የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion ? @Share_Home
Last updated 2 weeks, 5 days ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 6 months, 3 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 8 months, 3 weeks ago
የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ
ቴሌግራም የህጻናት ወሲብ ብዝበዛን የሚያሳዩ ይዘቶችን ከፕላትፎርሙ ለማጽዳት ከኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን ጋር ስምምነት ማድረጉን አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን የህጻናት ወሲብ ብዝበዛን የሚያሳዩ ይዘቶችን ከኢንተርኔት በማስቀገድ ረገድ ብዙ ቀዳሚ ተቋም መሆኑ ይነገራል። በስምምነቱም ቴሌግራም ይዘቶቹን ቀድሞ ለመለየትና ለማስወገድ የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችንና ልምዶችን ያገኛል ተብሏል። ከዚህ ጋር በተገናኘ ሸጋ የተባለ የድረገጽ ሚዲያ ከቀናት በፊት ባስነበበው የምርመራ ዘገባ የኢትዮጵያውያን ሴቶችን እርቃን ምስሎች የሚያሳዩ ይዘቶች በቴሌግራም በስፋት እንደሚሰራጩ ያሳየ ሲሆን ጉዳዩ ባለፉት ቀናት የቲክቶክ መንደር ዋና መነጋገሪ መሆኑ ይታወቃል።
በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች እስካሁን የስርጭት መጠናቸው አነስተኛ መሆኑን ሜታ በትናትናው ዕለት አስታውቋል። በፈረንጆቹ 2024 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ በተደረጉ ምርጫዎችን በተመለከተ በፕላትፎርሞቹ ከተሰራጩ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችም በሰውሰራሽ አስተውሎት የተሰሩት ድርሻ ከ1% በታች መሆኑን ገልጿል። ይዘቶቹን ለመለየትና ለማስወገድም እንዳልከበደው አብራርቷል።
ሜታ በሙከራ ደረጃ ያስጀመረውን ቅጣትን በትምህርት የመቀየር አሰራር ለሁሉም የፌስቡክና የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ማስፋቱን በትናትናው ዕለት አስታውቋል። አሰራሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖሊሲ ጥሰት ፈጽመው የአካውንት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተጠቃሚዎች አጭር ትምህርታዊ ፕሮግራም በመከታተል ቅጣታቸውን እንዲሰረዝላቸው የሚያደርግ ነው። ሆኖም አሰራሩ ተደጋጋሚ ወይም ከባድ የፖሊሲ ጥሰት የሚፈጽሙትን አይመለከትም ተብሏል።
በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች:
-ቆየት ያሉ ልጥፎችን ለማሰስ የሚረዳ መገልገያን በአፋን ኦሮሞ አስተዋውቀናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2522
-የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚያስገነባውን የግዙፍ ኤርፖርት ፕሮጀክትን ያሳያሉ ተብለው የተጋሩ ምስሎችን አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2524
-የሴራ ትንታኔን መሰረት አድርገው ስለሚሰራጩ ሀሠተኛ መረጃዎች በትግርኛ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2525
ኢትዮጵያ ቼክ
#FactCheck እነዚህ ምስሎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚያስገነባውን የግዙፍ ኤርፖርት ፕሮጀክትን ንድፍ አያሳዩም
ከሰሞኑ በርከት ያሉ የፌስቡክ እና ኤክስ (ትዊተር) ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚያስገነባውን ሜጋ ኤርፖርት ፕሮጀክት ያሳያሉ ያሏቸውን ምስሎች እያጋሩ ይገኛሉ።
ለምሳሌም ‘FastMereja.com’ የሚል ስም ያለው እና ከ860 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ5 ቢሊየን ፓውንድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ” ሲል በስክሪን ቅጂው የሚታዩትን ሶስት ምስሎች አጋርቷል።
ይህን የፋስት መረጃ ልጥፍም ከ40 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው አጋርተውታል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምስልን በምልሰት መፈለጊያን በመጠቀም በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት በስክሪን ቅጂው የታችኛው ክፍል የሚታዩት ሁለት የኤርፖርት ንድፎች በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው የኢንቾን ኤርፖርት ንድፍ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችሏል።
የኢንቾን ኤርፖርት ንድፎች በተለያዩ ጊዝያት ሲጋሩ የቆዩ ሲሆን ከንድፎቹ የተወሰኑትን በነዚህ ማስፈንጠሪያዎች መመልከት ይቻላል፡ https://www.gensler.com/projects/incheon-international-airport እና https://www.koreaherald.com/view.php?ud=20191119000078
በሌላ በኩል በስክሪን ቅጂው የላይኛው ክፍል የሚገኘው ምስል ‘GSAAN’ በተሰኘ ድረ-ገጽ የተጋራ ሲሆን ተቋሙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚገነባው ሜጋ ኤርፖርት የቅድም ዲዛይን እና ማስተር ፕላን ጽንሰ-ሐሳብ አገልግሎት መስጠቱን ጠቅሷል፡https://www.gsaan.us/ethiopia-new-airport-logistics-industry-park-project-study-report/
ይሁን እንጂ ‘GSAAN’ ድረ-ገጽ ላይ የተጋራውን ንድፍ ከሌላ ምንጮች ማረጋገጥ አልቻልንም።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ በቢሾፍቱ ከተማ ለሚያስገነባው ሜጋ ኤርፖርት ከዳር አል ሀንዳሽ የግንባታ አማካሪ ድርጅት ጋር የቴክኒካል፣ የአርክቴክቸር፣ የኢንጅነሪንግ እና ፕሮጀክት ማኔጅመንት ስምምነት መፈራረሙን ባለፈው ነሐሴ 2016 በድረ-ገጹ ባጋራው መግለጫ አስታውቆ ነበር፡ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-signs-a-contract-with-dar-al-handasah-to-develop-a-mega-airport-city
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት በኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ በዳር አል ሀንዳሽ የግንባታ አማካሪ ድርጅት ይፋ የሆነ የሜጋ ኤርፖርቱ ንድፍ እንደሌለ ተመልክተናል።
በሌላ በኩል ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገነባ የተነገረው ሜጋ ኤርፖርት በአመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ-ገጽ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
ኢትዮጵያ ቼክ
የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ
1.ተጽእኖ ፈጣሪ ናይጄሪያውያን አርቲስቶችን ያካተተ ጥምረት በሀሠተኛና በተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ዙሪያ ንቃት ለመፍጠር ያለመ እንቅስቃሴ መጀመሩን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ጥምረቱ ናይጄሪያውያን ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች መለየት እንዲችሉ ትምህርታዊ ንቅናቄዎችን ያደርጋል የተባለ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎችንም ተጠያቂ የማድረግ ትልም እንዳለው ተገልጿል። ጥምረቱ #FWDWithFacts የሚል ሃሽታግ ይጠቀማል ተብሏል።
3.በስሩ ከ320,000 በላይ ጋዜጠኞችን ያቀፈው የአውሮፓ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን ከመጭው የፈረንጆች ዓመት የመጀመሪያ ወር መጨረሻ ጀምሮ ኤክስ/ትዊተር የተባለውን የማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም እንደሚያቆም አስታውቋል። ፌደሬሽኑ የማህበራዊ ሚዲያውን ባለቤት በፀረ-መደበኛ ሚዲያነት የከሰሰ ሲሆን ኤክስ “የሴራ ተንታኞች፣ የዘረኞችና የአክራሪ ቀኝ ዘመሞች” መናህሪያ ሆኗል ሲል ባወጣው መግለጫ አስነብቧል። በቅርቡ ዘጋርዲያን ጋዜጣን ጨምሮ በርከት ያሉ ተቋማትና ግለሰቦች ተመሳሳይ ምክን ያት በመጥቀስ ኤክስን መጠቀም ለማቆም መወሰናቸውን ማስታወቃቸው ይታወቃል።
በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች
-የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭት ለመቀነስ ጋዜጠኞች ምን ማድረግ ይችላሉ፧ የሚል መልዕክት አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2515
-ወቅታዊ መረጃዎችን በምንከታተልበት ወቅት ማድረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ የሚያስረዳ ጽሁፍ በትግረኛ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2516
-ድምጽ ማቸገን ምንድ ነው? ጉዳቱስ? እንዴት መከላከል እንችላለ? ለሚሉት ጥያቄወች ምላሽ የሚሰጥ ማብራሪያ አስነብበናል: https://t.me/ethiopiacheck/2517
-እንዲሁም ለመሆኑ ጎብኝ ሲባል ማንን ያካትታል? ከጎብኝዎች የተገኘ ገቢስ እንዴት ይሰላል? ለሚሉት ጥያቄወች ምላሽ የሚሰጥ ማብራሪያም አጋርተናል።
ኢትዮጵያ ቼክ
#Explainer ለመሆኑ ጎብኝ ሲባል ማንን ያካትታል? ከጎብኝዎች የተገኘ ገቢስ እንዴት ይሰላል?
የአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ከ3.4 ሚሊዮን በላይ ጎብኝዎችን ማስተናገዱን እና በዚህም ከ2.41 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በትናንትናው ዕለት አስነብቦ ነበር። ለመረጃውም በምንጭነት የክልሉን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጠቅሷል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች ክልሎችም እንዲህ ያሉ ቁጥሮችን በየጊዜው ሲናገሩ ይደመጣል። ይህን የተመልከቱ ሰዎች ቁጥሮቹ መጋነናቸውን በመጥቀስ አስተያየታቸው ሲሰጡ የሚታይ ሲሆን ለኢትዮጵያ ቼክም የአጣሩልን ጥያቄዎች ይመጣሉ።
- ለመሆኑ ጎብኝ ሲባል ማንን ያካትታል? ከጎብኝዎች የተገኘ ገቢስ እንዴት ይሰላል?
የተመድ የዓለም ቱሪስም ድርጅት (UNWTO) የቃላት መፍቻ ጎብኝ ወይም ዕንግዳ (visitor) ከአንድ አካባቢ ወደሌላ አካባቢ የሚጓዝ፤ በሄደበት አዲስ አካባቢ ከአንድ ዓመት በላይ የማይቆይ፤ ጉዞውም ከቅጥር ውጭ ለንግድ፣ ለጉብኝት፣ ለግል ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል ይዘረዝራል።
ተጓዡ በሄደበት አካባቢ ከአንድ ቀን በላይ ከቆየ ቱሪስት (tourist) ሊባል እንደሚችል የሚበይነው ድርጅቱ ከአንድ ቀን በታች ወይም በደርሶ መልስ ወደመኖሪያቸው የሚመለሱትን ሽርሽር አድራጊዎች (same-day visitor or excursionist) ይላቸዋል። ጎብኝ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ተጓዦችን ያጠቃልላል።
ከጎብኝዎች የሚገኝ ገቢ ደግሞ ጎብኝው በአካባቢው በቆየበት ጊዜ ለምግብ፣ ለምኝታ፣ ለአስጎብኝ፣ ለትራንስፖርት፣ ለስጦታ ዕቃዎች መግዣ ወዘተ ያወጣል ተብሎ የሚገመተው ወጭ ላይ መሰረት እንደሚያደርግ የዓለም ቱሪስም ድርጅት የቃላት መፍቻ ያስረዳል።
- የአማራ ክልልን በሩብ አመቱ የጎበኙት እነማናቸው? ገቢውስ ከምን ተገኘ?
የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ በሩብ አመቱ ክልሉን ጎበኙ ያላቸውን ዋና ዋና ተጓዦችን ዘርዝሯል። በቢሮው የቱሪዝም ልማት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ አዳም በግሸን ደብረ ከርቤ በዓል አከባበር ብቻ አንድ ሚሊየን ሃይማኖታዊ ጎብኝዎች ወደ አካባቢው መጓዛቸውን የገለጹ ሲሆን በሰሜን ሸዋ የሚገኙ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ መስህቦችን ለመጎብኘትም በየሳምንቱ መጨረሻ የእረፍት ቀናት ከአዲስ አበባ በርካታ ጎብኚዎች እንደሚመለጡ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ከነሐሴ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚከበሩት የሻደይ፣ አሸንድዬና ሶለል በዓል፣ የመስቀል፣ የግሸን ደብረ ከርቤ በዓላትና ሌሎች ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላትንም አስረድተዋል።
ከጎብኝዎቹ መካከልም 6,328 የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች መሆናቸው ተገልጿል።
ከጎብኝዎች ተገኘ የተባለው ገቢ የተሰላው አንድ የውጭ ወይም የሀገር ውስጥ ጎብኝ እንደ አካባቢው ሁኔታ በቀን ለመኝታ፣ ለምግብ፣ ለአስጎብኝ፣ ለጫማ ማስዋብና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚያወጣው ታስቦ መሆኑ ቢሮው ባጋራው መረጃ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ቼክ
#የሰኞመልዕክት የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭት ለመቀነስ ጋዜጠኞች ምን ማድረግ ይችላሉ?
አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ቀን ከቀናት በፊት በተለያዩ መርሐግብሮች ተከብሮ ውሏል። በዕለቱም በአስቸጋሪ የስራ አውድና ከባቢ ውስጥ ሁነው መረጃ የሚደርሱ ጋዜጠኞች ታስበው ውለዋል። ኢትዮጵያ ቼክም ለሙያ እና ለስነምግባር መርሆች ታምነው ማህበረሰባቸውን ያገለገሉ ጋዜጠኞችን ያመሰግናል!
ሆኖም የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶች ስርጭት ከፍተኛ ምስቅልቅል እየፈጠረ ባለበት በዚህ ወቅት የጋዜጠኞች ሚና መረጃን ከመዘገብም በላይ መሆን አለበት ብለን እናምናለን። በዚህ አኳያም ጋዜጠኞች ዘርፈ ብዙ አስተዋጾ ማበርከት ይችላሉ።
ጋዜጠኞች በቅድሚያ ማድረግ የሚችሉት በጎ አስተዋጾ የሙያ እና የስነምግባር መርሆችን በጥብቅ ማክበርና መፈጸም ሲሆን ይህም የሀሠተኛ መረጃን እና የጥላቻ መልዕክቶች ስርጭት በመቀነስ ረገድ የማይተካ ሚና አለው። ጋዜጠኞች ለሙያና ለስነምግባር መርሆችን በከፍተኛ ደረጃ ተገዥ በመሆን ዘገባቸው ትክክለኛ፣ ርዕታዊ፣ ከሀሠተኛ መረጃ የጸዳ፣ አካታችና ከጥላቻ መልዕክት የራቀ መሆኑን ማረጋገጥ የዕለት ስራቸው መሆን ይገበዋል። በተጨማሪም ግልጽነት የተሞላበት የዘገባ ሂደትን ማስፈን፣ ስህተት ሲፈጠር ቀጥተኛና ፈጣን ዕርምት መስጠት ከተከታታዮች ጋር የሚኖረውን የመተማመን ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።
በሌላ በኩል ጋዜጠኞች የመረጃ ማጣራት ስራን በመስራት እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን በማጋላጥ በጎ ተጽኖ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። ይህንንም በሚሰሩባቸው የሚዲያ ተቋማት የመረጃ ማጣሪያ ዴስክ በማቋቋም፣ የአየር ሰዐት ወይም የህትመት ቦታ በመመደብ፣ የግል የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን በመጠቀም እንዲሁም ገለልተኛ ከሆኑ የመረጃ አጣሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት መከወን ይችላሉ።
በተጨማሪም ጋዜጠኞች የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን መለየት፣ ማጣራት እና ማጋለጥ እንዴት እንደሚቻል የሚያስተምሩ የሚዲያ አጠቃቀም ንቃት ፕሮግራሞችን በመስራትም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ። ይህንንም የመረጃ ማጣራት ዘዴዎችና ቴክኖሎጅዎች በመማር እንዲሁም ባለሙያዎችን በመጋበዝ በቀላሉ መስራት የሚቻል ነው።
የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎች ከአሉታዊ ይዘቶች አንጻር የክትትልና የቁጥጥር ስራቸውን ጠበቅ እንዲያደርጉ በመወትወት እንዲሁም የህግ አውጭና ፈጻሚ አካላት የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕቶች በተመለከተ የሚያወጧቸውን ህጎችና ፖሊሲዎች ጉድለታቸውን በመፈተሽ እንዲሁም በትክክለኛ አግባብ መፈጸማቸውን በመከታተል በጎ ተጽኖ ማሳረፍ ይቻላል።
ጋዜጠኞች እነዚህንና ሌሎች የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭትን የሚቀንሱ ተግባራትን እንደሙያ ግዴታቸው በመቀበል በየዕለቱ መተግበር ከቻሉ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለን እናምናለን።
ኢትዮጵያ ቼክ
የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ
በሀሠተኛ መረጃ ዙሪያ የሚያጠነጥን ዌን ዎልቭስ ክራይ (When the Wolves Cry) የተሰኘ ፊልም በትናንትናው ዕለት በናይጄሪያ አቡጃ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ግቢ መመረቁን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ከናይጀሪያ፣ ቶጎ፣ ካሜሩን እና ቤኒን የተውጣጡ እውቅ ተዋኒያን የተሳተፉበት ይህ ፊልም ናይጄሪያንና ካሜሮንን ወደ ጦርነት ጫፍ አድርሶ የነበረን ሀሠተኛ መረጃ የታሪኩ ማዕከል ያደረገ ነው ተብሏል። በሀሠተኛ መረጃ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተሰራው ዌን ዎልቭስ ክራይ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም እውቅ በሆኑ የፊልም ፌስቲቫሎች እደሚታይም ተገልጿል።
ባሳለፍነው ዕሁድ በፈረንሳይ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው የቴሌግራም መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፓቬል ድሮቭ ከእስር በገንዘብ ዋስ መለቀቁን ቢቢሲ ዘግቧል። የፈረንሳይ ፖሊስ ቴሌግራምን በመጠቀም የተደራጁ ወንጀለኞች የሚያደርጉትን የገንዘብ ዝውውር ችላ በማለት፣ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ባለመተባበር እና በተደራጁ የወንጀለኛ ቡድኖች የሚሰራጩ የህጻናት ወሲብ ነክ ምስሎችን ባለመቆጣጠር ወንጀሎች ፓቬል ድሮቭ ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ በዘገባው ላይ ተገልጿል። በ5 ሚሊዮን ዩሮ ዋስትና ከዕስር ቤት የወጣው ፓቬል ድሮቭ ጉዳዩ እልባት እስከሚያገኝ ከፈረንሳይ መውጣት እንደማይችልም ተገልጿል።
ብራዚል ኤክስ/ትዊተር የተሰኘውን የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም ልትዘጋ እንደምትችል አለም አቀፍ ሚዲያዎች በመዘግብ ላይ ይገኛሉ። ብራዚል እርምጃውን የምትወስድው ኤክስ በሀገሪቱ መመደብ የነበረበትን የህግ ተወካይ (legal representative) ማቅረብ ባለመቻሉ መሆኑ ተገልጿል። የብራዚል ህግ ማነኛውም የማህበራዊ ሚዲያ ኣአገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ የህግ ተወካይ እንዲኖረው ይደነግ ጋል። ኤክ ባለፈው ወር የህግ ተወካዩን ከብራዚል ካሰወጣ በኅላ ከሀገሪቱ መንግስት ጋር የከረረ ጸብ ውስጥ መግባቱ ይታወቃል።
በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥
-የጥላቻ ንግግርን የተመልከተ መልዕክት በአፋን ኦሮሞ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2427
-በማህበራዊ ሚዲያ በሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሰለባ ላለመሆን የሚረዱ ነጥቦችን አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2428
-በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨን አንድ ሰነድ በተመለከተ የሚዲያ ዳሰሳ አቅርበናል: https://t.me/ethiopiacheck/2430
-የተጣራ መረጃን በቀላሉ ለማግኘት እና መረጃ ለማጣራት የሚጠቅሙ የጎግል መገልገያዎች የሚያስተዋውቅ ጽሁፍም አጋተናል: https://t.me/ethiopiacheck/2431
#MediaMonitoring 'ብወገን ትግራይ ዝተፈረመ ሰነድ የለን' - ጊዝያዊ ምምሕዳር ትግራይ
ሎሚ መዓልቲ: ግዝያዊ ምምሕዳር ትግራይ ኣብ ልዕሊ እቲ ክልል 'ጥልመትን ክሕደትን' ፈጺሙ ብዝብል ዝተዘርግሐ ሰነድ ንብዙሓት ከዘራርብን ሕቶ ከልዕልን ውዒሉ ኣሎ።
እዚ: "ኣብ መዋስንቲ ከባቢታት ኣምሓራን ትግራይን ህዝባዊ ምምሕዳር ንምውዳብ ዝተዳለወ ትልሚ" ብዝብል ርእሲ ዝተወዝዐ ሰነድ: ኣብ መንጎ ግዝያዊ ምምሕዳር ትግራይን ፌደራላዊ መንግስትን ዝተፈረመ ከም ዝኾነ ይገልጽ።
እዚ ባሻ ደስታ ብዝብል ኣካውንት https://www.facebook.com/share/p/pDLqsfGZTraGPptn/?mibextid=oFDknk ዝወጽአ ሰነድ በቲ ግዝያዊ ምምሕዳር ዝተፈጸመ "ጥልመት" ምዃኑ ዘርኢ እዩ ብምባል ክኸስስ ከሎ ብርክት ዝበሉ ሰባት ናብ ካልኦት ክባጻሕ ገይሮምን ጥርጣራታት ክሓድሮም ገይሩን እዩ።
ይኹን'ምበር: ርኢይቶኦም ንኢትዮጵያ ቼክ ዝሃቡ ምንጪታት እቲ ግዝያዊ ምምሕዳር "እዚ ሰነድ እንፈልጦ ኣይኮነን ብምባል" ነጺጎምዎ።
ፕሬዝደንት እቲ ግዝያዊ ምምሕዳር ኣቶ ጌታቸው ረዳ ብወገኑ ሎሚ ኣማስዩ ብኤክስ ኣብ ዝሃቦ ሓበሬታ እዚ መዘራረቢ ኮይኑ ዝወዓለ ዛዕባ
ኣብ መረባ ማሕበራዊ ሚድያ ካብ ሙሉእ ማዓልቲ መዘራረቢ ኮይኑ ዝወዓለ ሰነድ "ምስ ጊዚያዊ ምምሕዳር ትግራይ ዘራኽብ ዋላ ሓንቲ ነገር የብሉን" ኢሉ።
እዚ ሰነድ ብመን ተዳዩ ብዘየገድስ ኣካል "እቲ መሬት ሸይጦም" ብዝብል ኣብ ልዕሊ ምምሕዳሩ ዘቕንዐ ወፍሪ'ዩ ዝመስል ብምባል "ብወገን ትግራይ ዝተፈረመ ሰነድ የለን" ክብል ነጺጉዎ።
እዚ ሰነድ ኣብቶም ንክልላት ትግራይን ኣምሓራን ዘሰሓሕቡ ዘለው ከባቢታት ዝለዓሉ ሕቶታት ወሰን ንምፍታሕ መረጻ ግዝያዊ ከባቢያዊ ምምሕዳር ከምዝካየድ የመልክት።
ኣብ መጀመርታ ወርሒ ነሓሰ እቲ ዝለዓል ምስሕሓብ ንምፍታሕ ዝተዋደደ ብሄራዊ ኮሚቴ ድሕሪ ዘካየዶ ኣኼባ እዞም ኣብቲ ሕጂ ቀሪቡ ዘሎ ሰነድ ዝተልዓሉ ሓሳባት ዝሓዘ ኣንፈት ከም ዝቐመጠ ዝሕብር መግለጺ ሂቡ ነይሩ። ኣብዚ ሕጂ እዋን ኣብ መንጎ እቲ ግዝያዊ ምምሕዳርን ፖለቲካዊ ውድብ ህወሓትን ኣፈላላይ ተፈጢሩ ብምህላው ክልቲኦም ወገናት ንሓድሕዶም ዝካሰሱሎም ጉዳያት ኣብ ማሕበራዊ ሚዲያ የዘራርቡ ምህላዎም ይፍለጥ።
-Fakkeessuu: Qaamoleen miidiyaa hawaasaatti fayyadamuun gochaalee goyyomsuu raawwatan asxaa, chaappaafii teessoo dhaabbilee beekamoo baay’inaan fayyadamu. Maqaafii asxaa dhaabbilee kunneenii fayyadamuun akkaawuntiiwwan miidiyaalee hawaasaa banuufii xalayaa sobaa fakkeessanii qopheessuunis beekamu. Fuulawwan yookiin akkaawuntiiwwan miidiyaalee hawaasaa sobaa akkasumas xalayaawwan fakkeeffamanii qophaa’aniin akka hin goyyomfamnes ofeeggannoo gochuun barbaachisaadha.
Gochaalee goyyomsuu miidiyaa hawaasaatti fayyadamuun raawwatamaniif akka hinsaaxilamne ofeeggannoo yaa taasifnu, hawaasa keenyas yaa hubachiisnu.
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion ? @Share_Home
Last updated 2 weeks, 5 days ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 6 months, 3 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 8 months, 3 weeks ago