Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno
Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Last updated 2 months ago
🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person
Last updated 1 month, 1 week ago
🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ
📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ
📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot
Last updated 4 months ago
My silence means I am tired of fighting and now there is nothing left to fight for.
My silence means I am tired of explaining my feelings to you, but now I don't have the energy to explain them anymore.
My silence means I have adapted to the changes in my life and I don't want to complain.
My silence means I am on a self healing process and I am trying to forget everything I ever wanted from you.
My silence means I am just trying to move on gracefully with all my dignity.
{PS}
መሞቻ ቀንህ ቀርቧል ተባልኩ!!እየዋሸኋችሁ አደለም!!ትላንትና ለትንሽ ህመም ጎራ ያልኩበት ሆስፒታል ዶክተሩ መራሩን እውነት ሲያረዳኝ መጀመርያ እኔም አላመንኩትም ነበር። እንደውም ትሞታለህ ካለኝ ወዲህ ከአፉ እንቅስቃሴ በቀር ምንም አልሰማሁም ነበር።ከሀሳቤ ያባነነኝ ከውጪ የተቀበለኝ የቤተሰቤ የለቅሶ ድምፅ ነው።ሁሉም ሲያለቅስ እስካሁን አለማልቀሴ ገርሞኛል ብቻ ህይወት በአንዲት የዶክተር ቃል ተቀንብባ #ትሞታለህ ከተባልኩ አንድ ሙሉ ለሊት አለፈ እኔም በጠዋት ተነስቼ ልነግራችሁ ሳይሆን ላረዳችሁ ወሰንኩና ብንን ስል ግን ይሄ ሁሉ ሆኖ የነበረው በህልሜ እንጂ እውን አልነበረም።
ግን እስቲ ካወራን አይቀር የውሸት ታሬኬን ሰምታችሁ ትንሽም ቢሆን የምታቁኝ ደንገጥ ማለታችሁ አልቀረም አደል???ምናልባት ለኔ ከደነገጣችሁ እናንተ ብትባሉ ምን ልትሆኑ እንደምትችሉ አስቡት። ልክ እንደዶክተሩ መልአከ ሞት ድንገት መጥቶ አንድ ቀን ትሞታለህ ብሎ ሊያረዳን ይችላል።ሩቅ የሚመስለን ሞት ነገ ደጃችንን ሊያንኳኳ ይችላል።አላስገባም ተመለስ ብሎ ማባረርም በፍፁም አይቻልም!!!ብዙወቻችን ግን ሞትን አስበነው አናቅም፤ማሰብም አንፈልግም፤ለመዘጋጀት እንኳ ዝግጁ አደለንም አኗኗራችን ሁሉ በዘፈቀደ ከሆነ ሰንብቷል
እንግዲህ እውነቱን ልንገራችሁ። ከሆኑ አመታት በኋላ አሁን ያላችሁ አቋም አፈር ይሆናል ስም ብቻ ትሆናላችሁ እሱንም ካልተረሳችሁ ማለት ነው።so ብንሞት እንኳ ስንቅ እንያዝ እንተባበር እንዋደድ ይቅር እንባባል።ሬሳችን ከመሄዱ በፊት ለቤተመቅደሱ ለንሰሐው ቅርብ እንሁን ምናልባት ለመንቃት ሁላችንም ህልም መጠበቅ የለብን በተወራ በሰማነው ባየነው እንንቃ!!
ታሪካችን አያስደንስም፡፡ ትርክታችን ቺርስ የሚያስብል አይደለም፡፡ ኑሯችን ስጋ በልቶ ንፍሮ ነው፡፡ ተረኛውና ባለጊዜው ነው ለብቻው የሚጨፍረው፡፡ ስልጣኑን በጉልበት የጨበጠው ነው እርስበርሱ ቺርስ የሚባባለው፡፡ ሔግል ‹‹አፍሪካውያን ታሪክ የላቸውም›› እንዳለው ተጨባብጠን በሰላም የተለያየንበትና በዲሞክራሲያዊ ድል፣ በኢኮኖሚ ምጥቀት፣ በልማትና በስልጣኔ አስረሽ ምቺው ያልንበት የጋራ ታሪክ የለንም፡፡ በግኝት፣ በፈጠራ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት ያሳረፍነው አሻራ፤ ያስቀመጥነው ቅርስ የለም፡፡ ሁሌም የምንኮራው በጥንታዊ አባቶቻችን ገድል ነው፡፡ በራሳችን የምንኮራበት በእጃችን ምንም የለም፡፡ ቁስም ሃሳብም፣ ፈጠራም፣ ሳይንስም ኢምፖርት ነው የምናደርገው፡፡ ወደውጪ የምንልከው ወጣት ልጆቻችንን ለጉልበት ብዝበዛ እንጂ የተለየ የሃሳብ ውጤታችንን አይደለም፡፡ ከትናንት በስቲያም ይሁን ትናንታችን የለቅሶ ነው፡፡ አልቃሽና አስለቃሽ ሆነን ነው እድሜአችንን የጨረስነው፡፡ እርስበርስ እየተጨፋጨፍን ነው እዚህ የደረስነው፡፡ ጧት ማታ ስንነታረክ ነው የኖርነው፡፡ ጥግ ለጥግ ሆኖ መተኳኮስን እንጂ ወደመሃሉ ቀርቦ መነጋገርን አልለመድንም፡፡ እውቀታችን ጥራዝ ነጠቅ ነው፡፡ ሐገራችንንም፣ ህዝባችንንም፣ ራሳችንንም አልተረዳንም፡፡ የወንዜ ፖለቲካ ጠራርጎ ወስዶናል፡፡ የዘረኝነት ጎርፉ ቤት ንብረታችንን አፍርሷል፤ ከሰውነታችን አፈናቅሎናል፡፡
ወጣቱ ፀሐፊ ያዕቆብ ብርሃኑ ‹‹በባዶ ላይ መዝገን›› በተባለው መፅሐፉ ላይ አንድ ያነሳት ሃሳብ ግሩም ነች፡፡ በደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ መገርሰስ በኋላ ደራሲያኑ አንዲት ታዋቂ ደራሲ ጋር ቀርበው ‹‹በአፓርታይድ ጊዜ ብዙ የምንፅፍበት ጭብጥ ነበረን፡፡ ነገር ግን ለመፃፍ ነፃነቱ አልነበረንም፡፡ አሁን ነፃነቱ ሲመጣ ግን የምንፅፍበት ሃሳብ የለንም፡፡ ግራ ተጋብተናል፡፡›› አሏት፡፡ ይህች ደራሲም፡- ‹‹ስለነዚህ ግራ መጋባቶች ፃፉ (Write about those confusions)›› አለቻቸው ይለናል፡፡
እውነት ነው ያለንበት ግራ መጋባት የሚያፅፍ ነው፡፡ ደራሲያን ይሄን የመንታ መንገድ ላይ አቋቋማችንን ከትበው ለታሪክ ቢያስቀምጡት መልካም ነበር፡፡ ነገር ግን አብዛኛው ፀሐፍያን ወይ በእንኪ-እንካ ፆታዊ ፍቅር ድርሰት ተጠምደዋል፤ ወይ ደግሞ በዘመኑ የፖለቲካ ወጥመድ ተጠምደዋል፡፡ ያለንበትን ድንዛዜ፣ የገባንበትን እምጥና ስምጥ መከራ ተገንዝቦ ከድቅድቅ ጨለማ ሊያወጣን የሚችል፣ ጭላንጭል ብርሃን ሊያሳየን የሚደፍር ብዕርተኛ ማግኘት አዳጋች ሆኗል፡፡
እውነት ለመናገር ጦርነት ቢቆምና ሰላም ቢሰፍን፤ እርስበርስ መገዳደሉ ቀርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ መወያየት ቢጀመር የዛሬዎቹ የዩትዩብ ጋዜጠኞቻችንን ውሃ ይበላቸዋል፡፡ ነጋዴ ፀሐፊዎቻችን አጀንዳ ቢስ ሆነው ይቀውሳሉ፡፡ በትዕዛዝ የሚደርሱ አድርባይ ደራሲያን ጦማቸውን ያድራሉ፡፡ ሐገር የሚበጠብጡት አክቲቪስት ተብዬዎቹ መግቢያ ያጣሉ፡፡ ጥላቻ ጠማቂዎቹ ይከስራሉ፡፡ ካድሬዎቹ ስራ-አጥ ይሆናሉ፡፡ በተፈናቃይ ስም ቢዝነስ የሚሰሩ ቀፋዮቹ አንገት ይደፋሉ፡፡ ፍትህና እኩልነት ሲሰፍን ባለጊዜዎቹ ቅስማቸው ይሰበራል፡፡ ለዚህ ይመስለኛል ብዙዎቹ በሴራ በህዝቦች መካከል መቃቃር እንዲሰፋና ሰላም እንዳይመጣ አጥብቀው የሚሰሩት፡፡
"Small Kindnesses" by Danusha Laméris
I’ve been thinking about the way, when you walk
down a crowded aisle, people pull in their legs
to let you by. Or how strangers still say “bless you”
when someone sneezes, a leftover
from the Bubonic plague. “Don’t die,” we are saying.
And sometimes, when you spill lemons
from your grocery bag, someone else will help you
pick them up. Mostly, we don’t want to harm each other.
We want to be handed our cup of coffee hot,
and to say thank you to the person handing it. To smile
at them and for them to smile back. For the waitress
to call us honey when she sets down the bowl of clam chowder,
and for the driver in the red pick-up truck to let us pass.
We have so little of each other, now. So far
from tribe and fire. Only these brief moments of exchange.
What if they are the true dwelling of the holy, these
fleeting temples we make together when we say, “Here,
have my seat,” “Go ahead—you first,” “I like your hat.”
Book: Bonfire Opera: Poems by Danusha L
ወደ አሜሪካን ጎት ታለንት ( American Got Talent) ከሚመጡ ተወዳዳሪዎች መሃል Jane Marczewiski (በቅጽል ስሟ Nightbird) የምትባለውን ብዙዎች አይረሷትም፡፡ ተወዳዳሪዋ ወደ መድረክ በመጣች ጊዜ የዕለቱ ተረኛ ጠያቂ ሀዋርድ "እንዴት ነሽ!?" አላት:: በጣም ደስተኛ ነኝ:: እዚህ በመሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል አለች"
ሀዋርድ ቀጠለና "ምንድንው የምታቀርቢልን!?" አላት:: እሷም "It is Ok” የሚል የራሴን ስራ ነው" አለች:: ሁላቸውም ባንድ አፍ እሺ ቀጥይ አሉ:: ሀዋርድ ቀጠለና "ግን ሁሉ ደህና ነው ስለምንድነው?" ሲላት ከካንሰር ጋር ስትታገል የኖረችውን የሕይወት ውጣውረድ ነገረቻቸው:: የሁሉም ፊት ጨለማ የእሷ ፊት ግን የደስታ ጨረር ከመርጨት አላቆመም:: ኮምጨጭ አለችና "አረ ሁሉ ደህና ነው:: እኔ ሰላም ነኝ" አለቻቸው::
ከዚያም ሳይመን "አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? አሁን እንዴት ነሽ!?" አላት:: እሷም "የመጨረሻውን ምርመራ ሳደርግ በሳንባዬ፣ ጣፊያዬና ጉበቴ ላይ ካንሰር እንዳለ ተነግሮኛል ስትል ሳይመን በድንጋጤ ተመለከታት ፡፡ ቀጠለና ሀዋርድ "ስለዚህ ደህና አይደለሽም ማለት ነዋ" አላት:: "በርግጥ በሁሉም መልኩ አይደለም" ስትል ሀዋርድ ተገርሞ "ማንም ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሽ እስከማያውቅ ድረስ ለሌሎች የደስታ ጨረር የሚረጭ አስገራሚ ፈገግታ አለሽ" አላት ተገርሞ!!
Nightbird የሕይወት ታሪኳን አሳማኝ በሆነ መልኩ በዜማ ካቀረበች በሗላ የዳኞች ውሳኔ የሚሰጥበት ሰአት ደረሰ:: ሁሉም ሳግ እየተናነቃቸው በስሜት የተሞሉ አዎንታዊ አስተያየቶችን ሰጡ:: ተራው ሲደርስ ተጠባቂው ሳይመን ሌሎች ዳኞች በሰጡት አስተያየት ሙሉ በሙሉ እንደሚስማማ ገልፆ ተጨማሪ ስሜቱን እንዴት መግለጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ሲያመነታ ሳለ መኻል ላይ አቋርጣ በከፍተኛ ፈገግታ በመሞላት፡
"ደስተኛ ልትሆን ለመወሰን ሕይወት ከዚህ በፊት ከነበረው ከባድነት ቀላል እስኪሆን መጠበቅ የለብህም" የሚል እጅግ አስገራሚ አስተያየት ሰነዘረች::
ያ ንግግር ብዙዎችን ያስገረመ ቢሆንም ሳይመንን ለደቂቃዎች አፍዝዞ እንባ ከሁለቱ ዓይኖቹ ፈሰሱ::
ከፊቱ ያለውን ተጎንጭቶ ሳግና እንባውን አወራረደ:: በመቀጠልም አስተያየቱን ሰነዘረ:- "በዚህ ዓመት ታላላቅ ችሎታ ያለቸውን ሰዎች አይቻለሁ:: ሆኖም ላንቺ 'yes’ አልሰጥም" ሲል ከዳኞች እስከ ታደሚ በቅሬታ አጉተመተሙ:: ሳይመን አልጨረሰም ነበር:: "የሚሰጥሽ ከ'yes’ የተሻለ ነገር ነው" አለና እጆቹ ወደ Golden Buzzer ሄደ:: አደራሹ በከፍተኛ ደስታ ሲያስተጋባ Nightbird የወርቁ ብናኝ ላይ በደስታ እንባ ተደፋች!!
በአንድ ጽሑፏ ሕመሟን በተመለከት "ፈጣሪ አብዛኛውን ጊዜ ወሳጅ ሳይሆን ሰጪ ነው:: ከመውሰድ ይልቅ ይጨምራል" ትላለች:: “ጨለማዬን አልወሰደውም ግን ብርሃን ጨመረልኝ:: ብቸኝነቴን አልፈወሰደውም ግን እርሱ ይበልጥ ቀረበኝ" ትላለች:: በሕመሟ ተስፋዋ ይጨምራል እንጂ ተስፋ ቢስ አይደለችም:: በመሆኑም "በህመሜ ተስፋ የማደርገው የፈጣሪን ቅርበት በዚያ ስላወቅሁ ነው" ትልም ነበር፡፡በመጨረሸም እንዲህ ነበር ያለቸው፦
"ለመኖር ሁለት ፐርሰንት ዕድል ብቻ እንዳለኝ በሀኪሞች ተነግሮኛል:: ነገር ግን ሁለት ፐርሰንት ማለት ዜሮ ማለት አይደለም:: ሁለት ፐርሰንት ማለት የሆነ ነገር እንደሆነ ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ!!"
የሆነ ተዓምርማ አለን!
ይሄው ምግብን በከሰል ማብሰል የሚያስከትላቸውን ከ30 በላይ ጉዳቶች እያነበብኩ ነው። እንግዲህ እንደፅሁፉ ከሆነ ከጭሱ በተጨማሪ ከሰሉና ምግቡ ንክኪ ከፈጠረ ብዙ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል። ምላስ የለ አንጀት ፣ የደም ስር የለ አንጎል፣ አይን የለ የመተንፈሻ አካል ፣ ጨጓራ የለ ነርቭ፣ አጥንት አይቀር ቆዳ ሁሉም ላይ ከቀላል አለርጅ እስከሞት ወይም ዘላቂ የአካል ጉዳት ሊያጋልጥ የሚችል የጤና እክል ሊከሰት እንደሚችል ያትታል። ኤዲያ ዝም ብየ ነው የምደክመው እንጅ ትምህርታቸው ሁሉ ውሃ አያነሳም። ሌላው ሁሉ ይቅር ከሰል ላይ እየጠበስን እያገላበጥን የጋጥነው በቆሎ ፣ የበግ ቆ** ወዘተ ሰው ያደርገን ነበር ወገኖቸ? በቆሎ በከሰልኮነው ስንበላ የኖርነው። እንደአዋዜ እያጠቀስን በሉት። የሆነ ተዓምርማ አለን። ሳስበው ግን ወደመሠረታዊ የችግራችን መንስኤ እየተቃረብኩ ይመስለኛል።
በብዙ አንባቢዎች ሲጠበቅ የነበረው የናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) ሜሎሪና መጽሐፍ ክፍል 3 ለአንባቢያን ቀርቧል።
“ሜሎሪና” ታሪካዊ የሥነልቡና ልብወለድ የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበብ ሚና የሚተርክና ስለ ኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚያወራ ልብወለድ መጽሐፍ ነው ፡፡ በአቀራረቡም #የሥነልቡና_ምክሮችንና ሀሳቦችን
#የሥነ_አመራር ጥበቦችን #ከታሪካዊ_ክስተቶች ጋር አጣምሮ ይዟል፡፡በተጨማሪም በመጽሐፉ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደ አንድ ገጸ ባህሪ ተካተዋል።
ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ ሀሳቦች
? ‹‹ትልቁ ብቸኝነት ሰውን ማጣት ሳይኾን ራስን ማጣት ነው። በምድር ላይ ራሱን እንዳጣ ሰው ብቸኛ የለም። ራስን ማጣት፥ በኛ ውስጥ ያሉ ችሎታዎቻችንን አቅማችንንና ስሜቶቻችንን ማጣት ነው፡፡ እራሱን ያጣ ሰው በዙሪያው እልፍ ሰዎች ቢሰበስብ እሱ ግን ዘወትር ብቸኛ ነው።››
?‹‹...ትዝታ ለብዙ ሰው የዕድሜ ዘመን እስር ቤት ነው። ብዙ ሠዎችም ወደፊት መራመድ እየፈለጉ አስሮ የሚይዛቸው በገዛ አዕምሮአቸው ውስጥ ያስቀመጡት የትናንት ታዝታቸው ነው።››
?‹‹አፍሪካ ውስጥ ‹ሕዝቡ› እንደሚለው ቃል በመሪዎች የተነገደበት ቃል የለም። አንዳንዱ መሪ ሕዝቡ የሚለው የገዛ ራሱን እሳቤ ነው። ሌላው ደግሞ ቤተሰቦቹንና ዘመዶቹ ብቻ ነው ሕዝቡ ብሎ የሚቆጥረው።››
?‹‹በህይወት ስትኖር መቼም ቢሆን ኹሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም፤ ማወቅና መጠንቀቅ ያለብህ ዋናው ቁም ነገር ማስከፋት የሌለብህን ሰው ለይተህ ማወቁ ላይ ነው።››
?‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››
“Dirreen lolaa inni guddaan sammuu namaati, Injifannoo guddaan of mo’uudha
?የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡ ለካስ እስር ቤት ቦታ ሳይኾን አስተሳሰብ ነው፡፡ በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል።
?ሜሎሪና - ስውር ጥበብ
?ሜሎሪና - ቴሎስ
❤️ሜሎሪና- ሕይወቴ
መጽሐፉን በኹሉም የመጽሐፍ መደብሮችና ከአዟሪዎች እጅ ይገኛል።
ዓለማችንን በንስር ዓይን ለማየት ከቆረጥክ፣ ወደድክም ጠላህ መጻሕፍትን ማንበብ አለብህ::
(መልህቅ በዘነበ ወላ)
‹‹ያሬድ ግን በጣም ዲሲፕሊን ያለው ሁሉንም ነገር በሥነ ሥርዓት የሚመራ መርከበኛ ነው፡፡ ቁጭ ብለህ ብታወጋው ተሰጥኦና ዝንባሌህን አውቆ ‹ይህንን ብትሞክረው ጥሩ ነው› ብሎ አቅጣጫ የሚመራህ ሰው ነው፡፡ ያሬድን አመፀኛ ያደረገው ይህ የምንኖርበት ሥርዓት ነው፡፡ እንደምታየው ሥርዓቱ ያደፈና የጎደፈ በአንድ ፓርቲ የአምባገነንነት አገዛዝ ስልት አገር ልግዛ ብሎ አገሪቱን ወደ ዘለዓለማዊ ጦርነት የከተተ በመሆኑ ይበሽቃል፡፡ ለምሳሌ ልንገርህ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ሲወገዱ ሩብ ሚሊዮን የሚሆነው የወሎ ህዝብ ተራበ የሚል ነበር ወንጀላቸው፤ የሚገርመው በዚያን ወቅት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 8% ያድግ እንደነበር ታውቃለህ?› የኢትዮጵያን ብርስ የመግዛት አቅሙ በጣም ጠንካራ እንደነበር ግንዛቤ አለህ?››
‹‹እንዲያውም!››
‹‹ይኸውልህ ይህንን ከንባቡ ያወጋኝ ይህ አግድም አደግ የምትለው ያሬድ ሐጎስ ነው፡፡ ተጨባጭ ማስረጃም አለው፡፡ የሚያሳዝነው የንጉሡ ጥፋት እንጂ ልማት አልተለፈፈም፡፡ ደርግ ግን ኢትዮጵያን ይዟት መቀመቅ ሊወርድ ነው፡፡ ይህ ያሬድን ያበሽቀዋል፡፡››
‹‹ያሬድ መጽሐፍ ያነባል እያልከኝ ነው?››
‹‹በደንብ፤ ቀደም ብሎ ባህር ኃይል ውስጥ ከመቀጠሩ በፊትም የንባብ ስንቁ ነበረው፡፡ እዚህም ከመጣ ቀጥሎበታል፡፡ ለምሳሌ ረቡዕ፣ ረቡዕ እሱ የሚቀዝፍበት 201 ስኳድሮን ሆስፒታል ሄደው የሚታከሙበት እለት ነው፡፡ የዚያን እለት ያሬድም ያመኛል ይልና ሆስፒታል ለህክምና እንደሚሄድ ያሳውቃል፡፡ እሱ ግን ያቺን ግማሽ ቀን ቤተ መጻሕፍት ሄዶ ሲያነብ ይውላል፡፡ የሳምንታቱን ሕትመት ውጤቶች ጋዜጦቹን፣ መጽሔቶቹን አንድ በአንድ ያገላብጣል፡፡ በጊዜው አገሪቱ ያሰበችውን ከሕትመት ውጤቱ ይገበይና ወደ ኢንሳይክሎፒዲያው፣ ወደ ሌሎች መጻሕፍት ዳሰሳ ያመራል፤ በተለይም በሙያው በመርከብ፣ በመርከበኝነትና ባህር ላይ ጥብስቅ ያለ መረጃ አለው፡፡
‹‹እኔ'ኮ በዚህ ረገድ ጠብሰቅ ያለ እውቀት ያለው ስንታየሁ ገመቹ ነበር የሚመስለኝ›› አለ ኤብል ሲማን አህመድ፡፡
‹‹እሱንም አንባቢ ያደረገው ያሬድ ነው፤ ስንታየሁ ቅፅል ስሙ ፋራው ነበር፡፡ ይህንን ሲሰማ ስንታየሁ ተቆጣና ‹ለምንድነው ፋራ የምትሉኝ? እናንተ የምትለብሱት ፍሪንኮር ጂንስ ነው፤ እኔም እሱን ጂንስ ለብሻለሁ፤ እናንተ የምታደርጉት ዎኪንግ ሹዝ› ነው፡፡ እኔ እንዲያውም ከእናንተ የላቀውን ገዝቼ አድርጌያለሁ፡፡…………እና ለምንድነው ፋራ የምትሉኝ?! ከዚህ በኋላ ገመቹ ይሙት ፋራ ካለኝ ልጅ ጋር እጣላለሁ!››
‹‹አራዳ ለመሆን ከፈለግክ፣ ሁሉን አወቅ ለመሆን ካሰብክ፣ በአንድ ነፍስ ብዙ ለመኖር ከወሰንክ፣ ዓለማችንን በንስር ዓይን ለማየት ከቆረጥክ፣ ወደድክም ጠላህ መጻሕፍትን ማንበብ አለብህ፤ ያላነበበ ሁሉ ድብን ያለ ፋራ ነው፡፡ ዓይኑ የሩቁን አይደለም፣ የቅርቡንም አጥርቶ አያይም›› አለው ያሬድ።
‹‹ስንታየሁ አገሪቱ ካፈራቻቸው አራዶች ሁሉ አራዳ ለመሆን ማንበብን ተያያዘው፡፡ በአንድ መጥፎ አጋጣሚ ጀልባቸውን ለማደስ ወደ ዳህላክ ሄደው ጀልባቸውን ሲጠግኑ ስንታየሁ አንሸራተተውና ወደቀ፡፡ አወዳደቁ በእግሩ በመሆኑ የአጥንት መሰንጠቅ ደረሰበት፡፡ እስኪያገግም ሆስፒታል ብዙ ተኝቷል፡፡ ያ ጊዜ ድንቅ የማንበቢያና የሕይወት መመርመሪያው ሆነ። በመቀጠል ከሆስፒታል ወጥቶ ባህር ኃይል ወደብ ላይ እንዲያገግም ሲቀመጥ ትንሽም ብትሆን ቤተ መጻሕፍቷን ቦጥቡጧት ኢንሳይክሎዲያውን ከኤ እስከ ዜድ አንብቧል ነው የሚባለው፡፡››
‹‹ከኤ እስከ ዜድ ያለምንም ጥርጥር 20 ቅፅ በላይ ይሆናል›› አለ አህመድ ተገርሞ፡፡
‹‹ባይገርምህ ለእያንዳንዱ ፊደል አንድ ማስታወሻ ነበረው፡፡ ማስታወሻ አያያዙም ምንአልባትም አቻው የሚሆን ሰው ቢፈለግ ካርል ማርክስ ቢሆን ነው፡፡ ከሁለት ደርዘን በላይ ማስታወሻ ደብተር ሳይኖረው አይቀርም፡፡ አሁን ታዲያ ጀልባዋ ላይ በአንድ ጉዳይ ክርክር ሲነሳ እና አለመተማመን ሲፈጠር ለዳኝነት የሚጠሩት ያሬድና ስንታየሁ ናቸው፡፡ ለዚህ ተራ ነገር ነው እኔን የጠራችሁኝ? በሉ እናንት ፋሮች ተቀመጡ፤ ላብራራላችሁ› ይላል፡፡ ያንን ማስታወሻውን በዚህ ረገድ ብዙ እንደተጠቀመበት ይነገራል፡፡››
ጊዜና ቀጠሮ ሊከበሩ የሚገባቸው ነገሮች ናቸው።
(ሀዲስ በበዓሉ ግርማ)
"ተፈጥሮ አንዱ ከሌላው ጊዜ ውስጥ እንዲታሰር አድርጋለች።ጊዜ የሁሉም መለኪያ፤ መነሻና መድረሻ ነው።
ማንኛውም ነገር እንደጊዜው ይወደዳል ፣ ይጠላል ፣ ይነሳል ፣ ይወድቃል ፣ ከጊዜ ውጭ የሚሆን ነገር የለም።
ጊዜን ድል ማድረግ የሚቻለው ጊዜን በማክበር ብቻ ነው።ምክንያቱም ህልውና ማለት በራሱ ጊዜ ስለሆነ።ምክንያቱም ከጊዜ ውጭ የሆነ ነገር ከዚህ አለም አይደለምና!"
Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno
Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Last updated 2 months ago
🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person
Last updated 1 month, 1 week ago
🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ
📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ
📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot
Last updated 4 months ago