መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

Description
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
.
.
.
.
.
.
.
.
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Mgetem_Bot
@Mgetem_group
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago

hace 2 meses, 2 semanas
hace 4 meses, 3 semanas

የፈጣሪ_ልሳን
እጆቼን ዘርግቼ........
ልጸልይ ልማልድ ከደጅኽ ተገኘኹ
አንጋጥጬ ሽቅብ በሐሳቤ ዋኘኹ
ተንበርክኬ ለምሕላ በግንባሬ ተደፍቼ
ቀና ማለት ተዘነጋኝ የቃል ጸሎት ረስቼ

ያ'ንደበትኸ ልሳን ከየት ተሠወረ?
ቃል ከምላሴ ላይ እንደምን ታወረ?
ዝም....
ዝም ዝም....... !
እንደው ዝም! ዝምታዬ ቀረ
ሰምተኸኛል አንተ
በዝምታ ልሳን ጸሎቴ ሰመረ።

ገጣሚ #ተስፋሁን_ከበደ

@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem

hace 5 meses

ቅኔና ውዳሴሽ 21
@Mgetem

ቅኔና ውዳሴሽ ምግብ መጠጣችን
ማር የሆነው ስምሽ
የመንገድ ስንቃችን
ፍቅርሽ እንደ ዕሳት__ ይነዳል ውስጣችን
ንኢ ንኢ ስንል *ባርኪን እናታችን።

ልቡ ያዘነውን* አዳምን ሊያፅናና
ትካዜውን ሊቀብር__የሞቱን ጎዳና
ማደሪያው አድርጎሽ__የሰማዩ መና
አዳነው ክርስቶስ__ ይድረሰው ምስጋና
ከወጣበት ገነት___ ተመልሷልና።

ካንቺ ተወለደ__ ያለ ወንድ ዘር
የሔዋን እርግማን__ወድቆ ሊሰበር
ያሳታት ዲያቢሎስ__ሲዖል ሊታሰር
ሥጋ ለብሶ ታየ__ ወልደ እግዚአብሔር።

ሰው የሆነና በኛ ያደረ ቃል
ኢየሱስ ክርስቶስ
ቅዱስ አማኑኤል
መሆኑን ነገረን__ነበዩ ኢሳይያስ
አየነው ተጽፎ__ በመጽሐፍ ቅዱስ።

ሰው ሆይ ደስ ይበልህ__ተነስ ለምስጋና
እግዚአብሔር  ዓለሙን__እንዲሁ ወዷልና
በአንድ ልጁ እንድናምን
ልዑል ክንዱን
ሰደደልን።

የነበረው የሚኖረው__የማያልፈው ለዘለአለም
ከላይ ወርዶ  ሰጠን ሰላም
በሥራው ሁሉ
አልተለየም
ወልደ እግዚአብሔር__ ወልደ ማርያም።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን
በበደልነው
እንዳይቀጣን
ለንሰሀ ዕድሜን ይስጠን
በኪዳንሽ
ተማፀንን።

የእግዚአብሔር ቃል መለኮት
የለበትም
ሦስትነት
አንድ ብቻ__ነው እውነት
የሥላሴ__ቸርነት።

እንደ አበው__ ባንበቃ
ስምሽ ሆኖን__ ዋስ ጠበቃ
ደስታችን ሆኖ__ሲቃ
ልመናችን ሰምሮ ባንቺ
አማለደሽን
ሳትሰለቺ።

ተሰበሰብን ልንጠራሸ
ማርየም ሆይ
ቆምን ደጅሽ
የዘለአለም ዓንባችን ነሽ
ዕርስታችን
የወረስንሽ።

እመቤታችን ሆይ የቅዱስ ኤፍሬምን በረከት አሳድሪብን
ሀገራችንን ቅድስት ኢትዮጵያን ሰላም አድርጊልን
ልመናችንን አሳርጊልን።

✒️ ከእህተ ማርያ
__
___
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot

hace 5 meses

ቅኔና ውዳሴሽ 21
@Mgetem

ቅኔና ውዳሴሽ ምግብ መጠጣችን
ማር የሆነው ስምሽ
የመንገድ ስንቃችን
ፍቅርሽ እንደ ዕሳት__ ይነዳል ውስጣችን
ንኢ ንኢ ስንል *ባርኪን እናታችን።

ልቡ ያዘነውን* አዳምን ሊያፅናና
ትካዜውን ሊቀብር__የሞቱን ጎዳና
ማደሪያው አድርጎሽ__የሰማዩ መና
አዳነው ክርስቶስ__ ይድረሰው ምስጋና
ከወጣበት ገነት___ ተመልሷልና።

ካንቺ ተወለደ__ ያለ ወንድ ዘር
የሔዋን እርግማን__ወድቆ ሊሰበር
ያሳታት ዲያቢሎስ__ሲዖል ሊታሰር
ሥጋ ለብሶ ታየ__ ወልደ እግዚአብሔር።

ሰው የሆነና በኛ ያደረ ቃል
ኢየሱስ ክርስቶስ
ቅዱስ አማኑኤል
መሆኑን ነገረን__ነበዩ ኢሳይያስ
አየነው ተጽፎ__ በመጽሐፍ ቅዱስ።

ሰው ሆይ ደስ ይበልህ__ተነስ ለምስጋና
እግዚአብሔር  ዓለሙን__እንዲሁ ወዷልና
በአንድ ልጁ እንድናምን
ልዑል ክንዱን
ሰደደልን።

የነበረው የሚኖረው__የማያልፈው ለዘለአለም
ከላይ ወርዶ  ሰጠን ሰላም
በሥራው ሁሉ
አልተለየም
ወልደ እግዚአብሔር__ ወልደ ማርያም።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን
በበደልነው
እንዳይቀጣን
ለንሰሀ ዕድሜን ይስጠን
በኪዳንሽ
ተማፀንን።

የእግዚአብሔር ቃል መለኮት
የለበትም
ሦስትነት
አንድ ብቻ__ነው እውነት
የሥላሴ__ቸርነት።

እንደ አበው__ ባንበቃ
ስምሽ ሆኖን__ ዋስ ጠበቃ
ደስታችን ሆኖ__ሲቃ
ልመናችን ሰምሮ ባንቺ
አማለደሽን
ሳትሰለቺ።

ተሰበሰብን ልንጠራሸ
ማርየም ሆይ
ቆምን ደጅሽ
የዘለአለም ዓንባችን ነሽ
ዕርስታችን
የወረስንሽ።

እመቤታችን ሆይ የቅዱስ ኤፍሬምን በረከት አሳድሪብን
ሀገራችንን ቅድስት ኢትዮጵያን ሰላም አድርጊልን
ልመናችንን አሳርጊልን።

✒️ ከእህተ ማርያ
__
___
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot

hace 5 meses

ገብርኤል
@Mgetem

የንጉስ ጭካኔ ፥ ክንዱ ቢበረታ፤
ለጣዖት ሳንሰግድ፥ እኛ ሳንረታ፡፡
የምናምነው አምላክ፥ ሊያድነን ወደደ፤
ገብርኤል መጣና፥ እሳቱ በረደ፡፡

ፍላፃና ሠይፉን፥ አጠፈው መላኩ፤
ሰላም ይዞ መጣ፥ ባለም ለታወኩ፡፡
አትጠራጠሩ፥ ምልጃው ያስምረናል፤
የሚነደው እሳት፥ ሳይነካን ወተናል፡፡

የሰልስቱ ደቂቅ፥ የእጠሉጣ ብርታት፤
የድንግል አብሳሪ፥ የቂርቆስ ረዳት፡፡
በሚመጣው አለም፥ እንዳይበላኝ እሳት፤
አማልደኝ ከጌታ፥ ነፍሴን እንዲምራት፡፡

የነገርኩህ ሁሉ፥ በቀኑ ደረሰ ፤
በዘብር ገብርኤል፥ እንባዬ ታበሰ፡፡
ና ልጄ ስትለኝ፥ አልልህም እንቢ፤
ስለቴን ተቀበል፥ አባቴ ቁልቢ፡፡

የልቤን ነግሬህ፥ የቁልቢው ገብርኤል፤
ሳትረሳ ፈፀምከው፥ ስለቴን ተቀበል፡፡
ለንግስ እንመጣለን፥ አንተ አትረሳምና፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ አድርሰን በደህና፡፡
+++++++

እንኳን ለሃያሉ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!
________________________
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot

hace 5 meses, 1 semana

እንኳን ለዚህ ቀን አበቃቹ
@Mgetem

እንኳን ለዚህ ቀን አበቃቹ/3/
በእግዚአብሔር ቤት መረቅናቹ።
?‍??‍??‍??‍??‍??‍??‍??‍??‍?

አዝ
የድካም ውጤት ነው የመስቀሉ ፍቅር
እጅግ የሚያተጋ ለተሻለው ነገር
እሾህ ደፍቶ ጌታ ዘውዱን ጭኖብናል
የንጉስ ልጆች ነን ማን ይቃወመናል።

አዝ
ለፍተን ካሳረፍከን ሰርተን ከባረከን
እኛም ለአምላካችን የምንለው አለን
ቀልጧል እንደ ቅባት ፍቅርክ በውስጣችን
የማይታጠብ ነው አንተነህ ወዛችን

አዝ
መዳፍህ ሲያርፍብን እንለወጣለን
ለውርደት ሲያስቡን ለክብር እንሆናለን
ገና ነው ፍፃሜው ገና ነው አጽናፉ
እንነበባለን ሲገለጥ መፅሐፉ

አዝ
በለቅሶ የሚዘሩ በደስታ ያጭዳሉ
ትንሽ ሆነው ወጥተው እጅግ ይበዛሉ
የተከፈተ በር ስለተሰጣቹ
በማይሞተው አምላክ ኩሩ በአምላካቹ።

?‍?☀️?‍??‍??‍??‍?
ለ2016 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላቹ እንኳን እግዚአብሔር አምላክ ለዚህ ቀን አበቃቹ እንላለን!!!
?‍?☀️?‍??‍??‍??‍? __
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago