Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ሐመረ ኖህ በገና ክረር መስንቆ መገኛ💒

Description
📌 የግጥሞቹን ምንጭ ለማወቅ @Where_from_bot

📌 አስተያየት እና ግጥም ለመላክ ብቻ ይህን ይጠቀሙ ! 👉 @My_Comentbot

🙎Creater.


©All rights reserved
July/25 /2017
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago

1 year ago

#ቂም_በቀል!!

🌹ወዳጄ አንዳንድ ሰው ለደረሰበት እያንዳንዷ ችግር ለእያንዳንዷ መጥፎ ነገር በልቦናው ቂምን ይቋጥራል።ያ ደግሞ ለህሊና ሰላም አይሰጥም ባገኛት አጋጣሚ ሁሉ ስለዛ ሰው ስለሚያብሰለስል ህሊናው ጤነኛነቱን እያጣ ይሄዳል!!

ወዳጄ ውኃ የቋጠረ ጣሪያ ላይ የሚገኝ ሸራ/ላስቲክ ነገርን እንመልከት ውኃው ካቅሙ በላይ ሲሞላበት ባገኛት ትንሽ አጋጣሚ የያዘውን ውኃ ይዘረግፈዋል።በዛም ሰዓት አጠገቡ ያለ ሰው የዛ መፈጠር ተካፋይ ወይም በስባሽ ይሆናል።

🌹ወዳጄ ቂምም እንደዛው ነው አይምሮዓችን ሲያብላላው ይቆይና ካቅሙ በላይ ከሆነ ያገኘውን ከሙጉዳት አይመለስም!!!

🌹ወዳጄ ቂም የማይዙ ገራሚ ልብ ያላቸው አንዳንድ ሰዎች አሉ ግን ንግግራቸው መጥፎ የሆነ ፤ ቃላታቸው የሚሰብር ከዛም ከደቂቃዎች በኋላ የተናገሩትን እረስተው እነርሱ ጤነኛ ይሆናሉ ያንን መጥፎ ቃል ተሸካሚው አካል ግን ውስጡ የማይድን ጠባስ ሊፈጠርበት ይችላል ሆኖም የነዛን ሰው ባህሪ ቀድመን ከተረዳን ከነርሱ ጋር ማንኛውንም የቃላት ጦርነት አለማድረግ።

ወዳጄ የሚናገሯቸውን ነገሮች ሁሉ በስሜት እንደሚያወሩት መረዳት እና ከነርሱ ሸሸት በማለት ቀዝቀዝ እስኪሉ በመጠበቅ መግባባት እንዳትችሉ ያረጋችሁን ጉዳይ በሰከነ አይምሮ ማስረዳት ነው ትልቁ መፍትሔ።

ሰናየ ቀን ይሁንልን
አሜን!!!🙏

1 year ago

ገድል ያለመለመው የወንጌል ተክል
የጊዮርጊስ ስሙ ጥዑም እምአስካል
አይደርቅ አይጠወልግ ሁሌም ያብባል::
ሹመት ሽልማቱን ክብሩን ሁሉን ትቶ
ታስሮ ተገረፈ ለአምላኩ ክብር ቀንቶ:;
ኧረ እንደምን ቻለው ያን ሁሉ መከራ
ተቆልቶ ተፈጭቶ እንደእኅል ሲዘራ;;
እኔስ ይጨንቀኛል ገድሉን ሳስበው
ሰባት ዓመት ገድል እንደምን እፁብ ነው
ዛሬስ አንዳንዱ ሰው እጅግ ያሳዝናል
ገና ምንም ሳይሆን ክሩን ይበጥሳል
ሰው ጌታዉን ሲክድ ለሥጋ እያዘነ
ጊዮርጊስ ለአምላኩ እስክሞት ታመነ
አክሊልን የሚያሰጥ ይኸው ስለሆነ!!!
ሞቱ ገድሉ ለጊዩርጊስ ክብሩ ሆነ
ማቴ 10:39,ራዕ 2:10

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን::

1 year ago
1 year ago

ለምን በገና በግራ እጅ ይደረደራል**

መልስ 👇**

በገና የሚደረደረው በግራ እጅ ጣቶች ነው። በተለያዩ ምክንያቶች የግራ እጅ የሌለው፣ወይም የግራ እጁ ጣቶች የጎደሉበት ሰው ግን በቀኝ እጁ ጣቶች ይደረድራል። ትውፊቱ ግን የሚያዘው በግራ እጅ ጣቶች እንዲደረደር ነው።

•••
በሳይንሱ የግራ እጃችንን ስሜት ጣቢ የሆነው ቀኙ የአእምሯችን ክፍል ነው። ሳይንሱ ይህን የአእምሮ ክፍል (ኢሞሽናል ማይንድ)ይለዋል። እንደ ሳይንሱ ከሆነ ይህን የአእምሮ ክፍል እንደ ሙዚቃ፣ ፍቅር ...ወዘተ ያሉትን ጉዳዮች የሚያስተዳድር ነው።በዚህ ምክንያት በግራ እጃችን የምንጫወታቸው የዜማ መሳሪያዎች በርካታ ሆኑ ይለናል።እውነት ነው በርግጥ ሌሎች በርካታ የዜማ መሳሪያዎችንም የሚጫወቱት በግራ እጅ ነው።

•••
በቤተ ክርስቲያናችን በኩል ግን አባቶቻችን ለምን እንዲህ አንዳደረጉ ተጨማሪ ጥናት የሚያስፈልገው ነው። ትፊቱን መጠበቅና ማስተላለፍ ግን ተገቢ ነው። በድርደራ ወቅት የቀኝ እጅ ደግሞ በደረታችን በኩል የሚውለውን በፍቅረ ቢጽ በተመሰለው የግራ ምሰሶን ወደ ራስ ደግፎ በመያዝ የግራ እጃችን ከተጽኖ ነጻ ሆኖ እንዲደረድር ያግዘዋል።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ትቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ልማት ተቋማት አስተዳደር የአቡነ ጎርጎሪዎስ ትምህርት ሥልጠና ማእከል በ፳፻፲፩ ዓ.ም ካሳተመው “የበገና መማሪያ መጽሐፍ” የተወሰደ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

1 year ago

#አሻግረን_እንበል_ወዳጄ

🌹#ወዳጄ_ሆይ! ከታገሥህ ሁሉም ያልፋል ፣ በሕይወትህ ከወሰንህ ግን አለማለፍ ዘላለማዊ ይሆናል።ሞት ወዳንተ መምጣቱ አይቀርምና አንተ ወደ ሞት አትሂድ።

🌹ወደዚህ ዓለም ተመልሰህ አትመጣምና ሕይወትህን ተንከባከባት። ብረት ብታገላብጥ፣ ድንጋይ ብታንከባልል የቆምከው ግን በአፍንጫ እስትንፋስ ነውና በማስተዋልና በጥንቃቄ ኑር። አለመሳካት ማለት አለመኖር ማለት አይደለም።ራእይ አልባ ሰው ካርታውን የጣለ መንገደኛ ነው።ውጤቱም ተንከራታች መሆን ነው።

🌹#ወዳጄ_ሆይ! ሰዎች የዘሩትን ሲያጭዱ ስታይ አንተም ዛሬ እየዘራህ ነገ ደግሞ የምታጭድ መሆኑን አስብ። የዕድሜ ጀምበር የሚጠልቀው አንዱ ባንዱ ሲስቅ ነው። ዕድልን ዕድል ተሰጥቷቸው ካመለጣቸው ሰዎች ተምረሃት አክብረህ ያዛት።የወደደም ይጠላል፣ ያከበረም ያዋርዳል። ሳትዋዥቅ የምትኖር ግን እውነት ብቻ ናት።

🌹#ወዳጄ_ሆይ! በየዋህነቴ ተጎዳሁ ብለህ ጨካኝ አትሁን፣ ነገር ግን ብልህ ሁን። የደስታ ጊዜ ረጅም ቢሆን አጭር፣ የመከራ ጊዜ አጭር ቢሆንም ረጅም ነው።ጓደኛን አለማመን ሁልጊዜ በሥቃይ ውስጥ መኖር ነው።የምትሰራው የሚጠፋህ ራስህን ማድነቅ ስትጀምር ነው።መልካም ሰውን በውድ ገዝተን በርካሽ መሸጣችን ትልቁ ኪሣራችን ነው።

🌹#ወዳጄ_ሆይ! ሰው ስልክ ሲያወራ ሣንቲሜ ቆጠረ እንጂ ዕድሜዬ ቆጠረ አይልምና ከዕድሜው ይልቅ ለሣንቲም ዋጋ እንደ ሰጠ ያሳያል።በሽተኛ በሌለበት እንፈውሳለን የሚሉ፣ በሽተኛ ሲመጣ ግን የሚጠፉ ናቸው።

🌹ወዳጄ ሆይ! ፈውስ በፕሮግራም ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ማስታወቂያ የበዛበት አገልግሎት ከእውነት ይልቅ የዝና ፍቅር ያለበት ነው። ነቢያት ስላልመጣው ዘመን ያውቁ ነበር ፤ እኛ የምንኖርበት ዘመን ተሰውሮብናል። ሐዋርያት ሄደው ይሰብኩ ነበር ፣ እኛ ግን መጥታችሁ ተሰበኩ እንላለን።#ሰማዕታት_ለክርስቶስ ፍቅር ሞቱ ፣ እኛ ግን ለጥቅማችን እንገድላለን።

🌹ወዳጄ ሆይ! ጻድቃን ጣዕመ ዓለምን ንቀው መነኑ ፣ እኛ ግን ዓለም መራራ ሆናብንም ገና እንፈልጋታለን።ቅዱሳን ከሕግ አልፈው በትሩፋት ኖሩ ፣ እኛ ግን የታዘዝነውን መፈጸም ተስኖናል።ደናግል መነኮሳት የክርስቶስ ሙሽሮች ሆኑ ፣ እኛ ግን በአሚናችን/በአንድ መጽናት አቅቶናል።

🌹ወዳጄ ሆይ! ሊቃውንት አህያ የማትሸከመውን መጽሐፍ በቃላቸው አጠኑ ፣ እኛ ግን በአንድ ጥቅስ ያዙኝ ልቀቁኝ እንላለን።አይ የኛ ነገር መች ያበቃ ይሆን።አረ ምንድነው አንብበህ ዝም ማለት Share አድርግ እንጂ ስንቱ ይሄንን ያላገኘ አለ መሰለህ።

#ጌታ_ሆይ_ከዘመን_ማዕበል_እባክህ_አሻግረን
አሜን 🙏

1 year ago
1 year, 1 month ago

++ ንጉሥ በአህያ ላይ ++
(ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ)

"አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት። የዚህች በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው። በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣ ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት።
ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት።

ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ።

ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።

"የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት?

ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም።

እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል። መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሆሳዕና 2010
ናይሮቢ ኬንያ

2 years, 2 months ago

እንደምን ቆያቹ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች ።

Can you help me out by signing this petition?
https://chng.it/5kLFjHmm

የሞዐ ተዋሕዶ የፊርማ ማሰባሰቢያ መግቢያው ነው
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን ይቆየን ።

Change.org

Sign the Petition

Prevent Cultural and Religious Based Genocide of Ethiopian Orthodox Christians.

እንደምን ቆያቹ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች ።
2 years, 2 months ago
እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ወርኀዊ …

እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ወርኀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ጥንታዊውና አንጋፋው የ125 ዓመት እድሜ ባለጸጋው በሆነው በመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የፊታችን አርብ የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ አዘጋጅተናል፡፡

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አርዑተ ወንጌል በሚሸከሙ የመንፈስ ገበሬዎቹ መንፈሳዊ ዘሩን ይዘራልና እንዳትቀሩ ! ዝማሬን በሚያንቆረቁሩ አገልጋዮቹ የተጠሙ ነፍሳትን ያጠጣልና ተገኝታችሁ የንስሐ ፍሬን ታፈሩ ዘንድ ተጋብዛችኋል!!!

እርስዎም ቀደም ብለው ተገኝተው አጽናኝ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ይማሩ ፡፡

የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ደብረ መንክራት ሥዕል ቤት ኪዳነ ምህረት ገዳም እና የመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የአከባቢው ጎልማሶች እና ወጣቶች ማህበር

3 years, 11 months ago

#እሱ_ነው_እሱ

#ጥንት_ያለ የነበረ
#ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ
#ምድርን_በኃይሉ የፈጠረ
ዘመናትን የለካ የቀመረ
ነቢያትን ያናገረ
#ኃያል_ሱባኤ ያስቀጠረ
#ከይስሐቅ_ጋር የተሰዋ
#እስራኤልን ያከበረ
ከዮናስ ጋር በዓሣ ሆድ
ከዮሴፍ ጋር የታሰረ
እሱ ነው እሱ ለሙሴ
ሕጉን ትእዛዙን ያስተማረ
በተረዳ ሦስትነቱ
#በስም_በግብሩ በአካላቱ
#የሚመለክ_በአንድነቱ
#በሕልውናው በመለኮቱ
በአገዛዙ በጌትነቱ
እሱ ነው እሱ የጥንት የጠዋቱ
እንዘ አሐዱ ሠለስቱ
በእጹብ ብቻ ይወሰናል
ቀዳማዊ ልደቱ
#አይመረመርም_ረቂቅ ነው
#ዳግማዊ ሰውነቱ
ከወላዲተ - ቃል እናቱ
ግሩም ድንቅ ነው ጥበቡ
#ወሰን የለውም ቸርነቱ
#ወልደ አብ #ወልደ ማርያም
የሰማዩ የመሬቱ
እሱ ነው እሱ #አልፋና_ዖሜጋ
#የሚታዘዙለት መላዕክቱ
#የሚታሰብ በቀዳሚ በሳምንቱ
በዘወረደ በቅዳሴው በሰዓታቱ
እሱ ነው እሱ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ
#ይጠብቀን በምህረቱ
#ስለ_እናቱም_ከመዓቱ🙏

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago