አርማጌዶን

Description
መረጃ አቅራቢ ድርጅት



. ታሪክ እና ወጎች

. የ መፅሀፍት ጥቆማ እና ቅንጭብጭብ
Advertising
We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 5 days, 7 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 month, 3 weeks ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 2 months ago

9 months ago

የሚገባንን የቱሪዝም ጥቅም የሚያሳጣ ከሆነ፣ መጪው ትውልድ የአዲስ አበባ ዕምብርት የሆነችውን ፒያሳ መነሻ ለማየት አዳጋች  ይሆንበታል፡፡

ሌላው በአብዛኛው በሌሎች ሚዲያዎች እንደተባለው ፒያሳን እንደ አዲስ የመገንባትና በተጓዳኝ የሚከናወነው የኮሪደር ልማት ብዙዎችን ላልታሰበ ችግር የዳረገ፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎች ከሥራ በጊዜያዊነት ያፈናቀለ፣ ዜጎች ለፈረሱባቸው ንብረቶች ተገቢውን ካሳ ያላገኙበትና ለመላው ከተማም አዲስ ክስተት የሆነ ተግባር ነው፡፡ ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ በተለይ አሁን ካለው የወጣት ሥራ አጥነት እንዳለ ሆኖ፣ ያሉትን ጥቂት ክፍት የሥራ ቦታዎችን ፈልጎና ተወዳድሮ ለማግኘት በተለይ ወጣቶች ይጠቀሙባቸው የነበሩት የአራት ኪሎ መሰል የሥራ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ነበሩ፡፡ እንዲህ ዓይነት ቦታዎች ለወትሮ ሁሌም በሰዎች ከሚጨናነቁባቸው መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ሥፍራዎች በአብዛኛው አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በብዛት ይታዩባቸዋል፡፡ ከዓመት ዓመት ወጣቶች የሚመላለሱበት በተለይ የአራት ኪሎው የማስታወቂያ ሰሌዳ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ሰጪ ለሆኑ መንግሥታዊም ሆኑ መንግሥታዊ  ላልሆኑ ተቋማት  አሠሪና ሠራተኛ የሚያገናኝ ድልድይ ነበር፡፡ እኔን ጨምሮ ብዙዎች ከእንጀራ ጋር ያገናኘ፣ ከፍ ያለ ደመወዝ ከሚያስገኙ ሥራዎች ጀምሮ በተዋረድ አነስተኛ ክፍያ እስከሚያስገኙ ሥራዎች ድረስ ጠቃሚ ነበረ፡፡ በከተማው ጉልህ ድርሻ የነበረውና ለአብዛኛው ሥራ ፈላጊ ‹‹የተስፋ ሰሌዳ›› የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በነበር ቀርቷል፡፡ በእርግጥ ጊዜው የሥራ ማስታወቂያ በሰሌዳ ብቻ የሚፈለግበት ባይሆንም፣ ሁሉም ዜጋ ዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ሥራ ማግኘት ያዳግተዋል፡፡ ቀጣሪዎች ሁሉንም ሥራ በዲጂታል ሚዲያ የማይለቁ በመሆናቸው አራት ኪሎ ካለውና ከፈረሰው ሰሌዳ በቅርብ ርቀት የሚገኙት የትምህርት ሚኒስቴርና ፓርላማው ትኩረት በመስጠት፣ ምትክ ቦታ በማዘጋጀት  ወጣቱ ዕድሉን የሚሞክርበት ምቹ ሁኔታ ሊያመቻቹለት ይገባል፡፡

ሌላው በተለይ ካለፉት አሥር ዓመታት ወዲህ በእጅጉን እየተቀዘቀዘ የመጣው የአገሪቱ የኅትመት ኢንዱስትሪ ነው፡፡ ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች መነሳት ቢችሉም፣ በዋነኛነት ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ ዴሞክራሲያዊ መብት በአግባቡ አለመከበር፣ በፍጥነት እያደገ ያለው የዲጂታል ቴክኖሎጂና በእጅጉ እየናረ ያለው የወረቀትና የኅትመት ዋጋ ይጠቀሳሉ፡፡ ይህን ሐሳብ እዚህ ማንሳቴ በእጅጉ እየተዳከመ ባለው የኅትመት ኢንዱስትሪ በተለይ ጋዜጣን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ አልተቻለም፡፡ የጋዜጣ አከፋፋዮችና አዟሪዎች ሚና አሌ የማይባል ነው፡፡ በተለይ በመዲናይቱ ዕምብርት ፒያሳ የኅትመት ውጤቶች በተለይ ጋዜጦች በካፊቴሪያዎች በወጣቶችና በጎልማሶች እየተነበቡ ‹‹በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ›› እንዲሉ፣ ለኅትመት ኢንዱስትሪው ድጋፍ ያደርጉ የነበረ ቢሆንም አሁን ባለው ፈረሳ ምክንያት የማንበቢያ ቦታዎች ባለመኖራቸው ጋዜጣን በቀላሉ ማግኘት አይቻልም፡፡ የአገሪቱ አንጋፋ የኅትመት ድርጅት ከሆነው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋዜጣና ሌሎች የኅትመት ውጤቶች ከማተሚያ ቤት  እንደወጡ፣ በተለይ ወጣቶች አንድም ለሥራ አሊያም ለመረጃና ለዕውቀት የሚያነቡባቸው የአራት ኪሎ የጋዜጣ የማንበብያ ኮሪደሮች፣ በኮሪደር ልማት በመፍረሳቸው ሳቢያ የኅትመት ኢንዱስትሪው ላይ የሚያመጣውን አሉታዊ ጫና መገንዘብ አያዳግትም፡፡ በአገሪቱ የሚታተሙ በጣት የሚቆጠሩ ጋዜጦችን በከተማው ዋና ዋና ቦታዎች ማግኘት ባለመቻሉ፣ የአፍሪካ ኅብረት ዋና ከተማና ከአምስት ሚሊየን በላይ ነዋሪ ያላት አዲስ አበባ ጋዜጣ አልባ ከተማ (A City Without Newspaper) ወደ መሆን እየተቃረበች ትገኛለች፡፡

ለማጠቃለል ያህል በሰሞናዊው የፒያሳ የመልሶ ማልማትና የአዲስ አባባ ኮሪደር ልማት በየሚዲያዎች ዜጎች የተሰማቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ ከላይ እንደተጠቀሰው የአዲስ አበባ ዕምብርት የሆነቸው ፒያሳ በተለይ ነዋሪዎቿ ለኑሮ ባልተመቸ መኖሪያ ውስጥ መኖራቸው አይስተባበልም፡፡ ዜጎችን ወደ ተሻለ የኑሮ ሁኔታ ለመለወጥ የተጀመረው ሥራ ለአብነት ያህል በበላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን አማካይነት በተገነቡ ዘመናዊ ቤቶች የተዘዋወሩና የተሻለ መኖሪያ ያገኙ ከፒያሳና ከሰባ ደረጃ የተነሱ ዜጎች ሁኔታ በአዎንታዊ ጎኑ ቢታይም፣ ይህን ግዙፍ የሆነ ከአምስት ሔክታር በላይ መሬት በግል፣ በግልና በመንግሥት ትብብር ለሚያለሙ አልሚዎች የቀረበበት መልሶ ማልማት ሲታሰብ፣ ቀድመው ሊታሰቡ የሚገባቸውና ሊተገበሩ የሚገቡ ቅድመ ዝግጅቶች ተግባራዊ አለመደረጋቸው እንደ አገርም ሆነ እንደ ከተማ ያስከተላቸው አሉታዊ ነገሮች ብዙ ናቸው፡፡ ፒያሳን ያህል ከመቶ ዓመታት በላይ የተሻገረ ታሪክ ላለው ሥፍራ እንዲህ ዓይነት መልሶ ማልማት ሲታሰብ ከነዋሪዎች ጋር በቂ የሆነ መተማመን ላይ አለመደረሱ ቅሬታ አስነስቷል፡፡ ከአንድ ወር በፊት በቀድሞ ግለቷ ላይ የነበረችው ፒያሳ በአንድና በሁለት ሳምንት ወደ ምድረ በዳነት በአንዴ ስትቀየር፣ አዝጋሚ የሆነ ከተማን ማጥፋት እንደ አገር እየተለማመድን መሆኑን ያሳያል፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

The post በአገር ደረጃ ማፍረስ እየተለማመድን ይሆን? first appear on ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia and is written by አንባቢ

9 months ago

በጉጉት ተንጧል። ‘ሰሞኑን’ ትለዋለች። ‘ለምን ነገ አንገናኝም?’ ሲላት ‘ነገማ የልማት ስብሰባ’ አለ ትለዋለች። ‘እሺ ለምን ተነገ ወዲያ አንገናኝም?’ ብሎ ሌላ ጥያቄ ሲያቀርብ ‘የኮሪደር ልማት ጉብኘት አለብኝ’ አለችው፡፡ ‘በቃ እሺ ከዚያ ወዲያ’ አላት መጨረሻ ላይ። ‘የዚያን ቀን ደግሞ ግምገማ አለ’ ብትለው፣ ‘እንዴ ምነው ይኼን ያህል አገር የምትመሪው አንቺ ነሽ እንዴ?’ ብሏት አረፈው እልሃለሁ…›› ብሎት እነሱ ሲስቁ ቀልዱ የለዘዘባቸው ደግሞ ፀጥ ብለው ነበር። ድንቄም አትሉም ታዲያ!

ወደ መዳረሻችን ተቃርበናል። ጎልማሳው ቀልድ ተብዬውና የወጣቶቹ ሳቅ እያበሳጨው፣ ‹‹የመሠረታዊ አቅርቦቶች ዕጦት ከመራር ድህነት ጋር ግብግብ አጋጥሞን ከቴም ቀልድ እናንተ…›› ሲል በንዴት ይንተከተካል። ‹‹በትንሽ ትልቁ መንተክተክ እንዲያው እኮ…›› የሚሉት እኚያ እናት ናቸው፡፡ ለማጁ ወያላችን በጣም ዘግይቶ መልሳችንን ለመስጠት ብር ሲቆጥር ከእጆቹ እያመለጠ እሱን ለቀማ ፍዳችንን እናያለን። ‹‹ምን የዘንድሮ ገንዘብ እንኳን ተበትኖ መሬት ነክቶ ይቅርና ኪስ ውስጥ ተደላድሎ ተቀምጦ መቼ ዋጋ አለው?›› አዛውንቷ በምሬት ከእግራቸው ሥር ባለአምስትና አሥር ብር እየለቀሙ ይናገራሉ። ‹‹ኧረ የገንዘቡስ አንድ ነገር ነው። ሰውም እኮ ነው ዋጋ እያጣ የተቸገርነው…›› ባዩ ደግሞ ጎልማሳው ነው። መጨረሻ ወንበር ጥጉን ይዞ የተቀመጠው ምሁር መሳይ ደግሞ፣ ‹‹እኔን ደግሞ የሚገርመኝ ስለራሱ በቅጡ የማያውቅና ዋጋውንም ያልተረዳ እየተነሳ፣ በአገራችንና በብራችን ዋጋ ማጣት የሚሰጠው አጉል ፍርድ ነው…›› ይላል። ‹‹ዋጋችንን ለማወቅና በቅጡ ለመኖር ከዘመኑ ጋር በቅጡ መላመድ ያስፈጋል…›› ስትል ወይዘሮዋ ወያላው ‹‹መጨረሻ…›› ብሎ በሩን ከፈተው። ተራ በተራ ስንወርድ አዛውንቷ ወደ ወይዘሮዋ ጠጋ ብለው፣ ‹‹ግን ይህንን አስቸጋሪ ዘመን እንዴት እንልመድ?›› ብለው ሲጠይቁ፣ ‹‹የማይለመድ የለም…›› ብላቸው ተለያየን፡፡ መልካም ጉዞ!

The post የማይለመድ የለም! first appear on ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia and is written by በጋዜጣዉ ሪፓርተር

9 months ago

በአገር ደረጃ ማፍረስ እየተለማመድን ይሆን?
ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best and reliable news source in Ethiopia (RSS)

ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia

በአገር ደረጃ ማፍረስ እየተለማመድን ይሆን?

በቶፊቅ ተማም

‹‹አፈረሱት አሉ መሀል አራዳን

ያለ አባት ያለ እናት ያሳደገንን››

በዓለማችን የሕዝብ ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ሲሆን፣ አሁን ባለ መረጃ መሠረት ወደ ዘጠኝ ቢሊዮን ገደማ ይገመታል፡፡ ከዓለማችን ሕዝብ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውም ኑሮውን በከተሞች አድርጓል፡፡ የከተሞች ክፍለ ዘመን እየተባለ በሚጠራው ሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከተሜነት እየተስፋፋ ሲሆን፣ በየአገሮች የከተማ ኗሪዎች ብዛት ይለያያል፡፡ አፍሪካ ውስጥ ካሉ አገሮች መካከል ጋቦን፣ ሊቢያ፣ አልጄርያ ከ75 እስከ 90 በመቶ ዜጋቸው በከተማ ሲኖር፣ በአንፃሩ በከተማ የሚኖሩ ዜጎቻቸው ቁጥር አናሳ ከሆኑ አገሮች መካከል ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማላዊ፣ ሩዋንዳ፣ ኒጀርና ብሩንዲ ይጠቀሳሉ፡፡ እንደተቀረው የዓለም ክፍል ሁሉ በኢትዮጵያም ከፍተኛ የከተሞች ምጣኔ ሲኖር፣ አሁን በአገሪቱ ያሉ ከተሞች ከ2,500 በላይ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ከተሞች ከጥቅል አገራዊ ምርት (ጂዲፒ) ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውን እያመነጩ ነው፡፡

ከተሞች በኢኮኖሚ ተወዳዳሪና ዘመኑ ከደረሰበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን፣ በአገራችን በተለይ ባለፉት ዓመታት ይህ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ለዚህም ማሳያ ምድረ በዳ የነበሩ መሬቶችና ተገቢውን የከተማ ዲዛይንና ለመኖሪያ ተገቢውን መሥፈርት ያላሟሉ ቤቶች የነበሩባቸው የከተማ ክፍሎች በዘመናዊ ሕንፃዎች፣ ፋብሪካዎች፣ የጤና ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት  ተገንብተውባቸዋል፡፡ አሁን ዓለም በደረሰበት የከተማ ስታንዳርድ ለከተማ በማይመጥን ደረጃ ያሉ ቤቶችን በማስወገድ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በመገንባት፣ እንዲሁም በማዘመን የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሻለ የኑሮ ደረጃ እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ ተከናውኗል፣ እየተከናወነም ይገኛል፡፡ እንደሚታወቀው በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ከተሜነት እየተስፋፋና ከተሞችም ከመቼውም በበለጠ ከቴክኖሎጂ ጋር እየዘመኑ ቢሄዱም፣ ከዚህ በተቃራኒ የዓለማችን ከተሞች በተፈጥሯዊ አደጋዎች ማለትም በሰደድ እሳት፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በሰው ሠራሽ አደጋ ከእነ ቅርሶቻቸውና ኪነ ሕንፃዎቻቸው፣ ትዝታቸውና መስህባቸው  ወደ መጥፋት ደረጃ (Urbicide) ሲደርሱ እያየን ነው፡፡

በሰው ሠራሽ አደጋዎች ከሚከሰቱ የከተማ መጥፋቶች ዋናው ምክንያት ጦርነት ሲሆን፣ ለአብነት በሶሪያ በነበረው አስከፊ ጦርነት ሳቢያ ያቺ ውብ የነበረቸው የብዙ ጥንታዊ መስህቦች ባለቤትና ጥንታዊ የነበረችውን የሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ መጥቀስ ይቻላል፡፡ የዚህን ዳፋ ውጤት ደግሞ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመዲናችን የሚገኙ የሶሪያ ተወላጆችን በማየት መረዳት በቂ ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በተለይ ከአሜሪካ ጋር በነበረው ጦርነት እጅግ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ሌላዋ ታሪካዊ ከተማ የኢራቋን ባግዳድ ማንሳት ሲቻል፣ በቅርብ ዓመታት ከወደሙ ከተሞች መካከል ጋዛ፣ አሌፖ፣ ሰንዓና ኪቭ ይጠቀሳሉ፡፡ በሌላ በኩል አገሮች የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ሳይገቡና የተፈጥሮ አደጋ ሳይደርስባቸው ከበፊት ጀምሮ የያዙትን መስህብ፣ ማንነትና ትዝታ በተለያዩ ምክንያቶች ካጡና (Destruction of Memory) የበፊት አሻራቸውን ማግኘት ካልተቻለ፣ ቀስ በቀስ እየጠፉ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከተገታ፣ ሰዎች ከሚኖሩበት ቀዬ ወደ ሌላ ቦታ ከተዘዋወሩ (Population Displacement) መጠሪያቸው ከተለወጠ (ሙሉ ለሙሉ ከአሁን በኋላ የማይኖሩ ዶሮ ማኒቂያ፣ እሪ በከንቱና ሠራተኛ ሠፈርን መጥቀስ ይቻላል)፣ ከተሞች በመጥፋት አደጋ ላይ ለመሆናቸው ወሳኝ ምልክት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ወደ ዋናው ጉዳይ ስመጣ በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለይ የአገሪቱ ርዕሰ መዲና ዕምብርት የሆነቸው፣ የበርካታ ታሪካዊና ማኅበራዊ መስተጋብሮች መነሻ  የሆነችውን ፒያሳ እንደ አዲስ ለማልማት፣ ብሎም የከተማዋ ስም በሚመጥን ደረጃ ሰፋፊ የእግረኛ መንገድና ጎን ለጎን ከተማን የማስዋብ ለመተግበር ያቀደውን የኮሪደር ልማት ይመለከታል፡፡ ምንም እንኳን በአዲስ አበባ ታሪክ ሰፊ ጉልህ ድርሻ የያዘችው ፒያሳ እንደ ሌሎች የከተማው ክፍሎች ሁሉ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት ያወጣውን የመኖሪያ ቤት ስታንዳርድ ያላሟሉ እጅግ የተጣበበና አናሳ መሠረተ ልማት፣ በተለይ የንፁህ መጠጥ ውኃና የመፀዳጃ አገልግሎት በቅጡ ባልተሟላበት እጅግ በማይመጥን ደረጃ ላይ ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች (Slum Dwellers) ወደ ሌላ ለኑሮ ምቹ ወደ ሆነ ቦታ አዛውሮ ለማኖር ማሰቡ በበጎ ይታያል፡፡

መንግሥት ያሰበውን ልማት ለማከናወን ሲነሳ ለዜጎች ምትክ ቤት መስጠት ላይ ብቻ ማዕከል ያደረገ ግብታዊ ውሳኔ ከማስተላለፍ ይልቅ፣ በተለይ ለነዋሪዎችና በፒያሳና በዙሪያዋ በንግድና በአግልግሎት ለተሰማሩ ተቋማትና ግለሰቦች በቂ የሆነ የማዘጋጃ ጊዜ ሊሰጥ የተገባ ነበር፡፡ በፒያሳና በአካባቢው ለነበሩ አገልግሎት ሰጪዎች በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አማካይነት የተለያዩ ሱቆች በኪራይ ለማቅረብ ንግግር ቢጀመርም፣ በሚገባው ልክ ምትክ የመሥሪያ ቦታ ማግኘት አልቻሉም፡፡ ይህ በራሱ በዜጎች፣ በከተማው ብሎም በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ በሌላ በኩል በተለይ ለዓመታት አብረው የኖሩና ተዋልደው ጭምር የተቀናጀ ግንኙነት የነበራቸው ከትዝታና ከማኅበራዊ ዓውዳቸው የሚነቀሉ ከመሆናቸው አኳያ፣ መስተጋብራዊ መዋቅራቸው ሙሉ በሙሉ እንዳይፈርስ ቢያንስ በቂ ጊዜ ማግኘት እንደነበረባቸው ብዙዎች ያምናሉ፡፡

ሌላው ከፒያሳ ጋር ተያይዞ እንደ አገር የተነሳው ጉዳይ ሌሎች አገሮች የራሳቸው አሮጌ ከተማ (Old Town) ያላቸው ሲሆን፣ አሁን እየተከናወነ ያለው ተግባር ግን አዲስ አበባን አሮጌ ከተማ ከሌላቸው ከተሞች ተርታ ያሠልፋታል፡፡ የአሮጌ ከተማ ሁኔታ ሲነሳ የተወሰኑ ከተሞችን ለማየት ልሞክር፡፡ ለአብነት ያህል ‹‹የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ›› በሚለው ብሂል መሠረት አሮጌ ከተማ ካላቸው አገሮች መካከል የፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶ አንዷ ስትሆን፣ የቀድሞ ከተማዋ ‹ኦልድ ዋርሶ› ነው፡፡ ፖላንዶች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሙሉ በሙሉ የወደመችውን ዋርሶ ላለማጣት መሬቱ ላይ ሕንፃ ሳይገነቡ በከተማዋ የቀድሞ ምሥሎች በመታገዝ፣ እንደገና አዲሷን ዋርሶ (New Warsaw) ገንብተዋል፡፡ ይህን በማድረጋቸው የኋላቸውን ሳይለቁ ለቱሪስት መዳረሻ የሚሆን ከተማ እንዲገነቡ አስችሏቸዋል፡፡ ሌላም ለማንሳት ያህል የህንድ የቀድሞ ዋና ከተማ ‹ኦልድ ደልሂ› ስትሆን፣ በእሷ አምሳል የአሁኗን ኒው ደልሂ መገንባት ችለዋል፡፡ ዛሬም ቢሆን ቱሪስቶች ከኒው ደልሂ ይልቅ ኦልድ ደልሂን ለመዝናናት ይመርጡታል፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የቀድሞዋን ፒያሳ ሊየሳዩ የሚችሉ በእጅጉ ሊጠበቁ የሚገባቸውና በአዕምሯችን የሚመጡ ሥፍራዎችን የመልሶ ማልማት አካል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ መልሶ ማልማቱ በጥንታዊ መንደርነት (Old City) ከልለን ልናገኘው

11 months ago
የቻይና ሳይንቲስቶች ህጻን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሰሩ

የቻይና ሳይንቲስቶች ህጻን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሰሩ
جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS)

በቤጂንግ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተሰራችው ይህች አዲስ ፈጠራ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውደርዕይ ላይ ለጎብኚዎች ቀርባለች

11 months, 1 week ago
አርማጌዶን ጥበብ

አርማጌዶን ጥበብ

አርማጌዶን፧ t.me/wedefkr| Facebook (Facebook)

11 months, 1 week ago

በቻትጂፒቲ ሚስቱን የመረጠው ሩሲያዊ
جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS)

ወጣቱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ያፀደቀለትን ምርጫ ተቀብሎ ትዳር መስርቷል

11 months, 1 week ago

አሜሪካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም ያሳስበኛል አለች
جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS)

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኢርቪን ማስኛ የአዋጁ መራዘም እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል

11 months, 2 weeks ago
አርማጌዶን ጥበብ

አርማጌዶን ጥበብ

አርማጌዶን፧ t.me/wedefkr| Facebook (Facebook)

We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 5 days, 7 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 month, 3 weeks ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 2 months ago