረጃ ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን በአሜሪካ ውስጥ ከ54 ህጻናት 1ልጅ ይኖርበታል ተብሎ ይገመታል።

📌 በአብዛኛው ኦቲዝም ያለባቸው ግለሰቦች ለየት ያለ ትኩረት ችሎታ ፣ ለፈጠራ እና በተወሰኑ የፍላጎት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ እውቀትን የመሳሰሉ ልዩ ጥንካሬዎች እና ችሎታዎች አሏቸው።

📌 ቀድሞ ማወቅ እና ድጋፍ ኦቲዝም ባለባቸው ግለሰቦች ህይወት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል፣ ክህሎት እንዲያዳብሩ፣ ተግዳሮቶችን እንዲወጡ እና በማህበረሰባቸው ውስጥ እንዲበለጽጉ ይረዳቸዋል።

📌 ኦቲዝም እድሜ ልክ ቢሆንም ትክክለኛ ድጋፍ እና ግንዛቤ ሲኖር ኦቲዝም ያለባቸው ግለሰቦች ጥሩ ህይወት መምራት እና ለህብረተሰቡ ጠቃሚ አስተዋጾ ማድረግ ይችላሉ።

📣 የኦቲዝም ግንዛቤን፣ ተቀባይነትን እና እውቀትን ዛሬም ሆነም በየቀኑ እናስፋፋ። በጋራ፣ ኦቲዝም ላለባቸው ሰዎች የበለጠ አካታች ዓለም መፍጠር እንችላለን። 💙💜💛💚💙❤️ 🌍 #AutismAcceptance#DifferentNotLess#Neurodiversity#WorldAutismDay#AutismAwareness#Inclusion#wecareet

1 month, 3 weeks ago

📣የቴምር የተረጋገጡ የጤና በረከቶችበየቀኑ ቴምርን አዘውትረው መመገብ ቢጀምሩ ሰውነትዎ ላይ ምን ለውጦችን ያያሉ?

*🌴የድካም ስሜትን ይቀንሳል*ቴምር በውስጡ ከፍተኛ የሆኑ የሃይል ምንጮችን ስለያዘ ቀን ተቀን በሚያደርጓቸው ተግባራት በቀላሉ እንዳይደክሙ ይረዳዎታል። 100 ግራም በሚሆን ቴምር ውስጥ ወደ 300 የሚጠጋ ካሎሪ አብዛኛው ከካርቦሃይድሬት የሚመነጭ ሲሆን ፋይበር፣ ፕሮቲን፣ እና እንደ ፖታሲየም፣ማግኒዢየም፣አይረን፣ እና ቫይታሚን ቢ 6 የመሳሰሉ ንጥረነገሮችን ይዟል።

*🌴የምግብ አፈጫጨት ስርዐትን ያሳልጣል* ቴምር ከፍተኛ የፋይበር ይዘት ስላለው የአንጀታችንን ጤንነት ለመጠበቅ እና የሆድ ደርቀትን ለመከላከል ይረዳል።

*🌴የኮሌስትሮል መጠንን ይቆጣጠራል* ቴምር ጣፋጭ እና በውስጡ ስኳር ቢኖረውም ምንም አይነት የስብ እና የኮሌስትሮል ይዘት ስለሌለው በሰውነታቸው ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል መጠን መቆጣጠር ለሚፈልጉ ሰዎች ጥሩ የምግብ አማራጭ ነው።

*🌴 በካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል*ቴምር በውስጡ የተለያዩ የአንቲኦክሲደንት አይነቶች ይዟል። በተለይም phenolic acid የሚባለው ቴምር ውስጥ የሚገኘው አንቲኦክሲደንት የህዋሶችን free radical ተረፈ ምርት በማስወገድ የካንሰር ህዋሶች እንዳይፈጠሩ ይከላከላል።

*🌴የአእምሮን ጤንነት ይጠብቃል* ቴምር የህዋሶችን መቆጣት ስለሚቀንስ የነርቮችን መኮምሸስ በመከላከል እንደ አልዛይመርስ ወይም የመርሳት በሽታ የመሳሰሉትን አእምሮአችን ላይ እክል የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን በመከላከል የኣአምሮአችንን ጤንነት እንዲጠበቅ ያደርጋል።

🌴የአጥንት ጥንካሬን ይጨምራል እንደ ካልሺየም ያሉ ንጥረነገሮች እጥረት ምክኛት የሚመጣ ሲሆን ቴምር በውስጡ ከፍተኛ የሆነ የካልሺየም እንዲሁም የፎስፈረስ፣የማኚዢየም ይዘት ስላለው የአጥንት ጥንካሬን ለመጠበቅ ይረዳል

🌴የልብ እና የአይን ጤንነትን ለመጠበቅ ይረዳል

ቴምር ካሮቲኖኢድ የተባለ አንቲኦክሲደንት በውስጡ ስለያዘ ለልብ ጤንነት የሚሰጠው ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ ነው። ከዚህም አልፎ ይህ ካሮቲኖኢድ macular degeneration የሚባል የአይን በሽታን ለመከላከል ይረዳል።

*🌴ስኳርን ለመተካት መጠቀም እንችላለን*ሪፋይንድ የሆነ ፋብሪካ ውስጥ የሚመረት ነጭ ስኳር ከመጠቀም ይልቅ ቴምርን ከውሃ ጋር አደባልቆ በመፍጨት የሚሰራ ማጣፈጫን መጠቀም ከጤና አንጻር ተመራጭ ነው።

🌴በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳብራልቴምር በውስጡ የያዛቸው አንቲኦክሲዳንቶች በዋነኝነት ፋቪኖኢድ፣ካሮቲኖይድ እና ፌኖሊክ አሲድ የሚባሉ ሲሆን ፍላቪኖኢድ የህዋሶችን መቆጣትት ይከላከላል። ካሮቲኖይድ የልብ እና የአይን ጤንነትን ይጠብቃል። ፌኖሊክ አሲድ ደግሞ በካንሰር ህመም የመያዝ እድልን ይቀንሳል

🌴 የምጥ ህመምን ለመቀነስ ይረዳልየተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በመጨራሻዎቹ የእርግዝና ሳምንታት ቴምርን አዘውትሮ መመገብ ኦክሲቶሲን የሚባለውን ሆርሞን ስራ በማስመሰል ምጥ ያለህክምና እርዳታ በራሱ እንዲጀምር ያደርጋል ፤ ምጥ የሚቆይበትንም ጊዜ ይቀንሳል።

*📌* እነዚህን የጤና ጥቅሞች ለማግኘት በቀን ከ5 እስከ 6 ቴምር መብላት በቂ ነው። ከዚህ በላይ መውሰድ ውፍረት እንዲጨምሩ ሊያደርግዎት ይችላል እንዲሁም በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ሊጨምር ይችላል።

👉 የስኳር በሽታ፣ የኩላሊት በሽታ፣ አስም እንዲሁም የሚታወቅ አለርጂ ካለብዎት ቴምር ከመውሰድዎ በፊት ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል።

👨🏽‍⚕️👩‍⚕️ ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር 📞 9394 ላይ ይደውሉ ።** . #wecare #wecareet #9394 #ethiopian #hakim

1 month, 3 weeks ago
WeCare ET
1 month, 3 weeks ago

*🫁 የቲቢ በሽታ የማይተላለፍባቸው መንገዶች፡-
📌 በመጨባበጥ
📌 ምግብ ወይም መጠጥ በመጋራት
📌 የታማሚውን ልብስ በመንካት ወይም መፀዳጃ ቤትን አንድ ላይ በመጠቀም
📌 የጥርስ ብሩሽን በመጋራት እና
📌* በመሳሳም አይተላለፍም።

*🫁ለቲቢ በሽታ አጋላጭ ምክንያቶች*

📌 የኤች.አይ.ቪ በሽታ ካለ
📌 ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት
📌 ስኳር በሽታ
📌 አብረውት የሚኖሩት ሰው በቲቢ ከተያዘ
📌የቲቢ ክትባት ከአልተከተቡ
📌 ሲጋራ ማጨስ እና አልኮል መጠጥ መጠጣት
📌 የተጨናነቀ እና የኑሮ ዐቅማቸው (ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ) ዝቅ ያለ አካባቢ መኖር
📌 የአደንዛዥ ዕፆች ሱስ
📌 ከባድ የኩላሊት በሽታ
📌 ዝቅተኛ ወይም ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት
📌 የንቅለ ተከላ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው ሰዎች
📌 የካንሰር በሽታ
📌 በሽታ የመከላከል ዐቅምን የሚቀንሱ መድኃኒቶች
📌 የጤና ተቋም ሠራተኛ መሆን (ተገቢውን ጥንቃቄ የማያደርጉ ከሆነ)
*🫁 የቲቢ በሽታ ምልክቶች ምንድናቸው?*

የቲቢ ታማሚ አብዛኛውን ጊዜ የሳንባ ነቀርሳ (Pulmonary TB) ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ምልክቶቹ እንደታመመው የሰውነት አካል ይለያያሉ።
*🚨የሳንባ ነቀርሳ ምልክቶች
📌 ረዘም ላለ ጊዜ የቆየ ሳል ( ሁለት ሳምንት እና ከዚያ በላይ)
📌 የደረት ሕመም
📌 አክታ፣ አክታው ደም የቀላቀለ ሊሆን ይችላል፡፡
የሳንባ ነቀርሳ እና ከሳንባ ውጭ ያለ የቲቢ በሽታ የሚያሳዩአቸው የጋራ ምልክቶች አሉ። እነዚህም ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆዩ ናቸው።
📌 የድካም ስሜት
📌 ክብደት መቀነስ
📌 የምግብ ፍላጎት አለመኖር
📌 ብርድ ብርድ ማለት
📌 መካከለኛ ትኩሳት እና
📌* የሚያረጥብ የለሊት ላብ ናቸው።

ሌሎች የቲቢ በሽታ (Disseminated & Extra Pulmonary) ምልክቶች በሽታው በተከሠተበት የሰውነት ክፍል ይወሰናሉ።

*👨🏽‍⚕️*👩‍⚕️ ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር 📞 9394 ላይ ይደውሉ ።**

💜💜💜💜

#TB #wecareet #wecare #digitalhealth #tuberculosis #ethiopianhealth #lung #selamdoctor #9394#doctors #health

3 months, 3 weeks ago
ይሳተፉ ይመልሱ ይሸለሙ***🎉******🎉******🎉***

ይሳተፉ ይመልሱ ይሸለሙ🎉🎉🎉

*👩‍⚕️የማህጸን በር ካንሰርን መከላከል ይቻላል?*

ይህን ጥያቄ በትክክል ለሚመልሱ 3 ሰዎች የ1GB ዳታ ጥቅል ሽልማት እንሰጣለን።

የ WeCare ET የስልክ መተግበሪያ ያሻዎትን ሐኪም በፈለጉት ሰአት እና ቀን የሚያማክሩበት ነው።

መተግበሪያውን አውርደው ዛሬዎኑ ይሞክሩት።
👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

👨🏽‍⚕️👩‍⚕️ ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር 📞 9394 ላይ ይደውሉ ።

Wecare ET social medias

📌 Facebook https://www.facebook.com/WeCareET/

📌 Telegram: https://t.me/WeCareET

📌YouTube: https://tinyurl.com/rv4zjmwk

📌Instagram: https://www.instagram.com/wecareet/

📌 Tiktok: https://vm.tiktok.com/ZMLbbyTXr/

📌Website: wecare.et

#wecare #doctors #hakim #wecareet #health #digitalhealth #healthcare #selamdoctor #9394

3 months, 3 weeks ago
WeCare ET
3 months, 3 weeks ago
የ WeCare ET ሕክምና መተግበሪያ ሥመጥር …

የ WeCare ET ሕክምና መተግበሪያ ሥመጥር ሐኪሞችን በቤትዎ ሆነው በኦንላይን ለማማከር የሚያስችል መተግበሪያ ነው።

wecare ET መተግበሪያን ስልክዎት ላይ በመጫን ዶ/ር ናርዶስ ለማን ጨምሮ ሌሎች ብቁና ስመጥር ሃኪሞችን ያማከሩ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

Wecare ET social media- Telegram https://t.me/WeCareET
-YouTube: https://tinyurl.com/rv4zjmwk
- Facebook https://www.facebook.com/WeCareET/
- Instagram https://www.instagram.com/wecareet/

#selamdoctor #wecareet

5 months, 3 weeks ago
**የሚያስፈልግዎት ህክምና በቤትዎ!!*****👩‍⚕️******👨‍⚕️***

የሚያስፈልግዎት ህክምና በቤትዎ!!👩‍⚕️👨‍⚕️

የምናቀርባቸው የህክምና ቁሳቁሶች

📌 ዊልቼየር

📌የኦክስጂን ሲሊንደር

📌የመምጠጫ ሰክሽን ማሽን

የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች

👉 አጠቃላይ ምርመራ

👉 የሐኪም ምክር

*👉 የፊዚዮቴራፒ አገልግሎት*

👉 የስነአእምሮ ስፔሻሊስት ህክምና እና ምክክር

👉 አጠቃላይ የነርሲንግ አገልግሎት

☎️ ለበለጠ መረጃ እና አገልግሎቱን ለማግኘት 📞 9394 ላይ ይደውሉ።

#wecareet #nurses #nursingcare #elderlycare #equipment #healthcare #midwifes #drbethel #pallativecar #wecare #doctors #homecare #wecareet #health #digitalhealth #healthcare #selamdoctor #9394

We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 1 day, 12 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 6 days, 8 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago