Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Description
በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago

1 month, 1 week ago

ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ከስድብ፣ ከውሸት፣ ከማታለል፣ ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም

1 month, 1 week ago

#ተሳክቷል

እግዚአብሔር ይመስገን ለሰሙነ ሕማማት አገልግሎት የሚውል #ጥቁር_ልብሰ_ተክህኖ ለማሰራት ጥሪ ባደረግኹት መሠረት ከሚፈለገው 37ሺህ ብር ከአስራ ስምንት (18) በጎ አድራጊዎች 37,205 ብር አግኝቻለሁ።

በዚህ የበረከት ሥራ የተሳተፋችሁ ለመሳተፍ አስባችሁ ያልተሳካላችሁ እንዲሁም እንዲሳካ በጸሎት ያገዛችሁኝ በሙሉ የቅዱሳን አምላክ የልባችሁን መሻት ይሙላ።

እግዚአብሔር አብዝቶ ይስጥልን!

1 month, 1 week ago

ከኃጢያታችን የበለጠ እግዚአብሔርን እጅግ የሚያሳዝነው ይቅር አይለንም ብለን ማሰባችን ነው። በደል የሌለበት አምላክ ከእኛ ከትቢያዎቹ ጋር ራሱን አቻ አድርጎ "ኑና እንዋቀስ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዛቶ ትጠራለች" ብሎ የምሕርት ጥሪ እያቀረበ ይቅር አይለኝም ሰንል ሲሰማን ያዝናል። (ኢሳ,፩፥፲፰)

አንተ በክፉ ሥራህ ራስህን ብትጠላውም እንኳን እግዚአብሔር ግን አይጠላህም፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው «እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር አንተ ለራስህ ካለህ ፍቅር ይበልጣል» እንደ ይሁዳ ብትክደው ፣ ወዳጅህን ብትሸጥ፣ ንጹሕ ደም በግፍ ብታፈስስ፣ ሙዳየ ምጽዋቱን ብትዘርፍ፣ እንደ ይሁዳ በአምላክነቱም ጨርሶ ባታምን እንኳን ፈጣሪ የሚጠብቀው የምትሞትበትን ሳይሆን የምትጸጸትበትንና የምትመለስበትን ቀን ብቻ ነው።በወንጌሉ «እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት» እንደሚል እግዚአብሔር ከእርሱ እጅግ በጣም ርቀህ እያለህ እንኳን እያየ ያዝንልሃል እንጅ አያዝንብህም። (ሉቃ. ፲፭፥፳)

(ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሕማማት መጽሐፍ የተወሰደ)

3 months, 1 week ago

አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ የተተረጎመ

3 months, 1 week ago

ስጋዋንም ያሳዪት ዘንድ ወደ መቃብርዋ በአደረሱት ጊዜ በመቃብር ውስጥ ስጋዋን አላገኙም ደንግጠውም አደነቁ ያን ጊዜ ከመላእክት ጋር ወደ ሰማይ ስታርግ እመቤታችንን እንዳገኛት ቶማስ ነገራቸው። ሀዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ የእመቤታችንን እርገቷን ስለ አላዩ እጅግ አዘኑ ስጋዋን በምድር ውስጥ ይተው ዘንድ እንዳልወደደ መንፈስ ቅዱስ አስገነዘባቸው። ከዚህም በኃላ አንድ ጊዜ ደግሞ እርሷን ያሳያቸው ዘንድ እንዳለው ጌታችን ቃል ኪዳን በማድረግ ተስፋ ስጣቸው እነርሱም እስከ ነሀሴ አስራ ስድስት በረስፋ ኖሩ።

የእመቤታችንም የእድሜዋ ዘመን ስልሳ አራት አመት ነው በአባትና እናቷ ቤት ሶስት አመት ከሰባት ወር በቤተ መቅደስም አስራ ሁለት አመት በዮሴፍም ቤት ሰላሳ አራት አመት ከሶስት ወር ከጌታ እርገት በኃላ በወንጌላዊ ዮሀንስ ቤት አስራ አራት አመት ነው።

የህይወት የድኅነት አለኝታ የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በፀሎቷም ከክፉ ነገር ይጠብቀን፤ በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

(ስንክሳር ዘተዋሕዶ - #ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)

3 months, 1 week ago

#በዓለ_አስተርዕዮ_ማርያም - #ጥር_21
ጥር ሀያ አንድ በዚች ቀን አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም የእረፍቷ በአል መታሰቢያ ነው። ያን ጊዜ እመቤታችን በልጅዋ በጌታችን በፈጣሪያችንና በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ መቃበሩ ቦታ ትፀልይ ነበረ ከዚህም አለም እንደምትለይ መንፈስ ቅዱስ ነገራት ከዚህም በኃላ ከደብረ ዘይት ደናግል መጡ ጌታችን ነግሮዋቸዋልና እርሷም ነገረቻቸው።

በዚያንም ጊዜ እመቤታችን እንዲህ ብላ ፀለየች፦
"ልጄ ወዳጄ ጌታዬና ፈጣሩዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሀንስን በዚች ሰአት አምጣው።እንዲሁም ህያዋን እንደሆኑ ሀዋርያትን ሁሉንም ነፍሳቸውንም የለየሀቸውን አምጣቸው አንተ የህያዋንና የሙታን አምላክ ነህና ላንተም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

በዚያንም ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ ከኤፌሶን አገር ዮሀንስን ደመና ተሸክማ ወደ እመቤታችን ማርያም አደረሰችው ሰገደላትና በፊቷ ቁሞ እንዲህ አላት ሰላምታ ይገባሻል ጌታችንን ፈጣሪያችንንና መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለድሺው ፀጋን የተመላሽ ደስ ይበልሽ አንቺ ከዚህ አለም ተለይተሽ በክብር በምስጋና ወደ ዘላለም ህይወት ትሄጂአለሽና። ይህም ስሙ ክብር ምስጉን የሆነ ጌታችንና ፈጣሪያችን ድንቆች ተአምራቶችን በአንቺ ላይ ከገለጠ በኃላ ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ይህን በሰማች ጊዜ እጅግ ደስ አላትእግዚአብሄርንም እንዲህ ብላ አመሰገነችው ፈጣሪዬ ጌታዬ ላንተ ምስጋና ይሁን አንተ የለመንኩህን ሰጥተኸኛልና አሁንም ነፍሴን ተቀብለው ወደ ሰማይ ወደ አንተ ሊአሳርጓት ከሚመጡ መላእከቶችህ ጋር በመምጣትህ የምለምንህን ሁሉ ስጠኝ።

በዚያንም ጊዜ ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል መጣ እነሆ አሁን መላእክት ይደርሳሉ ሀዋርያትም ሁሉ ከምድር ዳርቻ በደመና ተጭነው ለሰማይና ለምድር ጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ወደ ሆነች ወደ ቅድስት ድንግል ይደርሳሉ።

ወዲያውኑ ሁሉም ሀዋርያት የሞቱትም ከመቃብራቸው ተነስተው ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት አምላከችን ከአንቺ የተወለደ ፀጋን የተመላሽ ሆን ደስ ይበልሽ እርሱ ከዚህ አለም ለይቶ ቃል ኪዳን እንደሰጠሽ በክብር በምስጋና ከርሱ ጋር ያሳርግሻልና አሏት።

በዚያንም ጊዜ እመቤታችን በአልጋዋ ላይ ተቀመጠች ሀዋርያትንም እንዲህ አለቻቸው ፈጣሪዬ ፈጣሪያቸው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚመጣ እናንተንም እንዳየኃችሁ እንደማየው አሁን አውቅሁ ከዚህ ከስጋዬም ወጥቼ ወደዘላለም ህይወት እሄዳለሁ ነገር ግን ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ ከዚህም አለም እንደምለይ ከወዴት አወቃችሁ ።

ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉም ወዳንቺ እንመጣ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን በደመና ላይም በተጫን ጊዜ ወዳንቺ እንደ አይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን አሏት።

እመቤታችንም ማርያምም ይህን ነገር ከሀዋርያት በሰማች ጊዜ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች ጌታዬና ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈፅሜ አመሰግናለሁ።የእኔን የአገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ ኃይልህን አድርገህልኛልና ከእንግዲህ ወዲያ ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሰግኑኛል።

