Ethiopia Check

Description
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Advertising
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 3 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

✅ ተወዳጁን አደይ ድራማ በዚህ የቴሌግራም ቻናል በጥራት ማግኘት ይችላሉ።
Contact Us @Aduventure
ሼር በማድረግ ያግዙን 🙏
@Adey_Drama_Ebs
@Adey_Drama_Ebs

Last updated 4 months, 1 week ago

1 month, 1 week ago
[#FactCheck](?q=%23FactCheck) ይህ ቪዲዮ የ4 ኪሎ-ፒያሳ ኮሪደር …

#FactCheck ይህ ቪዲዮ የ4 ኪሎ-ፒያሳ ኮሪደር ልማት ወቅታዊ ይዞታን አያሳይም

በፌስቡክ ከ160 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት 'ፋሲል የኔዓለም' የተባለ ግለሰብ በአዲስ አበባ ከተማ በመሰራት ላይ ከሚገኙ የኮሪደር ልማቶች መካከል የአንዱን ወቅታዊ ይዞታ ያሳያል ያለውን ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል።

ቪዲዮው ከቲክቶክ የተወሰደ ሲሆን "ዛሬ ያለቀው 1ኛው የኮሪደር ልማት በአራት ኪሎ" የሚል ጽሁፍ ይነበብበታል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው ቪዲዮ የኮሪደር ልማቱ ከመጀመሩ በፊት የተቀረጸ መሆኑን አረጋግጧል።

ቪዲዮው የሚያሳየው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 4 ኪሎ ግቢ ዋና በር ፊት ለፊት ያለው አካባቢ ሲሆን በቪዲዮው ላይም የ4 ኪሎ-ፒያሳ የኮሪደር ልማት በተጀመረ የመጀመሪያዎቹ ቀናት የፈረሱ ህንጻዎች ይታያሉ።

ከነዚህም መካከል በቀይ ቀለሙ ጎላ ብሎ የሚታየውና 'ኮርዲያል ካፌ' ይገኝበት የነበረው ህንጻ ይገኝበታል። በተጨማሪም ከቀዩ ህንጻ ጎን የነበረው አባድር ሱፐር ማርኬትም በተመሳሳይ ወቅት መፍረሱ ይታወቃል። ኢትዮጵያ ቼክ በወቅቱ የህንጻዎቹን ፈረሳ መታዘብ ችሎ ነበር።

ይህም ከላይ የተጠቀሰው የፌስቡክ አካውንት ያጋራው ቪዲዮ የ4 ኪሎ-ፒያሳ ኮሪደር ልማት ከመጀመሩ ቀደም ብሎ የተቀረጸ መሆኑን ያረጋግጣል።

በአዲስ አበባ ከተማ በመሰራት ላይ ከሚገኙ የኮሪደር ልማቶች መካከል አንዱ የሆነው የ4 ኪሎ-ፒያሳ ፕሮጀክት መጠናቀቁን የከተማዋ ከንቲባ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

@EthiopiaCheck

1 month, 2 weeks ago
[#FactCheck](?q=%23FactCheck) የጫካ ፕሮጀክትን ያሳያል በሚል በሚድያዎች …

#FactCheck የጫካ ፕሮጀክትን ያሳያል በሚል በሚድያዎች እየተጋራ የሚገኘው ምስል በካንኩን፣ ሜክሲኮ ሊሰራ የታቀደ ፕሮጀክት ነው

ተያይዞ የሚታየዉ ምስል መንግስት በየካ ተራሮች ላይ እያስገነባዉ የሚገኘዉ የጫካ ፕሮጀክትን የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ በተለይ የመንግስት ሚድያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።

ፕሮጀክቱ ቤተመንግስትን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በዉስጡ የያዘ ሳተላይት ከተማ (satellite city) እንደሆነ የተነገረለት ነዉ።

ይሁን እንጂ ይህ ምስሉ የሚታየዉ ንድፈ-ሀሳብ በጣሊያናዊዉ አርክቴክት ስቴፋኖ ቦኤሪ የተሰራ ሲሆን በሜክሲኮ ካንኩን ከተማ ለመሰራት የታሰበ ዘመናዊ ከተማ ነው። ማስረጃ: https://transsolar.com/projects/smart-forest-city-cancun-masterplan-boeri

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የዛሬ ሁለት አመት ገደማ በተካሄደ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባዔ ላይ በየካ ተራሮች ላይ እየተገነባ የሚገኘው ፕሮጀክት ዘመናዊ እና ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካም ኩራት የሚሆን እንደሚሆን ተናግረዉ ነበር፣ ፕሮጀክቱም ከ 400 እስከ 500 ቢልየን ብር የሚፈጅ እንደሆነም ገልፀው ነበር።

@EthiopiaCheck

1 month, 2 weeks ago
[#FactCheck](?q=%23FactCheck) ይህ ቪዲዮ በትግራይ ክልል የወደመ …

#FactCheck ይህ ቪዲዮ በትግራይ ክልል የወደመ የፓፓያ እርሻን አያሳይም

ከ1,600 በላይ ተከታዮች ያሉት እና 'Mulue G Medhanye' የሚል ስም የሚጠቀም ማረጋገጫ (verification) ያለው የኤክስ (ትዊተር) አካውንት በትግራይ ክልል የወደመ የፓፓያ እርሻን ያሳያል ያለውን ቪዲዮ ከሶስት ቀን በፊት ማጋራቱን ተመልክተናል።

የተጋራው ቪድዮ ከ54,200 ሺህ በላይ እይታዎችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም መልሰው አጋርተውታል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው አካውንት ያጋራው ቪዲዮ ከሌላ ሀገር የተወሰደ መሆኑን አረጋግጧል።

ይህ ቪዲዮ የተቀረጸው በምስራቃዊ ባንግላዴሽ ሲሌት (Sylhet) በተባለች ከተማ አቅራቢያ ሲሆን ቪዲዮውን ከሳምንት በፊት ያጋራውም 'Artcelnazmulofficial'  የተባለ የዩቱብ ቻናል ነበር። በዩቱብ ቻናሉ መረጃ መሰረት የፓፓያ እርሻው የወደመው በአካባቢው የተከሰተ ንፋስ የቀላቀለ ውሽንፍርን ተከትሎ ነበር።

ትክክለኛውን ቪዲዮ ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል: https://youtube.com/shorts/vqs1LBBFRQ8?si=aBcd3faS4UA5BUvn

በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት በእርሻዎች እና በእርሻ መገልገያ መሳሪያዎች ላይ ውድመት መድረሱን በስፋት መዘገቡ ይታወሳል።

ይሁንና ከአውድ ውጭ ተወስደው የሚሰራጩ ቪዲዮዎች ለሀሠተኛ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችንና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄና ማጣራት እናድርግ።

@EthiopiaCheck

1 month, 3 weeks ago

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኮሪያ-አፍሪካ ጉባዔ “ብቸኛው አፍሪካዊ ተናጋሪ” እንደሆኑ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

የዘንድሮው የኮሪያ-አፍሪካ ጉባዔ በሁለቱ የደቡብ ኮሪያ ከተሞች ሴኡል እና ኢልሳን እየተካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በጉባዔው በመገኘት ንግግር አድርገዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የጉባዔው ተሳትፎ በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ሲሆን ከነዚህ መካከልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባዔው “ብቸኛውና ተጠባቂው አፍሪካዊ ተናጋሪ” እንደሆኑ የሚገልጽ መረጃ አንዱ ነው።

ይህን መረጃ ካጋሩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከልም Ethio info Center፣ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ አርበኞች እና Gibe Media /GM/ የተሰኙ የፌስቡክ ገጾች ይገኙበታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በጉባዔው ‘ብቸኛው አፍሪካዊ ተናጋሪ’ እንዳልሆኑ ማረጋገጥ የቻለ ሲሆን የተለያዩ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች በመድረኩ ንግግር አድርገዋል።

ከነዚህ መካከል የርዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አንዱ ሲሆኑ ፕሬዝዳንቱም አፍሪካና ኮሪያ በሰው ሰራሽ አስተውሎትና ሮቦቲክስ እንዲሁም አነስተኛ የኑክሌር ማብላያዎች ዘርፍ አብረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ በቪድዮ የተደገፈው የርዋነዳው ፕሬዝዳንት ንግግርም በተረጋገጠው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኤከሰ (X) አካዉንት ተጋረቷል፡ https://x.com/urugwirovillage/status/1797911676794388730?s=48&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶም በኮሪያ-አፍሪካ ጉባዔ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ግብርና፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም ሰላምና ጸጥታ ኮሪያና አፍሪካ በትብብር እንዲሰሩባቸው ያነሷቸው ጉዳዮች ናቸው።

ይህ ንግግርም በፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ‘X’ አካውንት ላይ ተለጠፏል፡ https://x.com/williamsruto/status/1797998068388045023?s=48&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ

በሌላ በኩል የመጀመሪያው በሆነው የ2024 የኮሪያ-አፍሪካ ጉባዔ 48 የአፍሪካ ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን የ25 አፍሪካ ሀገራት መሪዎች በጉባዔው መገኘታቸው ተዘግቧል።

@EthiopiaCheck

X (formerly Twitter)

Presidency | Rwanda (@UrugwiroVillage) on X

Africa will be a central driver of global growth before too long, so long as we do not take our future for granted.” President Kagame | 1st Korea-Africa Summit

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኮሪያ-አፍሪካ ጉባዔ “ብቸኛው አፍሪካዊ ተናጋሪ” እንደሆኑ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው
1 month, 3 weeks ago
Ethiopia Check
1 month, 3 weeks ago

#EthiopiaCheck የሀሠተኛና የተዛባ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል ሚድያዎች ሊኖራቸው የሚገባ ሚና!

የሀሠተኛና የተዛባ መረጃ ስርጭት የሚያደርሰውን ዘረፈ ብዙ ችግር በመግታት ረገድ የገለልተኛ የመረጃ አንጣሪ ተቋማት ሚና በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል። ሆኖም ከችግሩ ስፋትና መልከ ብዙነት አኳያ ከነዚህ ተቋማት በተጨማሪ የሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ግድ ይላል፤ በተለይም የሚዲያ ተቋማት።

የሌሎች ሀገራት ልምድ እንደሚያሳየው የሚድያ ተቋማት መረጃን ከማሰራጨት ጎን ለጎን የሀሠተኛና የተዛባ መረጃ ስርጭትን በመከላከል ረገድ ሚናቸው የላቀ ነው። ሚናቸውም ለመረጃ ማንጠር የሚረዱ የተለያዩ መድረኮችን ቀርጾ ተግባር ላይ ከማዋል እስከ የሚዲያ ንቃት መርሀግብሮች ይዘልቃል።

በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት የሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ዕለታዊ ጋዜጣ ታምፓ ቤይ ታይምስ በዘመናዊ የመረጃ ማንጠር ስራ ፈርቀዳጅ የሆነውን ፖሊቲፋክትን (PolitiFact) በመጀመር በምሳሌነት ይጠቀሳል። የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን በማጋለጥ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ፕላትፎርሞች መካከል አንዱ የሆነው የዋሽንግተን ፖስት ፋክት ቼከርም (The Washington Post Fact Checker) የተጀመረው በሌላኛው የአሜሪካ ጋዜጣ ዋሽንግተን ፖስት መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች የአሜሪካ ጋዜጦች፣ የቴሌቪዥንና የራዲዮ ጣቢያዎች በተቋማቸው ውስጥ የመረጃ አንጣሪ ዴስኮችን በማቋቋም የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት ይዋጋሉ። 

የህንድ ሳምታዊ መጽሔት ኢንዲያ ቱዴይ በመጽሔቱና በድረግጹ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን የሚያጋልጥባቸው ራሳቸውን የቻሉ ገጾች ያሉት ሲሆን የኬኒያው ዴይሊ ኔሽም በኔሽን ኒውስፕሌክስ (Nation Newsplex) ገጹ በዳታ የተደገፈ የመረጃ ማንጠር ስራ ይከውናል። በናይጄሪያና በጋና ራዲዮ ጣቢያዎች የአየር ሰዐት መድበው ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ያጋልጣሉ።

ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ የሚዲያ ተቋማት ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን በመጋለጥ ረገድ ይህ ነው የሚባል ስራ ሲሰሩ አይታይም።

ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ቅኝት አንዳንድ ጅማሮዎች ቢኖሩም አሁን ላይ ለምሳሌ የአየር ሰዐት መድበው ወይንም የጋዜጣ አምድ መድበው መረጃ የማንጠር ስራ የሚሰሩ ሚዲያዎች ማግኘት አልቻለም። በተለይም ሚዲያዎቹ ካላቸው ሰፊ ተደራሽነትና የሰው ሀይል አኳያ የሀሠተኛና የተዛባ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የራሳቸውን አስተዋጽዖ ቢያበረክቱ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይቻላል።

@EliasMeseret

2 months ago

#EthiopiaCheck Explainer ጊዜው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ነው፤ ለዚህም የዛሬ ሁለት አመት ገደማ እንደመጣው ቻትጂፒቲ አይነት ወይም እንደ ዲፕፌክ ያሉ የምንፈልገውን ሃሳብ እና የሰው ድምጽ የሚሰጡን መሳሪያዎች ማሳያ ናቸው።

በዚህ ዙርያ ያዘጋጀነውን ዘገባ ያንብቡ:

https://ethiopiacheck.org/home/disinformation-threats-posed-by-ai-generated-images-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%ad%e1%89%b4%e1%8d%8a%e1%88%bb%e1%88%8d-%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%89%b0%e1%88%88%e1%8c%80%e1%8a%95%e1%88%b5/

ኢትዮጵያ ቼክ

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምስሎች የደቀኑት የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት ስጋት እና መለያ ዘዴዎች - ኢትዮጵያ ቼክ

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምስሎች የደቀኑት የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት ስጋት እና መለያ ዘዴዎች ጊዜው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ነው፤ ለዚህም ከባለፈው አመት መጨረሻ ወራት ጀምሮ እንደመጣው ቻትጂፒቲ አይነት ወይም እንደ ዲፕፌክ ያሉ የምንፈልገውን ሃሳብ እና የሰው ድምጽ የሚሰጡን መሳሪያዎች ማሳያ ናቸው።

[#EthiopiaCheck](?q=%23EthiopiaCheck) Explainer ጊዜው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ነው፤ ለዚህም የዛሬ ሁለት አመት ገደማ እንደመጣው ቻትጂፒቲ አይነት ወይም እንደ ዲፕፌክ ያሉ የምንፈልገውን …
2 months ago
ፎቶዎችን ከማጋራታችን በፊት ልብ እንበል!

ፎቶዎችን ከማጋራታችን በፊት ልብ እንበል!

በማህበራዊ ሚድያ የሚዘዋወሩ ፎቶዎችን ከማጋራታችን ወይም ከማመናችን በፊት አለመነካካታቸውን እናጣራ፣ ለማጣራትም እነዚህን ልብ እንበል:

@EthiopiaCheck

2 months ago
[#EthiopiaCheck](?q=%23EthiopiaCheck) ቑጽርታትን ማሕበራዊ ሚድያን! ቑጽርታት ንሓሶትን …

#EthiopiaCheck ቑጽርታትን ማሕበራዊ ሚድያን! ቑጽርታት ንሓሶትን ዝተዛብዐን መረዳእታ ከየቃልዑና ነስተውዕል።

#MediaLiteracy

@EthiopiaCheck

4 months ago
[#EthiopiaCheck](?q=%23EthiopiaCheck) Explainer

#EthiopiaCheck Explainer

ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት ለመግታት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለማድረግ ምን ማድረግ እንችላለን?

#MediaLiteracy

@EthiopiaCheck

We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 3 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

✅ ተወዳጁን አደይ ድራማ በዚህ የቴሌግራም ቻናል በጥራት ማግኘት ይችላሉ።
Contact Us @Aduventure
ሼር በማድረግ ያግዙን 🙏
@Adey_Drama_Ebs
@Adey_Drama_Ebs

Last updated 4 months, 1 week ago