Sumeya sultan

Description
ነጻ ሃሳብ! ነጻ ግጥም!!
ሃሳብ አስተያየት በ @Sumeyaabot አድርሱኝ
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 3 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 8 months ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month, 3 weeks ago

2 months, 2 weeks ago

"ልባችሁን አውሱኝ"
በሱመያ ሱልጣን
አንዳንድ ሰዎች ሰደቃ መስጠት በደማቸው ውስጥ ነው። ወላሂ ኖሮት አንዴ የሚለግስ አውቃለሁ። ብዙ ኖሮት ያልገራለትም አይቻለሁ። የአንዳንድ ሰው መስጠት ግን ይለያል። በ ኢፋዳ ማህበረሰብ 22የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮዎችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ገጠራማ ቦታዎችን በዚህ 2ወር ውስጥ ለማድረግ እንደመነሳታችን የብዙሃንን ልብ እያየሁ ስቀና ከረምኩ። ያላቸውን ደጋግመው ሰጥተው 1ብር የጨመሩልንን ተማሪዎች፣ ደጃቸው ሳያመላልሱ በ 100ሺዎች የለገሱ ሃብታሞች፣ የቲምነት እና የዱንያ አለመሙላት ያላጎደላቸው ምስኪን ነፍሶችን በ 10ሺዎች መሰብሰብ መቻል፣ ሙስሊም ያልሆኑ አካላትም የ ቴሌግራም ስቶሪዎቻችን እያዩ የሰጡትን እያየሁ ወላሂ ልቦቻቸውን ተመኘሁ😍😍በምን ስራ ነው አላህ ያን ልብ የሚሰጠው? አታውሱኝም?
ከዚህ አጅር መካፈል የሚፈልግ
@sumeyasu
@sumeyaabot
ላይ ያውሩኝ

2 months, 2 weeks ago

በጣም ጮክ ብዬ እያወራሁ እና እየሳቅኩ ነበር። እንደ 17 አመት ልጅ ቅዥቅዥ እያልኩ። "ሱምሊ እኮ ታድለሽ ሁሌ መሳቅ" እያሉኝ ነበር። እሷ የምትጠጣውን ቡና ቁጭ አድርጋ ሳብብብ አድርጋ ይዛኝ ወጣች።
"ሱም ደህና ነሽ?" ስትለኝ ነው "ከየት መጣ?" የማይባል እንባዬን ያዘራሁት። ብቻችንን ነበርን። በሳቄ መሃል ያየችውን ሃዘኔን ተወጣሁባት። በመሳቅ ውስጥ የደበቅኩትን ሃዘን በመንቀዥቀዤ ውስጥ የሸፈንኩትን ተስፋ መቁረጥ ትከሻዋ ላይ አረገብኩት። ከዛ "ሱምሊ እኮ ታድለሽ ሁሌ መሳቅ" የሚለውን እያስታወስኩ ፈገግግግግ።
የሳቅን ሁላ ደልቶን አይደለም። እኛን እያያችሁ ህይወት በናንተ ላይ ብቻ የዞረች አይምሰላችሁ
@sumeyasu
@sumeyaabot

2 months, 3 weeks ago

ያማረ ኺታም
የ እርሷማ ኺትማ ከብረት መዝጊያ
ከመልከ መልካም ከ አይን መርጊያ
እየተባለ
ከ አንዱ አንዱ ሲገፋ ከርሞ
               ለርሷ ሳይመጥን
በሃብት በ ዘር ሲታይ ሲመዘን
ከ ቀናት በ አንዱ ጌትየው ሲሻው
ከባሮቹ አንዱን ለሷ መረጠው
ከመልክ ያልሰጠው ከሃብትም እንዲያ
መጠሪያ የለው ከሙስሊም ወዲያ
አባት ቅር አለው ለ'ንደሱ ላለ
                 ብሌኑን ሊያጭ
እምቢ አይል ነገር አሸማጋዩ
              የ አለም በላጭ
እናት አቃታት ልቧን እምቢ አለው
እንዴት ለዚህ ሰው ልጇን ትዳረው?
ሙሽሪት ሰማች
የጠየቃት ሰው
መልክተኛውን አጥብቆ ይወዳል
ከአኺራ ውጪ
       ሃጃ የለውም ልቧ ያን ያውቃል
የተላከባት
  ከነፍሷ አልቃ ምትወዳቸው ሰው
ሳታመነታ "እሺ" ን መለሰች
            ሰው ያጥላላውን ለ አላህ ሰጥታው
ያላቀቻቸው ታላቁ ነብይ እርሷን መረቋት
ባትታደለም ያፈቀረችው መዝለቅን አብሯት
ከ እለታት ባንዱ ጀግና የልቧ ሰው
ገዝዋ ሄደና አፈር ዱንያን ተሰናበተው
ከነቢ ውጪ
ሁሉም ሰው ረሳ መሞት መኖሩን
እሳቸው ብቻ ልባቸው አወቅ
            ይህ ሰው መጉደሉን
ከፈን ከፍነው ሊሰገድበት እያዘጋጁት
እርሱ ከሳቸው እሳቸው ከርሱ
         መሆናቸውን መሰከሩለት
ምስኪን ጁለይቢብ ዱንያ ጤፉ
መመረጡ ነው በጌታው
              መንገድ ልቡ ማረፉ
@sumeyasu
@sumeyaabot

4 months, 4 weeks ago
የኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የYouTube ቻናል ላይ …

የኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የYouTube ቻናል ላይ እሁድ የምናስተላልፈውን የላይቭ ስርጭት ለማስተላለፍ ቻናሉ 1k ሰብስክራይበር ያስፈልገዋል በመሆኑም እኛ ኢፋድዮች የወደድነውን ለሰዎች ማካፈል ማይሰለቸን ነንና ቻናላችን ሰብስክራይብ እንዲደረግ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበርክት።

ለምናቃቸው በሙሉ ሼር እናድርግ እስከ ጁምአ ማታ ዘመቻ እናድርግ።

ከላይ በተቀመጠው QR code ስካን በማድረግ ወደ ኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የማህበራዊ ሚዲያ ድህረገጾችን መቀላቀል ይችላሉ ።

ይህ የyoutube ቻናላችን ሊንክ ነው ።???

https://youtube.com/@ifadaislamicorg?si=WQ--SeP_VHVnsegm

6 months, 3 weeks ago

ቂያማ እና አየር መንገድ
(ሱመያ ሱልጣን)
እንደ አየር መንገድ ትልቅ የቂያማ ማስታወሻ መኖሩን እጠራጠራለሁ። መያዝ የሚችለውን ብቻ ይዞ መሄዱ፣ ከወዳጅ ዘመድ እየተላቀሱ እና እየተቃቀፉ መለያየቱ ፣የያዝነውን በሚመለከተው አካል ማስመዘኑ፣ የ አየር መንገዱን ፕሮሰስ አልፎ እስከ ፕሌኑ መገኛ መጓዙ እና ለመዳረሻ መሮጡ ሁሉም ቂያማን የማስታወስ ሃይል አለው። ከዛ ደግሞ የናፈቁን ወዳጆቻችንን ስናገኝ ያለው ጀነትን ይመስለኛል። የሚጠብቀንን የተደበቅነውን መርዶ መስማቱ ደግሞ ጀሃነምን ያስታውሰኛል። እነዛ የናፈቅናቸውና የናፈቁንን የምናገኝበት የጌትዬን ጀናህ አላህ ይወፍቀን?
@sumeyasu
@sumeyaabot

7 months, 2 weeks ago
"ፍትህ"

"ፍትህ"
(ሱመያ ሱልጣን)
ታናሽ እህት አለችኝ ስሟን በስሜ አስከትዬ እራሴን "ሱምሊና" ብዬ የምጠራባት። ሊንዬ ሲደክማት ሁላ አዝናለሁ! በጣምምምም ብዙ አመታትን "ጠበቃ" መሆን እመኝ የነበረው የመደፈር ዜናዎችን እኔም ቤት ደርሶ እስኪገድለኝ ድረስ "አዑዙ ቢላህ፣ አስተግፊሩላህ!" እያልኩ ቲቪዬን ላለማጥፋት እና ፍትህ ለማምጣት ነበር። እያንዳንዱ የመደፈር ዜናዎችን ሳይ የማለቅሰው "ሊንዬ ብትሆንስ" እያልኩ ነው። ጓደኞቼ " የሊናን ጦስ" ይላሉ። እኛ ቤት የማይደርስ ይመስል!
ሴት ሆነን ስንወለድ ጀምሮ ከሞት እኩል ተሸክመነው የምንወለደው ጉዳችን፣ ሰቀቀናችን ነው። የማዝነው እኔ እራሴን እንኳን መከላከል በማልችልበት ሁኔታ ታናሽ እህት እንዳለኝ ማሰብ ነው። ስለ 1ሄቨን አይደለም ነገሩ ስለ እያንዳንዱ ቀናችን ነው ፍትህ የምንለምነው፣ በ አባያ እና ጅልባባችንም ውስጥ ለማይቀርልን ትንኮሳ ነው፣ የመደፈራችን መልስ "ምን ለብሳ ነበር?" ስለሆነብን ነው፣ ፍትህ የምንለው እያንዳንዱ ቀናችን ላይ "ማነሽ ሰሚራ፣አታወሪም እንዴ? አንቺን እኮ ነው!" እየተባልን እየተጎተትንም ወጥተን ስለምንገባው ነው፣ በ እያንዳንዱ ቀን ሶሻል ሚዲያ ላይ ፎቶ ኖረን አልኖረን፣ ፖስት አደረግን አላደረግን በውስጥ ለሚደርሱን የጾታዊ ንግግሮች እና ዝም ስንል ለሚደርሱብን ስድቦች ነው፣ "ፍትህ" እያልን የምናለቅሰው ስለሞተችው ሄቨን ብቻ አይደለም ስለምንሞተው ብዙዙዙ ሄቨኖች ነው። እኔ "ፍትህ" ን ከመንግስትም ሆነ ከሰው ፍጥረት አልጠብቅም። ፍትህ ያለው በጌታዬ እጅ ነው "አልጀባር" በጀባርነቱ ፍትህ እንዲሰጠን ነው ዱዓዬ። ይኔ ልመና "አልሰታር" ሁሉንንንንንምምም ሴት ከ አረመኔዎች እንዲሰትረን ብቻ ነው። ፍትህ የ አላህ ነው!!!!!
ተቃጠልን
@sumeyasu
@sumeyaabot

8 months ago

ሰሪውን ነው ማመን
(በሱመያ ሱልጣን)
የ ልጅ እጄን በ ወፍራም መዳፉ ጥብቅ አድርጎ ይዞኝ መንገድ እየሄድን የምናውቃትን ከኔ በ 2አመት ከፍ የምትልን ልጅ ስም ጠርቼ 2ጥርስ እንዳወለቀች ነገርኩት። ወደኔ ዞር ብሎ ፈገግ ካለ በኋላ "አንቺም አሁን 6አመትሽ አይደል ልክ 7 ሲሆንሽ ታወልቂያለሽ" አለኝ። አስታውሳለሁ የጥርሶቼን ጥንካሬ ለማስረዳት የዘባረቅኩትን ብዛት። "የኔ ድርድር ያሉ የተጣበቁ ጥርሶቼ ሊወጡ?"
ደጋግሜ ስሙን እየጠራሁ" እየኝማ እየኝማ ጥርሴ እኮ አልተነቃነቀም ሁላ የኔ እኮ ጠንካራ ነው" ለፈልፋለሁ። "እሺ" ብቻ አለኝ። ከ አመት በኋላ ጥርሴ ተነቀለ። 1ብቻ አይደለም እየቆየ ብዙ ነቀልኩ። ከዛ ደግሞ ተመልሶ በቀለ።
ካደግኩም በኋላ "በጭራሽ እኔ ላይ አይሆንም" ያልኩት ሲሆን በሌላ ሲተካ አየሁና ህይወት ገባችኝ።
ዱንያ ላይ በሰሪው እንጂ በስራው መተማመን ያከስራል።
@sumeyasu
@sumeyaabot

8 months, 3 weeks ago

አሹራዕ
(ሱመያ ሱልጣን)
"አለቀልን! በቃ ተያዝን" ብለው ነበር የሙሳ ህዝቦች ከፊታቸው ባህር፣ ከኋላቸው ፊርዓውን ከነ ሰራዊቱ እየደረሰባቸው መሆኑን ሲያዩ።
"በበትር ባህርን መክፈል?" የልጅ ጨዋታ እስኪመስል የማይታመን!
ሁሉን ቻይ ጌታ ግን ያንን ያስቻለው በዛሬው እለት ነበር። ጌታችንን በጾመ አካላችን እጆቻችንን ከፍ አድርገን "የማይቻል" የመሰለንን የኛን የሃጃ ባህር "በ ሰጪ እጆችህ ክፈልልን።" እንለዋለን። አላህዬ እኮ ይችላል። ወላሂ ይችላል።
@sumeyasu
@sumeyaabot

8 months, 4 weeks ago

የምንፈልገውን
(ሱመያ ሱልጣን)
ህይወት ላይ ስላጋጠማት ነገር እያለቀሰች ቲክቶክ ቪዲዮ የለቀቀችውን አየሁት እና አሳዘነችኝ። የተሰጡትን አስተያየቶች ሳነብ ካሳቀኝ ውስጥ አንዱ
"በከባድ ሁኔታ ውስጥ እያለፍሽ እንደሆነ ይገባኛል። ካላስቸገርኩሽ የተቀባሽውን ሊፕስቲክ ስም ትነግሪኛለሽ?" የሚል ነው።
ያው ችግራችንን ለሚገባው ሰው ተገቢው ቦታ ላይ እንንገር ለማለት ነው?
@sumeyasu
@sumeyaabot

10 months, 2 weeks ago

ፍቅሬን በ አደባባይ
የልቤ ሰው ናት። ሳውቃት የኖርኩበት ሱመያነት በሷው ልብ እኔው ላይ ገነንብኝ። "እንዲህ ደስ እላለሁ እንዴ?" አልኩ። ወደደችኝ። አብሮ በተቀማመጠው ሰው ጸባይ አይደል ማንነት የሚሰራው? ገነባችኝ ። ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እና ያለምንም ምላሽ ፍቅር እንዳለ እኔነት በሷ ሲወደድ መሰከርኩ። ትለያለች!! ጥፋት እና መጥፎ ጎኔን አይታለች። ሰተረችልኝ። ጥሩዬን አየችና ደግሞ አውጥታ ዘርታ የሰው መውደድ በዙሪያዬ ሲበቅል ተመለከትኩ። ዛሬ "ሱመያ" ን ስታስቡ የሚመጣላችሁ መልካም ጸባይ ሃያት በምትባል እህት ተለፍቶበታል። መልካም ያልሆነ ትዝታ ከተጫረባችሁ ሃያት ለመለወጥ እየጣረች ያለችበት ባህሪ ነው ማለት ነው። በርግጥ ዛሬ ላይ ብዙ መልካም ወዳጆች አሉኝ። ግን እርሷ በሰራችው ማንነት ነው የተወዳጀሁት እና ማንም ከቦታዋ አያንቀሳቅሳትም። በድብቅ ለሆነችልኝ መልካምነት ዛሬ በ አደባባይ ፍቅሬን እና ምስጋናዬን መግለጽ ስለፈለግኩ ነው። ይህች ልቤ አብዝታ ትወድሻለች እህቴ!
እናንተም ተመሰጋገኑ
@sumeyasu
@sumeyaabot

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 3 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 8 months ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month, 3 weeks ago