ፀሎቷንና ምስጋናዋን ስትጨርስ ሀዋርያትን እንዲህ አለቻቸው እጣን አምጥታችሁ በማጠን የጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ጥሩት እነርሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ ።በዚያንም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፍት መላእክት አጅበው እያመሰገኑት መጣና አረጋጋት ያዘጋጀላትንም ተድላ ደስታ ነገራት በዚያንም ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተደረገ እውሮች አይተዋልና፣አንካሶች ቀንተው ሄደዋልና ደንቆሮዎች ሰምተዋልና ለምፃሞች ነፁ አጋንንትም ከሰዎች ወጥተው ሄዱ ዲዳዎች ተናገሩ በሽታና ደዌ ያለበት ሁሉ ዳነ እመቤታችን ድንግል ማርያም ወዳለቸወበት ቤት በቀረብ ጊዜ ከደዌያቸው ይፈወሳሉና።

ከዚህም በኃላ እመቤታችን ተወዳጅ ልጅዋን እንዲህ አለችው በአየር ውስጥ ተበትነው ከሚኖሩ ከሚያስደነግጡ ግሩማን መላእክት የተነሳ ከእሳት ባህርም እፈራለሁ ጌታችንም ከእናንተ ለማንም በአለሁ ላይ ስልጣን የለውም አላት።

ከስጋዋም የምትለይበት ጊዜ ሲደርስ ሀወሰርያትና ደናግል ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ለመኑዋት እጃዋን በላያቸው ዘርግታ ባረከቻቸው በዚያንም ጊዜ ጌታችን ንፅህት ነፍሷን ከስጋዋ ለይቶ በመለኮታዊ እጆቹ ይዞ በብርሀን ልብስ አጎናፅፎ ወደ ከፍተኛ መኖሪያ ከእርሱ ጋር አሳረጋት ስጋዋን ግን እንደሚገባ ገንዘው ወደ ጌቴሴማኒ ተሸክመው እንዲወስዷት ሀዋርያትን አዘዛቸው።

ነፍሷ ከስጋዋ ከመውጣቷ በፊት በሰው አንደበት ይህ ነው ተብሎ የማይነገር ብርሀንን እያየች ነበር የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስም እንግዲህ ስጋሽን ተድላ ወዳለበት ገነት አፈልሳለሁ ዳግመኛም ስጋሽን ከነፍስሽ ጋር አዋህጄ አስነስቼ መላእክት በውስጡ በፊትሽ ሆነው በሚያመሰግኑበት ተመሳሳይ በሌለው ተድላ ደስታ በአለበት ማደሪያ አኖርሻለሁ አላት።

እመቤታችንም እንዲህ አለች አቤቱ በረቀቀ ጥበብህ ይህን ሁሉ የሰራህ አመሰግንሀለሁ ሁለተኛም ልመናዬን ትሰማ ዘንድ እለምንሀለሁ በስሜ ወደ አንተ የሚለምነውን ሁሉ ልመናውን ተቀበለው በመከራም ውስጥ ሆኖ ስሜን ጠርቶ ወዳንተ የሚለምነውን ከመከራው ሁሉ አድነው በሰማይም በምድርም በስራው ላይ ሁሉ አንተ ከሀሊ ነህና መታሰቢያዬን በውስጧ የሚያደርጉትን ቦታ ሁሉ ባርክ በእኔ ስም የሚያቀርቡትን የሁሉንም መስዋእታቸውን ተቀበል።

ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰላት የለመንሽኝን ሁሉ አደርግልሻለሁ ደስ ይበልሽ ከእኔ ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ፀጋ ክብር ባለሟልነት ተሰጥቶሻልና ስምሽንም ጠርቶ የሚለምን ሁሉ በዚህም አለም በሚመጣውም አለም አይጠፋም።

እመቤታችንም ከአረፈች በኃላ ጌታችን እንዳዘዘ ወደ ጌቴሴማኒ ሊወስዷት ሀዋርያት ገንዘው ተሸከሟት። አይሁድም በሰሙ ጊዜ ስጋዋን ሊአቃጥሉ ወጡ ከእነርሱም አንዱ ከምድር ላይ ይጥላት ዘንድ የእመቤታችንን አልጋዋን ያዘ ያን ጊዜ ከእግዚአብሄር የታዘዘ መልአክ እጆቹን በእሳት ሰይፍ ቀጣውና እጆቹ በአልጋዋ ላይ ተንጠለጠሉ።

ያን ጊዜ በጌታችን አምኖ ወደ እመቤታችን እያለቀሰ እንዲህ ብሎ ለመነ የእውነተኛ አምላክ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናት አንቺ በእውነት ድንግል የሆንሽ በእኔ ላይ ይቅርታ ታደርጊ ዘንድ እለምንሻለሁ በሀዋርያትም ልመና እጆቹ ተመልሰው እንደቀድሞው ደኅነኞች ሆኑ።

በቀበሩዋትም ጊዜ ከዚያ ሶስት ቀን ኖሩ እረፍቷም የሆነው እሁድ ቀን በጥር ወር በሀያ አንድ በዚች ቀን ነበረ ጌታችንም ብርሀናውያን መላእክትን ላከ እነርሱም ስጋዋን ከመቃብር ወስደው በገነት ውስጥ በእፀ ህይወት ስር አኖሩዋት።

ሀዋርያ ቶማስ ግን ያን ጊዜ አልነበረም በደመና ላይ ተጭኖ እርሱ ሲመጣ መላእክት ሲአሳርጓት እመቤታችንን አገኛት መላእክትም ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ና እጅ ንሳ አሉት እርሱም ሰገደላትና ተሳለማት ከእርሷም ተባረከ ከዚህም በኃላ ወደ ሀዋርያት ደረሰ ። እነርሱም እመቤታችንን ማርያምን እንደ አረፈችና እንደ ቀበርዋትም ነገሩት ቶማስም ስጋዋን እስከማይ አላምንም አላቸው።

3 months, 2 weeks ago

#ማግባት_ለሚሹ
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡

ስለዚህ #ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡ የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡

#አባቶች_ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡

#እናቶች_ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡

እናንተ ማግባትን የምትሹ #ወጣቶች_ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡

#እናንተ_ልጃገረዶች_ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡

3 months, 2 weeks ago

" በልያ ላይ ታማኝ ከሆንክ እግዚአብሔር 'ራሔልን' አደራ ይሰጥሃል እና 'በጲጥፋራ ቤት' ታማኝ ከሆንክ እግዚአብሔር 'በፈርዖን ቤተ መንግሥት' ላይ ያሳድግልሃል።  ‘በሚታየው’ ላይ ታማኝ ከሆንክ፣ እግዚአብሔር ‘የማይታየውን’ አደራ ይሰጥሃል፣ ‘በዚህ ሥጋዊ አካል’ ላይ ታማኝ ከሆንክ፣ እግዚአብሔር ‘መንፈሳዊውን አካል’ አደራ ይሰጥሃል።  ምስጢሩን በምታውቀው እና በሚታዘዝልህ 'በራስህ' ላይ ታማኝ ከሆንክ፣ እግዚአብሔር 'በሌሎች ነፍስ' ላይ አደራ ይሰጥሃል።  እግዚአብሔር በብዙ አደራ እንዲሰጥህ በጥቂቱ ታማኝ ሁን"

  • ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሺኖዳ +
3 months, 2 weeks ago

እጅግ የተወደደና የተከበረው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ

“ወዳጄ ሆይ ወንድምህ ከአንተ ይልቅ አስተዋይና አዋቂ ብርቱም ቢሆን በዚህ ቅር አይበልህ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔርን አመስግን

ከወንድምህ አስተዋይነትና ብርታት ትጠቀማለህና በዚህ ሳታቆም ራስህን ስጦታየ ምንድነው?ወንድሜን እህቴን በምን ልጥቀም ?ብለህ ጠይቅ

ይህን ጥያቄ በትክክል ስትመልስ እንደመለስከው ምላሽም ስትተገብር በአንድ መልኩ በሚበልጥህ ሰው ቅር መሰኘትህን በሌላ መልኩ ደግሞ የምትበልጠውን ወንድምህን መናቅህን ታቆማለህ”

3 months, 3 weeks ago

ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago